Pages

Pages

Thursday, May 9, 2013

የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 30 ይከበር! የዲሞክራሲ መብታችን ወደፊት እንጂ ወደኃላ መንሸራተት አይገባውም-ሚያዝያ 30፣1997 ዓም የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ (ቪድዮ)

ሚያዚያ 30፣1997ዓም ዕሁድ አዲስ አበባ ምናልባትም በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የ ዲሞክራስያዊ ለውጥ የሚጠይቅ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጎ ነበር። በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ በሰላም ወጥቶ በሰላም የገባበት- ሁሉም ነገር ካለ አንዳች እረብሻ የተጠናቀቀበት ታሪካዊ ሰልፍ ነበር።ይህ ሰልፍ ከተደረገ እነሆ ስምንት አመታትን አሳለፈ።
  • የዲሞክራሲ መብታችን ወደፊት እንጂ ወደኃላ መንሸራተት አይገባውም።
  • አዲሱ ትውልድም ለመጪው ትውልድ ፍርሃትን እና አምባገነንነትን ማውረስ የለበትም። 
  • የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 30 ማንኛውም ሰው በሰላማዊ መንገድ ሰላማዊ ሰልፍም የማድረግ መብት እንዳለው ይገልፃል።
  • ይህ ግን በተለያየ መንገድ ተሸራርፎ ሕጉ ስለመፃፉም ለመርሳት የሚዳዳቸው አለቆች በዝተውብናል።
  • ዜጎች ሃሳባቸውን በነፃ የመግለፅ መብታቸው ይከበር!
  • የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 30 ይከበር!


ሚያዝያ 30፣1997 ዓም የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ (ቪድዮ)

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን እዚህ ላይ ይስጡ