- የቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ከተከሉት የቤተ ክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ አባላት ውስጥ አርበኛው አብዲሳ አጋ እንዳሉበት ያውቃሉ?
ህዳር 15/2012 ዓም በቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሄው የፅንፍ ቡድን በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሞክሯል።ጳጉሜን 3/2011 ዓም ላይም በአውደ ምህረት ላይ ''አላህ ወአክበር'' ለማለት የሞከረ እና ብጥብጥ ለመፍጠር የሞከረ ነበር። በሰሞኑ ጥቃት ግን አንዱ በተለይ ከጅማ የመጣ የተባለውን ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ አስገብተው ከህዝብቁጣ ያዳኑት እና ለሕግ አካላት በመስጠት መልካም ተግባር የፈፀሙ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ሊመሰገኑ ይገባል።
በነገራችን ላይ የእዚህ ፅሁፍ አቅራቢ የቦሌ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ለረጅም ጊዜ የሚያውቀው ከመሆኑ አንፃር የቤተ ክርስቲያኑ የኃላ ታሪክ ላይ ቤተ ክርስቲያኑ ተከላ ላይ ኮሚቴ ከነበሩት አባቶች መካከል በቦሌ መንገድ ወሎ ሰፈር መኖርያቸው የነበረው አርበኛው አብዲሳ አጋ እንደነበሩ መረጃውን በወቅቱ ከነበሩት አባቶች በቀጥታ መስማቱን በእዚህ አጋጣሚ ለመግለጥ ይፈልጋል። ዛሬ በቄሮ ስም የተደራጁ የፅንፍ አካሎች የአርበኛ አብዲሳ አጋን ሥራ ለማፍረስ የሚደረግ ሙከራም መሆኑን ልብ ይሏል።
ህዳር 15/2012 ዓም በቦሌ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምን ተፈጠረ? ቪድዮውን ይመልከቱ።
ከደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር እና የሰንበት ትምህርት ቤቱ አገልጋይ ከአቶ መስፍን በዳዳ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment