- በውጪ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ጋር አብረው ባለመቆም እራሳቸውን እና ልጆቻቸውን በመጠበቅ ከጸጸት የሚድኑበት ጊዜ አሁን ነው።
- በኃላ ኢትዮጵያን ለመበተን ከቆሙ ጋር ተሰልፎ በሚከተለው ቅጣት 'እየዬ' አይጠቅምም።
በኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል የሕግ ማስከበር እርምጃ ተወስዶበት ከኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ የተወገደው ህወሓት ዋና ግቡ እና ዓላማው ኢትዮጵያን መበተን እና መከፋፈል እንደነበረ ብዙ ጊዜ በማስረጃ ተደግፎ ተገልጧል።ህወሓት በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ውስጥ አንቀፅ 39 ላይ የመገንጠል አንቀፅ በብሔር ብሔረሰብ ስም ሲያስገባ ኢትዮጵያን መበተን ዋና ግቡ ነበር።ለእዚህ እኩይ ዓላማው እንዲሳካ ደግሞ ኢትዮጵያን በጎሳ እና ክልል ከልሎ ሕዝብ ከህዝብ ጎጥ ከጎጥ እያጋጨ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመላዋ ኢትዮጵያ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ እንዲፈናቀሉ እና እርስ በርስ እንዲጋጩ በማድረግ በኢትዮጵያ የእልቂት ዘመን አንግሶ ኖሯል።
ህወሓት በቀጥታ የኢትዮጵያን መበተን ከሚፈልጉ ባዕዳን ጋር አብሮ ከመስራት አልፎ ሀገሪቱን ባዕዳን እንዲቀራመቷት ከለም የእርሻ መሬት እስከ የከተማ ቦታ በርካሽ ዋጋ ሲቸበችባት ከርሟል።የኢትዮጵያ ለም መሬት ለጥቅሙ ሲል በኬሚካል ማዳበርያ ስር እንዲወድቅ ያደረገው፣በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከአረብ ሀገር እስከ ሊብያ ተሰደው ሲሄዱ በኤምባሲዎቻቸው ሰው አሸጋጋሪ ሰራተኞች ሳይቀር ዜጎቿን ሲቸበችብ ኖሯል።
ህወሓት ኢትዮጵያን ለመበተን የመጨረሻ ቃታዋን የሳበችው በጥቅምት 24/2013 ዓም በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የከፈተው ጥቃት ነው።ይህ ጥቃት ግቡ ኢትዮጵያን መበተን ነበር።የመከላከያ ሰራዊቷ የተጠቃ ሀገር ለባእዳን የተጋለጠች ብቻ ሳትሆን ወደ እርስ በርስ ጦርነት የመግባቷ ክፉ ዕጣ እንደሚኖር ግልጥ ነው። ህወሓት ይህንን ሁሉ የእልቂት ድግስ በኢትዮጵያ ላይ አውጃ ነበር በኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ጥቃት የፈፀመችው።ይህ ሁሉ ሙከራዋ ግን ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።
አሁን ህወሓት የቀራት የርዝራዦች ምላሷ ነው።ይህ ምላሷ ደግሞ ቀድሞም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የነበራትን ሕልም ለኢትዮጵያ ጠላቶች እንደ ገፀ በረከት በማቅረብ በምትኩ የደም ገንዘብ ለመቀበል እየሮጠች ነው።በአሜሪካ ተቀምጦ የኢትዮጵያን መፍረስ ላይ የረከሰ ላንቃ የሚለቀው አሉላ በትውተር ገፁ ላይ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ላይ እንስራ የሚል ፅሁፍ አሰራጭቷል።ይህ ለታሪክ ይቀመጣል።ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ አስመራ እና ባሕርዳር ድረስ የሚወነጨፍ ሚሳኤል ይዛ ያልቻለችውን ዛሬ ከስሯ ተነቅላም አጀንዳዋ ኢትዮጵያን መበተን እንደነበር ሌላው ማስረጃ ነው።
በመጨረሻም በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በስማቸው እየነገዱ ኢትዮጵያን እናፍርስ የሚሉት ጋር ባለመተባበር እና ልጆቻቸውን ከእዚህ እኩይ ተግባር አራማጆች በማራቅ እራሳቸውን እና ልጆቻቸውን የሚያድኑበት ጊዜ አሁን ነው።በኢትዮጵያ ላይ የተኮሰ እና ያለመ አይደለም በክፉ የተመለከተ ፍርዱ ከምድር ብቻ ሳይሆን ከሰማይም መሆኑን የማያምን ካለ የጊዜ ጉዳይ ነው ሁሉንም በፀፀት የሚያይበት ጊዜ እሩቅ አይደለም።ወላጅ ልጆቹን፣ልጅ ወላጁን፣ወዳጅ ወዳጁን ተው! የሚልበት ጊዜ አሁን ነው።በኃላ ኢትዮጵያን ለመበተን ከቆሙ ጋር ተሰልፎ በሚከተለው ቅጣት 'እየዬ' አይጠቅምም።አሁን ጥይቄው ኢትዮጵያን እንበትናለን ከሚሉት ነህ? ወይንስ ከኢትዮጵያ ነህ? ነው።
***************************
ማስታወቂያ /Advertisement
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ?
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ -
No comments:
Post a Comment