ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, March 7, 2013

ከመቃብር የተላከ ደብዳቤ ክፍል አንድ

ሞገስ በማለዳ ተነስቶ የሚናፍቀው የእድር ጡሩንባ ሲነፋ መስማት ነው።በሰፈሩ የሞተ ሰው መኖሩን ስለሚያመላክት ''ዛሬ ሥራ አለ ማለት ነው'' ይላል ለራሱ።በመቀጠል በሩ መቆርቆሩ ስለማይቀር ፈንጠር ብሎ ከአልጋው ላይ ይወርድ እና ልብሱን መልበስ ይጀምራል።
ባለፈው ሳምንት እንደተለመደው መቃብር ሲቆፍር ከሰባ አመት በፊት በእንስራ ተቀብሮ ያገኘው ደብዳቤ ከእራሱ ጋር እንዲያወራ አድርጎታል።ብቻውን ሲሆን መልሶ መላልሶ ያነባታል።እንዲህ ይላል።



'' ይህንን ከእኔ በኃላ ለሚመጣ ትውልድ ፃፍኩት።የሆነብንን ነገር እነሆ እነግርሃለሁ።ጣልያን የባንዳ ቅጥረኞቹ ያደረሱትን ጉዳት ያህል ማን ጎዳን?  ሃገሬን መቸም ጠላት አያጣትም እና ወደፊትም ቢሆን እንደ እስስት የሚቀያየርብህን ባንዳ በመጀመርያ በምክር ቀጥለህ በበትር አርቅ ስል ለመጪው ትውልድ ይህን ፅፌ ከመቃብሬ ጋር እንዲቀበር አደረግሁ።ለምን ከመቃብርህ አኖርከው ትሉኝ እንደሆነ መጪው ትውልድ መቃብር አንድም ቦታ ሲጠበው አልያም ነገር ፍለጋ መቆፈሩ  እንደማይቀር ስለማውቅ።ሌላው እንድትረዳልኝ የምሻው እኛ ሀገር የጠበቅነው አይን የሆኑ ጀግኖቻችንን እንደ እንቁ ይዘን ብዙ ጀግኖችን በ እነርሱ ላይ አፍርተን ነው።የአቡነ ጴጥሮስ ሞት ለጊዜው ቢያሳዝነንም ቆይቶ ግን ፍሬውን ስናይ ተደሰትትን አቡነ ጴጥሮስ መስዋዕትነት ሺዎች ለአርበኝነት ተነሱ። በደብረ ሊባኖስ መነኮሳትን ጣልያን ሲገድልብን ልባችን ቆሰለ።ቆይቶ ግን የጣልያንን ማንነት ሕዝብ አወቀልን።ብዙው ሰው  ከመዋጋት ሌላ 
ምን አማራጭ አለን? ብሎ ጣልያንን ተፋለመ።ባንዳው ግን የ ጣርማ በር ተራራን በሰለጠነ መንገድ ሲናድ ስላየ አንዳንድ ባላገር ጣልያን ትንሽ ፋታ ቢያገኝ ብዙ መንገድ ይሰራልን ነበር አለ።ጥልያንም ፀሐዩ መንግስታችሁ ሮማ ገና ብዙ ታሳያለች እያለ በየገበያው ላይ ለፈፈ።እኛን ለሀገር ነፃነት ለመሞት እንደሚታረድ ከብት የቆምነውን እንደ አልሰለጠኑ ህዝቦች የሚቆጥረን ጣልያን ብቻ ሳይሆን ባንዳውም ነበር።እናም መጪው ትውልድ ይህ አይደርስበትም ማለት አይቻልም ባንዳ መቸም ይኖራል።ነጩን ጥቁር የሚል ሁሌም አለ፣ሃገሩን የሚወደውን እንደ ጠላት የሚያይ አለ፣ሃገሩን አሻግሮ የነገ እሷነቷን መመልከት ትቶ የዛሬውን ፀሐይ ብቻ የሚያይ አለ። ይህ ሁሉ የባንዳነት የጋራ ባህርያት ናቸው።
እንደዘመኑ ነው።አንዳንዴ ባንዳው ከሀገር ወዳዱ የበለጠ የሚመስልበት ጊዜ አለ።ግን አይደለም ጀግና ስላጣ የሚቆዝመው ብዙ አለ።ጀግና ከሰማይ የሚወርድ የሚመስለው ከበዛ መሳሳቱን ንገረው እግዚአብሔር ጀግና ሲፈልግ ካንተው ነው የሚሾመው። ያንተ ልብ ዳገት ያለውን ሌላው ቁልቁለት እንዲልልህ አትጠብቅ---------''

ደብዳቤው አላለቀም ወረቀቱን ከ እንስራው ውስጥ ከታጎሩት ድንጋዮች ውስጥ  ተቆርጦበት ነበር። ተመልሶ ወደ እንስራው አመራ የታጎረውን
ድንጋይ ዘረገፈው።ብዙ ብጥስጣሽ ወረቀቶች አገኘ ገጣጥሞ  ለማንበብ ሰበሰባቸው።ደብዳቤው ካልተወሰነ ጊዜ በኃላ ይቀጥላል።

አበቃሁ 
ጌታቸው 

ኦስሎ 

2 comments:

Anonymous said...

Betam tikikil new.

Anonymous said...

ante lij tinbit mawrat jemerk ende? qedmeh new yemitilew .

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)