ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, March 3, 2013

ሙያ ከጎረቤት (ቪድዮ)

 የ ኬንያ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውድድር ለመላው ኬንያውያን በቀጥታ በቴሌቪዥን በሚተላለፍ የ ዕጩ ፕሬዝዳንቶች ክርክር ማራክነቱን ቀጥሏል።ነጻ ውድ ድር ለእድገት ወሳኝ ነው። የእዚህ አይነት ዲሞክራሲ መቸ ይሆን ሃገሬ የማየው? በትእግስት ክርክሩን መመልከት ከቻልን እና ሃገራችን ያለችበትን የዲሞክራሲ ደረጃ ብናስተውለው በጣም እራስ ያማል።
 የፕሬዝዳንት እጩዎችን ለመጠየቅ የመጡት ከተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ለምሳሌ ተማሪዎች፣መምህራን፣ገበሬዎች፣ ወዘተ ሲሆኑ ጥያቄዎቻቸው የመጡበትን የ ህብረተሰብ ክፍል ጥያቄ በትክክል የወከለ ነው። 

የእኛ ሃገር ሁኔታ ስንመለከት የገዢ ፓርቲው አመታዊ ስብሰባ መቼ ነው? ምን አይነት ውሳኔ ያሳልፍ ይሆን? ከሚል ባለፈ ምንም አይነት የዲሞክራሲ ጭላንጭል አለማየታችን አሁንም እጅግ አሳዛኝ ነው።
ኢቲቪም ያሳዝናል የእዚህ አይነት ግልጽ ክርክር አድርጎ አለማወቁ፣
መንግስትም ያሳዝናል ከእርሱ በላይ አማራጭ ጭንቅላት እንደሌለ ሁሉ ሲሻው ስለ ሌጋሲ ሲሻው ስለ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ እርጥባን እንድንጠብቅ እየነገረን ዲሞክራሲን ለእራሱም ሳያጣጥም ከዘመን ዘመን መሸጋገሩ።
እኛም እናሳዝናለን ኬንያ ያየችውን ዲሞክራሲ ማየት ያልቻልን ምስኪን ህዝብ መሆናችን። 
አንዳንድ ምሁሮቻችንም ያሳዝናሉ ከቤተ እምነቱ እስከ ቤተመንግስቱ ድረስ በውሸት የተሞሉ ምርጫዎች ሲደረጉ በመማራቸው ውሸቱን ሁሉ ሎጂክ ሎጂካ ሎጂክ እየጨመሩ ሃሰቱን ሃሰት ማለት ትተው ናላችንን ለሚያናውዙን።
ሙያ ከጎረቤት እንማር።


ኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ክርክር በቀጥታ ለህዝብ ሲተላለፍ የካቲት

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...