ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, November 1, 2019

ኢትዮጵያውያን ከአገር ቤት እስከ ባህር ማዶ እጃችሁ ይያያዝ፣የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቀርቧል። (ጉዳያችን መልዕክት)

ጉዳያችን / Gudayachn
ጥቅምት 22/2012 ዓም  (ኖቬምበር 2/2019 ዓም)

ከንፈር ሳይነቃነቅ ልሳን ሳይጋራ፣
በዝምታ ድባብ በዝምታ ጎራ፣
ሳየወሩ ማውራት መልካም ባልንጀራ።

የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ግጥም ለመሞነጫጨር አንድ ሰሞን ተፍ ተፍ ያረገኝ ነበር።ከላይ ያለው ስንኝ አንድ በዝምታ በማውራት የሚግባቡ ገፀ ባህርያት ከአፋቸው አንዳች ቃላት ሳይወጣ የተግባቡ ሰዎች በገለጥኩበት መጣጥፍ ላይ የተጠቀምኩበት አገላለጥ ነበር። ዛሬ ይህንን ፅሁፍ ሳስብ ሃሳቤን የሚገልጥልኝ መሆኑን ስላሳመነኝ መግቢያ አደረኩት።

በዛሬው የጉዳያችን መልዕክት በረጅሙ ሃሳቦችን በማርዘም አላደክማችሁም።ሳይጀመር አለቀ እንዳትሉ እንጂ፣ የመልእክቱ ዋና ጭብጥ ሲጠቃለል ኢትዮጵያውያን ከደብረ ዳሞ፣ምፅዋ  እስከ ሞያሌ፣ ከአኮቦ እስከ ፈርፈር፣ከአሜሪካ እስከ ጃፓን፣ከፊንላንድ እስከ ደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ የምንያያዝበት፣ በጎሳ፣በሃይማኖት ሳንለያይ እና በልዩ ልዩ ጉዳዮች፣ በማኅበራዊ ቦታዎች ሁሉ ወጣቶች፣እናቶች፣አባቶች፣ሁላችሁ የምትያያዙበት ጊዜ ነው።

ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ለማያያዝ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ ሁሉ ኢትዮጵያውያን  እርስ በርስ ግንኙነታቸውን እንዲያዳብሩ ለመስራት ተነሱ።እናቶች ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን እጅ ለእጅ አያይዙ እንጂ ከቤታችሁ ሆናችሁ የምትተክዙበት ጊዜ አይሁን። አባቶች ወደ ጎዳናው ውጡ  ኢትዮጵያውያንን እጅ ለእጅ አያይዙ፣ የሃይማኖት አባቶች ወደ ጎዳናው ውጡ፣ በክልል መሬት የተጣሉትን እና የፖለቲካ እሾህ የተዘራባቸው የግጭት ቀጠናዎችን ባዶ የተረት ተረት ሥራ መሆኑን አውጁ። እናቶች ቡና ከቤታችሁ አታፍሉ፣ አውራ ጎዳናው ዳር ውጡ፣ጉዝጉአዙን ጎዝጉዙት ወጣቶቹን ጥሩ የሰፈራችሁን ሰው ጥሩ እጅ ለእጅ አያይዙ። የኢትዮጵያ አምላክ ኢትዮጵያውያንን ሊታደግ ከበር ላይ ቆሟል።እንዳይገባ በር የዘጋበት ኢትዮጵያውያን እጅ በእጅ አለመያያዝ ነው።

በባሕር ማዶ ያላችሁ።በአገር ቤት ሰላም ከማውራታችሁ በፊት በዋሽንግተን ጎዳና የተገለማመጠ ካለ እጅ ለእጅ አያይዙ፣ አገር ቤት ለሚመጣ ፈተና ሁሉ አለሁልህ ለማለት የባሕር ማዶዎቹ በቅድምያ ሳትውሉ ሳታድሩ እጅ ለእጅ ተያያዙ። የኢትዮጵያ ትንሣኤ በር ላይ ነው።ትንሣኤዋን ለማየት የምትታለፈውን ትንሽ መራራ መዝለል ብቻ ይፈለጋል።ይህችን ትንሽ መራራ  ለመዝለል ኢትዮጵያውያን ከአገር ቤት እስከ ባሕር ማዶ ሳትተያዩ የምትግባቡ እና አንዱ አንዱን ሳይጠብቅ እጅ ለእጅ የምትያያዙ  መሆን ያስፈልጋል። ለእዚህ ደግሞ እናቶች፣ወጣቶች እና አባቶች በሙሉ የማንንም ትእዛዝ ሳትጠብቁ ኢትዮጵያውያንን  ለማያያዝ ራሳችሁ ኃላፊነት ወስዳችሁ ከሰፈራችሁ ጀምሩ።ከንፈር ሳይነቃነቅ ተግባቡ፣ልሳን ንግግር ሳያወጣ ተግብሩት።ኢትዮጵያውያን ሳታወሩ ተግባቡ እና እጅ ለእጅ ተያያዙ።የኢትዮጵያ ትንሣኤ በር ላይ ነው።ይህ ተራ እና ባዶ ምኞት አይደለም።እውነት ነው።ውጤቱ እያንዳንዱ ግለሰብ በሚያሳየው ፍሬ ይወሰናል።

ከንፈር ሳይነቃነቅ ልሳን ሳይጋራ፣
በዝምታ ድባብ በዝምታ ጎራ፣
ሳየወሩ ማውራት መልካም ባልንጀራ።

ድምፃዊው ጥላሁን ገሠሠ መልዕክት አለው።



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...