ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, April 19, 2016

የስብሀት ነጋ ምልምሎች ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲያምሷት (ዘአዲስ Ze Addis)



ከእዚህ በታች ያለው ፅሁፍ የተገኘው ከዘአዲስ (Ze Addis) ገፅ ነው
በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተደረገው ድብድብ 62 ሰዎች ቆስለዋል
******************************************************
ኦርቶዶክሱ ዝምታውን እስካልሰበረ ድረስ ገና ይቀጥላል::የፍርሃት ክርስትና ይቁም:: መብታችንን እናስከብር!!
====================================
የህወሀት( ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ) መስራችና ኮማንደር የነበሩት ያያኔው ታጋይ ፤ ያሁኑ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በቅርቡ A Political History of the Tigray People’s Liberation Front ( 1975-1991) የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመዋል። መጽሐፉ አስራ ሁለት ምእራፎችና 355 ገጽ ያሉት ሲሆን በይዘቱም በርካታ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

የመጽሐፉ ደራሲ ደግሞ የህወሀት የፖሊት ቢሮ አባልና ከህወሀት ጥንሥስ ጀምሮ ፖሊሲ አውጪ አመራር ስጭና አዋጊ ስለነበሩ በተራ አባላቶቸ የማይታወቁ በርካታ ሚስጥሮችን ይፋ አድርገዋል። መጽሀፉ ÷ ስለ ብሔር ፓለቲካ አደገኛነት ÷ ስለ ማሌሊት ማኒፌስቶ 1976 አና ትግራይን ስለመገንጠል የነበረውን ውዝግብ÷ ስለ ስብሀት ነጋና መለስ ሚስጥራዊ ሰንስለቶች÷ ስለ ጦርነቱ ÷ ከኤርትራው ኢሳያስ ጋር ስለነበረው ፍቅርና ጠብና አሁን ድረስ እያዋጉ ስላሉት መሰረታዊ ምክንያቶችና ሌሎች ብዙ አስገራሚ ሚስጥሮችን ይተነትናል።
you can find the book here. Just click and read pages 299 -302
እኔን ግን የሳበኝ ህወሀት ወይም ወያኔ ÷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ላይ ከበረሀ ጀምሮ የሰራውን ደባ የሚያትተው ክፍል ነው።ዶክተር አረጋዊ በዚሁ መጽሀፋቸው ምእራፍ አስር ላይ “Neutralizing the Church and Mobilizing Muslims “ በሚለው ንኡስ ርእስ ስር ህወሀት የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን እንዴት እንደተዋጋትና አሁን ቤተ ክርስትያና ውስጥ የሚታዩት አበይት ችግሮች በሙሉ ህወሀት ከበረሀ ጀምሮ ያቀዳቸው መሆኑን በዝርዝር አስቀምጠውታል።
ወያኔ ቤተክርስትያንን መታገል ለምን ፈለገ?
ይህን መጽሀፍ ሳነብ ዋናው ጥያቄዬ የነበረው ፤ “ወያኔ ቤተክርስትያንን መታገል ለምን ፈለገ? “ የሚለው ነበር።ወያኔ በወቅቱ ቤተክርስትያንን አምርሮ መታገልና ማዳከም የፈለገበትን ምክንያቶች ዶክተር አረጋዊ አንድ ባንድ አስቀምጠውታል።በሚገርም ሁኔታ አንዱና ዋናው ምክንያት የቤተክርስትያኗ ብሔራዊ አስተምህሮ ÷ መገንጠልን መቃወምና የሀገሪቱን አንድነት ደጋፊ መሆንና በባንዲራና መሰል ኢትዮጲያዊ መገለጫዎች ላይ የነበራት አስተምህሮ እንደሆነ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠውታል።

“A combination of factors made relations between TPLF and the EOTC church difficult …the church taught its followers to respect their allegiance to the Ethiopian state and was, in effect , a school for national consciousness, using national symbols such as the flag in all religious and social events. No church ever conducted major ceremonies without hoisting the Ethiopian flag – an act also regularly observed …’ page 244
“The pragmatic TPLF understood the church’s role in village social life and its support for the unity of the country .It also understood a possible alliance between the Church with its forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as separatism .The church was viewed as a force standing in the way of TPLF. …there was no doubt that it wanted to subordinate the church to its cause” page 245

የአኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በህዝቡ ውስጥ ያላት ተቀባይነትና ቤተ ክርስትያና በሀገር አንድነት ላይ ያላት ጽኑ አቋም ፡ እግዚአብሄር የለም ብሎ የሚያስተምረውን ሶሺያሊዝምን መቃወሟና በባንዲራ ላይ ያላት ጽኑ አስተምህሮናና የመገንጠል ተቃዋሚ መሆኗ በወያኔ ጥርስ ውስጥ እንድትገባ ምክንያት እንደሆነ ዶክተር አረጋዊ እማኝነታችውን ከገለጡ በሁዋላ ወያኔ ቤተከርስትያኗ ላይ ያሳረፈውን በትር እንዲህ ሲሉ ጠቅሰውታል።
የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ማደንዝዝና መቆጣጠር በብሔራዊ ማንነትና በሀገር አንድነት ላይ ቤተክርስትያኗ የያዘችው ጽኑ አቁዋም ያበሳጨው ህወሀት ቤተ ክርስትያኗን ለማደንዘዝና ለመቆጣጠር የለኮሰውን ባለ ሶስት ዘርፍ የጥቃት ዘመቻ እንዲህ ሲሉ ይዘረዝሩታል:
አንደኛ ፡ ቤተክርስትያኗ በህዝቡ ዘንድ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተ ከርስትያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ
“the second step was to try and move the socio economic focus of life from the church to the peoples assemblies. All administrative and social activities were taken over by the associations and the baitos and even church affair such as the rights and obligations of the church and its followers fell under the jurisdiction of the assemblies. The capacity of the church to mobilize and influence waned. The church lost its status as mediator in conflicts, rights over spiritual and familiar issues because the new political authorities….”
የሚገርመው ቤተክርስትያኗ በራሷዋ መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ እንኩዋን ለመወሰን መብቱን አጣች። በ 1970ዎቹ እና ሰማነያዎቹ ህወሀት ነጻ አወጣሁዋችው በሚላቸው ቦታዎች በሙሉ የቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ውሳኔዎች በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ስብሰባዎች መወሰን ጀመሩ።
ሁለተኛው ደግሞ የቤተ ክርስትያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስትያኗን አመራረ ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች መተካት እንደነበረ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል
“thirdly , the TPLF launched a series of conferences or seminars for selected parish priests in 1970 to win them over. The underlying motive of the seminars was to isolate the church in Tigray from the wider Ethiopian Church in order to foster Tigraian nationalism along the lines of the TPLF strategic objective. Suppressed Tigraian nationalism was invoked to challenge the dominant Ethiopian Orthodox Church. The initial wereda seminars for the priests were conducted by an eloquent TPLF fighter,Gebre Kidan Desta, a graduate of the theological College at Addis Ababa university .The themes of the seminars were to replace the Ethiopian Church authority by TPLF – minded church and the language in the church with Tigrigna and ultimately, to further Tigraian nationalism and identity ‘ page 246
የቤተ ክርስትያኗን ሀይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማስመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና በማስሾም በስብሐት ነጋ የሚመራ የስለላ ቡድን ለዚሁ ጉዳይ ሲባል መዋቀሩን እንዲህ ይገልጹታል
“this process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to infiltrate the wel-established monasteries in Tigrai, such as Debre Damo , by planting TPLF members’ camouflaged as monks and influencing church activities in the interests of TPLF”
+++++++
የማነ ዘመንፈስ ከትግርኛ ጋዜጣ አንባቢነት ተነስቶ : የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ለምን እንደሆነ እካሁን ምስጢሩ ካልገባችሁ ;-ይሄ ነው:: በየቦታው ባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስትያናት ላይ የሚፈጠረው ውዝግብ - ምክንያቱ ምን እንደሆነ ማወቅ ካሻችሁ -ይሄ ነው:: 
ኦርቶዶክሱ ዝምታውን እስካልሰበረ ድረስ ገና ይቀጥላል::የፍርሃት ክርስትና ይቁም:: መብታችንን እናስከብር!!

ዘአዲስ (Ze Addis)  

ቪድዮውን ከእዚህ በታች በመጫን ይመልከቱ https://www.facebook.com/100008042808114/videos/1706908829587194/



No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።