ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, April 17, 2016

ጣይቱ የተሰኘ ደረጃውን የጠበቀ የኢትዮጵያውያን ሬስቱራንት ባለፈው ቅዳሜ በኦስሎ፣ኖርዌይ ተከፈተ

Ny Ethiopian Restaurant er åpen i Oslo.
New Ethiopian Restaurant is open in Oslo.

ኦስሎ የተከፈተው የጣይቱ ሬስቱራንት ዋና መግቢያ 

ቅዳሜ ሚያዝያ 8/2008 ዓም በኦስሎ፣ኖርዌይ ደረጃውን የጠበቀ ጣይቱ የተሰኘ አዲስ ሬስቱራንት ተመረቀ።እርግጥ ነው በውጭ አገራት የኢትዮጵያ ሬስቱራንቶች እና ሆቴሎች ብዙም አዲስ ዜና የማይሆንባቸው ከተሞች አሉ።ይህ ግን ለኦስሎ አዲስ ዜና ነው።ምክንያቱም በስፋቱም ሆነ በደረጃው ባለፈው ቅዳሜ የተመረቀውን ጣይቱ የኢትዮጵያውያን ሬስቱራንትን የሚያክል የለም።ለእዚህ ነው የእዚህ ሬስቱራንት መከፈት በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ደስታን የፈጠረው።በትናንት የምረቃው ስነ ስርዓት ላይ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሬስቱራንቱን አጨናንቀውት ውለዋል።ከሁሉም ፊት የሚነበበው የደስታ ስሜት ነበር። በባዕድ አገር እየኖሩ የእራስን ባህል የሚያስተዋውቅ ሲገኝ ለምን አንደሰት?


የሬስቱራንቱ ውስጣዊ ክፍል 

አንደኛ ፎቅ ቨረንዳ 

የኢትዮጵያ ቡና እና ባህላዊ ክፍል 

የአንድ አገር ሕዝብ ባህል ከሚገለጥባቸው መገለጫዎች ውስጥ አለባበስ እና አመጋገብ ተጠቃሽ ናቸው።እኛነታችንን ለባዕዳን ከምናሳይበት እና ከምናስተዋውቅበት ውስጥ አንዱ አመጋግባችን ነው።በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያውያን ምግብ በዓለም ላይ ታዋቂ ከሆኑት ከህንድ እና ቻይና ምግቦች እኩል ተፈላጊነታቸው ቀላል አይደለም።እርግጥ የህንድ እና የቻይና ሬስቱራንቶች በካፒታል ደረጃ እና በዘመናዊ የንግድ አመራር የሚለዩበት መንገድ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።

ደንበኞች መስተንግዶ ላይ 

በርካታ አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን የማያውቁት አገር ሄደው የሚመገቡት ምግብ እንደማይስማማቸው ሲረዱ ቶሎ ብለው ወደ ድረ-ገፅ ገብተው የሚፈልጉት የኢትዮጵያውያን ሬስቱራንቶችን ነው።የኢትዮጵያን ምግብ ጣፋጭነቱ ብቻ ሳይሆን  ለጉዞ ተስማሚ እንደሆነ በርካታ የውጭ ዜጎች ይስማሙበታል። እዚህ ላይ የሚያሳዝነው ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ  የኢትዮጵያ ምግብ ለመንገደኞቹ አያቀርብም።እንጀራ መብላት እፈልጋለሁ ያለ መንገደኛ በእራሱ አገር አየር መንገድ ውስጥ ሆኖ የፈረንጅ ምግብ እንጂ እንጀራ አይሰጠውም።የአውሮፓ እና የአሜሪካ ትልልቅ ''ሱፐር ማርኬቶች'' ግን የኢትዮጵያን እንጀራ ለገበያ አቅርበው ለሕዝባቸው እና ባብዛኛው ለኢትዮጵያውያን እንዲቀርብ ፈቅደዋል።አንድ ቀን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ውስጥ እንጀራ በወጥ እናይ ይሆናል።መቼም የእራሳችንን ነገር ሁል ጊዜ ዝቅ የማድረግ አባዜ አለብን።

የሬስቱራንቱ  ፊተኛ ክፍል 

ወደ ኦስሎ አዲሱ ጣይቱ ሬስቱራንት ልመለስ እና ይህ በሁለት ወጣት ኢትዮጵያውያን ኢንተርፕረነሮች  የተከፈተው ጣይቱ ሬስቱራንት ለኦስሎ ከተማ ማዕከል የአምስት ደቂቃ ብቻ እርቀት ያለው ሲሆን ለባቡርም ሆነ ለአውቶብስ ትራንስፖርት አመቺ በሆነው ጎዳና ዳር ላይ የሚገኝ ነው።በነገራችን ላይ የእዚህ አይነቱ ደረጃውን የጠበቀ ሬስቱራንት በኦስሎ ከተማ መኖር የኦስሎ ከተማን የልዩ ልዩ ባህል መገለጫነት የሚያጎላ እና የአፍሪካውያን አንዱ የባሕል ማሳያ ቦታ ይሆናል።ወደ ኦስሎ ጎራ የሚል ኢትዮጵያዊም ሆነ የሌላ አገር ዜጋ ትንሿን ኢትዮጵያን የሚመለከትበት አንዱ እና አይነተኛ አማራጭ ቦታ ጣይቱ ሬስቱራንት ይሆናል።

ከእዚህ ጋር ተያይዞ ሌላው ሳይገለጥ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ።በአዲስ አበባ ሳይቀር በርካታ ሆቴሎች እና የንግድ ድርጅቶች ኢትዮጵያዊ የሆነ ስም እየጣሉ በባዕዳን ስም በሚጠሩበት በእዚህ ወቅት  ጣይቱ ሬስቱራንት የመጀመርያው የኢትዮጵያ ሆቴል ስም በሆነው እና በስመ ጥር ንግስት ጣይቱ ስም መጠራቱ የኢትዮጵያን ስም ለውጭው ዓለም ለማስተዋወቅ የእራሱ ድርሻ አለው። ጣይቱ ስትነሳ የመጀመርያ ሆቴል ስራዋ፣የጦር ስልት አዋቂነቷ፣የመንግስት አማካሪነቷ፣ በውጫሌ  ውል አንቀፅ 17  እንዲመረመር በማድረግ የዓለም አቀፍ ሕግ አዋቂነቷ እና ኢትዮጵያዊት ባለሙያ እናት መሆኗ ሁሉ ይታወሳል።አሁንም  ኢትዮጵያውያን ኢንተርፕሬነሮችን ያብዛልን



በሬስቱራንቱ ሌላኛው  ክፍል የሚገኘው ምሳ በመሶበ ወርቅ 

ጣይቱ ኢትዮጵያ ሬስቱራንት አድራሻ: Toyen data 2, 0190, Oslo
                                                               Greenland Basar 


ጉዳያችን GUDAYACHN
ሚያዝያ 9/2008 ዓም

 www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...