ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, May 15, 2015

ይቅርታ! ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ዲሞክራሲ እና ነፃነትን በተግባር እንጂ በፎቶ አያሳዩንከእዚህ በላይ ያለውን ፎቶ ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ ለጥፈው ስመለከት የሚሰራው እና የሚለቀቀው የፕሮፓጋንዳ ፎቶ ብዛት አሳዛኝ ሆኖ አገኘሁት።ፎቶው የአጋጣሚ ነው።ምናልባት ኢቲቪ ቢሮ ስቱድዮ እስኪዘጋጅ ሻይ እንዲጠጡ ተብሎ የተነሱት ፎቶ ሊሆን ይችላል። ምንም ይሁን ምን ግን ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የደረሰው እና በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ጉዞ የቁልቁለት ጉዞ አንፃር ይህ ፎቶ የበለጠውን የታይታ ቀልድ መስሎ የሚታይ ነው።
ለማንኛውም ዶ/ር ቴዎድሮስ ፎቶውን የማላደንቅልዎ ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው -

1/ አቶ መለስም የዛሬ አስር ዓመት ይህንን አድርገውት ነበር 

ይህንን ፎቶ ተመልክቶ 'አሳሪ እና የነገ ታሳሪ አንድ ላይ ሻይ ጠጡ'' ብሎ ጮቤ የሚረግጥ ኢትዮጵያዊ የለም።ይህንን ስል ለምን አብራችሁ ሻይ ጠጣችሁ እያልኩ አይደለም።ይህ የላይ ከላይ የኢህአዴግ ሽፋን እንደሆነች እኔ አይደለሁም የምትጠጡባት ስኒም ይገባታል።ለእዚህም ማስረጃው አቶ መለስም በ1997 የምርጫው ሰሞን እንዲሁ አድርገውት ነበር።እንዲያውም ሲተቃቀፉ አይተን ነበር።ልክ የዛሬ አስር ዓመት ግንቦት 7 ምሽት ላይ በአንደበታቸው አዋጅ ሲያውጁብን የምርጫ ጣቢያዎች ገና አልተዘጉም ነበር።እዚህ ድረስ ነው ታይታችሁ ማለቴ ነው። በእኛ እርዳታ ነፃነታቸውን ያገኙ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ከተቃዋሚዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት እና የዲሞክራሲ ሂደት ከእኛ ምን ያህል የላቀ እንደሆነ የማያውቀውን የዋሁን ሕዝብ ለማታለል  ከሆነ አይሳካም።

2/ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ ነፃነቱን እና እውነተኛ ዲሞክራሲ እንጂ ታይታ አይፈልግም።

ለኢትዮጵያ ሕዝብ መስጠት ያለባችሁ ምርጫ ስትደርስ የምትነሱትን ፎቶ ሳይሆን ሙሉ ነፃነቱን ነው።ደካማ የድርጅትዎ ካድሬዎች ይህንን ይዘው አዲስ ሃሳብ ማፍለቅ የተሳነውን አዕምሯቸውን ሊያሟሹበት ይሞክሩ ይሆናል።እኔ ግን የእርስዎ ድርጅት የኢትዮጵያውያንን ነፃነት ምን ያህል እንደገፈፈ እና በእኛው እርዳታ ነፃነታቸውን ካገኙ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት አንፃርም ሲታይ ምን ያህል ወደ ኃላ እንደወሰዳችሁን ለማነፃፀር እነ ጋናን መመልከቱ ብቻ ይበቃል ባይ ነኝ።
እናንተ ከመኪና ላይ ገፍትራችሁ አልሞት ያላችሁን መሃንዲስ ጋር አብራችሁ ሻይ ስለጠጣችሁ እንደ ትልቅ ውለታ እንደማልቆጥረው ይረዱልኝ። ኢትዮጵያ በመንግሥትነት እረጅም ዓመት ያሳለፈች ሀገር ነች።ዛሬ በ21ኛው ክ/ዘመን ላይ ክላሽ ደግናችሁብን ምርጫ እያላችሁ የምትመፃደቁባት ሀገር አልነበረችም።ይህ ሕዝብ መብት እና ግዴታውን የሚያውቅ፣ማን እንደነበረ እና ወዴት መድረስ የሚገባው እንደሆነ የሚረዳ ሕዝብ ነው።ተቃዋሚን አይደለም የማረኩትን የጦር ምርኮኛ  እኩል የሚያስተናግዱ መሪዎች ያፈራች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ! እናም ገና ብዙ ብዙ እርቀት ይቀርዎታል።ከፎቶ ታይታ ይልቅ የተግባር ነፃነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይመለስለት።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ግንቦት 7/2007 ዓም (ሜይ 15/2015)

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...