ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, October 26, 2015

ሰበር ዜና - የሳውዲ አረብያ ንጉሳዊ ቤተሰብ ልዑል ሁለት ቶን (2 ሺህ ኪሎ ግራም) አደገኛ አደንዛዥ እፅ ጭነው ተያዙ Saudi prince arrested on private plane with 2 tons of drugs - reports

FILE PHOTO © Jaime Saldarriaga / Reuters


የሊባኖስ የፀጥታ ኃይሎች ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 15/2008 ዓም የሳውዲ አረብያ ንጉሳዊ ቤተሰብ ልዑል አብዱል ሞሸን ቢን አልዋሊድ ሁለት ቶን አደንዛዥ እፅ በግል አይሮፕላናቸው እንደጫኑ በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል።በቤሩት ራፊቅ  ሐሪሪ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ላይ የተያዙት ልዑል አደንዛዥ እፁን ወደ ሳውዲ አረብያ ይዘው ለመብረር ዝግጅት ላይ እንደነበሩ መገለፁን የሩስያ ቴሌቭዥን ''ሩስያ ቱዴይ'' (አርቲ) የሊባኖስ ዜና ምንጮችን ጠቅሶ ገልጧል።''አል ማያድን'' የተሰኘው  የሊባኖስ ቴሌቭዥን ዘገባ ደግሞ ሁለት ቶን አደንዛዥ እፅ በ40 ጥቅል የታሸገ እንደነበር ይገልፃል።

የሩስያው ቴሌቭዥን የኢራኑን የ24 ሰዓት የእንግሊዝኛ ቴሌቭዥን ''ፕሬስ ቲቪ'' በመካከለኛው ምስራቅ የሚደረጉ ጦርነቶች ባብዛኛው በአደንዛዥ እፅ ንግድ እንደሚደጎሙ መጥቀሱን በመግለፅ ዘገባውን ይደመድማል።

ኢትዮጵያ ከሳውዲ አረብያ መንግስት ጋር የሚያቀርርባት ጉዳዮች እየበዙ ነው።በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሳውዲ ከርመው ነው የመጡት።ኢትዮጵያ ውስጥ ከመንግስት ቀጥሎ ከፍተኛ የሰው ኃይል ቀጥሮ የሚገኘው ሚድሮክ ኩባንያ ባለቤት ከሳውዲ ልዑላውያን ቤተሰቦች ጋር ጥብቅ የንግድ ሽርክና እንዳላቸው ይታወቃል። በሌላ በኩል ደግሞ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ሴት ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት የጤና እና የደህንነት ዋስትና በሌለበት አካባቢያዊ ሁኔታ ጉልበታቸውን የሚገብሩባት አገር ነች ሳውዲ አረብያ።

በነገራችን ላይ የሳውዲው ልዑል 2 ሺህ ኪሎ ግራም (1 ቶን 1ሺህ ኪሎ ነው) አደገኛ ናርኮቲክ የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ መያዛቸው ቀዳሚ የዓለም አስገራሚ ዜና ቢሆንም ከሳውዲ አረብያ ጋር የተለያየ የጥቅም ግንኙነት ያላቸው የምዕራቡ የዜና አውታሮችን ጨምሮ እንደማያናፍሱት ይጠረጠራል።የሆነው ሆኖ ግን ጉዳዩ የሳውዲ አረብያን ልዑላውያን ቤተሰብ ጨምሮ በርካታ ባለሃብቶቻቸውን ሌላ የሀብት ምንጭ ያመላከተ ዜና ለመሆኑ አያጠራጥርም።

ምንጭ - ሩስያ ቱዴይ (አር ቲ)

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ጥቅምት 15/2008 ዓም  (ኦክቶበር 26/2015)

No comments: