ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, March 15, 2013

የናታን ጉዳይ ፍርድቤት ሲቀርብ እኛ ሁላችን መቅረባችንን መዘንጋት የለብንም(አጭር ማስታወሻ)


በእዚህ ሳምንት በኖርዌይ ትልቅ ኢትዮጵያን በተመለከተ ከተዘገቡት ጉዳዮች አንዱ እና ዋናው ሕፃን ናታን በኖርዌይ የመኖር ፈቃዱ በፍርድቤት መወሰኑ ነበር።ሕፃንናታን ከወላጆቹ ጋር በግድ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ የኖርዌይ የኢሚግሬሽን ይግባኝ ቦርድ (The Immigration Appeals Board (UNE)) ወስኖ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።የፍርድቤቱ የእዚህ ሳምንት  ውሳኔ ብዙዎቻችንን አስደስቷል።እርግጥ ነው ይህንን ያህል አንድ ስደተኛ አለምአቀፍ ሕግን ባልተከተለ መንገድ የስደተኛ መብቱ የፍርድቤት ጉዳይ መሆን ነበረበት ወይ? የሚለው እራሱን የቻለ ጥያቄ ቢሆንም።ሆኖም ግን የኖርዌይ የሕግ አሰራርን የተመለከተ ስለሆነ እና ውሳኔው ከሌሎች ሕጎች ጋር የሚኖረው ተቃርኖ አና  ስምምነት ኖርወጅያኖችን ብዙ አከራክሯል።ብዙዎችም መንግስታቸውን ወቅሰውበታል።ከእዚህ ባለፈ ደግሞ በአለምአቀፍ ግንኙነት ላይ የሚያመጣው አንደምታ ብቻ ሳይሆን አሁን በሀገሪቱ ውስጥ እየኖሩ ላሉት አያሌ የውጭ ሀገር ሕፃናት ላይ የፈጠረው የስነ-ልቦና ጉዳት በእጅጉ ተፈርቷል።ለእዚህም ነው የኖርዌይ የመገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ዜጎች ጉዳዩን የመነጋገርያ አርስት ያደረጉት።

ለእኔ የሚታየኝ ግን አንድ አሳሳቢ ጉዳይ አለ። ናታን በኖርዌይ ቴሌቭዥን ዜናው ሲቀርብ እርሱ የመጫወቻ ዕቃዎቹን ይዞ ሲጫወት ነው የሚታየው። ሰው  ምን እያወራ እንደሆነ፣በቴሌቭዥን ይቅረብ አይቅረብ የእርሱ ጉዳይ አይደለም።ጫወታ ላይ ነው። ነገ ግንናታን ያድጋል።ሲያድግ ወላጆቹ ያዩትን ፈተና እርሱም ምን ተብሎ እንደነበር ከእነመረጃው ይመለከታል።ያንጊዜ ናታን ጥያቄዎች ይኖሩታል። እንዲህ የሚሉ -
''በሀገሬ ለምን መኖር አልቻልኩም? ለምን አባት እና እናቴ ተሰደዱ? እኛ ኢትዮጵያውያን ሀገር አጥተን ከኢትዮጵያ በብዙ ማይሎች የምትልቅ ሀገር መኖርያ ስጭን እያልን መለመን ነበረብን? '' የመሳሰሉት ጥያቄዎች። ይህን ጉዳይ የማነሳው ወላጆቹን ለመውቀስ አይደለም። በሀገራችን ያለውን ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ችግር እናውቀዋለን።ወላጆቹም ከእዚህ የተለየ ማድረግ የሚችሉት ነገር ሊኖር አይችልም።

የናታን ጥያቄ ግን አሁን ላለነው ትውልዶች ሁሉ ነው። ችግር አለብን።አዎን ሀገራችን የመናገር፣የመፃፍ ወዘተ ችግሮች ብቻ ሳይሆን የማሰብ ነፃነት እራሱ ደብዛው ጠፍቷል።የኑሮው ችግር ተባብሷል።ነገር ግን ናታንን ይህ ጉዳይ አሁን አይመለከተውም ።ሕፃን ነውና።ትውልዱን ግን ይመለከታል።ባእዳን ሃገራት ለተወሰነ ጊዜ ያጠስልሉ ይሆናል።ዘለቀታነት ግን ሊኖራቸው አይችልም።አንድቀን ሀገሬ የማለት ጥያቄ ይነሳል።ዛሬ ያላሰናዱት ሀገር ደግሞ ነገ ሀገር ሊሆን አይችልም።ናታን እና የዮናታን እኩዮች ሀገራቸውን ማየት እንዲችሉ እና ትውልዱም በውጭ ሀገር ፍርድቤቶች እየተንከራተተየመኖርያ ፍቃድ ስጡን’ ብሎ እንደፍልስጤማውያን ሀገር ለማኝ እንዳይሆን፣ናታንም ነገ አድጎ እናንተስ የሀገራችሁን ችግሮች ለመፍታት ምን አደረጋችሁ?ብሎ ሳይወቅሰን ሀገራችንን ማሰናዳትችግሯን መፍታት፣ጉድፏን መጥረግ የእዚህ ትውልድ ዕዳ ነው። የናታን ጉዳይ ፍርድቤት ሲቀርብ እኛ ሁላችን በ አካል ባይሆን በዜግነት መቅረባችንን መዘንጋት የለብንም።
Refer Yonatan case court decisions
Click http://www.norwaypost.no/index.php/news/latest-news/28255-nathan-7-wins-against-the-immigration-appeals-board
http://theforeigner.no/pages/news/norway-immigration-officials-lose-ethiopia-case/ 

አበቃሁ 
ጌታቸው በቀለ 
ኦስሎ 

1 comment:

Anonymous said...

Zis is z way we need to think about

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...