ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, October 29, 2015

ኢትዮጵያ ሕዝባቸውን በመረጃ መረብ (ኢንተርኔት) ሃሳቡን እንዳይገልፅ ካገዱ አምስት ቀንደኛ አገሮች ውስጥ ተመደበች። (ሙሉ ሪፖርቱን ይመልከቱ)




  •  ከአፍሪካ ቀዳሚ የመረጃ አፋኝ መንግስት ያላት ተብላለች። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአምስቱ አገራት ውስጥ ተመድባለች።
  • ''Ethiopia is among the world’s top five jailers of journalists''
የሁለተኛው ዓለም ጦርነት እንደተጀመረ እንደ አውሮፓውያን አቆታጣጠር በ1941 ዓም ኒውዮርክ ላይ የተመሰረተው ''ፍሪደም ሃውስ'' በየአመቱ የዓለም አገራትን የሰብአዊ መብት እና በተለይ በኢንተርኔት ላይ ያላቸውን ሃሳብን የመግለፅ የመፍቀድ ደረጃ እያጠና ሪፖርት ያቀርባል።የዘንድሮ አመት ተመሳሳይ ሪፖርትንም በእዚህ ሳምንት አቅርቧል።

በዘንድሮው ሪፖርት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ህዝቦቻቸውን መረጃ እንዳያገኙ ከሚያፍኑት አምስት ቀንደኛ አገራት ውስጥ ሲመድባት ከአፍሪካ በቀዳሚነት ይስቀምጣታል።ይህ ምን ማለት ነው? ብለን ለመተንተን ብንነሳ ብዙ ነገር ማለት መሆኑን እንረዳለን።በ21ኛው ክ/ዘመን የምትገኝ አገር ኢትዮጵያ መረጃ ሕዝቧን ነፍጋ ምን ያህል ወደኃላ እየቀረች ማሰብ በራሱ በቂ ነው።በርካታ የአፍሪካ አገሮች በገጠር የሚገኙ ትምህርት ቤቶቻቸውን በመረጃ መረብ አስተሳስረው ትምህርት ማሰራጨት በጀመሩበት ዘመን አንድ የስርዓቱን ድምፅ እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡ ጋዜጦች እና አንድ ቴሌቭዥን ለ92 ሚልዮን ሕዝብ የተወረወረላት ኢትዮጵያ በመረጃ መረብ (ኢንተርኔት) ሃሳባቸውን በነፃነት የማይገልጡባት አገር ሆናለች ኢትዮጵያ።

ሁኔታው በእዚሁ ከቀጠለ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመቱ በራሱ ይዘገንናል።ይህ ማለት ወጣቶቿ ያላቸውን አዲስ ሃሳብ ለህዝባቸው የሚገልጡበት መንገድ የለም ማለት ነው።በድፍረት ሃሳባቸውን ለመግለፅ ለመፃፍ ቢነሱ ደግሞ ለእስር ይዳረጋሉ። የዞን 9 ጦማርያን የደረሰባቸውን ማሰቡ ብቻ በቂ ነው። አዎን! መረጃ ሲታፈን እውቀት ይጠፋል፣እውቀት ሲሞት አገር ይሞታል፣አገር ሲሞት አላዋቂ ይገዛዋል።

የ''ፍሪደም ሃውስ'' ሙሉ ሪፖርትን ከእዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠርያ ተጭነው ያንብቡት።
  

ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com  

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።