ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, March 17, 2013

ለ ኢትዮጵያ ማን ይናገርላት?

(ይህ ፅሁፍ በ ህዳር/2005 ዓም በ እዚሁ  በጉዳያችን ጡመራ ላይ የወጣ ነው።)
ባለፈው ወር 'አፍሌ' በምትባል ጣልያን ከተማ ለፋሽስቱ ግራዚያኒ ሐውልት እንዲቆምለት በመደረጉ ኢትዮጵያውያን በየቦታው የተቃውሞ ድምፆች ሲያሰሙ ሰንብተዋል፡፡ የአፍሌ ከተማ ከንቲባ ''ግራዚያኒ ለፍርድ የቀረበው በፀረ ፋሺስት ኢጣሊያውያን ተዋጊዎች ፊት እንጂ በዓለም አቀፍ ችሎት ፊት ቀርቦ አልተፈረደበትም እናም መታሰቢያ ሐውልቱን በመንግሥት ገንዘብ ማቋቋም ስህተት አይደለም፡፡''የሚል ፌዝ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

1943 እኤአ የፋሺስቱ የጦር መሪ ባድጎሊዮ ጓደኛውን ጀርመንን በመክዳት ለተባበሩት መንግሥታት እጁን በመስጠት በጀርመን ላይ ጦርነት አወጀ፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት አጋር የሆነችው ኢትዮጵያ ሐሳቧን ሳትጠየቅ ግፈኛዎቹ የፋሽስት ቀንደኛ ወንጀለኞች በተባበሩት መንግሥታት እንደ አጋር በመወሰዳቸው የፋሺስት የፓርቲና የጦር መሪዎች ከተጠያቂነት በ ሸፍጥ  አመለጡ። ይህ ማለት ግን ሰሩት ግፍ በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ ያልታወቀ ለመሆኑ አለም የሚያውቀው ነው። ሌላው ቀርቶ ጣልያን አለም መንግሥታት ፊት የፈረመችውን' መርዝ ጋዝ ጦርነት ያለመጠቀም' ስምምነት ወደጎን ተደርጎ ንፁሁ ኢትዮጵያ ገበሬ ላይ የወረደበት መርዝ ውርጅብኝ ኢትዮጵያ ብቻ አይደለም መላው አፍሪካዊ ላይ ብሎም በሰው ልጅ ላይ የተፈፀመ ፍትህ ያላገኝ ግፍ ነው።

በወቅቱ ግራዝያን ኢትዮጵያውያን መጠቀም ስለሚገባው የመሳርያ አይነት ሚስጥር ባስተላለፈው መልክት የ አሜሪካው 'ላይብረሪ ኦፍ ኮንግረስ' የሚገኝ ዶሴ  እንደሚከተለው በሚስጢርጽፎ እንደነበር ያጋልጣል፡፡  “ተልእኳችን እንዲሳካ ከተፈለገ ….በጠላት ላይ እጅግ ከፍተኛ ውድመት ከዚህም በላይ የሞራል ስብራት የሚያስከትለውን ልዩ የሆነ ፈሳሽ ቦምብና ሼል እንደፈለጉ በስፋት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡''

ልዑል ራስ ካሳ ደግሞ በወቅቱ ስለነበረው ኢጣልያ ሕዝቡን በመርዝ መፍጀት እና የነበርውን ሁኔታ እንዲህ ይገልፁታል።
ጥቅጥቅ ያለ የዝናብ ዓይነት ፍንጣቂ ሲዘንብብን አገሩ በሙሉ እሳት የተያያዘ ይመስል ነበር፡ቡናማ ቀለም ያለው፣ የማይጨበጥ¸ቆዳን አቃጥሎ የሚበላ እንፋሎት ዓይነት የመርዝ ጋዝ ነበር ወታደሮቻችን ላይ የሚዘንብበቸው፡፡ በዚች ቀን ብቻ ቁጥሩን መናገር የሚያሰቅቅ ወታደሮቻችን አለቁ፡፡ ከሁለት ሺሕ ከብቶች በላይም በመርዙ አለቁ፡፡ በቅሎዎች፣ ላሞች፣ በጎችና የጫካው ዱር አራዊት ሁሉ አየሸሹ ወደ ሸለቆው እየሮጡ ወደ ገደል ገቡ፡፡ (ልዑል ራስ ካሳ፣ ላቀች አክሊሉ ገጽ ገጽ 66/68)

ንጉሠነገሰ ነገስት ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ እራሳቸው በፃፉት ''ሕይወቴ እና ኢትዮጵያ እርምጃ በተሰኘው መፅሐፋቸው እንዲህ ብለዋል- “የኢጣሊያ የጦር ጠቅላይ ሹም መቀሌን የኢትዮጵያ ወታደሮች በከበቡ ጊዜ የኢጣሊያ የጦር ሠራዊት መፈታቱን ስለተረዳውና ስለ ሠጋ ሌላ ዓይነት የኤፕሪት አጣጣል አደረገ፡፡ ይህንም አደራረግ አሁን ለዓለም ገልጦ ማስታወቅ የተገባኝ ነው፡፡ በአይሮፕላኖች ላይ የኤፕሪት ውሃ የሚረጭ መኪና ተዘጋጅቶ ሰፊ በሆነው አገር ላይ ሞትን የሚያመጣ ረቂቅ ዝናብ እንዲወርድበት አደረገ፡፡ ….. እጅግ የሚያሳዝን ነገር የሚያመጣ ይህ ብልሃት ተፈጸመበት፡፡ ሰውም ከብቱም አለቀ፡፡ ….. እኔም ወደ ጄኔቭ ለመምጣት የቆረጥኩት የኢትዮጵያ ሕዝብ የደረሰበትን ሥቃይ ለሠለጠነው ዓለም ለማስታወቅ ነው፡፡'' (ቀኃሥ፣ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ 1 መጽሐፍ ገጽ 255)

ይህ ብቻ አይደለም ግራዚያኒ የካቲት 12/1929 ቀን ተሞከረበት ግድያ ሙከራ ተከትሎ ከተማዋ ነዋሪ ላይ አካፋ፣በዶማ እና በተገኘው መሳርያ ሁሉ ባደረሰው ጭፍጨፋ ሰላሳሺህ በላይ ሕዝብ እና የሚቆጠሩ ቤቶች አንዲት ጀንበር ብቻ መቃጠላቸውን ታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ (http://gudayachn.blogspot.no/2012/02/75.html)


እዚህ አይነቱን ''ሰው'' ነው እንግዲህ ጣልያኗ' አሌፍ' ከተማ ሃውልት እና የመናፈሻ በስሙ እንዲቆምለት የከተማዋ ከንቲባ እና ቫቲካን ተወካይ በተገኙበት ያውም በመንግስት ገንዘብ የተመረቀለት።ይህ የሆነው እንግዲህ ኢትዮጵያ ጣልያንም ሆነ ቫቲካን ይፋዊ የሆነ ይቅርታ ባላገኘችበት እና ኢትዮጵያ ለተፈፀመባት ግፍ አለም ፍርድቤት ካሳ ባልተከፈላት ሁኔታ ላይ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል። በነገራችን ላይ ጣልያን ገነባችው የሚባለው ቆቃ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ የጉዳቱ መጠን እና ካሳ አለም ፍርድቤት ባልተዳኘ፣ ግን ጊዜው ወዳጅነትን ለማደስ በሚል የተሰራ መሆኑን መዘንጋት አይገባም።እዚህ ላይ ቫቲካን ቤተክርስትያንንም ሆነ ጣልያንን ይፋ ይቅርታ ተገቢ ካሳ ጋር መፈፀም አለበት ያሉ ኢትዮጵያውያን GLOBAL ALLIANCE FOR JUSTICE: THE ETHIOPIAN CAUSE The Fascist Genocide of Ethiopian People 1935 - 1941 (http://www.globalallianceforethiopia.org/)በተሰኘ ስብስብ ስር ሆነው ድምፃቸውን እያሰሙ ፊርማም እያሰባሰቡ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት መገናኛ ብዙሃን በሰጧቸው መግለጫዎች ማስታወስ ተገቢ ነው። ሆኖም ግን ይህ ግለሰቦች ጥረት እንደመሆኑ በተገቢው መንገድ መንግስት ዲፕሎማሲ ሲታገዝም ሆነ ማበረታቻ ሲደረግለት አይታይም።

ስብስቡ ግን ጥረቱ የሚደነቅ ነው።ጉዳዩ የትውልድ ጥያቄ ነው እና በተለያየ መንገድ ጉዳዩን ከማሳሰብ አለመቆጠባቸውን መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ እዚሁ ፋሽሽት ግራዝያን ሃውልት እና መናፈሻ ሥራ በመቃወም መስከረም 5/2012 ' GLOBAL ALLIANCE FOR JUSTICE: THE ETHIOPIAN CAUSE' ጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዛንቱ በላከው የተቃውሞ ደብዳቤ እንዲህ የሚል ይገኝበት ነበር።''...Today, Italy must immediately act to halt a handful of right-wing extremists from ruining Italy’s international reputation and credibility. No park or memorial should be named in honor of Rodolfo Graziani and those who perpetuate it should be stopped from doing so. If someone were to paint a portrait of Mussolini on the side of the Coliseum, wouldn’t it be a national imperative to reverse that? We expect such action now to reverse the opening of the “Rodolfo Graziani Park and Memorial” which occurred on August 11, 2012 in the little town of Affile, 50 miles east of Rome.Ethiopians and Italians around the world join the international community in proclaiming: “Never Again!”to genocide and we expect immediate action by the Italian government to revers This disgraceful attempt to celebrate hatred and racism which violates Italy’s own Law N° 205/1993 prohibiting the dissemination of ideas based on superiority or racial and ethnic discrimination...''


ኢትዮጵያ ማን ይናገርላት?

ኢትዮጵያውያን ሮም እስከ ዋሺግተን ድረስ ግራዚያን ሃውልት ሥራ እና መናፈሻ ምረቃ ላይ ተቃውሞ ሰሞኑን አሰምተዋል።ባለፈው ሰኞ ህዳር 26/2004 አሜሪካ የተደረገው ተቃውሞም አንዱ አካል ነው።ግን ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ለምን ዝም አለ?

እስራኤል ሁለተኛው አለም ጦርነት ወቅት ናዚዎች በደረሰባት 'የዘር ማፅዳት' ዘመቻ አሁን ድረስ እስራኤል ፀጥታ ኃይልም ሆነ ዲፕሎማሲው ናዚዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮችን ሁሉ ዋዛ አያልፏቸውም። ጀርመንም አይሁድ ላይ ለተፈፀመው ግፍ ማዘኗን በተደጋጋሚ ከመግለፅ አልፋ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይቅርታ ጠይቀዋል።


  


 የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ፖስተሮች (ምንጭ:-አባይ ሜዳ ድህረ -ገፅ )                                                                             
 
ወደ እኛ ስንመጣ ግን በመርዝ ሕዝባችንን የፈጀ፣በዋና ከተማችን ላይ አንዲት ጀንበር ብቻ ሰላሳ ሕዝብ በላይ የጨረሰ፣ ሌላም ሌላም ብዙ ግፍ የፈፀመው ግለሰብ ሃውልት ሲቆምለት እና መናፈሻ ሲሰየምለት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ ለምን አላወጣም? (እስካሁን አልሰማሁም) ቢያንስ ጣልያንን አምባሳደር ጠርቶ ተቃውሞን አለመግለፅ የት የተማርነው ዲፕሎማሲ ነው? ነው ወይንስ ታሪክ ሁነቱ ገና መግባባት አልተደረሰም? ንግድ ግንኙነት እና እርዳታ እጅ እንዳያጥር ተፈርቶ ከሆነ በጣም አሳፋሪ ድርጊት ነው። የመጀመርያው የመርዝ ገፈት ቀማሽ የነበሩት የተንቤን፣የ አምባላጌ እና የመቀሌ ሕዝብ እና 'እንብኝ  ለሀገሬ ' ብሎ መላው ኢትዮጵያ የዘመተው አርበኛ፣ገበሬ፣ወጣት፣ሕፃን፣ሽማግሌ ደም ገና ሰባ ሰባት አመት እድሜ ላይ መሆኑን ዘነጋነው? ኢትዮጵያውያን በመንግስት ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ነው ሲባል ሪፖርት የሚቻኮሉት  ዲፕሎማሲ ቢሮዎቻችን ምነው ኢትዮጵያን  ሰው የሌላት ሀገር አስመሰሏት? ኢትዮጵያ ማን ይናገርላት?
ማስታወሻ፡ ዛሬ መጋቢት8፣2005ዓም ከስድስት ኪሎ ተነስተው ወደ ጣልያን ኢምባሲ የሃውልቱን መሰራት ለመቃወም የተንቀሳቀሱ ወጣቶች በፖሊስ መያዛቸውን ከ አዲስ አበባ የወጡ ዘገባዎች እየገለጹ ነው።ይህ ታላቅ የታሪክ ስብራት ነው። አንድ ወንድሜ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንደጠየቀው ጣልያን እስካሁን ድረስ ከኢትዮዽያ አልወጣም ኢንዴ? ያሰኛል።


3 comments:

Anonymous said...

Fantastic post, I really look forward to updates from you.

Anonymous said...

ke 77 Amet behuwala Ethiopia ye Italy fascist sra yemidegf mengs alat malet aychalm? kalteqawemu endemesmamat yqoteralna

Anonymous said...

Today weyane has sent those demonstrators who oppose the building of Mosoloni's monuments. This is shame to weyane.