የኢትዮጵያ ዓባይ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ኢንጅነር ስመኘው በቀለ
===============================ጉዳያችን/Gudayachn
ሐምሌ 20/2010 ዓም (ጁላይ 27/2018 ዓም)
የኢትዮጵያ ዓባይ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ኢንጅነር ስመኘው ትናንት ሐምሌ 19/2010 ዓም በመስቀል አደባባይ በመኪናቸው ውስጥ እያሉ በጥይት ተገድለው ተገኝተዋል።ድርጊቱ እጅግ አሳዛኝ ነው።ወንጀለኞቹ አደባባይ መጋለጣቸው አይቀርም። አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ደግሞ ማንንም በተንኮል የምትከስ አለመሆኗ ምርመራው ተጣርቶ በመንግስት በኩል የሚቀርበውን ውጤት ሕዝብ በሙሉ መተማመን የሚቀበለው ውጤት ነው።
ዛሬ ሐምሌ 20/2010 ዓም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ ዋሽንግተን ላይ ለተሰበሰቡ የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ማሕበረሰብ አባላት ባደረጉት ንግግር : -
"ለሀገሩ እየሰራ የነበረው ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ትናንት ተገድሏል። ግድያው በማን እንደተፈፀመ ምርመራው ገና እየተጣራ ነው። ሽፍታ በጫካ ውስጥ ዝርፊያና ግድያ መፈፀሙ የተለመደ ነው።ነገር ገን በጠራራ ፀሀይ መሀል ከተማ ላይ የሚፈፀምባት ሀገር ከመምራት በላይ የሚያሳፍር ነገር የለም።ሰይጣን ሲጀመርም ነበር፣እስከ መጨረሻውም ይኖራል።ክፉ ነገር ስንመለከት ሰው ነን እና ማዘናችን አይቀርም ፣ ሆኖም ግን ጥርሳችንን ነክሰን እንሻገራለን እናሸንፋለን።" ብለዋል።
የቀብር ስነ ስርዓታቸው በመጪው እሁድ ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን በመንግስታዊ የጀግና ስነ ስርዓት የሚፈፀመው ኢንጅነር ስመኘው ቀብር ላይ በርካታ ሕዝብ እንደሚገኝ ይጠበቃል።
በመጨረሻም ጉዳያችን መንግስትን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትጠይቃለች። እነርሱም : -
1ኛ) ያለፈ የግድቡ የስራ ሂደት ላይ የነበሩበት የአፈፃፀም ችግሮች እና መልካም ጎኖች እንዲሁም የወደፊቱ እቅድ ማብራርያ በመገናኛ ብዙሃን እንዲሰጥ፣
2ኛ) መንግስት በቀብራቸው ቀን የግድቡን ስያሜ በኢንጅነር ስመኘው በቀለ ስም እንዲሰይምልን፣
3ኛ) የግድቡ መግቢያ ላይ ''ለኢትዮጵያ እድገት መስዋዕት የሆኑ'' በሚል አንድ ሐውልት እንዲያቆምላቸው እና
4ኛ) በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በግድቡ ዙርያ በገንዘብም ሆነ በሙያ ያላቸው ተሳትፎ እንዲያድግ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ።
ድምፃዊ ፀጋዬ እሸቱ ''ይዋል ይደር እንጂ ቀን ይመሰክራል''
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment