Saturday, March 6, 2021

በኢትዮጵያ ላይ ለመገመት በሚያዳግት ደረጃ ተነስተውባታል።ምክንያቱ ካልቀጨናት በስተቀር ለጥቁር ህዝቦች አርዓያ ትሆናለች የሚል ስጋት ነው - ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ዛሬ ያደረጉት ሙሉ ንግግር ይመልከቱ።

ቪድዮ ምንጭ - ኢቢሲ 

*******************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Tuesday, March 2, 2021

ሰበር ዜና - ግብፅ እና ሱዳን እርስ በርስ የመደጋገፍ ወታደራዊ ውል ዛሬ ተፈራረሙ።የአፍሪካ ቀንድን እና ቀይባሕርን ለመጠበቅ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ወደ የጋራ ወታደራዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና የውጪ ፖሊሲ ውል ማሳደግ ይገባቸዋል።


የግብፅ ወታደራዊ የጦር ቺፍ ኦፍ ስታፍ  ሞሃመድ ፋሪድ እና የግብፁ አቻቸው መሐመድ ኦትማን አል-ሁሴን በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከስምምነቱ በኃላ ሲጨባበጡ (Photo-AFP)

ግብፅ እና ሱዳን ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ ፡፡ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 23/2013 ዓም ግብፅ እና ሱዳን የመከላከያ ትብብር ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን የሁለቱ አገሮች ስምምነት ለኢትዮጵያ በተለይ በዓባይ ግድብ አንፃር ሁለቱም ባላቸው ስልታዊ ግንኙነት አንፃር ይህ ስምምነት ትልቅ ማስጠንቀቅያ እንደሆነ አያጠራጥርም።

የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ማርያም አል-ሳዲቅ አልማሃድ  ማክሰኞ  ከግብፅ አቻቸው ሽክሪ ጋር በካይሮ ተገናኝተው የተመለሱ ሲሆን ሁለቱም ሀገሮች በኢትዮጵያ የዓባይ ግድብ ውይይት ላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገባበት ለማድረግ ጥረታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።የግብፁ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም በጣም በቅርቡ ወደ ሱዳን እንደሚመጡ ተሰምቷል።የሱዳን እና የግብፅ ወታደራዊ ውል የተፈፀመው ሁለቱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዓባይ ጉዳይ ላይ በጋራ ከመከሩ በኃላ መሆኑን የግብፅ ዜና አውታሮች ዘግበዋል። በሁለቱ ሀገሮች የጦር ኃይል እታማዥር ሹም (ቺፍ ኦፍ ስታፍ) ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የሱዳኑ እታማዥኦር ሹም ጀነራል መሐመድ ኡትማን አል ሁሴን ሲናገሩ ''የግብፅ ጦር ኃይል ወንድሞቻችን ላደረጉልን የልግስና ስጦታ እና አሁን የገጠሙንን ችግሮች ለመጋፈጥ ላደረጉልን ድጋፍ ሁሉ እናመሰግናቸዋለን''ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ የሱዳን እና የግብፅ ወታደራዊ ስምምነት ኢትዮጵያ እና ኤርትራም በቶሎ ግልጥ ወደ ሆነ ወታደራዊ ስምምነት ውስጥ መግባት እንዳለባቸው የሚያሳስቡ ብዙዎች ናቸው።የግብፅ እና የሱዳን ስምምነት ጀርባ ያሉ የቅርብም ሆኑ የሩቅ ሀገሮች እንደሚኖሩ መገመቱ ቀላል ነው።የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላት ማለትም ከአንድ መቶ ሚልዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ በቀይባሕር ዙርያ የሚደረገው የውጪ ጣልቃ ገብነት አያሳስባትም ማለት አይቻልም።ኤርትራም በሱዳን እና በግብፅ ጥምረት አንፃር ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ የጥቃቱ ኢላማ እንደሆነች የታወቀ ነው።ለእዚህ አላማ ግን መጀመርያ ሁለቱን ሀገሮች በተናጥል ላማጥቃት ቀዳሚ ስልት ሊሆን ይችላል።በትግራይ የተደረገው የሕግ ማስከበር ሂደት በስኬት መጠናቀቁ እና የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የእርስ በርስ መናበብ በፍርሃት ያራዳቸው ግብፅ እና ሱዳን ቀደም ብለው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ ነበር የሰነበቱት።

ኢትዮጵያ ለዓመታት በእርስ በርስ ግጭት ከመዳከም ቀና የምትልባቸው ጊዜዎች እንደመጡ የተረዱ ጠላቶቿ ከአሁኑ ለመኮርኮም ሽር ጉድ ላይ ያሉ ይመስላል።ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ሙሌት ብቻ አይደለም የፈሯት።የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መንግስት ከ250 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በመስኖ ዘንድሮ ማልማቱ የሃገራቱ እራስ ምታት ሆኗል።ይህ ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ የመጪው የአፍሪካ ቱሪዝም ተደራሽ መሆኗ ግብፅ ምጣኔ ሀብቷን  የሚደጉመው ቱሪዝም ወደ ኢትዮጵያ ይፈሳል ብላ ስጋት አላት።ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ላይ የሚኖራት በርካታ ደሴቶች፣የጎርጎራ፣ኮይሻ እና ወንጪ ልማቶች ከፍተኛ ቱሪስት ወደ ኢትዮጵያ እንዲፈስ እንደሚያደርግ ግብፆች ገብቷቸዋል።ቱሪስት ደግሞ ከደረቃማ ቦታዎች የኢትዮጵያን በአእዋፋት እና ደኖች የተከበበ ስፍራዎችን እንደሚመርጡ የታወቀ ነው። 

ከአንድ ሺህ ኪሎሜትር በላይ የሚሆን ክልል የሚያካልለው የቀይ ባሕር ካለው እጅግ ስልታዊ የንግድ መተላለፍያ መስመርነቱ አንፃር ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በወታደራዊ መስክ ከተስማሙ ባዕዳን የመግባት ዕድላቸው ስለሚጠፋ ኢትዮጵያን ሳትነሳ ለማድከም ይታሰባል።ኢትዮጵያን የማድከም ሙከራው በተለይ በግብፅ በኩል ከግማሽ ክፍለ ዝመን በላይ የዘለቀ ሲሆን የእስካሁኑ ሙከራ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመግባት ኢትዮጵያን እርስ በርስ ማጋጨት ነበር። አሁን ኢትዮጵያ የውስጥ ግጭቷን ቢያንስ በታጠቀ ኃይል እየጠፋ ሲሄድ እራሳቸው ለመምጣት የሚያስቡ ይመስላል።የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም እንደዛሬ በአጭር መገናኛ እየተገናኘ ቀርቶ ቀድሞም በእግሩ እየሄደ ሃገሩን ለባዕዳን አሳልፎ ሰጥቶ አያውቅም።አሁን ግን ከጀግንነት ባለፈ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች በጊዜ ግልጥነት ያለበት የእርስ በርስ ወታደራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነት እና ጥምረት በፍጥነት መፈፀም አለባቸው።በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ችግር ኤርትራን የማይመለከት፣በኤርትራ እና ቀይባህር ያለው የባዕዳን ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያን የማይመለከት አድርጎ ማሰብ አይቻልም።ይህንን ሁኔታ ለመረዳት የኢትዮጵያን ያለፉትን አንድ መቶ ዓመታት ታሪክ መመልከት ብቻ በቂ ነው።ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በፍጥነት በግንኙነታቸው ላይ በተለይ በወታደራዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና የውጪ ፖሊስ ላይ የተናበበ ስምምነት ማድረጋቸው የጋራ ህልውናቸው መሰረት ነው።ኢትዮጵያም በባህር ኃይል በኩል አመርቂ ስራዎች እየሰራች እንደሆነ ይሰማል።የባህር ኃይል አዛዥ፣ምክትል አዛዥ እና የአስተዳደር አካል ሙሉ በሙሉ ሥራ የጀመረ ሲሆን የማዘዣ ጣብያውንም በጊዜያዊነት አደራጅቷል።ከእዚህ በተጨማሪ  በአሁኑ ጊዜ በሩስያ፣ቻይና እና ፈረንሳይ ውስጥ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ኢትዮጵያውያን የባህር ኃይል ባለሙያዎች በመሰልጠን ላይ እንዳሉ  የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ኢታማዥኦር ሹም ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለባላገሩ ቴሌቭዥን የቀድሞ ጦር ሰራዊት ሚድያ ዝግጅት በቅርቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።  

*******************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Thursday, February 25, 2021

ዓድዋ - ሙዚቃ በእንግሊዝኛ Adwa - Munit Mesfin - Official Lyrics Video - Ethiopian Music

ግጥም እና ዜማ ድርሰት እንዲሁም አቀንቃኝ ድምፃዊት ሙኒት መስፍን 

***************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Saturday, February 20, 2021

Children and adult Ethiopian Refugees from Tigray Region are under ''political and psychological hijack'' by the former TPLF cadres in Sudan Refugee camp.

ከትግራይ ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች (ሕፃናትም ጭምር) በሕወሐት ካድሬዎች ታግተዋል።የስነ-ልቦና ጥቃትም በካድሬዎች ከመድረሱም በላይ ለጦርነት እንዲነሱ በግድ እየተቀሰቀሱ ነው።የእዚህ ሳምንት በካምፑ ውስጥ የተነሱ ፎቶዎች ይመልከቱ።

====================

Gudayachn News Exclusive

====================

According to the UNHCR latest report there are about 56,000 Ethiopian refugees in Sudan from the Tigray region of Ethiopia. Among these refugees 30% are under 18 and 5% are over 60 years old. Based on different press releases of the Ethiopian government, it is ready to back the refugees to their home in the Tigray region. Ethiopian refugees cross the border during and after a law enforcement process was started after the TPLF army attacked the National Defence Force of Ethiopia (NDFE).


The recently established refugees camp in Sudan, which is near to Ethiopian border is quite strange in its administration.One of the main obligations of any refugee in any corner of the world, is not to be involved in any military activities or agitations.However, such a key condition is violated in the Ethiopian Refugees camp.Even Though,many refugees are interested to go back to their home in Tigray region,the former TPLF cadres who have been also participated in ‘Maikadra genocide’ crime are threatening them not to go back home. Now the situation is going from bad to worse. These cadres are obliging children and adults to gather and demonstrate the most hated organization in Ethiopia,the former TPLF. 


Here below are the latest photos of the refugees,Gudayachn could save, who have been obliged to attend the TPLF’s establishment day of  February 18/2021 (‘Yekatit 11’ in Amharic). In this program childrens were seen with artificial guns and agitating to war.Such action  is quite illegal,according to the international children’s right law. Here the critical question is : What is the reaction of UNHCR, UNICEF, the Sudan Government, International Community and even the Ethiopian government for such ‘’political and psychological hijacking’’ of childrens and adults in the 21st century?


For your easy information,please find here below the February 18 situation of the Ethiopian refugees in Sudan. Cadres of the former TPLF were motivating ,innocent refugees including childrens, to war. An immediate action is expected from all concerned bodies.















====================//================
***************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 




ወንጪ እና ጎርጎራን ተመልክቼ 'የተቃጠልኩባቸው' ቀኖች

ወንጪ ሐይቅ (Photo =viator.com)

ጌታቸው በቀለ 
================ 
ጊዜው የዛሬ 14 ዓመታት ገደማ ነው።በተለያየ ጊዜ ጎርጎራ እና ወንጪን ለማየት ዕድል ገጥሞኝ ነበር።ወንጪን ሁለት ጊዜ ነው የማየት ዕድሉን ያገኘሁት።ሁለቱም ጉዞዎች በቡድን ከሃምሳ ሰው ያላነሰ መንገደኛ ጋር ነበር ጉዞው።

የጎርጎራ 'መቃጠሌ'

ጎርጎራን ከማየቴ በፊት የጣና ገዳማትን ቀደም ብሎ መነሻ ከባህርዳር እያደረግን መዳረሻችንን ባህርዳር እያደረግን ካደረግነው ጉዞ ውስጥ አንዱ ጉዞ እኔ ጣና ቂርቆስን እና ዳጋ እስትፋኖስን አይቶ ጎርጎራ ወጥቶ ማደር የተያዘ መርሃግብር ነበር።ጎርጎራ ከአዲስ አበባ ሰሜን ምዕራብ 705 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።ጎርጎራ ከሐይቁ ዳር ላይ የቀድሞ ባሕር ኃይል (ስሙን ካልተሳሳትኩ) ክበብ የሆነ የተወሰኑ ምግብ እና መጠጥ መስተንግዶ ያለው እና ማደርያ ክፍሎችም ነበሩት።በእዚህ የጎርጎራ ክበብ ለሕዝቡ መስተንግዶ የሚሰጥ ይሁን እንጂ የረባ የምግብ መስተንግዶ አለመኖር ብቻ ሳይሆን የግቢው አያያዝ የቤቶቹ አለመታደስ ስመለከት እጅግ ተናድጄ ነበር።

በአንድ ቀን የጎርጎራ አዳራችን መንገደኞቹ ሁሉ ወሬያችን ይህ ሆኖ አመሸ።አንዱ ለምን ክበቡን ለግለሰብ ኮንትራት አይሰጡትም? እንዴት ይህን የመሰለ ቦታ እንዲህ ይባክናል? እዚህ ውሃው ዳር ላይ መቀመጫ ቢኖረው፣እዛ ማዶው ላይ የጀልባ ማከራያ ቢሰራ፣ ምናለፋችሁ የቀረን የቢዝነስ ፕላኑን መፃፍ ነበር።የሚገርመው የሚጠጣ ለስላሳ እና ቢራ ነው  አለቀ ተብለን በጋራ የያዝነው አገልግል ነበር እራታችን የነበረው።ከእዛን ጊዜ ጀምሮ ጎርጎራ ሲባል ስለቦታው ተፈጥሮ እያደነኩ ምንም አለመደረጉ ግን 'ሲያቃትለኝ ነበር የኖረው።ይህንን አንድ ቀን እፅፈዋለሁ እያልኩ አዘገየሁት።

ወንጪ 'ያቃጠለኝ'

ወደ ወንጪ የሄድነው የወንጪ ሐይቅን ተሻግሮ የሚገኘው የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስን ለመሳለም ነበር።ወንጪ በወሊሶ አልፎ ከአዲስ አበባ 153 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ በመኪና አራት ሰዓት የሚፈጅ መንገድ ነው።ወደ ወንጪ ሐይቅ የሚወስደውን ገረጋንቲ መንገድ አውቶብሱ እኛን ይዞ ከሐይቁ አፋፍ ላይ ሲደርስ ቆመ ትንሽ በእግራችን እንደሄድን ቁልቁል ሀይቁ ዙርያውን ካለው ምድረ ገነት ከመሰለ ደን ጋር ብቅ ሲል እውነት ለመናገር ግድግዳ ላይ ስዕል የምመለከት ነበር የመሰለኝ።ወደ ሐይቁ ለመውረድ ትንሽ ተዳፋት መሬት አለው።ተዳፋቱን ወርዳችሁ የሀይቁን ዳር ትንሽ ከሄዱ በኃላ የአካባቢው ነዋሪዎች (ባብዛኛው ኦሮምኛ የሚናገሩ ናቸው) ሁሉም ግን አማርኛ ያውቃሉ።ትንንሽ ጀልባዎች እየቀዘፉ ሃይቁን እያሻገሩ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ያደርሳሉ።በግምት ከ60 የማያንሰው መንገደኛ እየከፋፈልን ጀልባው ላይ ማሳፈር ያዝን።

ወደ ሀይቁ በጀልባዎቹ ስንሄድ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር እያወራን ነበር።በመሃል ጀልባው ስር ድም የሚል ድምፅ ይሰማል።ጥያቄ ጠየቅን ምንድነው ከስር የሚጮህ የሚሰማው።ጀልባው መሬት ነካ እንዴ? ጠየቅን።መለሱ ዓሳ ነው።ከስር ሲያልፍ እየነካው ነው አሉን።ዓሳ ትሸጣላችሁ? ጥያቄ አስከትልን።መልሱ ዓሳ እንደማያጠምዱ ብዙም እንዳልተሰራበት አጫወቱን።በኃላ ከወረድን በኃላ ከሌሎቹ ጀልባዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ኖሮ ተመሳሳይ መልስ አግኝተዋል።በወቅቱ ዓሳ የሚያሰርግ የለም ማለት ይቻላል።ከእዚህ በላይ በሐይቁ አንድም የሞተር ጀልባ የለም።የሞተር ጀልባ ገዝተን ለቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ለመስጠት እና የአካቢውን ሕዝብ እንድታገለግል ሃሳብ ተጠንስሶ ያደረው በእዚህ ወደ 60 የሚጠጋ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኛ ቤተክርስቲያኑን ተሳላሚ ነበር።በእርግጥ በኃላ ገንዘብ ተዋጥቶ በሀገረ ስብከት በኩል ቤተክርስቲያኒቱ የሞተር ጀልባ እንዲኖራት ተደርጎ ለሕዝቡ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በእዚህ በወንጪ ቂርቆስ ጉብኝታችንም ላይ ከአፋፍ ላይ ሁለት ሾጣጣ (የኮርያ ቤቶች የመሰሉ) ወደፊት መዝናኛ የሚሆኑ በሁለት የግል ባለ ሀብቶች እየተሰራ መሆኑን አይቻለሁ።ነገር ግን የአካባቢው ነዋሪዎችም የሁለቱ ኢንቨስተሮች አገባብ በሙስና እንደሆነ እና ትክክል አለመሆኑን በምሬት ሲናገሩም ተመልክቻለሁ። እንደ ጎርጎራ ሁሉ ወንጪ ብዙ የሚሰራበት ትልቅ የቱሪስት ቦታ እንደሚሆን በተለይ ዓሳ ከስር ጀልባውን እየደበደበ በአግባቡ አለመሰገሩ እና ጥቅም ላይ አለመዋሉ የመልስ ጉዞአችን ላይ የአውቶብስ ውስጥ ጫወታችን ነበር።ምን ጫወታ 'መቃጠላችን' ነበር።

'ለሁሉም ጊዜ አለው' እንደተባለ ዛሬ ለጎርጎራ እና ወንጪ እንዲሁም ለኮይሻ ልማት የገበታ እራት አዲስ አበባ ላይ መዘጋጀቱን ስሰማ ይህንን ከልቤ የነበረ ጉዳይ ላጫውታችሁ ብዬ ጫር ጫር ማድረግ ጀመርኩ።ቦታዎቹ ሳይለሙ ቀልብ የሚስቡ እና የሚያስደምሙ ናቸው።የተፈጥሮ ይዞታቸው ሳይናጋ በጥንቃቄ ከለሙ ተዓምር እንደሚሆኑ እመሰክራለሁ።ቦታውን አይታችሁ ወደ ልማት እንዲቀየር ሃሳብ ያቀረባችሁ እና ወደ ሥራ እንዲቀየር የምትሰሩ ሁሉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይን ጨምሮ ለማመስገን እፈልጋለሁ። ለትውልድ የሚሆን ቅርስ እየሰራችሁ ነው።አመስጋኙ ደግሞ የዛሬው ትውልድ ብቻ አይሆንም መጪውም እንጂ።
========================
***************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 







Friday, February 19, 2021

Statsminister Abiy: Mot en fredelig orden på Afrikas Horn

etiopiske statsministeren Abiy Ahmed (PhD)

Skrevet av den etiopiske statsministeren Abiy Ahmed (PhD)

MENINGER: Den etiopiske føderale regjeringen har frigjort befolkningen i Tigray fra flere tiår med vanstyre fra Tigrayfolkets frigjøringsfront (TPLF). Dette har tent nytt håp, men også ført til bekymringer om Etiopias framtid og vår rolle på Afrikas Horn.

Av Abiy Ahmed

18.02.2021

****************************

Kilde: - https://www.bistandsaktuelt.no/ 


Håpet stammer fra at det korrupte og diktatoriske TPLF er fjernet – for godt. Etiopiere kan nå seg for seg en framtid som ikke er basert på etnisk sjåvinisme, men på enhet, likhet, frihet og demokrati. Dessuten er opprinnelsen til etnisk splittelse som hadde forgiftet mellomstatlige forhold på Afrikas Horn nå overvunnet.

Men jeg kan ikke benekte at fjerningen av TPLF har ført til uro i det internasjonale samfunnet. Det har vært bekymringer for etnisk profilering i Tigray og hindringer for humanitær bistand. Min regjering er fast bestemt på å takle og fjerne disse bekymringene.

 

Hvorfor operasjonen i Tigray

La meg låne et sitat fra Thomas Jefferson: «en anstendig respekt for menneskers meninger». Det leder meg til å forklare hvorfor min regjering handlet slik den gjorde for å gjenopprette fred i Tigray, hvordan vi lindrer lidelsene der, og hvorfor vår innsats – støttet, håper jeg, av det internasjonale samfunnet – vil komme alle i landet til gode, inkludert de som bor i Tigray og på resten av  Afrikas Horn.

Ingen regjering vil kunne akseptere at soldater og uskyldige sivile blir overfalt og drept, slik TPLF var ansvarlig for i fjor høst. Min fremste plikt som statsminister og sjef for de nasjonale væpnede styrkene er tross alt å beskytte Etiopia og dets innbyggere mot interne og eksterne fiender.

Våre operasjoner i Tigray var planlagt for å gjenopprette fred og orden raskt. I dette lyktes vi, men lidelsen og dødsfallene som skjedde til tross for vår beste innsats smerter meg personlig og alle fredselskende mennesker her og i utlandet.

 

Prioriterer å avslutte lidelsene

Å få en slutt på lidelsene i Tigray og i resten av landet er nå min høyeste prioritet. Dette er grunnen til at jeg ber FN og internasjonale hjelpeorganisasjoner om å samarbeide med vår regjering slik at vi sammen kan levere effektiv nødhjelp til alle i Tigray som trenger det.

I mellomtiden jobber vi, dag og natt, med å levere nødvendige forsyninger til innbyggerne våre i Tigray og til trengende i naboprovinsene, samt sikre at menneskerettighetene respekteres og dagliglivet gjenopprettes. For å lykkes må mange utfordringer overvinnes. For eksempel er det å reparere kommunikasjonslinjer som bevisst er ødelagt av TPLF noe som gjør det vanskelig å levere humanitær hjelp. I dette gjenoppbyggingsarbeidet kan det internasjonale samfunnet være til stor hjelp.

Regjeringen er også forberedt på å bistå ledere i Tigray som er dedikert til fred. Vi strekker ut hånden til dem nå. Det internasjonale samfunnet forsto hva TPLF sto for. Mange hadde fordømt dets etnisk-baserte vold. Dessverre var det noen som valgte å overse TPLFs bruk av tortur, forsvinninger og utenomrettslige drap. Uten TPLF, ble det sagt, risikerte Etiopia å bli revet i stykker langs etniske linjer, som Jugoslavia på 1990-tallet. De argumenterte med at Etiopias sammenbrudd ville føre til kaos på Afrikas Horn.

 

Uten etnisk splittelse

Sunn fornuft tilsier at et regime basert på etnisk splittelse ikke kan vare; men som ordtaket sier, sunn fornuft er ikke alltid universell. Heldigvis kan ikke mennesker tolerere rasemessig, etnisk og religiøs vold i lengden.

I om lag fem foregående år før jeg i april 2018 ble utnevnt til leder for det daværende Det etiopiske folks revolusjonære demokratiske front (EPRDF), som inkluderte TPLF, vokste de folkelige kravene til regimet i styrke. TPLF svarte med sin vanlige brutalitet. 

Avstemningen i 2018 flyttet landet over i en ny og inkluderende retning. Det politiske partiet (Velferdspartiet, red. anm.) som jeg nå leder, er det første i Etiopia som ikke er basert på rase, religion eller etnisitet.

TPLFs utenrikspolitikk var en videreføring av dens hjemlige splitt- og hersk-strategi. Etiopia under TPLF innførte for eksempel en politikk for å ekskludere og presse Eritrea. Konsekvensen var at det ble ført krig ved å bruke stedfortredere i ustabile naboland. Et Etiopia fri fra TPLF vil kjempe for fred og inkluderende utvikling. Innad vil vårt «Nye Etiopia» være basert på likhet mellom alle folkegrupper, inkludert det lidende folket i Tigray. Utad vil vi handle på en måte som erkjenner at våre nasjonale interesser er uadskillelig knyttet til våre naboers nasjonale interesser.

Fredsavtalen som ble undertegnet med Eritrea i 2018 er et levende eksempel på hva Etiopia er i stand til og villig til å gjøre. Denne avtalen løste en voldelig og fastlåst situasjon som hadde vart i to tiår. Den gjør at Eritrea igjen kan integreres på Afrikas Horn og i det internasjonale samfunnet. Det viktigste er at dets innbyggere og de som bor langs vår felles grense nå kan leve uten at skyggen av krig henger over dem.

Vår regjering har også søkt å nullstille Etiopias forhold til våre andre naboer. Etter den politiske krisen i Sudan i 2019 medvirket Etiopia til å bringe landet tilbake fra randen av borgerkrig, og bidro til å skape en overgangsregjering av sivile og militære representanter. På samme måte står ikke Etiopias stabiliserende rolle i Somalia tilbake for noen, og vår innsats for å bringe stabilitet i Sør-Sudan er ubrutt.

 

Regional integrasjon

Etiopias nåværende utenrikspolitikk er basert på en tro på at tettere regional integrasjon kommer alle til gode. Vår innsats for å realisere det afrikanske kontinentale frihandelsområdet er en sentral del av dette. Mer konkret åpnet vi for bare noen uker siden en motorvei langs Addis Abeba-Nairobi-Mombasa-korridoren, et prosjekt som fjerner fysiske barrierer for grensehandel mellom Kenya og Etiopia. På samme måte utbedres veien fra Addis Abeba til den eritreiske havnebyen Assab til å bli en transportåre for internasjonal handel.

I samarbeid med privat sektor planlegges dessuten nye motorveier for å knytte Etiopia til havnebyene i Djibouti og Assab (for å erstatte den eldre veien som nå utbedres). Deretter vil veien bli knyttet til Juba, Sør-Sudans hovedstad, for å gi det fattige, innlåste landet adgang til internasjonal handel. Samarbeidsprosjekter innen havner og logistikk, industriparker og utvinning av kalium utvikles også. Og det er mitt dypeste håp at Den store etiopiske renessansedammen, når den er ferdig, vil få støtte fra alle våre naboer og gi enestående muligheter for alle i Øst-Afrika.

Bare et Etiopia i fred, med en regjering bundet av anerkjente normer for oppførsel, kan spille en konstruktiv rolle på Afrikas Horn og i forøvrig. Vi er fast bestemt på å samarbeide med våre naboer og det internasjonale samfunnet for å oppfylle dette løftet.

=============////=============

***************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Tuesday, February 16, 2021

አስመራ እና ባሕርዳር ድረስ የሚወነጨፍ ሚሳኤል ይዛ ኢትዮጵያን መበተን ያልቻለችው ህወሓት እና የምላስ ዘመቻዋ።አሁን ጥይቄው ኢትዮጵያን እንበትናለን ከሚሉት ነህ? ወይንስ ከኢትዮጵያ ነህ? ነው።

ከላይ የምትመለከቱት የትግራይ ልማት ማኅበር የሰሜን አሜሪካ ሊቀመበር አሉላ ሰለሞን በትውተር ገፁ ''ኢትዮጵያን እንግደል'' የሚለው ጥሪ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የካቲት 14/2021 የለጠፈው ነው።

  • በውጪ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ጋር አብረው ባለመቆም እራሳቸውን እና ልጆቻቸውን በመጠበቅ ከጸጸት የሚድኑበት ጊዜ አሁን ነው።
  • በኃላ ኢትዮጵያን ለመበተን ከቆሙ ጋር ተሰልፎ በሚከተለው ቅጣት 'እየዬ' አይጠቅምም።

በኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል የሕግ ማስከበር እርምጃ ተወስዶበት ከኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ የተወገደው ህወሓት ዋና ግቡ እና ዓላማው ኢትዮጵያን መበተን እና መከፋፈል እንደነበረ ብዙ ጊዜ በማስረጃ ተደግፎ ተገልጧል።ህወሓት በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ውስጥ አንቀፅ 39 ላይ የመገንጠል አንቀፅ በብሔር ብሔረሰብ ስም ሲያስገባ ኢትዮጵያን መበተን ዋና ግቡ ነበር።ለእዚህ እኩይ ዓላማው እንዲሳካ ደግሞ ኢትዮጵያን በጎሳ እና ክልል ከልሎ ሕዝብ ከህዝብ ጎጥ ከጎጥ እያጋጨ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመላዋ ኢትዮጵያ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ እንዲፈናቀሉ እና እርስ በርስ እንዲጋጩ በማድረግ በኢትዮጵያ የእልቂት ዘመን አንግሶ ኖሯል።

ህወሓት በቀጥታ የኢትዮጵያን መበተን ከሚፈልጉ ባዕዳን ጋር አብሮ ከመስራት አልፎ ሀገሪቱን ባዕዳን እንዲቀራመቷት ከለም የእርሻ መሬት እስከ የከተማ ቦታ በርካሽ ዋጋ ሲቸበችባት ከርሟል።የኢትዮጵያ ለም መሬት ለጥቅሙ ሲል በኬሚካል ማዳበርያ ስር እንዲወድቅ ያደረገው፣በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከአረብ ሀገር እስከ ሊብያ ተሰደው ሲሄዱ በኤምባሲዎቻቸው ሰው አሸጋጋሪ ሰራተኞች ሳይቀር ዜጎቿን ሲቸበችብ ኖሯል።

ህወሓት ኢትዮጵያን ለመበተን የመጨረሻ ቃታዋን የሳበችው በጥቅምት 24/2013 ዓም በኢትዮጵያ  መከላከያ ሰራዊት ላይ የከፈተው ጥቃት ነው።ይህ ጥቃት ግቡ ኢትዮጵያን መበተን ነበር።የመከላከያ ሰራዊቷ የተጠቃ ሀገር ለባእዳን የተጋለጠች ብቻ ሳትሆን ወደ እርስ በርስ ጦርነት የመግባቷ ክፉ ዕጣ እንደሚኖር ግልጥ ነው። ህወሓት ይህንን ሁሉ የእልቂት ድግስ በኢትዮጵያ ላይ አውጃ ነበር በኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ጥቃት የፈፀመችው።ይህ ሁሉ ሙከራዋ ግን ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።

አሁን ህወሓት የቀራት የርዝራዦች ምላሷ ነው።ይህ ምላሷ ደግሞ ቀድሞም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የነበራትን ሕልም ለኢትዮጵያ ጠላቶች እንደ ገፀ በረከት በማቅረብ በምትኩ የደም ገንዘብ ለመቀበል እየሮጠች ነው።በአሜሪካ ተቀምጦ የኢትዮጵያን መፍረስ ላይ የረከሰ ላንቃ የሚለቀው አሉላ በትውተር ገፁ ላይ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ላይ እንስራ የሚል ፅሁፍ አሰራጭቷል።ይህ ለታሪክ ይቀመጣል።ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ አስመራ እና ባሕርዳር ድረስ የሚወነጨፍ ሚሳኤል ይዛ ያልቻለችውን ዛሬ ከስሯ ተነቅላም አጀንዳዋ ኢትዮጵያን መበተን እንደነበር ሌላው ማስረጃ ነው።

በመጨረሻም በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በስማቸው እየነገዱ ኢትዮጵያን እናፍርስ የሚሉት ጋር ባለመተባበር እና ልጆቻቸውን ከእዚህ እኩይ ተግባር አራማጆች በማራቅ እራሳቸውን እና ልጆቻቸውን የሚያድኑበት ጊዜ አሁን ነው።በኢትዮጵያ ላይ የተኮሰ እና ያለመ አይደለም በክፉ የተመለከተ ፍርዱ ከምድር ብቻ ሳይሆን ከሰማይም መሆኑን የማያምን ካለ የጊዜ ጉዳይ ነው ሁሉንም በፀፀት የሚያይበት ጊዜ እሩቅ አይደለም።ወላጅ ልጆቹን፣ልጅ ወላጁን፣ወዳጅ ወዳጁን ተው! የሚልበት ጊዜ አሁን ነው።በኃላ ኢትዮጵያን ለመበተን ከቆሙ ጋር ተሰልፎ በሚከተለው ቅጣት 'እየዬ' አይጠቅምም።አሁን ጥይቄው ኢትዮጵያን እንበትናለን ከሚሉት ነህ? ወይንስ ከኢትዮጵያ ነህ? ነው።
***************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 



The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...