ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, May 15, 2018

በኢ/ኦ/ተ/ የኖርዌይ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሐይማኖት ቤተ ክርስቲያን አዲስ የገዛችውን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን በእዚህ ሳምንት በሶስት ጳጳሳት ታስባርካለች።ዝርዝር የበዓሉ መርሐግብር ወጥቷል።ጉዳያችን / Gudayachn
ግንቦት 8/2010 ዓም (ሜይ 16/2018 ዓም)

  • ዘማሪ ይልማን ጨምሮ ከልዩ ልዩ የዓለም ክፍል ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ፣
  • ከኖርዌይ መንግስት ልዩ ልዩ ቢሮ ኃላፊዎች ይገኛሉ።
  • ከቤተ ክርስቲያን ቡራኬ በተጨማሪ በዓለ ንግስም አለ።
  • ሰማይ ተከፈተ (መዝሙር ከጽሁፉ መጨረሻ ያድምጡ) 

የኖርዌይ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሐይማኖት ቤተ ክርስቲያን አዲስ የተገዛው ህንፃ ቤተ ክርስቲያን በእዚህ ሳምንት በሶስት ጳጳሳት ማለትም በአቡነ ኤልያስ፣ አቡነ ሚካኤል እና አቡነ ሕርያቆስ ታስባርካለች።በቤተ ክርስቲያኒቱ ድረ ገፅ ላይ የወጣው መረጃ  እንደሚያሳየው ከግንቦት 10 እስከ 12/2010 ዓም የቤተ ክርስቲያን ቡራኬ አስታኮ ከሚኖረው ልዩ ጉባኤ  በተጨማሪ ግንቦት 12 የሚከበረው የአቡነ ተክለ ኃይማኖት ዓመታዊ በዓል (ፍልሰተ አፅም)  እሁድ ብፁዓን አባቶች በተገኙበት ታቦታት ከመንበራቸው ተነስተው ዑደት እንደሚያደርጉ እና በዓለ ንግሥ መኖሩ ተጠቅሷል።

በእዚሁ የሶስት ቀናት ጉባኤ እና አዲስ ቤተ ክርስቲያን ቡራኬ ከብፁዓን ጳጳሳት በተጨማሪ ዘማሪ ይልማ ኃይሉ ከአሜሪካ፣ መላከ ሕይወት ቀሲስ ጌጡ ከስዊድን፣መጋቢ ሐዲስ ቀሲስ አባተ ከእንግሊዝ፣ መላከ ኃይል ቀሲስ ታደሰ ከጉቶቦሪ ስዊድን እና ሌሎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው ከኖርዌይ ቤተ ክርስቲያን እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የኖርዌይ መንግስት ቢሮ ልዩ ልዩ ክፍል ኃላፊዎች  በእሁዱ መርሃ ግብር ላይ እንደሚገኙ እና በኖርዌይ ቋንቋ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣አገልግሎት እና ማኅበራዊ ሱታፌ ማብራርያ ይሰጣቸዋል።

በሌላ በኩል ከቤተክርስቲያኒቱ የአይቲ ክፍል ለመረዳት እንደተቻለው በሶስቱ ቀናት የሚኖረው መርሐ ግብር በቤተ ክርስቲያኒቱ የፌስ ቡክ ገፅ (የፌስ ቡክ ገፁን ለመክፈት ይህን ይጫኑ) በቀጥታ ስርጭት እንደሚሸፈን ለማወቅ ተችሏል። ከእዚህ በታች ከቤተ ክርስቲያኒቱ ድረ ገፅ (ድረ ገፁን ለመክፈት እዚህ  ይጫኑ) የተገኘው የሶስቱ ቀኖች መርሐ ግብሮች ማጠቃለያ  ይመልከቱ።

መዝሙር ሰማይ ተከፈተ (ያድምጡ)ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...