Saturday, November 30, 2019

አቶ ለማ መገርሳ መደመር እና የኢሕአዴግ ውህደትን አስመልክተው ለቪኦኤ የሰጡት ቃለ ምልልስ ምክንያት ምንድነው? በቀጣይስ ምን ሊከሰት ይችላል?

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ እና አቶ ለማ መገርሳ 

ጉዳያችን / Gudayachn
ህዳር 20/2012 ዓም (ኖቬምበር 30/2019 ዓም)

ዓርብ ህዳር 19/2012 ዓም ምሽት ላይ  ቀደም ብሎ ሐሙስ ዕለት በኦስሎ፣ኖርዌይ ጃዋር መሐመድ የሰበሰባቸው የኦሮሞ ኮሚኒቲ አባላት መካከል በኦሮምኛ ከፊት በኩል የተቀመጡ አንዲት እናት የተናገሩትን ድምፁን በመሃል እያቆመ ኦስሎ የሚኖር የኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ወዳጄ እየተረጎመ ያሰማኝ ነበር።እኝህ እናትበጣም አክራሪ ብሄርተኛ እንደሆኑ ከወዳጄ ትርጉም ተረድቻለሁ።በንግግራቸው  ጀዋርን ይወቅሱታል።ጀዋርን የሚወቅሱት ደግሞ ለማ ብቻውን ሆኖ ሳታግዘው መቅረትህ ብቻውን እንዲሆን አርገህ፣ካሉ በኃላ ዓቢይ ማኅበረሰባቸውን (የኦሮሞን ማለት ነው) እንደከዳ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያወራሉ።በመሃል ላይ ንግግራቸው በመርዘሙ ራሱ ጃዋርም እየሳቀ ያያቸው ነበር።አሁንም ይሄው ወዳጄ እንደተረጎመልኝ በቃዎት ሰዓት አበቃ ተብለው ነው ማይኩን የሰጡት።የእርሳቸው ንግግር ግን የውስጥ አዋቂ ንግግርም ይመስል ነበር።ከእዚሁ ወዳጄ ጋር እንዴት ዓብይን በእዚህ ደረጃ እንደከዳ ይቆጥሩታል? በማለት ጥያቄ ሰነዘርኩ። 

ቪድዮውን ማየት ቀጠልኩ በእዚሁ በጃዋር ስብሰባ ላይ የትግራይ ማኅበረሰብ በኖርዌይ ሰብሳቢ አቶ ዳዊት በአማርኛ ንግግር እንዲያደርግ ዕድል ተሰጠው።አቶ ዳዊት ንግግሩን ሲጀምር ከተሰብሳቢዎቹ አንዱ ድምፁን ከፍ አድርጎ ''በትግርኛ ተናገር!'' ብሎ ሲናገር በቪድዮው ውስጥ ይሰማ ነበር።ዳዊት ለጥቂት ሰኮንዶች ንግግሩን ቆም አደረገ እና በአማርኛ ቀጠለ። ዳዊት ተሰብሳቢው እና እርሱን የሚያገናኘው አማርኛ መሆኑ ገብቶታል።ዳዊትን ከእዚህ በፊት ሁለት ጊዜ  ኦስሎ ውስጥ በተደረጉ  የማኅበረሰብ ስብሰባዎች አግኝቼዋለሁ።አድ ጊዜ የኢትዮጵያን የጋራ መድረ በኖርዌይ ባዘጋጀው የሁሉም የፖለቲካ አተያዮች መድረክ ላይ ሲሆን ሌላው በቅርቡ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በኖርዌይ ባዘጋጀው ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነበር።ከእርሱ ጋር  በሃሳብ የማንስማማባቸው ብዙ ነጥቦች ዙርያ ተከራክረናል።ስንከራከር ግን ስርዓት ባለው መልክ ስለነበር የዳዊት ሃሳብ አቀራረብ ከብዙ የህወሓት ደጋፊዎች የተሻለ አቀራረብ ያለው ግን  ያንኑ በመደጋገም የሃሳቡን ስፍራ ላለመልቀቅ የሚሟገት ሰው ነው።በጀዋር ስብሰባ ላይ መገኘቱ እና ንግግር ሲያደርግ በቪድዮ ላይ ሳየው ግን በቅርቡ ስለሞቱት ሰማንያ ስድስቱ ኢትዮዮጵያውያን አንስቶ ጀዋርን ተጠያቂ እንደሆነ ይነግረዋል ብዬ አስቤ ነበር። አላደረገውም።

ወደ አቶ ለማ ጉዳይ ልመለስ።የኦስሎው ስብሰባ ላይ ለማን እያሞገሱ ከተናገሩት ሴት መለስ ስል የማኅበራዊ ሚድያው አቶ ለማ የመደመር ሃሳብ እንዳልተቀበሉ ገለጡ የሚል ዜና ተለጥፎ አየሁ።ወደ ቪኦኤ ገፅ ስገባ ዜናውን አረጋገጠልኝ።ግን ሙሉ ዜናው ስላልነበር ምንም ለማለት አላስቻለኝም። ዛሬ ምሽት ግን ቪኦኤ አማርኛው ሙሉውን ዘገባ ለቆታል። በዘገባው ላይም አቶ ለማ የመደመር ሃሳብ ከመጀመርያው እንዳልተቀበሉት እና እንዳልገባቸው፣ይልቁንም ጉዳዩ የኦሮሞ ሕዝብ  አምኖ የሰጣቸውን እንደመክዳት እንደሚቆጠር ገልጠዋል።የአቶ ለማ ንግግር ለምን ቀድሞ አልተነሳም? በውህደቱ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይስ  ድምፃቸውን ሲሰጡ ለምን ተቃውሞ አልተነሳም? በተለይ ዛሬ ዘሐበሻ ዜና ላይ እንደዘገበው የኦዴፓ  ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ታዬ ደንዳ ለኤስኢቢኤስ ራድዮ ተናገሩት ባለው ዘገባ ላይ አቶ ለማ ከእዚህ በፊት በየትኛውም ቦታ የውህደቱን እና የመደመርን ጉዳይ አስመልክቶ ተቃራኒ ሃሳብ እንዳላቀረቡ  መግለጣቸውን ዘግቧል።ይህ ከሆነ ዛሬ ለምን አነሱት?

አቶ ለማ ምን ሆነው ነው?

እነኝህን እና ሌሎች ሁኔታዎችን ስንመለከት አቶ ለማ በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያዊነት ስሜቱ ይልቅ ያየለባቸው (ያስጨነቃቸው) በኦሮሞ ማኅበረሰብ ውስጥ እንደ ከሃዲ ልቆጠር ነው የሚለው ጭንቀት ነው።ከእዚህ ውጪ ከእዚህ በፊት በእየመድረኩ ከነገሩን አንፃር ስናየው የአቶ ለማ ሃሳብ ማጠንጠኛ ምላሽ የሚያገኘው ከመደመር እና ከኢሕአዴግ ውህደት ውጪ የተሻለ የሚያረካቸው ሃሳብ ሊገኝላቸው አይችልም።  እና አሁን አቶ ለማ ለምን እጃቸውን ሲያወጡ ባላፈሩበት ጉዳይ  ዛሬ ተቀይረው ሌላ ሃሳብ አነሱ? ጉዳዩ ጊዜ የሚፈታው ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ ግን  የሚከተሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎች ጠይቆ ማለፍ ይቻላል። እነርሱም -

  • አቶ ለማ መደመር እና የውህደቱ ሂደት እዚህ ደረጃ እንደማይደርስ እርግጠኛ የሆኑበት የማናውቀው በሚስጥር የያዙት ፕሮጀክት ስለነበር ነው እስከዛሬ ዝም ብለው የቆዩት?
  • አሁን ያ ያሉት ፕሮጀክት መክሸፉን ሲመለከቱ እራሳቸው በቀጥታ ሊገቡበት አሰቡ?
  • ወይንስ እንዳሉት መደመር እና ውህደቱ ሳይገባቸው እና ሳይስማሙበት ቆይተው ነበር?
በማስከተል የሚነሳው ጥያቄ አቶ ለማ ይህንን በማለታቸው በመደመር እና የኢህአዴግ ውህደት ላይ የሚመጣው ተፅኖ አለ ወይ? የሚለው ነው።የውህደቱ ጥያቄ ከኢህአዴግ በላይ እየገፉበት ያሉት የአጋር ድርጅቶች ናቸው።ከእስነርሱ ጋር የውህደት ደጋፊዎች ኢሕአዴጋውያን  እና የጎሳ ፖለቲካ ያሰጋው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከውህደቱ ጋር ቆሟል።ከእዚህ በተጨማሪ የተቃዋሚ የዜግነት እና የአንድነት ኃይሎች ሁሉ የውህደቱን ሂደት ይደግፋሉ። በአንፃሩ የጀዋር የፅንፍ ኃይል እና በኦዴፓ ውስጥ የተሰገሰጉ  የብሔር ድርጅቶች ውህደቱን ይቃወማሉ።ከእነሱ በተጨማሪ ህወሓት ዋነኛ ተቃዋሚ ብቻ ሳትሆን በመጪው ሳምንት ወደ ስድስት መቶ ሰዎች የሚሳተፉበት የፈድራሊስት አስተሳሰብ አራማጆች በማለት የተራቻቸውን አበል እየከፈለች መቀሌ ላይ ለመሰብሰብ አቅዳለች። 

በሌላ በኩል የውህደቱን ሃሳብ ካለምንም ድርድር እንደሚቀበለው በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው የጦር ሰራዊቱ ነው።በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አደረጃጀቶች የህዝቡ የጎሳ ስሜት ያላጠቃው አካል የሚገኘው በጦር ሰራዊቱ በተለይ በመካከለኛ እና የመስመር መኮንኖች እስከ ተራ ወታደር ያለው የውህደቱን ሃሳብ ይደግፋል። ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው።የጦር ሰራዊቱ የአንዲት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚያተኩር ሆኖ የተሰራ እንጂ በብሄር የተከፋፈሉ ፓርቲዎች የራሱ ራስ ምታት እንደሆኑ ስለሚያውቅ ፈፅሞ መከፋፈልን ሳይሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩን የውህደት እና የመደመር ሃሳብ የሚቀበል  ለመሆኑ መጠራጠር አያስፈልግም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በጦር ሰራዊቱ መካከለኛ እና የመስመር መኮንኖች ጀምሮ እስከታችኛው ወታደር ድረስ በጣም የሚወደዱ መሪ ናቸው።ስለሆነም የውህደቱ ሂደት ፈፅሞ ሊገታ የሚችልበት ደረጃ አይደለም።  ለእዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የብልፅግና ፓርቲ ገና የምስረታ ጉባኤ ሳይጠራ በኦሮምያ ክልል ያለውን ቢሮ እንዲያደራጅ ሹመት መስጠት የጀመሩት።

በቀጣይስ ምን ሊከሰት ይችላል?

የአቶ ለማ የአመለካከት ለውጥ ትናንሽ ጭረቶችን ከማምጣት ያለፈ በውህደቱም ሆነ በመደመር ሂደት ላይ አንዳች ለውጥ አያመጣም። ምክንያቱም ኢትዮጵያ አሁን ከገባችበት የፖለቲካ ቀውስ ለመውጣት በምንም መመዘኛ ለማየት ብንሞክር ከኢህአዴግ እውነተኛ ውህደት እና ከመደመር እሳቤዎች ውጪ  ህመሟን ልታስታግስበት  የሚችል አንዳች ነገር የለም።ይልቁንም ይህ የመፍትሄ ሂደት በፍጥነት ባይመጣ ኖሮ በኦደፓ እና በአደፓ ውስጥ የገባው የፅንፍ አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ወደ አልታወቀ የማዕበል አዘቅት ውስጥ ሊወስዳት ተዘጋጅቶ እንደነበር ለማየት ይቻላል። በሌላ በኩል የአቶ ለማ የሃሳብ ልዩነት ምንም ጭረት አያመጣም ማለት አይደለም።በመጀመርያ ደረጃ አቶ ለማ ለይተው ወደ ፅንፍ ኃይሎች ጎራ ይገባሉ ወይንስ የራሳቸውን አስተሳሰብ ይዘው  የራሳቸውን እና የተከታዮቻቸውን ሃሳብ ይዘው ፓርቲ ይመሰርታሉ? የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ጥያቄ ነው።ሌላው ጥያቄ አቶ ለማ በኦደፓ ውስጥ የለዘብተኛ መስመርን ነው ወይንስ የኦነግን መስመር ይከተላሉ? የሚለው  ነው።አቶ ለማ ወደ ፅንፍ ጎራ ይገባሉ ብሎ ማሰብ የሚቻል አይመስልም። ወደ ኦነግ ጎራም ይገባሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም።ምክንያቱም ኦነግ እራሱ የፖለቲካ መሰረቱ ከመናጋት አልፎ ሃሳቡን መግለጥ ሲያቅተው እየተኮሰ እና እያስተኮሰ የራሱን ወገን የሚወጋ  አካል ሆኗል።ስለሆነም አቶ ለማ ለጊዜው የሚያደርጉት አንድ በልዩነት ተቀምጠው ለጥቂት ጊዜ ማየት አልያም የራሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲ መስርተው በምርጫ መወዳደር ሊሆን  ይችላል።አቶ ለማ ሶስቱንም መንገድ ቢሄዱ ግን ኦደፓ ለሶስት መሰንጠቁ የማይቀር ነው።ኦደፓ ለሶስት ተሰነጠቀ የሚል ታሪክ ሳይፃፍበት ብልሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ  ውህደቱን በማብሰር ያለፈ ታሪኩ ሳይጎድፍ እንዲፃፍ ሊረዱት ይችላሉ። አቶ ለማ ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሃሳብ ቢረዱ ኖሮ ዝም ቢሉትም ለሶስት ማለትም የውህደት ደጋፊዎች፣የፅንፍ አቅራሪ ኃይሎች እና የለዘብተኛ ብሄርተኞች ክፍል ሆኖ መከፈሉ የማይቀር ነበር።አቶ ለማ ትናንት የሰጡት ሃሳብም የእዚህ የስንጥቁ  አንድኛው ድምፅ ነው።

ማጠቃለያ 

ለማጠቃለል አቶ ለማ መገርሳ የፈለጉትን ሃሳብ መስጠታቸው የሚከበር እና ሊከበር የሚገባ ነው።ግለሰቡ ስብእናቸውም  የሚናቅ አይደለም።ቆራጥ እና ሀቀኝነት የታየበት አሰራር አሳይተዋል።ወደፊትም የኢትዮጵያ የክብር ሰው ሆነው መቀጠላቸው አይቀርም። በተለይ በቅንነት የኦሮሞ ብሔርተኝነት ይጨፈለቃል ብለው ለሚሰጉ እንደ አቶ ለማ ያሉ ኢትዮጵያዊ ሃሳብ ያላቸው ግን ብሔርተኝነትን  በአንክሮ የሚያዩ ሰዎች መኖራቸው ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ጠቃሚ እንጂ ጉዳይ የለውም። አቶ ለማ አንዴ በጎ ኢትዮጵያዊ ሃሳባቸውን ገልጠዋል።ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚወስድባቸውም ሆነ በችሮታ የሚሰጣቸው የለም። ድሮም አብሯቸው የኖረ  እና ወደፊትም የሚኖር ነው።ይህ ሁሉ ሆኖ አቶ ለማ የሚመዘኑት ከእዚህ በፊት ከሰሩት ይልቅ ከአሁን በኃላ በሚያደርጉት ነው።እንደ ብዙ ኢትዮጵያውያን ሃሳብ አቶ ለማ የውህደቱን ሂደት የሚያደናቅፍ አንድም ድርጊት ባያደርጉ እና  የመደመርን ሃሳብም በሳይንሳዊ መንገድ ከመተቸት አልፈው ወደ ሌላ አላስፈላጊ ተግባር እንዳይሄዱ  ምክሮች ሁሉ ተሰብስበው መናገር አለባቸው።ኢትዮጵያ በ21ኛው ክ/ዘመን እንደመሆኗ የብሔር ፖለቲካ ደክሟታል። ከእዚህ በላይ ትከሻዋ አይሸከምም።የብሔር ፖለቲካ ቶሎ ቆስሉ ስለማይድን እንጨፈለቃለን ብለው ለሚሰጉ እንደ አቶ ለማ ያሉ ወጣ ብለው ሁኔታውን እየተከታተሉ አገር ያረጋጉ ይህ ክፋት የለውም።የመጨረሻው መጨረሻ ሃሳብ ግን አቶ ለማ ሃሳብ ሌላ ጊዜ ሲኖርዎት እባክዎን የአገር ውስጥ ሚድያዎችን ይጠቀሙ።ይህ ሰነድ ነው።ይህ አገራዊ ጉዳይ ነው። በእዚህ ዘመን ሃሳብን ለመግለጥ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ድረስ መሄድ ብዙም አያሳምንም። ይልቁንም አላስፈላጊ የባዕዳን ተወዳጅነት ለማትረፍ የተደረገ ቁጭ ብድግ ያስመስላል።ከእዚህ ውጪ አቶ ለማ በሃሳብዎ ልዩነት እናከብርዎታለን እንጂ አንጠላዎትም።ወደፊት በሚሄዱት አካሄድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመዳኘት በአንክሮ እርስዎን እና ተከታዮችዎን ይከታተላል። ውህደቱ እና መደመር ግን ይቀጥላል። የሚቀጥለው ደግሞ የተሻለ መንገድ ስለሌለ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም አዋጪ ስለሆነ ነው።በመጪው ጊዜም በግልጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፉን የበለጠ የሚገልጥበት ጊዜ ይሆናል።  



ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Friday, November 29, 2019

በያዝነው ሳምንት መጀመርያ በቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ቄሮ በሚል ስም ግጭት ከፈጠሩት ውስጥ አንዱን ያዳኑት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ናቸው። (ቪድዮ ይመልከቱ)

  • የቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ከተከሉት የቤተ ክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ አባላት ውስጥ አርበኛው አብዲሳ አጋ እንዳሉበት ያውቃሉ?
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተደራጀ መልክ ጥቃት እየተፈፀመ እንደሆነ የሚታይ ነው።በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት የሚያደርሱት አካላት በዋናነት በፅንፍ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እና በተደራጀ መልክ ከፅንፈኞች አመራር እንደሚቀበሉ ይነገራል። እራሱን ቄሮ ከተሰኘው ቡድን ውስጥ ብዙዎች በሰላማዊ መንገድ እንደሚንቀሳቀሱ  እና ፅንፈኘነትን እንደማይደግፉ በእየሚድያው ላይ ሲናገሩ ይሰማል።ሆኖም ግን ከቄሮ ውስጥ አሁንም በፅንፍ አደረጃጀት ከፅንፍ አካል መመርያ የሚቀበሉ እንዳሉ የሚናገሩ ግን ብዙዎች ናቸው።

ህዳር 15/2012 ዓም በቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሄው የፅንፍ ቡድን በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሞክሯል።ጳጉሜን 3/2011 ዓም ላይም በአውደ ምህረት ላይ ''አላህ ወአክበር'' ለማለት የሞከረ እና ብጥብጥ ለመፍጠር የሞከረ ነበር። በሰሞኑ ጥቃት ግን አንዱ በተለይ ከጅማ የመጣ የተባለውን ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ አስገብተው ከህዝብቁጣ ያዳኑት እና ለሕግ አካላት በመስጠት መልካም ተግባር የፈፀሙ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ሊመሰገኑ ይገባል።

በነገራችን ላይ የእዚህ ፅሁፍ አቅራቢ የቦሌ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ለረጅም ጊዜ የሚያውቀው ከመሆኑ አንፃር የቤተ ክርስቲያኑ የኃላ ታሪክ ላይ ቤተ ክርስቲያኑ ተከላ ላይ ኮሚቴ ከነበሩት አባቶች መካከል በቦሌ መንገድ ወሎ ሰፈር መኖርያቸው  የነበረው አርበኛው አብዲሳ አጋ እንደነበሩ መረጃውን በወቅቱ ከነበሩት አባቶች በቀጥታ መስማቱን በእዚህ አጋጣሚ ለመግለጥ ይፈልጋል። ዛሬ በቄሮ ስም የተደራጁ የፅንፍ አካሎች የአርበኛ አብዲሳ አጋን ሥራ  ለማፍረስ የሚደረግ ሙከራም መሆኑን ልብ ይሏል።

ህዳር 15/2012 ዓም በቦሌ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምን ተፈጠረ? ቪድዮውን ይመልከቱ።

ከደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር እና የሰንበት ትምህርት ቤቱ አገልጋይ ከአቶ መስፍን  በዳዳ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ 


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Thursday, November 28, 2019

The 2019 Nobel Peace Prize ceremony is coming soon! የኖቤል ሽልማት ቀን አንድ ሳምንት ቀረው

የኖቤል የሰላም ሽልማት ስነ ስርዓት በህዳር 30/2012 ዓም (ዴሴምበር 10/2019 ዓም) በኦስሎ ኖርዌይ ይከናወናል።
Nobel Peace Prize ceremony will be held in Oslo, Norway on December 10,2019.
Listen to the call between Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed Ali and Olav Njølstad, Secretary of the Norwegian Nobel Committee, recorded shortly after the public announcement of the 2019 Nobel Peace Prize.

Source : - Nobel Peace Prize


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Sunday, November 24, 2019

Breaking News Ethiopia - ''There is a terrorist command center in USA working to destabilize Ethiopia and the horn of Africa'' Ethiopian journalist Eskindir Nega disclosed in Washington DC on November 24,2019.ማዕከሉን አሜሪካ ያደረገ የሽብር ቡድን ኢትዮጵያን ለማተራመስ እየሰራ ነው። (ቪድዮ)


  • የሽብር ቡድኑ በኢትዮጵያ ሴሎች፣የዕዝ ሰንሰለት እና ከመካከለኛው ምስራቅ የሚያገኘው የገንዘብ ፈሰስ አለ።
  • The terrorist team has his own cell, command chain and financial assistance from middle east
**********************************

ጉዳያችን / Gudayachn / November 24/2019 
ህዳር 14/2012 ዓም 
**********************************
Eskindir Nega is Economics graduate from American University (private research University in Washington DC) . He has completed his high school from Sanford American High school in Addis Ababa. In 1980s he traveled to USA for further study and came back home in 1991, when the dictator Mengistu rule was overthrown.Since 1991 Eskindir is working in Ethiopia with chief editor to his own  News paper. His News papaer is one of the  highest circulating news paper in the country. Eskindir is also a human rights activist as a result he has been jailed seven times by the former regime of Ethiopia before the reformists came to power in 2018.

Eskindir Nega is a winner of a number of international awards including -


  • 2012 PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award
  • 2014 World Association of Newspapers' Golden Pen of Freedom Award
  • 2017 International Press Institute World Press Freedom Hero
  • 2018 Oxfam Novib/PEN Award 

The below video is Eskindier Nega's speech, on the the existence of terrorist command center in USA, for thousands of Ethio-Americans residing in Washington DC and peripherals.





ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Friday, November 22, 2019

ጃዋር አሕመድ አውሮፓን እንዲረግጥ ሊፈቀድለት አይገባም። We care for Europe - UK,Belgium,Sweden,Norway and others must stop Jawar Mohamed from entering to their territory.

(አማርኛ ከእንግሊዝኛ ስር ያንብቡ)

Attention! to Europe - UK, Belgium, Sweden, Norway and other countries.

We care for Europe!

Jawar Mohamed is well known with his hate speeches and extremist position in Ethiopia. Recently he is claimed  and caused for the death of over 80 innocent people in Ethiopia. Next week, Jawar is planning to travel to European countries including UK, Belgium, Sweden and Norway for the purpose of collecting illegal public fund to use for the same hate speeches plus to inject his clashing  project among Ethiopians at home under the cover of ethnicity. Now a days he is challenged even from Oromo ethnics that he propagandized as if he stand for.

This is a notice to European countries to be aware and take the necessary action by stopping Jawar not to enter to Europe. For your detailed information about the mentioned individual, please click and read this link (https://www.gudayachn.com/2019/10/analysis-ja-war-aljazeera-bloodshed-and.html).

We care for Europe.


====================================

ጥላቻን በተሞላ ንግግሮቹ እና በማኅበራዊ ሚድያ ላይ በሚፅፋቸው ህዝብን ከህዝብ በሚያጋጩ ንግግሮቹ ምክንያች የበርካታ ኢትዮጵያንን ሕይወት እንዲቀጠፉ፣ወላጆች ካለ ልጆች፣ልጆችን ከወላጆቻቸው ውጭ እንዲኖሩ ምክንያት የሆነ ሰው ጃዋር መሐመድ ወደ አውሮፓ በመምጣት ለበለጠ ግጭቶች  የሚረዳው  ገንዘብ ለማሰባሰብ ወደ አውሮፓ ቤልጅየም፣ስዊድን፣ኖርዌይ እና እንግሊዝ ጨምሮ ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ለመምጣት ማሰቡ ተሰምቷል።

ከእዚህ በፊት በአሜሪካ ሊያደርጋቸው ያሰባቸው ስብሰባዎች በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኢትዮጵያውያን በተቃውሞ አንዳንዶቹ ጋር ተረጋግጦ ስብሰባውን እንዳያደርግ፣በሌላ ቦታ ደግሞ ፈፅሞ ስብሰባውን እንዳያደርግ ማድረግ ችለዋል።በአውሮፓ እና አሜሪካ ማንም የፈለገውን ሃሳብ የመግለጥ እና የመሰብሰብ መብት አለው።ይህ በሕግ የተረጋገጠ መብት ነው። ሆኖም ግን በቅርቡ ብቻ ከ80 በላይ ንፁሃን ሕይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆነ ሰው ለበለጠ ጥፋት የሚረዳው ገንዘብ እንዲያሰባስብ  የአውሮፓም ሆነ የአሜሪካ ሕግ አይፈቅድም።ስለሆነም ኢትዮጵያውያን ለአውሮፓ ሕብረት፣ለእንግሊዝ መንግስት እና ለሌሎቹም መንግሥታት ጃዋር የሚሰበስበው ገንዘብም ሆነ ስብሰባ ህገወጥ መሆኑን በቅድምያ ማሳወቅ በመቀጠልም በየትኛውም ቦታ ስብሰባው እንዳይደረግ በተቃውሞም ማስቆም ይገባቸዋል። 


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Wednesday, November 20, 2019

የኢትዮጵያ ወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ (ጉዳያችን ምጥን)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ 

በእዚህ ፅሁፍ ስር በምጥን መልኩ የሚከተሉት ጉዳዮች ተነስተውበታል።
  • ወቅታዊው የፖለቲካ ትኩሳቱ፣
  • የኢህአዴግ የውሕደት ሂደት መውሰድ የሚገባው  ጥንቃቄ፣
  • የአክራሪ እስልምና ውጪያዊ እንቅስቃሴ ፣
  • የኦሮሞን ሕዝብ ለመረማመጃ የተጠቀመው ፅንፈኛ እንቅስቃሴ የሚቀጥለው እርምጃው  ምንድነው?
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ 
  • ከፖለቲካ ፓርቲዎች ውጭ የሆነው ብዙሃኑ እና ወሳኙ ሕዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዴት ተፅኖ ፈጣሪ ይሁን?
**********************
ጉዳያችን /Gudayachn
ህዳር 10/2012 ዓም  (ኖቬምበር 20/2019 ዓም)
**********************
በኢትዮጵያ ፖለቲካ፣የመገናኛ ብዙሃን እና ካላይኛው አመራር በታች ያለው አመራር ጨምሮ የኢትዮጵያ ችግር የሃሳብ የማመንጨት አቅም ማነስ ነው።አዳዲስ ሃሳቦች ለሚገጥሙ ችግሮች ብቻ ሳይሆን የሚገጥሙ ችግሮችን በወጉ መትሮ ሰው በሚረዳው መልኩ የማቅረብ ችግርም ሌላው ችግር ነው።ለእዚህም ነው የሁኔታዎች ቅርፅ አስይዞ የሚተነተንበት ማዕከል ሲጠፋ ክፉ ሃሳብ ያላቸው ባለ ትንንሽ የሃሳብ ክሮች ብዙዎችን ይዘው  ወደፈለጉት የተሳሳተ መንገድ ይዘው የመንገድ ዕድል ያገኛሉ።ስለሆነም በሁኔታዎች ላይ አተያይን በሚገባ ማቅረብ አስፈላጊ ነው።

በእዚህ የጉዳያችን ምጥን ፅሁፍ  የሚከተሉት ሃሳቦች ላይ ጉዳያችን ምጥን ሃሳብ ትሰጣለች። እነርሱም -

  • ወቅታዊው የፖለቲካ ትኩሳቱ፣
  • የኢህአዴግ የውሕደት ሂደት መውሰድ የሚገባው  ጥንቃቄ፣
  • የአክራሪ እስልምና ውጪያዊ እንቅስቃሴ ፣
  • የኦሮሞን ሕዝብ ለመረማመጃ የተጠቀመው ፅንፈኛ እንቅስቃሴ የሚቀጥለው እርምጃው  ምንድነው?
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ 
  • ከፖለቲካ ፓርቲዎች ውጭ የሆነው ብዙሃኑ እና ወሳኙ ሕዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዴት ተፅኖ ፈጣሪ ይሁን?
ወቅታዊው  የፖለቲካ ትኩሳቱ 

በአሁኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ በዋናነት የመንግስት የሕግ የማስከበር አቅምን የሚገዳደሩ ቡድኖች በእየቦታው እያቆጠቆጡ  ነው።በእዚህም ሳብያ ሕዝብ በዋናነት የፀጥታ እና የሕግ እንዲሁም የፍትህ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ክፍተት መታየቱ  መጪውን ጊዜ እንዲፈራ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ቦታዎች ሕዝብ እራሱን ለመከላከል የስነ ልቦናም ሆነ የትጥቅ ዝግጅት የሚያደርግበት  ጊዜ ሆኗል።እነኚሁ ህገ ወጦች በዩንቨርስቲዎች ውስጥ ሳይቀር ተማሪዎችን እስከ መረበሽ እና ማጋጨት ይህ አሁን ላለው የፖለቲካ ትኩሳት ዋነኛ መንስኤ ሆኗል። 

የኢህአዴግ የውሕደት ሂደት መውሰድ የሚገባው  ሶስቱ  ጥንቃቄዎች 

ኢህአዴግ ለመዋሃድ ባለፈው ቅዳሜ ህዳር 6/2012 ዓም ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ወስኗል።በእዚህም መሰረት የውሁዱ አዲስ ስም ብልፅግና ፓርቲ  በሚል ስሙን ሰይሟል።የውህደቱ ሃሳብም ሆነ መተግበሩ በሕዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን ቀድሞ አጋር በሚል ይጠሩ የነበሩት እንደ ሱማሌ እና አፋር ክልሎች በተለየ ደስታ ፈጥሯል።በአንፃሩ የኢትዮጵያዊ ሃሳብ አገንግኖ መውጣቱ ያሰጋቸው የብሔር ፖለቲካ ከኖረ ብቻ እንደሚኖሩ የምይስቡ ኃይሎች ነገሩ አልታማቸውም።

በውህደቱ ሂደት አዲሱ የኢህአዴግ ውሁድ ፓርቲ ሶስት የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ አለበት።የመጀመርያው ጥንቃቄ በክልሎች የነበረ ክልላዊ ስሜት እና በፓርቲው ውሁድ ሂደት ላይ መጋጨት እንዳይኖር በአንፃሩ የክልሎች ጉዳይ አከላለል ላይ ውሳኔ በቶሎ ያስፈልጋል።ይህ ካልሆነ የሁለት የምቃረኑ ሃሳቦችን አንድ ላይ ለማስኬድ የሚደረግ ጥረት እንዳይሆን ያሰጋል። ሁለተኛው ጉዳይ አዲሱ ውሁድ ፓርቲ በብዙ የፍላጎት ቡድኖች (interest groups) ጉተታ ውስጥ እንዳይገባ መጠንቀቅ አለበት።አንዳንዶች ፓርቲው በአውሮፓ የኢንዱስትሪ አብዮት ጋር ሚና ነበረው በሚሉት የግለኝነት አስተሳሰብ ከፕሮቴስታንት እምነት ጋር የምያገናኙበት ስሜት በብልፅግና ፓርቲ ውስጥም የተወሰኑ ቡድኖች ፍላጎት ማጠንጠኛ እንዳይሆን  እና ከነበረው የኢትዮጵያ ዕሴት ጋር ግጭት ውስጥ እንዳይገባ ከፍተኛ የመርህ፣የዲስፕሊን እና ሁሉን የማቀፍ ሂደት መከተል አለበት። በሶስተኛ ደረጃ ፓርቲው ኢትዮጵያዊ መገለጫው ላይ በግልጥ እና በትኩረት መስራት እና የማንም ባዕዳን አስተሳሰብ  በገንዘብ ኃይልም ሆነ በተፅኖ ብዛት ስር እንዳይወድቅ እራሱን የሚፈትሽበት መንገድ እንዲኖር ሥርዓቶችን በታማኝነት መዘርጋት የሚሉት  ናቸው። 


የአክራሪ እስልምና ውጪያዊ እንቅስቃሴ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከየትኛውም ክፍል በበለጠ መልክ የአክራሪ እስልምና የትኩረት ቦታ ነች።ለእዚህም ዋነኛ ምክንያት አክራሪ እስልምና ከዓለም ላይ ካሉት አገሮች በቀላሉ  ሊሸገግበት ብቻ ሳይሆን የተወሰኑ የህብረሰብ ክፍሎችን ይዞ በአፍሪካውያን ውስጥ በሚነሱ ቅራኔዎች ሳብያ የራሱን ሥራ መስራት ስለሚፈልግ ነው።ስለሆነም ወደ አፍሪካ በሚያደርገው መስፋፋት ኢትዮጵያን እንደ አንድ ስጋት ይመለከታታል።ለእዚህም ከሃምሳ ሚልዮን በላይ ክርስቲያን መኖርን በመጥቀስ እና የኢትዮጵያ መሬት አቀማመጥ እስከ ሶስት ሺህ ሜትር ከባህር ጠለል በላይ መገኘቱ የመካከለኛውም ምስራቅንም ሆነ ዋነኛውን  የዓለም የንግድ መንቀሳቀሻ የቀይ ባህርን ኢላማ ውስጥ ለማስገባት ብቸኛው አመቺ ቦታ በመሆኑ ነው።

ሰለሆነም በኢትዮጵያ የወቅቱ ፖለቲካዊ ሽግግር ላይ ሂደቱን በሚፈልጉት መንገድ ለመዘወር የሚፈልገው አክራሪ አካል በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ጭምር ገብቶ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት እንደፈለጉት ለመዘወር ማሰባቸው አይጠረጠርም።በእዚህ በኩል ኢትዮጵያውያን በሚገባ መንቃት እና በትንንሽ ጉዳዮች ከመጠመድ በዋና ዋና እና ስልታዊ ሂደቶች ላይ ማተኮር አስፈላጊ አው። 


የኦሮሞን ሕዝብ ለመረማመጃ የተጠቀመው ፅንፈኛ እንቅስቃሴ የሚቀጥለው እርምጃው  ምንድነው?

የኦሮሞ የብሄርተኝነት ጥያቄ ያነሱ ኃይሎች ላለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን ያራመዱት ፖለቲካ የብሔር ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ሙከራም ነው።የኦሮምያ እስላሚያ የሚባለው  እንቅስቃሴ እራሱን በተለያዩ የኦነግ አንጃዎች ውስጥ በማስገባት የኦሮሞ የብሔር ጥያቄዎችን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በሚያጋጭ መልኩ  ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ኖሯል።የእዚሁ ዓላማ አራማጅ የኦኤምኤን ሚድያ በመክፈት ለኦሮሞ ብሔር የቆመ መስሎ የሚታየው  ጃዋር በኦሮሞ ብሄርተኝነት ስም  የሚሄድበት ነዳጅ በቅርቡ እንደሚያልቅበት እና ሌላ ጭንብል ይዞ እንደሚወጣ ይጠበቃል።ጃዋር  መሐመድ ከእዚህ በፊት በአሜሪካ ባደረገው ስብሰባ ላይ አክራሪ እስልምናን ኢትዮጵያ ላይ ለማስፈን የሚሄድበት መንገድ የኦሮሞ ብሄርተኝነት እንደሆነ ኦሮምያ የአክራሪ እስልምና ምቹ መጋለብያ እንደሆነች ''የሜጫ'' ንግግሩ በተሰኘው ንግግሩ መግለጡ አይዘነጋም። 

 የፅንፈኛ ቡድኑ ቀጣይ እርምጃ የሚሆነው ኦሮምያን መከፋፈል እና የራሱ የሆነ የመፈንጫ ቀጠና መመስረት ነው።ለእዚህም እንዲመቸው በመጀመርያ በኦሮምያ የምትገኘውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈል ''ዮሮምያ ቤተ ክህነት'' የሚል ከፋፋይ ቢሮ እንዲከፈት በኦሮምያ ሚድያ ኔት ዎርክ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል።  ስለሆነም የፅንፈኛ ቡድኑን ቀጣይ አላማ በተለይ በኦሮምያ ፖለቲካ ላይ እውቀቱ አለን የሚሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ 

በኢትዮጵያ የለውጥ ነፋስ በነፈሰባቸው ሂደቶች በሙሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጀመርያ ተጠቂ ነች።የውጭ ወራሪ በመጣባቸው የኢትዮያ የፈተና ዘመናት ሁሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀዳሚ ዕላማ ሆና ኖራለች።ፋሺሽት ጣልያን በወረራው ጊዜ አይሮፕላኞቹ ቀድመው የሚያጠቁት የቤተ ክርስቲያኒቱን ህንፃ ሲሆን በአምስት ዓመታት ቆይታው የደብረ ሊባኖስ መነኮሳትን እያሰረ ወደ ገደል ከእነ ሕይወታቸው ከመጨመር ባለፈ ፓፓሳቶቿን በአደባባይ እስከመስቀል ያልተፈፀመ የግፍ አይነት የለም።የ1966 ዓም የለውጥ ንፋስ፣የ 1983 ዓም  የመንግስት ለውጥ እና በ2010 ዓም የኢህአዴግ ለውጥ ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ኢላማ ሆነዋል።

ባሳለፍናቸው ስድስት ወራት ውስጥም በኦሮምያ ክልል በተለየ መልኩ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ ምእመናንም እየተገደሉ ነው። ሁኔታው በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮያውያን ዘንድ ሁሉ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።በጉዳዩ ላይ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እና ማብራርያ እንዲሰጥ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ የማህበራት ህብረት ጭምር ጠይቀዋል።በቅርቡም በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ማኅበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በቀጥታ ደብዳቤ መፃፉን ማኅበሩ ማስታወቁ ተሰምቷል።ይህ ሁሉ ድምፅ በመንግስት በኩል ተገቢው ምላሽ መሰጠት ያለበት እና የለውጥ ሂደቱን ጤናማ እንዲሆን ወሳኝ ሚና የሚጫወት ነው።ይህ ሁኔታ ኦርቶዶክሳውያንን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት የመገለል አዝማምያ እንዲሰማቸው ከማድረጉም በላይ ከፍተኛ ያለመረጋጋት ምክንያት ሊሆን እንደምች ማንም ጥርጥር ሊገባው አይገባም። ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኒቱ ኢትዮጵያን የማረጋጋት አቅም ብቻ ሳይሆን ያለው ጠንካራ ማኅበራዊ አንድነት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በሚፈፀመው የጥፋት ሥራ ሳብያ የመናጋት አደጋው ትልቅ ያደርገዋል።ይህንን ደግሞ የፅንፍ ኃይሎች የሚፈልጉት ጉዳይ ነው። 

በኢትዮጵያ የመንግስትነት ታሪክ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ አመታት በላይ ነገሥታቱን ህዝቡ የሚቀበላቸው ከቆለኛው የአክራሪ እስልምና የሚያድኑት ከሆነ ብቻ ነው። ይህንን የማያደርጉ ነገስታት ላይ ሕዝብ የመሸፈት እና እራሱን በራሱ የመከላከል ሥራ አይ ብቻ ተግባር ላይ ያተኩራል።አሁንም የሚታየው ከእዚህ ብዙ የራቀ አይደለም።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕልውናን ለመጠበቅ እና ከፅንፈኛ አካሎች ለመከላከል ትጋት የማያሳይ መንግስትም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር በስልጣን ላይ የመቆየት  አቅሙ ፈፅሞ የመነመነ ነው።ይልቁንም በአሁኑ በያዝነው በ21ኛው ክፍለዘመን በተበታተነ መልክ ያለ የሚመስለው የቤተ ክርስቲያኒቱ የሰው ኃይል ብቃት፣ጆግራፍያዊ ስብጥር እና ዓለም አቀፍ አቅም ሁሉ የሚንቁት ጉዳይ አይደለም።ስለሆነም የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መንግስት በፍጥነት ትኩረት መስጠት የሚገባው ይሄው የቤተ ክርስቲያኒቱን አጥቂዎች ለፍርድ ከማቅረብ እስከ  የመጠበቅ መንግስታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይዋል ይደር የማይባል አንገብጋቢው ጉዳይ ነው። ይህ ካልሆነ ግን የተጠቃ አካል ሁል ጊዜ እራሱን ለመከላከል ከመንቀሳቀሱ አንፃር ጉዳዩ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ መልክ የሚቀይር ጉዳይ አይመጣም ማለት ፈፅሞ አይቻልም።

ከፖለቲካ ፓርቲዎች ውጭ የሆነው ብዙሃኑ እና ወሳኙ ሕዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዴት ተፅኖ ፈጣሪ ይሁን?

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ተከታታይ እንጂ ዋና ተዋናይ አይደለም።ይህ ደግሞ በሁሉም አገር ያለ ነው።ተዋናዮች ጥቂት ተመልካቾች ግን ብዙዎች ናቸው።ሆኖም ግን በሌሎች አገሮች ያለው ሁኔታ ተመልካቹ በልዩ ልዩ መንገድ ተመልካች ብቻ ሳይሆን ተዋናዮቹ ላይ ተፅኖ አሳዳሪ ነው።በኢትዮጵያ ግን ይህ አይታይም።መሆን የሚገባው ግን ከተመልካችነት ተፅኖ ፈጣሪነት ማደግ አለበት።ተፅኖ  ፈጣሪነቱ በሚድያ፣በሰላማዊ የተቃውሞ መንገድ ሃሳብን በመግለጥ፣ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ በማንቀሳቀስ እና በመከታተል ሁሉ ይገለጣል።

የኢትዮያን ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳይ በተመለከተ ባጭሩ ከላይ የተጠቀሱት ከብዙ በጥቂቱ እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንደሆኑ ጉዳያችን ታምናለች። የፖለቲካው ዋና አንቀሳቃሽ የምጣኔ ሃብቱ ጉአይ በርግጥም በአግባቡ መታየት ያለበት እንደሆነ ይታመናል። 

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...