ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, February 12, 2021

የትግራይን ሕዝብ እንረዳለን።ትግራይን ለዛሬው ርሃብ ያደረሳት የኢትዮጵያ መንግስት ሳይሆን ኢትዮጵያን ሊበትን ሲሞክር የተበተነው ህወሓት እንደሆነም ጠንቅቀን እናውቃለን።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል መቀሌ የመድሃኒት አቅርቦት ሲያወርድ 

  • ከ20 ዓመታት በላይ ሲጠብቀው የነበረ ወታደር በተኛበት ከገደለ በኃላ ''የኤርትራ ወታደር ገባ'' የሚለው ድምፅም ህወሓት ትግራይን ለእዚህ እንዳበቃት ሲናገር መሰማት አለበት። 

በትግራይ ካለፈው ጥቅምት 24/2013 ዓም የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ጦር ኃይል ላይ ከፈፀመው ጥቃት እንዲፈፀም ትእዛዝ ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ (የቀድሞው ህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሴኮቱሬ እንዳረጋገጡት) የኢትዮጵያ የምድር እና የአየር ኃይል የሕግ ማስከበር ስራውን በአጭር ጊዜ ካጠናቀቀ በኃላ በውጭ ሀገር የሚኖሩ የህወሓት አባላት አስፋልት ላይ ከመተኛት እስከ የጎዳና ላይ ትያትር እየሰሩ ሲያሳዩ ሰንብተዋል።

የቀድሞው ህወሓት በትግራይ ሕዝብ እንደ የልጆች መጫወቻ 'ጢባጥቤ' ሲጫወትበት ዓመታትን አስቆጥሯል።ጥቂት ቅምጥሎች ፍርፋሪ  ለተከታዮቻቸው እየወረወሩ እነርሱ ከአዲስ አበባ እስከ ዱባይ፣አውሮፓ እና አሜሪካ ስንደላቀቁ የትግራይን ሕዝብ ከኤርትራ እስከ አፋር፣ከአማራ እስከ ሱማሌ ድረስ ብልግና፣ግፍ፣እና ዝርፍያ በተሞላ ተግባራቸው ከማጋጨታቸውም በላይ ግልጥ የሆነ የዘር ፍጅት ሊያስነሱበት አሲረዋል። ሆኖም ሀገሩ ኢትዮጵያ፣ሕዝቡም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆነና በአስተዋይነት ሁሉንም  አለፈው።

አሁን በሕግ ማስከበሩ ሂደትን ተከትሎ በትግራይ ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ቁጥራቸው ብዙ እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግስት፣የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ባወጡት የተለያዩ መግለጫዎች አስታውቀዋል።ለክልሉ ዕርዳታ የማሰባሰብ ስራም በአርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ የሚመራው የግሎባል አልያንስ፣በናትናኤል አስመላሽ የተደረገው እና አደባባይ ሚድያን ጨምሮ ያስተዋወቀው የጎፈንድሚ የገንዘብ ማሰባሰብ እና ሌሎችም እየተካሄዱ ነው። በውጤቱም በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ እና በርካታ የምግብ እርዳታዎች ተገኝተዋል።እነኝህ ድጋፎች የአዲስ አበባ፣አፋር፣አማራ እና ሌሎች ክልሎች በራሳቸው እያሰባሰቡ ወደ ትግራይ የላኩት ጋር ሲደመር ችግሩን ለመቅረፍ የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።ይህም ሆኖ ግን አሁንም ተጨማሪ ዕርዳታዎች እንደሚያስፈልጉ ተነግሯል።በትግራይ ክልል ከአንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ሕዝብ በላይ በዘመነ ህወሓትም በምግብ ሴፍት ኔት የሚኖር እንደነበር የሰላም ሚንስትር በቅርቡ የክልሉን የግብርና መረጃ ጠቅሶ ማስታወቁ ይታወሳል።

ለማጠቃለል፣በትግራይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚገባ ይረዳል።ላለፉት ሶስት ዓመታት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ እስከ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፣ከጳጳስ እስከ ሙፍቲ፣ከሴቶች እስከ ወጣቶች ወደ መቀሌ ተጉዘው ጦርነት አይገባም፣በሰላም መነጋገር ብቻ ነው አማራጩ በሚል ህወሓት ተለምናለች።ህወሓት እና ጀሌዎቹ ግን ይህንን ሁሉ ልመና እረግጠው ከ20 ዓመታት በላይ በበርሃ ሆኖ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የኖረውን ወታደር በተኛበት ከመግደል ልብሱን እያስወለቁ እስከማባረር ደረሱ።ለ27 ዓመታት በመላዋ ኢትዮጵያ ህወሓት ያፈሰሰችው ደም ሳይበቃት ከቤተሰቡ ለዓመታት ተለይቶ በትግራይ የሚንከራተተው  የመከላከያ ሰራዊት ላይ የግፍ ግፍ ፈፀመች።ዛሬ ይህንን ግፍ በትግራይ ባለው ረሃብ ለማረሳሳት የሚሞክሩ በትግራይ ለደረሰው ረሃብ መንግስትን እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አመራርን ለመውቀስ ሲሞክሩ ትንሽ እፍረት አይሰማቸውም።መንግስት የሕግ ማስከበሩን ሥራ ባይሰራ ኖሮ መላዋ ኢትዮጵያን ኤርትራም ጭምር በደም ሊነክሩ እንደነበር የሚያውቅ ዜጋ ያለ አይመስላቸውም።አልቻሉም እንጂ ንፁሃን የባህርዳር፣ጎንደር እና አስመራ ነዋሪዎች ላይ ሮኬት ሲወረውሩ ዓላማቸው ንፁሃንን መፍጀት ነበር።ኢትዮጵያን ለመበትን ያልተሳካላት ህወሓት እራሷ ተበተነች። ስለሆነም የትግራይን ሕዝብ እንረዳለን።ትግራይን ለዛሬው ርሃብ ያደረሳት የኢትዮጵያ መንግስት ሳይሆን ኢትዮጵያን ሊበትን ሲሞክር የተበተነው ህወሓት እንደሆነም ጠንቅቀን እናውቃለን።ከ20 ዓመታት በላይ ሲጠብቀው የነበረ ወታደር በተኛበት ከገደለ በኃላ ''የኤርትራ ወታደር ገባ'' የሚለው ድምፅም ህወሓት ትግራይን ለእዚህ እንዳበቃት ሲናገር መሰማት አለበት። 
*******************

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...