ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, May 17, 2015

ደብረ ሊባኖስ እና ትኩረት ያልተሰጠው ግንቦት 13 የሰማዕታት ቀን (የቪድዮ ምስክርነት)

ደብረ ሊባኖስየአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በየዓመቱ ግንቦት 12 የፃድቁ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሰተ አፅም ዓመታዊ በዓል ይከበርባታል።በማግስቱ ግንቦት 13 ቀንም ብዙ ጊዜ ትኩረት የማይሰጠው ታሪካዊ ቀን ነው።ፋሽሽት ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ከሶስት መቶ በላይ መነኮሳት በአንድ ቀን የፈጀበት ዕለት።

ከእነኝህ ሰማዕታት ውስጥ እውቁ የቀዶ ጥገና ሐኪም፣የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ የግል የጤና ዶ/ር  የነበሩት በኃላም የመአሕድ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሠር አስራት ወልደየስ አባት ይገኙበታል።ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አባታቸውን
ጣልያን ደብረ ሊባኖስ ገዳም ውስጥ ሲገድልባቸው የዘጠኝ ዓመት ልጅ ነበሩ።ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በኢህአዴግ እስር ተፈርዶባቸው በእስር ቤት በህመም ሲሰቃዩ ቆይተው በሕይወታቸው መጨረሻ ላይ ለህክምና ወደ አሜረካ እንዲሄዱ በተደረጉ በቀናት ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

ከእዚህ በታች የምትመለከቱት ፊልም ፋሽሽት ሀገራችንን በወረረ ወቅት በሕይወት የነበሩ አባትን ምስክርነት ያሳያል።
ቪድዮ - ከሰማዕቱ እስጢፋኖስ ገፅ




ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...