Friday, September 30, 2016

´´የአማራ ብሔርተኝነት አገንግኖ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ እየወጣ ነው´´ ዋዜማ ራድዮ ውይይት ያዳምጡ።



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

የአሰብ አየር ማረፍያን እና ባሕር ኃይል ጣብያ በየመን ሁቲ ሺያት ሚሊሻዎች ተጠቅቶ ነበር Yemen’s Houthi forces attack Eritrea’s Airport, Navy base



Source = Sudan Tribune 

An Eritrean opposition group, Red Sea Afar Democratic Organization (RSADO) on Wednesday said that Yemen’s Houthi group have attacked the international Airport of Assab, a port city in the Southern Red Sea Region of Eritrea.
JPEG - 25.8 kb
A Houthi Shiite rebel carries his weapon as he joins others to protest against Saudi-led airstrikes at a rally in Sanaa, Yemen on 1 April 2015 (Photo: AP/Hani Mohamed)
Ibrahim Haron, leader of the armed opposition group told Sudan Tribune that Houthi forces stationed in the island of Hanish and Zagar have also attacked the headquarters of the Eritrean naval forces in Assab by firing mortar rockets thereby causing a serious damage.

The attack comes days after reports disclosed that Saudi Arabia has transferred some 5,000 Yemeni militants to Eritrea for military exercise in the Red Sea country.
According to the reports, Riyadh is transferring the militants from Aden to Eritrea’s Assab port to go under military trainings and then be sent to the Saudi provinces bordering Yemen to back the Saudi led war in Yemen.
The Eritrean government has dismissed the reports saying “a preposterous lie peddled for some ulterior motives”The opposition leader said Eritrean authorities have imposed a tight security cordon in the areas following Monday’s attack.
Ibrahim said Eritrea government motive to cooperate with the Saudi-led coalition is because Asmara has a long standing border dispute with Yemen.The countries had previously engaged in a bitter war with Yemen over the disputed Islands of Hanish and Zagar.
In 1998, the international Tribunal of the international Committee ruled the islands in favour of Yemen; Eritrea however refused to accept the ruling.He added that Eritrea had been serving as a base for military training for anti-Yemen groups in order to create destabilization and instability in Yemen and in the region at large.
“When the situation in Yemen changed and appeared new events and the emergence of coalition forces, Eritrea favoured the Arab coalition to ensure financial, political and military gains” Ibrahim told Sudan Tribune by telephone from the Eritrean-Ethiopian common border.

ERITREAN PILOT DEFECTS

Meanwhile the Eritrean opposition group today alleged that an Eritrean Air force pilot has defected to Saudi Arabia by flying a military Aircraft.According to opposition officials, the Eritrean pilot defected on Tuesday along with his two aides becoming the latest members of the Eritrean Air force to defect from the reclusive east African Sea nation.The Captain pilot and two of his aides flew to Jizan region in south of the Kingdom of Saudi Arabia.The defectors have asked for political asylum but it is not yet clear if the kingdom has grant them an asylum.

Ibrahim said the latest defection is a big blow to President Isaias Afeworki led regime.
He says it is an apparent sign of growing discontent of the air force personnel and the military against the oppressive region.In previous years, there have been defections in thousands from the Eritrean army, navy and air forces as the regime retains grip on power for over two-decades.President Isaias has been in power since the country gained independence from Ethiopia in 1993.

Sudan Tribune September 21,2016


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Tuesday, September 27, 2016

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ´´የወያኔ አገዛዝ እና የኢትይጵያ ወደፊት´´የሚለው ፅሁፋቸውን በተመለከተ የገቡኝ እና ያልገቡኝ ነጥቦች

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም 

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ሶስተኛው ትውልድ ላይ ሆነው የኢትዮጵያን ጉዳይ እድሜ ዘመናቸውን ያልተዉ እና አሁን በእርጅና ዘመናቸውም ለችግሮች መፍትሄ ያሉትን ከመስጠት የማይደክሙ ኢትዮጵያ በዘመናዊ ዘመኗ ካፈራቻቸው ጥቂት ትጉ  ምሁራን ውስጥ ናቸው።ዛሬም ፕሮፌሰሩ አሁን ኢትዮጵያ ለገባችበት የፖለቲካ ችግር መፍትሄ ያሉትን´´የወያኔ አገዛዝ እና የኢትይጵያወደፊት´´ በሚል ርዕስ በድረ-ገፃቸው ላይ አስነብበውናል።

ፅሁፉን አንብቤዋለሁ።የምስማማበት እና የማልስማማበት ወይንም የማያስኬድ ነው የምላቸው ነጥቦች አሉኝ።ነገር ግን ርዕሴን የማልስማማበት ከማለት ያልገባኝ በሚለው ማስቀመጡ የተሻለ እንደሆነ ተሰምቶኛል።ላለመስማማት ለማለት ፅሁፍ በእራሱ ሁሉንም ነገር አይገልጥም እና እርሳቸው ያዩበት የዕይታ ጥግ እና ምክንያቶቹን በደንብ ቃል በቃል እየጠየኩ የተረዳሁ ቢሆን ነበር።ሆኖም ግን ያ ባልሆነበት ሁኔታ አለመስማማት የሚለውን ያልገባኝ የሚለው አገላለፅ የተሻለ ሆኖ ተሰምቶኛል።
የፕሮፌሰር መስፍን ፅሁፍን ባጠቃላይ ዋና መልዕክቱን በሶስት ነጥቦች የሚጠቃለል ይመስለኛል። እነርሱም : -

1/ የወቅቱ ጥያቄ ወያኔን ማውረድ ነው ግን ትግራይን ካላሳተፈ ለውጡ  ውጤታማ አይሆንም፣

2/ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የሕወሓት ባለስልጣናት ከሚመሰረተው  ነፃ የተወካዮች ምክር ቤት ዋስትና እና የኑሮ ድጎማ ማግኘት  እና

3/ የትግራይ ሕዝብ ከሕወሓት ወይንም ከኢትዮጵያዊነት አንዱን ይምረጥ።ኢትዮጵያዊነቱን ቢመርጥ ይሻለዋል።የሚሉት ናቸው።

1/ የወቅቱ ጥያቄ ወያኔን ማውረድ ነው ግን ትግራይን ካላሳተፈ ለውጡ ውጤታማ አይሆንም 

የወቅቱ ጥያቄ ወያኔን ማውረድ ነው። ትክክል ነው።ይህ እራሱ ወያኔ በተግባሩ ሕዝቡን ገፍቶ ያመጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ የህልውና ጥያቄ ነው። ትግሉ የትግራይን ሕዝብ ማሳተፍ እና ወያኔን ማሳተፍ በሚለው መካከል ትክክለኛ መስመር ቢሰመርበት ግን ጥሩ ነው ባይ ነኝ።ምክንያቱም የትግራይ ህዝብን ችግር ከኢትዮጵያ ችግር ጋር እንዲቆላለፍ ያደረገው ሕወሓት መሆኑ እስከተገለፀ ድረስ የትግራይ ችግር ከሚባል የሕወሓት ችግር ተብሎ ቢጠቀስ የበለጠ ገላጭ ይሆናል።ይህ ማለት ትግራይን ማሳተፍ እንደ ሀገር አካል የሚለውን እሳቤ በሚገባ ያሳያል ማለት ነው።

ፕሮፌሰር በፅሁፋቸው ላይ ´´ኢትዮጵያን በትግራይ ገመድ፣ ትግራይን በኢትዮጵያ ሰንሰለት አስሮ የያዘው ወያኔ ገመድና ሰንሰለቱን እንዲበጥስና ሁለቱም ነጻ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? ወይም ትግራይንም ሆነ ኢትዮጵያን ሳይጎዳ ገመዱንና ሰንሰለቱን መበጠስ የሚችል ሌላ ማን ነው?የሚል ነው፡፡´´ ይላሉ።እዚህ ላይ ሁለቱንም ነፃ ማድረግ የሚለው መፍትሄው ህወሓት ተነጥሎ ሲመታ ወይንም እራሱን ሲያከስም ነው። ለማክሰምም ሆነ ለመመታት ደግሞ የትግራይ ሕዝብ እራሱን ከሕወሓት በፈቃዱ ለይቶ ፕሮፌሰር መጨረሻ ላይ እንደጠቀሱት ኢትዮጵያዊነቱን ሲያስበልጥ እና በፖለቲካም ሆነ ምጣኔ ሀብት ለእራሱ ከማድላት አስተሳሰብ ወጥቶ  እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል እኩል ተሳታፊ ሲሆን ነው።

በወያኔ ማውረድ ጥያቄ ውስጥ ግን ሰላማዊ ትግል ነው ወይንስ የትጥቅ ትግል የሚል ብዥታ በአሁኑ ወቅት አለ ብዬ አላምንም።የሰላማዊ ትግል ሁሉንም በአንድነት በተቀናጀ መልክ ማሳተፍ ከቻለ እና ፅናትን ካሳየ አዋጭ ለመሆኑ የሚከራከር የለም። ሆኖም ግን በወራት ውስጥ በሺህ የሚቆጠር አስከሬን ለሚከምር ወያኔ የሰላማዊ ትግል ነው ወይንስ ትጥቅ ትግል የሚል ክርክር ከቆመ ቆይቷል።ስለዚህ ብዥታው አለ የሚለው አባባል አልገባኝም።በሌላ በኩል ለውጡ ትግራይን ማሳተፍ አለበት አዎን!ነገር ግን የግድ ወያኔ በየትኛውም መልክ ማለትም በፖለቲካ፣በምጣኔ ሃብት ወይንም በማኅበራዊ መልክ ለውጡ ላይ የመሪነት ሚና ሊኖረው አይገባም።ይህ የመሪነት ሚናውን ያጎላዋል የሚለው ስጋቴን የሚያጠናክረው ፕሮፌሰር በመቀጥለው ተራ ቁጥር  2 ላይ በጠቀለልኩት ሀሳባቸው ውስጥ ነው።

2/ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የሕወሓት ባለስልጣናት ከሚመሰረተው ነፃ የተወካዮች ምክር ቤት ዋስትና እና የኑሮ ድጎማ ማድረግ   

ፕሮፌሰር በፅሁፋቸው ላይ  በሚመሰረተው ነፃ የተወካዮች ምክር ቤት ላይ ተጣርቶ የተገኘው ሀብት እንዴት እንደሚከፋፈል ሲገልፁ 
´´ተጣርቶ የተገኘው ሀብት (የማይንቀሳቀስ ንብረትን ጨምሮ) እንደሚከተለው ሊደለደል ይቻላል፡– ይህ መነጋገሪያ ሀሳብ ብቻ ነው፡–
- ለትግራይ ልማት፤
- ለሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች ልማት፤
- ለትግራይ የጦር ጉዳተኞች፤ ለእያንዳንዳቸው መጠነኛ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣
- ለትግራይ የሟች ቤተሰቦች፤ ለእያንዳንዳቸው መጠነኛ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣ 
- ለሌሎች ኢት. የሟች ቤተሰቦች፤ ለእያንዳንዳቸው መጠነኛ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣
- ለሌሎች ኢትዮጵያውያን የጦር ጉዳተኞች፤ ለእያንዳንዳቸው መጠነኛ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣
- ለወያኔ መሪዎች፤ ለመኖሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጡረታ መስጠት፤´´ ይላሉ።

እዚህ ላይ ገና ባልተሠራ ሥራ ላይ ምቀኝነት ልገልፅ አይደለም።ነገር ግን ይህ ሃሳብ ባጭሩ ወያኔ በአገር ውስጥ እና በውጭ ያለውን ሀብት በሰላም መልሶ እንደገና እንዲደለደል ይፈቅዳል ከሚል እሳቤ የመነጨ ይመስላል።እሺ! እንደተባለው ሆነ እንበል።የወያኔ መሪዎች የሚጠየቁበት እልቆ መስፈርት የሌላቸው በኢትዮጵያ ላይ እንደ አገር የተፈፀሙ ወንጀሎች ጉዳይስ? እንዲሁ በደምሳሳው ይታለፉ? አሁንም እሺ እንደተባለው ወንጀሉ ሁሉ ተትቶ ፕሮፌሰር እንዳሉት  ´´ለወያኔ መሪዎች መኖርያ እና ጡረታ መብት ተሰጣቸው´´ እንበል።ይህ ለመጪው ትውልድ  ምን ያስተምራል? ነገ ማንም በጎሰኝነት ተነስቶ የፈለገውን ያህል ዘርፎ እና አገር አጠራምሶ ጡረታ እና መኖርያ እየሰጠን እናኑረው ? ወይንስ በትክክለኛ ዳኝነት በነፃነት እና ምንም አይነት የሰብአዊ መብቱ ሳይጣስ ለፍርድ ቀርቦ ክፍት በሆነ ችሎት እንስማ እና የህሊና ዳኝነት  ወስደን የታመመውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁስል እናድን? የመፍትሄ ሃሳቡ በእራሱ አልገባኝም። ያጠፋ ሰው ገና ለፍርድ ቀርቦ ጉዳዩ ሳይታይ የጡረታ እና ድጎማ መቁረጥ ላይ ከሄድን ፍትሃዊነትን እንደናፈቅን ሌላ ክ/ዘመን ልንዘልቅ አይደለም ወይ?

በሌላ በኩል የትግራይ ልማትን ከቀሪው ኢትዮጵያ ጋር በእኩል ድርድር የቀርቡበት መንገድ ግልፅ አይደለም።የመጪዋ ኢትዮጵያ ናፍቆታችን እኩልነት የሚያስተዳድረን መንግስት የማግኘት ነው እንጂ አሁንም የኢትዮጵያ ሌሎች ክልሎችን ከትግራይ ጋር እየመዘነ  የሚያስቀምጥ መንግስት አይደለም።ለምሳሌ ተጣርቶ ከተገኘው ሀብት ሲደለደል ለትግራይ ልማት፣ብሎ ለተቀረው የኢትዮጵያ ክልል ልማት የሚለው አገላለፅ በእራሱ ግልፅ አይደለም። ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ነች።ኢትዮጵያዊነት በትግራይ ይገለፃል።ትጋራይነትም በኢትዮጵያ ይገልፃል ካልን ለምንድነው የኢትዮጵያ ሀብት እኩል ለጋምቤላውም  ሆነ ለሱማሌው ስናከፋፍል የትግራይንም በተርታ አስቀምጠን በነባራዊ ሁኔታ የማናየው? በመጪው ምክር ቤትም የትግራይ ልማት በእራሱ አንድ አጀንዳ ሆኖ ከኢትዮጵያ በተዘረፈው ንብረት  ቅድምያ ተቀምጦ የተቀረው በሚል ስማቸው ያልተጠቀሱ የኢትዮጵያ ክልሎች ተብለው መቀመጣቸው እራሱ ምቾት ይሰጣል ወይ? ይህንን አካሄድ እራሱ የትግራይን ሕዝብ ወደነበረበት የተሳሳተ የአስተሳሰብ ጥግ የሚገፋ አይደለም ወይ? ደግሞስ ላለፉት 25 ዓመታት በትግራይ የተሰራው ልማት ትግራይ ለማዕከላዊ መንግስት ባስገባችው የቀረጥ ልክ ነው እንዴ? ብሎ ሂሳብ ውስጥ የሚገባ ቢነሳ መልሱ ምን ይሆናልና ነው በመጪው ምክር ቤትም ላይ የትግራይ ልማት የኢትዮጵያ የብቻ እና ዋናው ጉዳይ ሆኖ ከሌላው ቀሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልማት ጋር እኩል ሚዛን የሚቀመጠው።እዚህ ጋር እኩል ሚዛን ስል በተናጥል እንጂ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ልማት ተመጣጣኝ የሀብት ድልድል መኖር የለበትም እያልኩ አይደለም።ሚዛኑ ግን  አልገባኝም።

3/ የትግራይ ሕዝብ ከሕወሓት ወይንም ከኢትዮጵያዊነት አንዱን ይምረጥ።ኢትዮጵያዊነቱን ቢመርጥ ይሻለዋል።

ይህ ጥሩ ሃሳብ ነው።እንዲያውም የእዚህ አይነቱ ሥራ እና ምክር ላለፉት አስር ዓመታት በደንብ ተደርጎ በተለይ ለትግራይ ሀገር ወዳድ  እና ወያኔ ወለድ ምሁራን መነገር ነበረበት።ዛሬ ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ እጅ እና እግሩን በጥቅም እና ሌላው ኢትዮጵያዊ ሊያጠፋህ ነው የሚል የማስደንበርያ  ንግግር ግራ ሳይጋባ ቢሆን ባማረ ነበር። አሁንም ግን ይህ መነገር ያለበት በኢትዮጵያዊነቱ አምኖ ነገር ግን በማንነቴ በሕወሓት ተረገጥኩ ለሚለው ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን ለእራሱ ህወሃት ሕልውናዬ ነው በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ለሚባዝነው  የትግራይ ሕዝብ ነው። እዚህ ላይ ፕሮፌሰር ያስቀመጡት አማራጭ ልብ ላለው በጣም ትክክለኛ ይመስለኛል።ኢትዮጵያዊ ነትን በማፅናት እና የትግራይ ብሔርተኝነትን በትዕቢት በማቀንቀን መካከል ያለው ትርፍ እና ኪሳራ በትትክል ተቀምጧል። ፕሮፌሰር የትግራይ ሕዝብ ያለውን ሁለት ምርጫዎች ሲያስቀምጡ እንዲህ ብለዋል - 

ምርጫ አንድ፡ የትግራይ ሕዝብ እንደጥንቱ እንደጠዋቱ ታሪኩን ይዞ በኢትዮጵያዊነቱ ይቀጥላል፤ በኢትዮጵያዊነት ታሪኩ በግምባር-ቀደም ተሰልፎ በፖሊቲካም ሆነ በመንፈሳዊ ጸጋው የኢትዮጵያዊነት ግዴታውን ይወጣል፤ ይህ ምርጫ የኢትዮጵያዊነት ግዴታ ነው፤ ይህ ምርጫ ታሪካዊ ግዴታ ነው፤ ይህ ምርጫ የዜግነት ግዴታን ከጎሣ ግዴታ ማስቀደም ነው፤ ይህ ምርጫ ከጨለማው ዘመን ወጥቶ ወደሃያ አንደኛው ምዕተ-ዓመት መሸጋገር ነው፤ ከሁሉም በላይ ይህ ምርጫ የሰፊ ሀብት ባለቤትና የመቶ ሚልዮን ዜጎች ማኅበረሰብ አባል ያደርጋል፡፡
ኢትዮጵያ የትግራይ ነች፤ ስለዚህም ትግራይ ኢትዮጵያን ነች፤ ሁለቱ አይለያዩም፤ ይህንን ወያኔም በሚገባ የተረዳው ይመስላል፤ አለዚያ ከጎንደር፣ ከላስታም፣ ከራያም፣ ከጎንደርም … የሚለቃቅመው ለምንድን ነው!

ምርጫ ሁለት፡ የትግራይ ሕዝብ የወያኔ መሣሪያ እንደሆነ ይቀጥላል፤ ይህ ሲሆን ትግራይ በመሠረቱ ከኢትዮጵያ ይገነጠላል ማለት ነው፤ በትግራይ ዙሪያ ኤርትራ በሰሜን፣ በደቡብ ደግሞ ጎንደር፣ ወሎና አፋር ይገኛሉ፤ ወያኔ ሆን ብሎ ትግራይን ከኤርትራ፣ ከጎንደር፣ ከወሎና ከአፋር ጋር አጋጭቶ ደም እንዲቃቡ አድርጓል፤ (በትግራይ ዙሪያ ያሉትን ብቻ ለማንሳት ነው እንጂ ከጂጂጋ እስከጋምቤላ፣ ከወሎ እሰከሲዳሞ ቦረና የግፍ ጠባሳዎች አሉ፤) ስለዚህም ትግራይ በወያኔ ስር ሆኖ ከአነዚህ ከከበቡትና በጠላትነት ከተፋጠጡት ሕዝቦች ጋር ዘለዓለም ሲቆራቆዝ ሊኖር ነው፤ ዙሪያውን ካሉት ሕዝቦች ሁሉ ጋር መቆራቆዝ የትግራይን ሕዝብ ያደኸያል፤ የትግራይ ሕዝብ መሸሻ ስለሌለው በአጥንቱ እየሄደ የወያኔ አገልጋይ ይሆናል፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ በምሥራቅ በአሰብ በኩል፣ በምዕራብ በጎንደር በኩል የልማትና የጋራ ደኅንነታቸውን ይመራሉ፤

ባጠቃላይ ፕሮፌሰር ያቀረቡት ሃሳብ ከብዙ አስተሳሰቦች አንፃር አንዳንድ አከራካሪ ነጥቦች ቢኖሩበትም ለትግራይ ሕዝብ ምናልባት የኢትዮጵያን የነፃነት እና የእኩልነት ጥያቄ  ላይ ከምሩ ማሰብ እና ሕወሓት አይኑን አስሮ ወደሚመራው ገደል መግባት እንደሌለበት የሚያሳየው ሌላው ትልቅ የደውል ማንቂያ ነው። የትግራይ ሕዝብ በሆይ ሆይታ በታጠቀው መሳርያ የትቢት ፕሮፓጋንዳ የሚነዙለት ሕወሐቶች የስልጣን ወንበራቸው ሲያጋድል  እንዴት ጥለውት እንደሚሄዱ እና የሚቀረው ነገር ከቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ያጋጩት ቁርሾ ብቻ እንደሚሆን ማወቅ አለበት። ዛሬ ወንበር ላይ ተቀምጠው የምናያቸው እነ አባይ ፀሐዬ፣ አባይ ወልዱ ሳምሶናይታቸውን ይዘው ትተውት እንደሚሄዱ የትግራይ ሕዝብ ካላመነ ከታሪክ አልተማረም ማለት ነው። ኮ/ል መንግሥቱም አገር ትተው ይሄዳሉ ብሎ የሚያምን የቀድሞ ሰራዊት አባልም ሆነ ኢትዮጵያዊ አልነበረም። ግን ሆኗል።በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ ፕሮፌሰር የጠቀሱትን ምርጫ አንድ ማለትም ኢትዮጵያዊነትን ተቀብሎ  በኢትዮጵያዊነት ታሪኩ በግምባር-ቀደም ተሰልፎ በፖሊቲካም ሆነ በመንፈሳዊ ጸጋው የኢትዮጵያዊነት ግዴታውን መወጣት የወቅቱ ጥያቄ ነው።እዚህ ላይ ግን የትግራይ ሕዝብ አለመሳተፍ የትግሉን ዋጋ ያንረው እንደሆነ እንጂ  በማንኛውም ወጪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነቱን ይቀዳጃል።ይህ እንደማይቀር ህዝቡ የቆረጠበት ደረጃ በእራሱ አመላካች ነው። የናዚዎች ፈቃደኝነት የዓለምን ሕዝብ ለነፃነት እንዳላበቃው ሁሉ የጥቂት ሕውሐት አመራሮች እና አቀንቃኞቻቸው ፍቃደኛ አለመሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ በነጻነቱ ድል ከማድረግ አያግደውም።


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Monday, September 26, 2016

ሰበር ዜና - አቡነ አብርሃም በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት በአደባባይ ገሰፁ።Ethiopian Orthodox Tewahido Church synod member and Archbishop Abune Abraham strongly criticised the current regime of Ethiopia.


አቡነ አብርሃም የምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

አቡነ አብርሃም የምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ መስከረም 16፣2009 ዓም በባህርዳር በተከበረው የደመራ መስቀል በዓል ላይ ለተሰበሰበው ምዕመን ስለ እውነት  በአደባባይ መስክረዋል። በአሜሪካ የዲሲ እና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም የነበሩት አቡነ አብርሃም በእዚሁ  አገልግሎታቸው በምእመናን በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ፍቅርን አትርፈው እንደነበር ብዙዎች ይመሰክራሉ። በተለይ በምእመናን መካከል የሚነሱ ግጭቶችን በማስታረቅ እና መናገር እና መስማት የማይችሉ ወጣቶች መንፈሳዊ አገልግሎት በምልክት እንዲማሩ ያደረጉት ጥረት ተጠቃሽ ነው።ከአሜሪካ አገልግሎታቸው በመቀጠል የምስራቅ ሐረርጌ እና የጅጅጋ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው አገልግለዋል።በአሁኑ ወቅት የምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናችው።

አቡነ አብርሃም በዛሬው የባህር ዳር ደመራ ላይ ከመሰከሩት እውነት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል። 
´´ 
´´ችግሩ ያለው ከመሪዎች እንጅ ከተመሪ አይደለም ....መንግስትን ና የራሱን ሚድያ ገስጹ የህዝብ ጥያቄ መመለስ አለበት ....እኔ ከመፍራቴ አንጻር በዓሉ ባይከበር ደስተኛ ነበርሁ ነገር ግን አባቶቼን ሳይ በየሳምንቱ ቢከበርም አይቆጨኝም።ትናንት አስከሬን እያወጣ አልቅሱ ሲለን ነበር።.....የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት። .....ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም።....በየሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለብት ። ......እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም።እኛ የተናገርነውን ትቆራርጡ ታቀርቡ እና ምእመኑ ምን አባት አለን እንዲል ታደርጋላችሁ። ክርስቲያን እውነት ይናገራል።.......ለእዚች አገር መጠበቅ ቤተ ክርስቲያን አስተዋፅኦ ትልቅ ነው።ቤተ ክርስቲያን ስለ ወታደርም ትፀልያለች።ሕዝብ የሚጠብቁትን ጠብቅ እያለች የምትፀልይ ይህች ቤተ ክርስቲያን ነች።ስለዚህ ልትደመጥ ይገባታል።አንድ ሰው ባልሰራው ከታሰረ፣እግዚአብሔርስ እንዴት ዝም ይላል።ሁላችንም እንደወንድምነት እንተባበር። ስንት ወገናችን በበረሃ አለቀ።........ዛሬ ስጋት ነው።አሁን የመጣው ሕዝብ ለሃይማኖቴ ልምጣ ብሎ የመጣ እንጂ ማንም ይጠብቀናል ብሎ አይደለም የመጣው።......

........ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው። .....ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን? የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም። .....ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልይ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ። ´´ የሚሉ ይገኙበታል።

አቡነ አብርሃም ይህንን ሲናገሩ ምእመናን በእልልታ እና በእንባ ስሜታቸውን ይገልፁ ነበር።ከዛሬው የባህርዳር ደመራ በኃላ አቡነ አብርሃም ሕዝብ ወደ ቤቱ ሳይገባ እኔ አልገባም በማለት ህዝቡ ከሄደ በኃላ በእግራቸው ወደ ቤታቸው በፖሊስ ታጅበው ሄደዋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ አባል ደረጃ በመስቀል ደመራ ላይ አሁን በስልጣን ላይ የሚገኘው የሕወሓትን መንግስት በግልጽ ስገሰፅ የአቡነ አብርሃም የመጀመርያው ይሆናል። አቡነ አብርሃም እናከብርዎታለን።በእዚህ የመከራ ዘመን ለኢትዮጵያ እንደ አቡነ ጴጥሮስ በአደባባይ ስለ እውነት የመሰከሩ ምስክር ሆነዋልና።እርስዎ የተጋረደውን አዚም ገፈውታል።ፈለግዎን ተከትለው ሌሎች አባቶችን ድምፅ አሁንም በብዛት መስማት እንፈልጋለን። ድምፅ ብቻ አይደለም ምእመኑን በመከራው ሰዓት አብረው እየተንገላቱ የሚያፀኑ ካህናት መብዛት አለባቸው።

አቡነ አብርሃም ያደረጉት ንግግር ኦድዮ ለመስማት ይህንን ይጫኑ ።


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Sunday, September 25, 2016

አዲስ የሽምቅ ተዋጊ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ተመሰረተ መንግስት የመቀየር ዓላማ አንግቧል። NEW REBEL MOVEMENT FORMED IN SOUTH SUDAN


September 25, 2016 (JUBA) - South Sudan’s former minister of agriculture minister, Lam Akol, has formed a new rebel faction after spending several weeks of consultations with different unarmed and armed opposition parties in the country.

Lam Akol, chairman of South Sudan’s main opposition party (AFP/Samir Bol Photo)

Akol, according to a statement issued over the weekend and extended to Sudan Tribune has named the new rebel group as National Democratic Movement (NDM) and said that his aim is to overthrow by all means the government of South Sudan under the leadership of President Salva Kiir.

“The National Democratic Movement was born to wage the struggle, together with others in the field, against the totalitarian, corrupt and ethnocentric regime in Juba that is bent on dragging our country into the abyss,” the statement reads in part.

Akol, who previously chaired the Democratic Change Party (DCP) said he resigned and left the party last month because the members and the other leaders of the DCP believed in peaceful dialogue and non-violence as the only means to bring about change in South Sudan.

He described his new rebel faction as a front bringing together the social and democratic political forces as well as civil society activists, who want the political discourse in the country to be centred on the “transformation of the centuries-old conditions of extreme poverty, ignorance, illiteracy and cultural backwardness of the masses of our people.”

The movement, it explained, is founded on the principles and concept of national democratic revolution based on the core values of freedom, equality, justice and fraternity, and solidarity anchored in historical and philosophical perspectives. These values, it stressed, translate into fundamental rights and freedoms as provided for in the UN Conventions of civil, political, economic, social and cultural rights.

The political statement of the NDM set out in details what the NDM stands for and how to rid the people of the totalitarian ethnocentric regime in Juba and replace it with a pro-people inclusive government.

“It must be clear from the outset, the NDM is not just for change of personalities in Juba to replace them with others of the same feathers; it is out for a radical change in the country that will bring about genuine state-building and nation-building,” it emphasized.

He also said his new faction will closely work with the Sudan People’s Liberation Movement (SPLM-IO) under the leadership of the former First Vice President, Riek Machar.

It is not clear from whether the prominent politician will get military forces for his new faction.

(ST)

Source - Sudan Tribune, September 25,2016 


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Wednesday, September 21, 2016

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የት-መጣነት(origin) ጉዳይ ባደረጉት ጥናት ላይ የተደረገ ቃለ መጠይቅ (ኦድዮ)

ከእዚህ በታች ያለው ጽሁፍ እና የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ (ኦድዮ) በጉዳያችን ገፅ ላይ ከሶስት አመታት በፊት ማለትም በ2005 ዓም  ተለጥፎ ነበር። ዛሬ እንደገና ቃለ መጠይቁን ማውጣቱ አስፈላጊ ሆኗል።በአሁኑ ወቅት የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በእዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ ያነሳቸውን ነጥቦች በመጽሐፍ አትሟቸዋል።
=======================================
  
''እኛ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ሕዝብ ነን።እራሳችንን ዝቅ ማድረግ አይገባንም።ለምን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለች አሁን? ይህ ማለት ኢትዮጵያን ያስጠሩ ሰዎች ቀድመው ነበሩ ማለት ነው።......ቀድሞ 'ኢትዮጵ' የሚባል ሰው ስለነበረ ነው።ለሀገር ሲሆን 'ኢትዮጵያ' አሰኛት እናም ከእርሱ ዘር የተወለድነው ሁሉ ኢትዮጵያውያን እንባላለን።እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ጃማይካ ነኝ ወዘተ ብልም ሃቁ እንዳፈጠጠ አለ።ይህ ሰው የኢትዮጵ ልጅ ስለሆንኩ እኔ ሁላችንም ብታምኑም ባታምኑም፣ብትክዱትም ባትክዱትም  ሁላችንም የእርሱ ልጅ ነን።እርሱ ከየት መጣ ለሚለው በሚወጣው መፅሐፌ ላይ ተዘርዝሯል። እኛ ኢትዮጵያውያን ከየት እንደመጣን ከስር መሠረታችን የሚታወቅ እንጂ ሜዳ ላይ የተጠልን አይደለንም።ማንነታችን በትክክል የተመዘገበ እና የታወቀ ከማንም በላይ በእዚህ ምድር ላይ ከአይሁዳውያንም ቀዳሚ ነን።''

በመቀጠል ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ስለ ኩሽ፣ሴም፣ሰለሞናውያን ስርወ-መንግስት፣ስለ የኦሮሞ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግስና ታሪክም ሆነ የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ የነበረውን ታሪክ ሁሉ በሰፊው ተንትነዋል።''ለእዚህ ሁሉ ታሪክ ማስረጃ ምንድነው?'' ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ መልሰዋል- 

''ታሪኩ እስከ ዛሬ አንድ ሺህ አመት ድረስ  በደንብ ይታወቅ ነበር።ዮዲት ጉዲት ስትነሳ መፃህፍትን ሁሉ ስታጠፋ እና  የአክሱም መንግስት ሲፈርስ 'አክሱማይ ሲራክ'  የተባለ ሰው  ፅሁፉን ይዞ ወደ ኑብያ(የአሁኗ ሱዳን) ተሰዶ እዝያው ሞተ።በኃላ ንጉስ ላሊበላ ከኢየሩሳሌም ስደት ሲመለስ መፅሐፉን ከኑብያ ወስዶ አፃፈው።በኃላ ግን የግብፅ ጳጳሳት ታሪኩን ለማስጠፋት ብዙ ሰሩ።አንዱ ምክንያታቸው መፅሐፉ ከጥንት የኢትዮጵያ ታሪክ ጀምሮ እስከ ዮዲት መነሳት ጊዜ ብቻ የሚናገር ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ ማስተማር ሳይጀምር ለኢትዮጵያውያን ለሶስት አመት ያክል ቀ 22 ዓመቱ እስከ 25 አመቱ ድረስ ማስተማሩን በትክክል ይናገር ነበርና ነው።በእዚሁ መሳደድ ዳግም መፅሐፉን ይዘው አባቶች ወደ ኑብያ ተሰደዱ። ......መፅሐፉ የዛሬ 50 አመት ገደማ አንድ መነኩሴ ኑብያ ከፈራረሱ ህንፃዎች መካከል ሱዳናውያን የጥንት መፃህፍት መኖራቸውን ነገረዋቸው አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ አመጡት።ከእዛ ወዲህ በተቆራረጠ መልክ መፅሐፉ ታትሟል።'' ብለዋል።
የታሪክ ምርምር ቀጣይ ነው። ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በማስረጃ የተደገፈ የምርምር ውጤታቸውን አቅርበዋል።በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ እራሱን የቻለ መረር ያለ ምርምር ማስፈለጉን የሚያመላክት ነው።ቃለ ምልልሱ ሙሉውን በአንክሮ ሊሰሙት የሚገባ ነው።ያዳምጡት።
 የቀድሞው የኢቲቪ ዝነኛ ጋዜጠኛ ብዙ ወንድማገኘሁ  በፓልቶክ ስሟ (ሙያዬ) አወያይነት ይህ ዶ/ር ፍቅሬ ያደረጉት ቃለ መጠይቅ የተካሂደው  በኢትዮጵያ የመወያያ መድረክ ፓልቶክ (ECADF)  ነው። 
በቃለ መጠይቁ መጀመርያ ላይ የሚሰማው ፉከራ እና የእንግሊዝኛ ንግግር  የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ነው የቃለ መጠይቁ አካል ስለሆነ በትዕግስት ማዳመጡን ይቀጥሉ።





ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Tuesday, September 20, 2016

መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ሀብተየሱስ የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ጳጉሜን 5፣2008 ዓም ወቅታዊውን ሁኔታ አስመልክተው ያስተማሩት ትምሕርት



መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ሀብተየሱስ የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ጳጉሜን 5፣2008 ዓም በኦስሎ፣ኖርዌይ  በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ እና የኢትዮጵያ የጋራ መወያያ መድረክ በፒ ሆቴል ያዘጋጁት የ2009 ዓም የአዲስ ዓመት መቀበያ እና የኢትዮጵያ ቀን በሚል ተዘጋጅቶ  በነበረው የውይይት እና የፀሎት መርሃ ግብር ላይ የሰጡት ትምሕርት።
በቪድዮ መሃል የሚመጣው ተንቀሳቃሽ ምስል  በዕለቱ የቀረበው ጭውውት አካል ነው።በትምሕርቱ መሃል በመታየቱ በቅድምያ ይቅርታ እንጠይቃለን።



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አሁን ያለውንም ሆነ መጪውን ትውልድ የሚያስተምሩ እና የሚታደጉ ሑለት ሕጎችን ማውጣት አለበት።

የኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ====== ከጉዳያችን ===== መነሻ ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ታሪክ፣የረጅም ዓመታት የመንግስት ሥሪት እና የትውልዶቿ ያልተቋረጠ ተጋድሎ ውጤት ነች። ኢትዮጵያ እንዳትኖር፣እንድትበታተን እና የማ...