ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, November 20, 2019

የኢትዮጵያ ወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ (ጉዳያችን ምጥን)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ 

በእዚህ ፅሁፍ ስር በምጥን መልኩ የሚከተሉት ጉዳዮች ተነስተውበታል።
  • ወቅታዊው የፖለቲካ ትኩሳቱ፣
  • የኢህአዴግ የውሕደት ሂደት መውሰድ የሚገባው  ጥንቃቄ፣
  • የአክራሪ እስልምና ውጪያዊ እንቅስቃሴ ፣
  • የኦሮሞን ሕዝብ ለመረማመጃ የተጠቀመው ፅንፈኛ እንቅስቃሴ የሚቀጥለው እርምጃው  ምንድነው?
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ 
  • ከፖለቲካ ፓርቲዎች ውጭ የሆነው ብዙሃኑ እና ወሳኙ ሕዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዴት ተፅኖ ፈጣሪ ይሁን?
**********************
ጉዳያችን /Gudayachn
ህዳር 10/2012 ዓም  (ኖቬምበር 20/2019 ዓም)
**********************
በኢትዮጵያ ፖለቲካ፣የመገናኛ ብዙሃን እና ካላይኛው አመራር በታች ያለው አመራር ጨምሮ የኢትዮጵያ ችግር የሃሳብ የማመንጨት አቅም ማነስ ነው።አዳዲስ ሃሳቦች ለሚገጥሙ ችግሮች ብቻ ሳይሆን የሚገጥሙ ችግሮችን በወጉ መትሮ ሰው በሚረዳው መልኩ የማቅረብ ችግርም ሌላው ችግር ነው።ለእዚህም ነው የሁኔታዎች ቅርፅ አስይዞ የሚተነተንበት ማዕከል ሲጠፋ ክፉ ሃሳብ ያላቸው ባለ ትንንሽ የሃሳብ ክሮች ብዙዎችን ይዘው  ወደፈለጉት የተሳሳተ መንገድ ይዘው የመንገድ ዕድል ያገኛሉ።ስለሆነም በሁኔታዎች ላይ አተያይን በሚገባ ማቅረብ አስፈላጊ ነው።

በእዚህ የጉዳያችን ምጥን ፅሁፍ  የሚከተሉት ሃሳቦች ላይ ጉዳያችን ምጥን ሃሳብ ትሰጣለች። እነርሱም -

  • ወቅታዊው የፖለቲካ ትኩሳቱ፣
  • የኢህአዴግ የውሕደት ሂደት መውሰድ የሚገባው  ጥንቃቄ፣
  • የአክራሪ እስልምና ውጪያዊ እንቅስቃሴ ፣
  • የኦሮሞን ሕዝብ ለመረማመጃ የተጠቀመው ፅንፈኛ እንቅስቃሴ የሚቀጥለው እርምጃው  ምንድነው?
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ 
  • ከፖለቲካ ፓርቲዎች ውጭ የሆነው ብዙሃኑ እና ወሳኙ ሕዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዴት ተፅኖ ፈጣሪ ይሁን?
ወቅታዊው  የፖለቲካ ትኩሳቱ 

በአሁኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ በዋናነት የመንግስት የሕግ የማስከበር አቅምን የሚገዳደሩ ቡድኖች በእየቦታው እያቆጠቆጡ  ነው።በእዚህም ሳብያ ሕዝብ በዋናነት የፀጥታ እና የሕግ እንዲሁም የፍትህ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ክፍተት መታየቱ  መጪውን ጊዜ እንዲፈራ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ቦታዎች ሕዝብ እራሱን ለመከላከል የስነ ልቦናም ሆነ የትጥቅ ዝግጅት የሚያደርግበት  ጊዜ ሆኗል።እነኚሁ ህገ ወጦች በዩንቨርስቲዎች ውስጥ ሳይቀር ተማሪዎችን እስከ መረበሽ እና ማጋጨት ይህ አሁን ላለው የፖለቲካ ትኩሳት ዋነኛ መንስኤ ሆኗል። 

የኢህአዴግ የውሕደት ሂደት መውሰድ የሚገባው  ሶስቱ  ጥንቃቄዎች 

ኢህአዴግ ለመዋሃድ ባለፈው ቅዳሜ ህዳር 6/2012 ዓም ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ወስኗል።በእዚህም መሰረት የውሁዱ አዲስ ስም ብልፅግና ፓርቲ  በሚል ስሙን ሰይሟል።የውህደቱ ሃሳብም ሆነ መተግበሩ በሕዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን ቀድሞ አጋር በሚል ይጠሩ የነበሩት እንደ ሱማሌ እና አፋር ክልሎች በተለየ ደስታ ፈጥሯል።በአንፃሩ የኢትዮጵያዊ ሃሳብ አገንግኖ መውጣቱ ያሰጋቸው የብሔር ፖለቲካ ከኖረ ብቻ እንደሚኖሩ የምይስቡ ኃይሎች ነገሩ አልታማቸውም።

በውህደቱ ሂደት አዲሱ የኢህአዴግ ውሁድ ፓርቲ ሶስት የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ አለበት።የመጀመርያው ጥንቃቄ በክልሎች የነበረ ክልላዊ ስሜት እና በፓርቲው ውሁድ ሂደት ላይ መጋጨት እንዳይኖር በአንፃሩ የክልሎች ጉዳይ አከላለል ላይ ውሳኔ በቶሎ ያስፈልጋል።ይህ ካልሆነ የሁለት የምቃረኑ ሃሳቦችን አንድ ላይ ለማስኬድ የሚደረግ ጥረት እንዳይሆን ያሰጋል። ሁለተኛው ጉዳይ አዲሱ ውሁድ ፓርቲ በብዙ የፍላጎት ቡድኖች (interest groups) ጉተታ ውስጥ እንዳይገባ መጠንቀቅ አለበት።አንዳንዶች ፓርቲው በአውሮፓ የኢንዱስትሪ አብዮት ጋር ሚና ነበረው በሚሉት የግለኝነት አስተሳሰብ ከፕሮቴስታንት እምነት ጋር የምያገናኙበት ስሜት በብልፅግና ፓርቲ ውስጥም የተወሰኑ ቡድኖች ፍላጎት ማጠንጠኛ እንዳይሆን  እና ከነበረው የኢትዮጵያ ዕሴት ጋር ግጭት ውስጥ እንዳይገባ ከፍተኛ የመርህ፣የዲስፕሊን እና ሁሉን የማቀፍ ሂደት መከተል አለበት። በሶስተኛ ደረጃ ፓርቲው ኢትዮጵያዊ መገለጫው ላይ በግልጥ እና በትኩረት መስራት እና የማንም ባዕዳን አስተሳሰብ  በገንዘብ ኃይልም ሆነ በተፅኖ ብዛት ስር እንዳይወድቅ እራሱን የሚፈትሽበት መንገድ እንዲኖር ሥርዓቶችን በታማኝነት መዘርጋት የሚሉት  ናቸው። 


የአክራሪ እስልምና ውጪያዊ እንቅስቃሴ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከየትኛውም ክፍል በበለጠ መልክ የአክራሪ እስልምና የትኩረት ቦታ ነች።ለእዚህም ዋነኛ ምክንያት አክራሪ እስልምና ከዓለም ላይ ካሉት አገሮች በቀላሉ  ሊሸገግበት ብቻ ሳይሆን የተወሰኑ የህብረሰብ ክፍሎችን ይዞ በአፍሪካውያን ውስጥ በሚነሱ ቅራኔዎች ሳብያ የራሱን ሥራ መስራት ስለሚፈልግ ነው።ስለሆነም ወደ አፍሪካ በሚያደርገው መስፋፋት ኢትዮጵያን እንደ አንድ ስጋት ይመለከታታል።ለእዚህም ከሃምሳ ሚልዮን በላይ ክርስቲያን መኖርን በመጥቀስ እና የኢትዮጵያ መሬት አቀማመጥ እስከ ሶስት ሺህ ሜትር ከባህር ጠለል በላይ መገኘቱ የመካከለኛውም ምስራቅንም ሆነ ዋነኛውን  የዓለም የንግድ መንቀሳቀሻ የቀይ ባህርን ኢላማ ውስጥ ለማስገባት ብቸኛው አመቺ ቦታ በመሆኑ ነው።

ሰለሆነም በኢትዮጵያ የወቅቱ ፖለቲካዊ ሽግግር ላይ ሂደቱን በሚፈልጉት መንገድ ለመዘወር የሚፈልገው አክራሪ አካል በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ጭምር ገብቶ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት እንደፈለጉት ለመዘወር ማሰባቸው አይጠረጠርም።በእዚህ በኩል ኢትዮጵያውያን በሚገባ መንቃት እና በትንንሽ ጉዳዮች ከመጠመድ በዋና ዋና እና ስልታዊ ሂደቶች ላይ ማተኮር አስፈላጊ አው። 


የኦሮሞን ሕዝብ ለመረማመጃ የተጠቀመው ፅንፈኛ እንቅስቃሴ የሚቀጥለው እርምጃው  ምንድነው?

የኦሮሞ የብሄርተኝነት ጥያቄ ያነሱ ኃይሎች ላለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን ያራመዱት ፖለቲካ የብሔር ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ሙከራም ነው።የኦሮምያ እስላሚያ የሚባለው  እንቅስቃሴ እራሱን በተለያዩ የኦነግ አንጃዎች ውስጥ በማስገባት የኦሮሞ የብሔር ጥያቄዎችን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በሚያጋጭ መልኩ  ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ኖሯል።የእዚሁ ዓላማ አራማጅ የኦኤምኤን ሚድያ በመክፈት ለኦሮሞ ብሔር የቆመ መስሎ የሚታየው  ጃዋር በኦሮሞ ብሄርተኝነት ስም  የሚሄድበት ነዳጅ በቅርቡ እንደሚያልቅበት እና ሌላ ጭንብል ይዞ እንደሚወጣ ይጠበቃል።ጃዋር  መሐመድ ከእዚህ በፊት በአሜሪካ ባደረገው ስብሰባ ላይ አክራሪ እስልምናን ኢትዮጵያ ላይ ለማስፈን የሚሄድበት መንገድ የኦሮሞ ብሄርተኝነት እንደሆነ ኦሮምያ የአክራሪ እስልምና ምቹ መጋለብያ እንደሆነች ''የሜጫ'' ንግግሩ በተሰኘው ንግግሩ መግለጡ አይዘነጋም። 

 የፅንፈኛ ቡድኑ ቀጣይ እርምጃ የሚሆነው ኦሮምያን መከፋፈል እና የራሱ የሆነ የመፈንጫ ቀጠና መመስረት ነው።ለእዚህም እንዲመቸው በመጀመርያ በኦሮምያ የምትገኘውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈል ''ዮሮምያ ቤተ ክህነት'' የሚል ከፋፋይ ቢሮ እንዲከፈት በኦሮምያ ሚድያ ኔት ዎርክ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል።  ስለሆነም የፅንፈኛ ቡድኑን ቀጣይ አላማ በተለይ በኦሮምያ ፖለቲካ ላይ እውቀቱ አለን የሚሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ 

በኢትዮጵያ የለውጥ ነፋስ በነፈሰባቸው ሂደቶች በሙሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጀመርያ ተጠቂ ነች።የውጭ ወራሪ በመጣባቸው የኢትዮያ የፈተና ዘመናት ሁሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀዳሚ ዕላማ ሆና ኖራለች።ፋሺሽት ጣልያን በወረራው ጊዜ አይሮፕላኞቹ ቀድመው የሚያጠቁት የቤተ ክርስቲያኒቱን ህንፃ ሲሆን በአምስት ዓመታት ቆይታው የደብረ ሊባኖስ መነኮሳትን እያሰረ ወደ ገደል ከእነ ሕይወታቸው ከመጨመር ባለፈ ፓፓሳቶቿን በአደባባይ እስከመስቀል ያልተፈፀመ የግፍ አይነት የለም።የ1966 ዓም የለውጥ ንፋስ፣የ 1983 ዓም  የመንግስት ለውጥ እና በ2010 ዓም የኢህአዴግ ለውጥ ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ኢላማ ሆነዋል።

ባሳለፍናቸው ስድስት ወራት ውስጥም በኦሮምያ ክልል በተለየ መልኩ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ ምእመናንም እየተገደሉ ነው። ሁኔታው በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮያውያን ዘንድ ሁሉ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።በጉዳዩ ላይ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እና ማብራርያ እንዲሰጥ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ የማህበራት ህብረት ጭምር ጠይቀዋል።በቅርቡም በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ማኅበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በቀጥታ ደብዳቤ መፃፉን ማኅበሩ ማስታወቁ ተሰምቷል።ይህ ሁሉ ድምፅ በመንግስት በኩል ተገቢው ምላሽ መሰጠት ያለበት እና የለውጥ ሂደቱን ጤናማ እንዲሆን ወሳኝ ሚና የሚጫወት ነው።ይህ ሁኔታ ኦርቶዶክሳውያንን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት የመገለል አዝማምያ እንዲሰማቸው ከማድረጉም በላይ ከፍተኛ ያለመረጋጋት ምክንያት ሊሆን እንደምች ማንም ጥርጥር ሊገባው አይገባም። ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኒቱ ኢትዮጵያን የማረጋጋት አቅም ብቻ ሳይሆን ያለው ጠንካራ ማኅበራዊ አንድነት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በሚፈፀመው የጥፋት ሥራ ሳብያ የመናጋት አደጋው ትልቅ ያደርገዋል።ይህንን ደግሞ የፅንፍ ኃይሎች የሚፈልጉት ጉዳይ ነው። 

በኢትዮጵያ የመንግስትነት ታሪክ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ አመታት በላይ ነገሥታቱን ህዝቡ የሚቀበላቸው ከቆለኛው የአክራሪ እስልምና የሚያድኑት ከሆነ ብቻ ነው። ይህንን የማያደርጉ ነገስታት ላይ ሕዝብ የመሸፈት እና እራሱን በራሱ የመከላከል ሥራ አይ ብቻ ተግባር ላይ ያተኩራል።አሁንም የሚታየው ከእዚህ ብዙ የራቀ አይደለም።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕልውናን ለመጠበቅ እና ከፅንፈኛ አካሎች ለመከላከል ትጋት የማያሳይ መንግስትም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር በስልጣን ላይ የመቆየት  አቅሙ ፈፅሞ የመነመነ ነው።ይልቁንም በአሁኑ በያዝነው በ21ኛው ክፍለዘመን በተበታተነ መልክ ያለ የሚመስለው የቤተ ክርስቲያኒቱ የሰው ኃይል ብቃት፣ጆግራፍያዊ ስብጥር እና ዓለም አቀፍ አቅም ሁሉ የሚንቁት ጉዳይ አይደለም።ስለሆነም የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መንግስት በፍጥነት ትኩረት መስጠት የሚገባው ይሄው የቤተ ክርስቲያኒቱን አጥቂዎች ለፍርድ ከማቅረብ እስከ  የመጠበቅ መንግስታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይዋል ይደር የማይባል አንገብጋቢው ጉዳይ ነው። ይህ ካልሆነ ግን የተጠቃ አካል ሁል ጊዜ እራሱን ለመከላከል ከመንቀሳቀሱ አንፃር ጉዳዩ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ መልክ የሚቀይር ጉዳይ አይመጣም ማለት ፈፅሞ አይቻልም።

ከፖለቲካ ፓርቲዎች ውጭ የሆነው ብዙሃኑ እና ወሳኙ ሕዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዴት ተፅኖ ፈጣሪ ይሁን?

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ተከታታይ እንጂ ዋና ተዋናይ አይደለም።ይህ ደግሞ በሁሉም አገር ያለ ነው።ተዋናዮች ጥቂት ተመልካቾች ግን ብዙዎች ናቸው።ሆኖም ግን በሌሎች አገሮች ያለው ሁኔታ ተመልካቹ በልዩ ልዩ መንገድ ተመልካች ብቻ ሳይሆን ተዋናዮቹ ላይ ተፅኖ አሳዳሪ ነው።በኢትዮጵያ ግን ይህ አይታይም።መሆን የሚገባው ግን ከተመልካችነት ተፅኖ ፈጣሪነት ማደግ አለበት።ተፅኖ  ፈጣሪነቱ በሚድያ፣በሰላማዊ የተቃውሞ መንገድ ሃሳብን በመግለጥ፣ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ በማንቀሳቀስ እና በመከታተል ሁሉ ይገለጣል።

የኢትዮያን ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳይ በተመለከተ ባጭሩ ከላይ የተጠቀሱት ከብዙ በጥቂቱ እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንደሆኑ ጉዳያችን ታምናለች። የፖለቲካው ዋና አንቀሳቃሽ የምጣኔ ሃብቱ ጉአይ በርግጥም በአግባቡ መታየት ያለበት እንደሆነ ይታመናል። 

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)