ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, September 14, 2018

የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ ይከሽፋል ! አዲስ አበቤዎች የኦነግ ደጋፊዎች አቶ ዳውድ ኢብሳ ሊቀበሉ ሲመጡ በፍቅር ያስተናግዳሉ።የኦነግ ደጋፊዎችም አዲስ አበባ የሀገራቸው ዋና ከተማቸው በመሆኗ ከተማዋን ይንከባከባሉ። (የጉዳያችን ማስታወሻ)

አዲስ አበቤዎች 

 • ለእውነተኛ የአራዳ ልጅ እና ለእውነተኛ የኦነግ ደጋፊ ፈጠራ ልብሱ ነው።የአራዳ ልጆች እና የኦነግ ደጋፊዎች ነገ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በልዩ የፈጠራ ክህሎት ፍቅር የምታሳዩበት ቀን አድርጉት። እስከ ንጋት ድረስ ተነጋገሩ፣ ልዩ የሆኑ ቃላት ፍጠሩ።ቃላቱን ወደ ዜማ እና መፈክሮች ቀይሩ።የኪነት ሰዎች ተባበሯቸው።በሁለቱም በኩል ያላችሁ ታዋቂ ወጣቶች  ይህንን በማስተባበር ሕዝቡን አስደምሙት።ሴቶች ወጣቶች ሚናችሁ ከፍ ያለ ነው።ነገ የፍቅር፣በልዩነት የአንድነት ቀን መሆኑን አስመስክሩ።


 • ጉዳያችን/Gudayachn
  መስከረም 4/2010 ዓም (ሴፕቴምበር 14/2018 ዓም)

  ነገ መስከረም 5/2010 ዓም የኦነግ  አንዱ አንጃ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ።የአዲስ አበባ ነዋሪም በወያኔ ተገፍተው የወጡ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በክብር መቀበል ልማዱ ነው።በእዚህ ላይ ችግር የለበትም።ላለፉት ሁለት ቀናት በሰሜን አዲስ አበባ የተፈጠረው ግጭት በከተማዋ አካፋይ ላይ የተቀባ ቀለም ሳብያ እና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውርዶ የኦነግን አርማ ለመቀየር በተደረገ ሙከራ ምክንያት እንጂ ማንም የኦነግን አርማ በፈለገበት ቦታ የማውለብለብ እና የመስቀል መብቱን በመቃወም  አለመሆኑን የአዲስ አበባ ነዋሪ ወጣቶችን ያነጋገረው የአሜሪካ ራድዮ የአማርኛ አገልግሎት መስከረም  3/2010 ዓም ባስተላለፈው መርሐግብር ገልጧል።

  በነገው ዕለት አቶ ዳውድ ኢብሳ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ  ደጋፊዎቻቸው በሰላም ተቀብለው እና ደስታቸውን እንዲገልጡ የአራዳ ልጆች የእራሳቸውን ፈጠራ እየጨመሩ ማስተናገድ እና ፍቅር ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።የሩቁን እና እረጅሙን የሕዝብ አብሮ የመኖር ዋጋ በአጫጭር ስሜታዊ ጉዳዮች እንዳይዋጡ መጠንቀቅ መልካም ነው።በእዚህ ሁሉ ውስጥ ደግሞ የግጭት ነጋዴዎች ሕዝቡን ለማጋጨት  ጥረት እያደረጉ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።


  • የአዲስ አበባ ወጣቶች የኦነግ ደጋፊዎች የፈለጉትን ዓርማ እንዲያውለበልቡ አለመከልከላቸውን ይልቁንም በኢትዮጵያዊነት መብታቸውን የሚያከብሩ መሆናቸውን አሁንም ልዩ ልዩ ዜማ፣አቀራራቢ መፈክሮች፣ ወጣቶች ነገ አደባባይ ወጥተው ከኦነግ ደጋፊዎች ጋር በሚደግፉት ድርጅት ሳብያ ጥላቻ እንደሌላቸው እና ሐሳብ ወደ ግጭት እንደማያመራ የሚያሳዩበት አንዱ መልካም አጋጣሚ ነው። 
  • ነኝህን ለማድረግ ወጣቶች ዛሬ እስከምሽት ድረስ ከኦነግ ደጋፊዎች ጋር ተገናኝተው የአመለካከት መብታቸውን እንደሚያከብሩ፣መንገድ ላይ  ቀለም መቀባት እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ  በማውረድ ተግባር ላይ የተሰማሩት ብቻ ለግጭት እንደዳረጉ ለማሳየት የፈጠራ ክህሎታቸውን በፍጥነት መጠቀም አለባቸው። 
  • ለእውነተኛ የአራዳ ልጅ እና ለእውነተኛ የኦነግ ደጋፊ ፈጠራ ልብሱ ነው።የአራዳ ልጆች እና የኦነግ ደጋፊዎች ነገ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በልዩ የፈጠራ ክህሎት ፍቅር የምታሳዩበት ቀን አድርጉት።ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ ተነጋገሩ፣ ልዩ የሆኑ ቃላት ፍጠሩ።ቃላቱን ወደ ዜማ እና መፈክሮች ቀይሩ።የኪነት ሰዎች ተባበሯቸው።በሁለቱም በኩል ያላችሁ ታዋቂ ወጣቶች  ይህንን በማስተባበር ሕዝቡን አስደምሙት።ሴቶች ወጣቶች ሚናችሁ ከፍ ያለ ነው።ነገ የፍቅር፣በልዩነት የአንድነት ቀን መሆኑን አስመስክሩ።  ጉዳያችን GUDAYACHN
   www.gudayachn.com

  No comments:

  ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

  የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...