ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, March 14, 2013

የሰንደቅ አላማ ክብር እና የብሔራዊ መዝሙራችን ጉዳይ(የሶስቱን ዘመናት መዝሙራት በድምፅ እና በግጥም ያገኛሉ)






አንዲት ሀገር አንድነቷን፣ሉዓላዊነቷን እና የወደፊት ተስፋዋ ከሚግለፅበት መንገድ አንዱ ብሔራዊ መዝሙሯ ነው።የብሔራዊ መዝሙር መከበር፣መወደድ እና ዋጋ መሰጠት ከሚገለፅባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ ትምህርትቤቶች ናቸው። ከትምህርት መጀመር በፊት ተሰልፈው የሚያደርጉት ሰንደቅ አላማ ማውጣት እና ማውረድ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።የነገ ተረካቢ ልጆች የብሔራዊ መዝሙርን እንዲዘምሩ ብቻ ሳይሆን ከሁለንተናቸው ጋር ተዋህዶ ነገ ለሀገራቸው ፍቅር ያላቸው ዜጎች እንዲሆኑ የማድረጉ ፋይዳ ትልቅ ነው።

አለመታደል ሆኖ ግማሽ ምዕተ አመት ባልሞላ ጊዜ ብቻ ሁለት ጊዜ የብሔራዊ መዝሙር መቀያየር መንጋሥታት መቀየር ጋር ገጥሞናል።ይህም ሁል ጊዜ ዜሮ የመጀመር አባዜ አዲስ መጤውን  ባለዙፋን የመጠናወቱ ውጤት መሆኑ ነው።የቀደሙት ሁለት መንግሥታት ንጉሱም ሆነ የደርግ ስርዓታት የብሔራዊ መዝሙር በየዘመናቸው ለነበሩት ትውልዶች ውስጥ የማስረፁ ሥራ እንደተሳካላቸው በየዘመኑ የነበሩት ትውልዶች እስካሁን ድረስ ከህሊናቸው ያለመጥፋቱ ጉዳይ ምስክር ነው። የንጉሱን ዘመን ባላስታውስም በደርግ ዘመን ግን ትምህርትቤቶች ዝናብ ሆነ ፀሐይ ሳንል በክብር ሰንደቅ አላማ የመስቀል ስነስርዓት ይከናወን እንነበረ እና ትምህርት ሚኒስቴርም ቁጥጥር የሚደረግበት ጉዳይ ነበር።የመስርያቤት ሰንደቅ አላማዎችም በጥበቃ አባላት ከንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ተሰቅሎ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ በክብር ወርዶ ይቀመጥ የነበረ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ያክል የብዙ አመት የመንግስትነት ታሪክ ያላት ቀርቶ በቅርቡ ንግስትነት ቅርፅ የያዙ መንግሥታትም ትኩረት የሚሰጡት ትልቅ አብይ ክንውን ነው።

ኢህአዲግ ወደስልጣን ከመጣ ጀምሮ ''የሰንደቅ አላማ ቀለም  ይቀየር ወይንም በነበረበት ይቆይ?'' በሚል በምክርቤቱ ውስጥ  የመነጋገርያ አጀንዳነት ድምፅ ማሰጠቱም በላይ የብሔራዊ መዝሙሩም እንዲቀየር ሆኗል።ባንዲራ (ሰንደቅ አላማ) የመቀየር ጉዳይ በውይይት የሚነሳውም ሆነ አንጀንዳነት የበቃበት ጊዜ በዓለም ታሪክ ላይ እንደምንረዳው ሀገሮች ከቅኝ ግዛት ላቀቁ ብቻ ነው።በኢትዮጵያ ግን ለውይይት ቀርቦ በመጨረሻ የህዝቡ ስሜት ከፍተኛ መሆኑ ስለታወቀ በሰንደቅ አላማው መሃል ላይ የኮኮብ ምልክት ብቻ እንዲደረግ አስመወሰነ።

የዛሬው ጥያቄዬ ግን ይህ ብቻ አይደለም። የአሁኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ኢትዮጵያ ትምህርትቤቶች ከገጠር እስከ ከተማ ይዘመራል ወይ? ትምህርት ሚኒስቴር ምን ያህል በምን አይነት ደረጃ ይቆጣጠራል?ሰንደቅ አላማውስ የክልሉን ነው እንዲያከብር የሚደረገው ወይስ ብሄራዊውን?አሁን ያለው ትውልድ ነገ ኢትዮጵያን እንዴት እንዲገልፃት እየተደረገ ነው? የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በተለይ ሰራዊቱ መኮንኖች ብሔራዊ መዝሙርን ከቀድሞ ታጋይ ዘፋኞች ዘፈኖች በላይ በምን ያህል ክብር እና ዋጋ ይወዱታልሕብረተሰብ አመለካከቱ በአንድቀን አይቀየረም የዘመናት ስራዎች ውጤት ነው ሀገር ወዳድም ሆነ የሀገር ጠላት የሆነ ትውልድ የሚፈራው በየዕለቱ በሚሰሩ ስራዎች ጥርቅም ነው። ብሔራዊ መዝሙር መዘመር እና ሰንደቅ አላማ በክብር መስቀል ደግሞ ሀገር ገንቢ ትውልድ የመፍጠር አካል ነው

ተቃዋሚ ፓርቲዎች (በተለይ በሀገር ቤት ያሉት) ያነሱዋቸው እና የህብረተሰቡን አትኩሮት የሚስቡ ብቻ ሳይሆኑ ለውጥ ማምጣት የሚገባቸው እንደ ብሔራዊ መዝሙር የመሰሉ የሀገር አንድነት እና የተከታታይ ትውልድ የማፍራት ስራዎችን ልብ ሊሉ ይገባል።ስልታዊ የአንድነት የመናድ ስራዎች እንደ ብሔራዊ መዝሙር ባሉት ጉዳዮችን ችላ በማለት ይገለጣሉ ትምህርት ሚኒስቴር ምን እየሰራ ነውምን አይነት ትውልድ ለኢትዮጵያ እየደገሰላት ነውኢህአዲግም በፓርላማ መክፈቻ መርሃግብር ላይ (መስከረም ወር ላይ በሚደረገው ስነ-ስርአት) አስር በላይ የሆኑ የባንዲራ ጨርቆች ሕፃናትን አስይዞ በመዘመር መከፋፈሉን እያረዳን ነው።ፓርላማ ያሰባሰበ ጉዳይ ኢትዮጵያ በሚል ስም እስከ ሆነ ድረስ አስር አይነት ጨርቅ ማሳየት እና በፓርላማው መድረክ ላይ ማዘመር ለምን አስፈለገ? ለእዚህም ለምን ሕፃናት ተመረጡ? ትምህርትቤቶች በተለይ በክልል ደረጃ ባሉ ትምህርትቤቶች የክልሉ ባንዲራ ከኢትዮጵያ ባንዲራ የበለጠ ዋጋ ሲሰጣቸው አንዳንዱ ጋር እንዲያውም የክልል መዝሙሮች እንዲዘመሩ ሲደረጉ ምን ያህል የተለያየ ትውልድ ለመፍጠር ተተተግቶ እየተሰራ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው
በ ሃምሳ አመታት ውስጥ ብቻ ሶስት የብሔራዊ መዝሙራት አስተናግደናል እዚህ በታች የሶስቱን መንግሥታት ብሔራዊ መዝሙራት ያዳምጡ።

1. ከ 1967 እስከ 1983 ዓ ም



2.ከ 1928 እስከ 1967  ዓ ም 



3.ከ 1984 እስከ አሁን



1 comment:

Anonymous said...

sostum des yilal yehaylesilase tinish ferenjigna honebign.

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...