ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, September 15, 2014

አስራ ዘጠነኛው የኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ጥናት ጉባኤ በመጪው ነሐሴ/2007 ዓም በዋርሶ፣ፖላንድ ይደረጋል፣የዋርሶ ዩንቨርሲቲ አዲስ ድረ-ገፅ ከፍቷል፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ትኩረት ሊሰጡት ይገባል።(የጉዳያችን ጡመራ ልዩ ዘገባ)

ዋርሶ ዩንቨርሲቲ 

በዓለም ላይ በጥንታዊነታቸው እና ለረጅም ዘመናት በስነ-መንግስት ስሪታቸውም እንዲሁም በሰው ልጅ የታሪክ ምርምር ላይ አበይት ቦታ ከሚይዙት ሃገራት ከቀዳሚዎቹ ተርታ የምትሰለፈው ሀገራችን ኢትዮጵያ መሆኗ ይታወቃል።ለእዚህም አንዱ አመላካች ጉዳይ ኢትዮጵያ በዘመናዊው ዓለም ምሁራን  ገና እየተጠናች ግን ብዙ አዳዲስ ግኝቶች ዛሬም እየተገኙላት መሆኑ ነው።

የእዚህ ፅሁፍ ዓላማ በምርምሮቹ ምንነት እና በግኝቶቹ ዙርያ ለማተት አይደለም።ነገር ግን በተከታታይ ስለተደረጉት እና ወደፊትም ስለሚደረጉት ''ዓለም ዓቀፍ የኢትዮጵያ ጥናት ጉባኤዎች'' ተገቢውን ትኩረት መስጠት በሁሉም ወገኖች ዘንድ አስፈላጊነቱን ለመጠቆም ነው።ይህ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ በርካታ ምሁራን ስለ ኢትዮጵያ ያለፈ፣ወቅታዊ እና መጪ ፖለቲካዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች የሚዳስሱ በርካታ ጥናታዊ ፅሁፎች አቅርበውበታል።ውይይቶች እና አቅጣጫ አመላካች ሃሳቦች ተሰንዝረውበታል።

ቀደም ባሉት አመታት በተለይ በዘመነ ደርግ በኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ እና የባዕዳን በሀገራችን ጉዳይ ውስጥ እጃቸውን ከመክተታቸው ጋር በተያያዘ እና ያለፉት ልምዶች ከሚሰጡት ተሞክሮ አንፃር እየተጠቀሰ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዓለም ዙርያ የሚደረጉት ጉባኤዎች እየተከታተለ ወቅታዊ ዘገባ ያቀርብ ነበር።ጉባኤያቱ ላይ የተሳተፉ ምሁራን ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ በኃላ ልዩ ጋዜጣዊ መግለጫ እና የውይይት መርሃ ግብር ነበራቸው።
ይህ ሁኔታ ግን ላለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት በመንግስት ቃል አቀባይነት የሚታወቁት የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት ሲሰጡት አይታይም።ይህም ገዢው መንግስት ኢትዮጵያን የሚመልከትበት መነፀር እራሱ ያልተወለወለ በብዥታ የታጠረ ለመሆኑ አመላካች ነው።ዓለም ትኩረት የሰጣት የእራሱን ሀገር ጉዳይ ጉዳዬ አለማለት በራሱ ትልቅ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው።

የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ 

የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ ጥናት ጉባኤ በጥናቱ ላይ የሚቀርቡት የጥናቶቹ ይዘትም ሆነ አጥኝዎቹ ከመላው ዓለም የተውጣጡ እጅግ ስመጥር ምሁራን ከመሆናቸው አንፃር ጉዳዩ ኢትዮጵያ ትኩረት ልትሰጠው የሚገባ እና የዓለም ዓቀፍ ተሰምነቷን የምታንፀባርቅበት ከእዚህም ባለፈ ለቱሪዝም መስብነት ልትጠቀምበት የምትችለው ዕድል ነው።

እዚህ ላይ ከእዚህ በፊት የተጠኑ ጥናቶች ለኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ በአግባቡ እንዲደርሱ ማድረግ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ የምጣኔ ሃብት እና የማኅበራዊ ተቋማት  ሊጠቀሙበት ይገባል።ሌላው እና እጅግ አንገብጋቢው ጉዳይ ደግሞ በርካታ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ስለጉባኤው ያላቸው መረጃ አናሳ መሆኑ ነው።በዓለም ላይ እንደ ሀገር የሚጠና እና ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሚደረግለት ሀገር ማግኘት በራሱ አስቸጋሪ ነው።ኢትዮጵያን ግን ዓለም ዛሬም እያጠናት ነው።ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣የመገናኛ ብዙሃን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ትኩረት ለጉባኤው መስጠት ይገባቸዋል።

የሚቀጥለው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የጥናት ጉባኤ የሚደረገው በአውሮፓዊቷ ሀገር ፖላንድ ዋና ከተማ በሚገኘው የዋርሶ ዩንቨርስቲ ነው።ዩንቨርስቲው የማስታወቂያ ስራውን ከአሁኑ ጀምሯል።ለጉባኤው ብቻ የሚሆን አዲስ ድረ-ገፅም ተከፍቷል።ድረ-ገፁን እና ይዘቱን ከእዚህ በታች ይመልከቱ።

Welcome to the 19th International Conference of Ethiopian Studies Website


Welcome to the official website of the 19th International Conference of Ethiopian Studies (Warsaw 24-28 August, 2015). All scholars interested in taking part in the Conference are kindly asked to follow this website for up-to-date information. The deadlines for submitting the panels will be announced shortly.

19th ICES will be held in Warsaw and organized by the University of Warsaw.

The aim of the Conference of Ethiopian Studies is to allow scholars, students, and others interested in Ethiopian Studies to present the outcome of their research, to exchange their experience, knowledge and ideas on different aspects of Ethiopian culture and that of the Horn of Africa, as well as on their history, and the interconnections within the area and with the outside world.

http://www.uw.edu.pl

https://www.um.warszawa.pl/en


Second circular
Call for panels - further details


Dear colleagues!

As we are waiting for your panel proposals, we would like to give you some additional information. We hope that this will encourage those of you who are thinking about participating to send in your proposals.

If you plan to organize a panel, please take into consideration the following information.

The range of subjects expected may vary, as long as they remain within the scope of scholarly interest in Ethiopia and the Horn of Africa and its interconnections with the outside world.

To submit your proposal, you are kindly asked to use the form available at: www.ices19.uw.edu.pl (under panels&papers)

A description of the panel is essential and it should be clear and comprehensive, not exceeding 300 words.

The deadline for submitting proposals is 31 August 2014.

The list of the selected panels will be published on our website by early November 2014 at the latest, and it will be followed by a call for papers.

The tasks of the panel organizers include selecting paper proposals from among those sent to our website, which we will then redirect to you, as well as delivering all the necessary information concerning your panels to all interested participants.

Please note the necessity to assist Conference participants from the Horn of Africa in searching for funds to cover costs of travel and accommodation, using various resources available to you, as we can only provide a limited number of scholarships.
The 19th International Conference of Ethiopian Studies Website

ጉዳያችን
መስከረም 5/2007 ዓም (ሴፕቴምበር 15፣2014)

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...