የሩስያው ፕሬዝዳንት ፑቲን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ኦባማ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ኦባማ ዛሬ ኢስቶንያን ጎብኝተዋል።ኢስቶንያ በቀድሞዋ ሶቭየት ሕብረት ስር የነበረች ሀገር ነች።ዛሬ ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢስቶንያ ውስጥ ከ 2000 ለሚበልጡ ተሰብሳቢዎች ያደረጉት ንግግር አለማችን ወደ አዲሱ የቀዝቃዛው ጦርነት እየገባች ለመሆኑ አመላካች ነው።የሩስያ ስጋት የናቶ (NATO) ወደ ምስራቅ መስፋፋቱ ነው።የችግሩ ምንጭም ይህ ነው።
የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ግዛት የነበሩት ኢስቶንያ፣ላትቭያ እና ሊትዎንያ 'በአዲሲቷ' ሩስያ አዲሱ ''ግልትነፅነት'' (glasnost) በተሰኘው የሚካኤል ጎርባቾቭ ፖሊሲ አማካይነት ሶስቱ ሃገራቱ ነፃነታቸውን አገኙ።በዘመነ ጎርባቾቭ የሩስያ እና የአሜሪካ የሚስጥር ውይይት እዚህ ላይ መጥቀስ ተገቢ ነው።ጎርባቾቭ እነኝህ ሃገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ ከአሜሪካ የተገባላቸው ቃል ነበር።ይሄውም ሃገራቱ የሩስያ ስልታዊ የፀጥታ ዋስትና ክልል ናቸውና ናቶ (NATO) (የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት) ወደ ምስራቅ የባልካን ሀገሮች እና ወደ ኢስቶንያ፣ላትቭያ እና ሊትዎንያ እንደማይስፋፋ ለእዚህም አሜሪካ ቃል እንደምትገባ ተነግሯቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠ ነበር። ብዙም አልቆየ ይህ ቃል አልተከበረም።እነኝህ ሃገራት የናቶ (NATO) የጦር ቃል ኪዳን ድርጅቱ አባል ሆኑ።
ዛሬ ፕሬዝዳንት ኦባማ ያደረጉት ንግግር የዓለማችን አዲስ ምዕራፍ መግባት ማሳሰብያ ነው።ከንግግራቸው ውስጥ ጎልቶ የሚጠቀሰው እና 'ሶስቱ ሃገራት ከተነኩ ጦርነት ይነሳል' የሚለውን መልከት ለሩስያ እንዲህ አስተላልፈውላ ታል።በንግግራቸው የናቶ NATO አንቀፅ 1 ጠቅሰው እንዲህ አሉ
"We will defend our NATO allies, and that means every ally .....In this alliance, there are no old members or new members, no junior partners or senior partners. They're just allies, pure and simple." ''ሁሉንም የኔቶ የጦር ቃል ኪዳን አባል ሃገራትን ከማናቸውም ጥቃት እንከላከላለን የቆየ ወይንም አዲስ አባል የሚባል ነገር የለም። በቀላሉ ሁሉም እኩል ባለ ቃልኪዳናችን ናቸው'' ብለዋል።
አሁን ጥያቄው የአሁኑ የናቶ አባል ሃገራት የቀድሞው የሶቭየት ሕበረት ግዛቶች (ኢስቶንያ፣ላትቭያ እና ሊትዎንያ) ዛሬ ለምን ሰጉ? የሚለው ነው።ጉዳዩ ከዩክሬን የእዚህ ዓመት ክስተት ጋር ተያይዟል።ዩክሬን ላይ ሩስያ በቀጥታ አልታየችም እረጅም እጇ ግን ''ወዶ ገቦች'' የሩስያ ዜጎችን ከዩክሬን ተቃዋሚዎች ጋር ተሰልፈዋል።አሁን የሶስቱ ሀገሮች ስጋትም ይህ ነው በተለይ ኢስቶንያ የሩስያ አመጣጥ አይታወቅም።በቀጥታ አትመጣም እንደ ዩክሬን ከስሬ ነገር ብታስነሳብኝስ? የሚል ነው።
አስቸጋሪው እሳት እንግዲህ እዚህ ላይ ነው።እሳትነቱ ለኔቶም ለሩስያም ነው።በእስቶንያ፣ላትቭያ እና ሊትዎንያ ላይ ከውጭ የመጣ ወረራ ከሆነ ኔቶ ጦሩን ሊያዘምት ይችላል።ከውስጥ የሚነሳ የዩክረንን ለመሰለ ግጭት ግን እራሳቸው የኔቶ አባላት ለመዝመት አንድ ሃሳብ መያዝ ይችላሉ ወይ? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው።ነገሩ አይመስልም። ምክንያቱም እንበል ኔቶ ጦሩን በሰላም አስከባሪነት ቢልክ ሩስያ የፀጥታ ቀጠና ዋስትና ባለችው ቀይ መስመር ላይ እንደፈለገ ሊንፈላሰስ ይችላል ወይ? ሩስያ በእዚህ ያህል እርቀት ናቶ እንዲንቀሳቀስ ትፈቅዳለች ወይ? ሌላው ጥያቄ ነው።ማለት የሚቻለው ነገር ግን አለ።ቀዛቃዛው ጦርነት ከምር መጥቷል።ፑቲን ምን እያሰቡ እንደሆነ አይታወቅም።ምናልባት የቀድሞዋ የሶቭየት ሕብረት የጦር ሸሪክ የነበረው ''ዋርሶው'' የመሰለ የጦር ቃል ኪዳን ማህበር ልትመሰርት እንደምትችል መጠርጠር ይቻላል።የፀጥታ ዋስትና ጉዳይ ነውና።
በመጨረሻም የቀድሞዋ ሶቭየት ሕብረትን ፍፃሜ ያቀላጠፉት ሚካኤል ጎርባቾቭ እስካሁን ድረስ ''ሶቭየት ሕብረትን በማፈራረስ ወንጀል'' ለመክሰስ እና አፋጣኝ ምርመራ እንዲጀመር የሩስያ ፓርላማ አባላት መጠየቃቸውን ሰምተዋል? በጉዳዩ ላይ ኤ ኤፍ ፒ ከሞስኮ ባለፈው ሚያዝያ ላይ ዘግቦበታል።አሁን ዓለማችን እየተቀየረች ነው።አሰላለፉም እንዲሁ።
ጉዳያችን
ነሐሴ 28/2006 ዓም (ሴፕቴምበር 3/2014)
No comments:
Post a Comment