Thursday, May 12, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 ወታደራዊ መግለጫ አወጣ።በአርባምንጭ አካባቢ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ላይ የተወሰደው ጥቃት በግንባሩ ኃይሎች መፈፀሙን ገለጠ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ምረቃ ላይ 


  • አቶ ጌታቸው ረዳ ጥቃቱን በድጋሚ በዛሬ መግለጫቸው አምነዋል፣
  • ጥቃቱ በህወሓት መንደር ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል፣
  • ፕሮፌሰር ብርሃኑ በመጪው ወር መግቢያ ወደ አውሮፓ ላጭር ጊዜ ያቀናሉ፣
  • የኢትዮጵያ ሰራዊት አርበኞች ግንቦት ሰባትን እንደ ስጋት አያየውም ይልቁንም በከፍተኛ ደረጃ   እምነት ጥሎበታል። 


ትናንት ግንቦት 3/2008 ዓም በአርባምንጭ አካባቢ በታጣቂዎች እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መካከል ግጭት መኖሩን ከአምስተርዳም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳት) እና አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እኩል አስታውቀው ነበር። ኢሳት በግጭቱ አንድ ከፍተኛ የአካባቢው  የኃይል አዛዥን ጨምሮ 20 የሚሆኑ የመንግስት ልዩ ኃይል አባላት መገደላቸውን ከማስታወቁም በላይ ጥቃት የፈፀሙት የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይሎች ናቸው በማለት የአካባቢው ሕዝብ እየተነጋገረ መሆኑን ገልጧል።የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በሌላ በኩል ከመንግስት የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ደረሰኝ ባለው ዜና ታጣቂዎቹ ከኤርትራ ተነስተው በዑጋንዳ አድርገው በሞያሌ  በኩል የገቡ ናቸው ብሏል።

ዛሬግንቦት 4/2008 ዓም ደግሞ የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደራዊ መግለጫ አውጥቷል።በእዚሁ ኢሳት በተሰጠው መግለጫም በአርባምንጭ አካባቢ የተፈፀመው ጥቃት የንቅናቄው የደቡብ ግንባር አንዱ ኃይል ብቻ የፈፀመው መሆኑን ገልጦ ''ጥቃቱ የተፈፀመው ከሚያዝያ 29 እስከ ግንቦት 1/2008 ዓም ድረስ በተደረገው የመረረ ፍልሚያ ከ20 በላይ የጠላት ኃይል ገድሎ ከሃምሳ በላይ የሚሆኑትን ማቁሰሉን እና ከግንባሩም የተሰዉ አሉ'' በማለት ያብራራል።በመቀጠልም መግለጫው  በወጣት አርበኞች የጎሬላ የውግያ ብቃት አስደናቂነትን ጠቅሶ ቀጣይ ጥቃቶች በሰሜን፣በደቡብ እና በመሃል እንደሚኖር ያብራራል።

 የአርበኞች ግንቦት 7 ግንባር ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥር 22/2008 ዓም ዋሽንግተን፣ደብል ትሪ ሂልተን ላይ በተጠራ ሕዝባዊ ስብሰባ  ባደረጉት ንግግር “ወታደሮቻችን ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፤ ትግላችንን ለመቀላቀል ካሁን በኋላ  ለምትፈልጉ  ወደ  ሰሜን ብቻ  መሄድ  የለባችሁም”  ማለታቸው ይታወሳል።(ለዝርዝሩ ይህንን ተጭነው ይመልከቱ አርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊቱ ከኤርትራ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖራቸውን ገለጠ)።

በሌላ በኩል የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ሐሙስ ግንቦት 4/2008 ዓም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ጥቃቱን በድጋሚ አምነው ''ከአስመራ ሲነሱ እናውቅ ነበር''በማለት ጋዜጠኞቹን ግራ አጋብተዋል። አንድ ጋዜጠኛ የአቶ ጌታቸውን ቃል እንደማያምን ሲገልጥ እንዲህ ብሏል ''በቀላል አመክንዮ (ሎጂክ) ለማየት የሚሞክር ማንም ሰው የአቶ ጌታቸው ንግግር የሚታመን አለመሆኑን ለማወቅ ይችላል።ምክንያቱም ከአስመራ ጀምሮ የሚያውቁ ከሆነ እንዴት ሞያሌ ሲገቡ ዝም አሉ።ደግሞስ ገብተው አርባምንጭ እስኪጠጉ ምነው ምንም እርምጃ አልተወሰደም?'' በማለት ጠይቆ  '' ይልቁንም አውቀው ዝም ብለናል ካሉም አርበኞች ግንቦት 7 ምን ያህል አራት ኪሎ ውስጥ ሰርጎ መግባቱን እና የድርጅቱ አቅም ትልቅ ደረጃ መድረሱን ያሳያል'' በማለት ገልጧል።

ከእዚሁ ጋር በተያያዘ የአርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት በህወሓት መንደር ከፍተኛ ድንጋጤ ከመፍጠሩ በላይ አሁን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ያለው የመንግስት ሰራዊት አርበኞች ግንቦት 7 ኃይልን እንደ ስጋት እንደማይመለከተው እና ይልቁንም ከፍተኛ መተማመን እንዳደረበት የመከላከያ ምንጮች ይጠቁማሉ።ለእዚህም ምክንያቱ ፕሮፌሰር ብርሃኑ በተለያየ ጊዜ ለኢሳት በሰጡት መግለጫ አርበኞች ግንቦት 7 ከህወሓት መወገድ በኃላ ሰራዊቱን እንደማይበትን በሰጡት ቃል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ዘግይቶ በደረሰ ዜና ደግሞ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ግንቦት 4/2008 ዓም ምሽት ለኢሳት ራድዮ የአርባንጭ ዙርያ ጥቃትን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ላይ መንግስት አውቅ ነበር ማለቱን አስመልክተው በሰጡት ምላሽ ይህ የማይመስል ነገር ነው እንዴት ነው አንድ መንግስት  ወታደሮቹ እስኪያልቁ ድረስ አውቄ ነው ዝም ያልኩት ማለት  ፈፅሞ ሐሰት መሆኑን ገልፀው ተዋጊው ኃይል ከኤርትራ ተነስቶ በአይሮፕላን በኡጋንዳ በኩል ገቡ የሚለው ሌላው አሳፋሪ አገላለፅ መሆኑን ሲያብራሩ እነኝህ ሰዎች በአይሮፕላን ሲመጡ መሳርያ ጭነው ነው የመጡት ማለት ነው? ማንም እንደሚያውቀው የአለምን የአየር መንገድ ጉዞ አንዲት የጥፍር መቁረጫ ማሳለፍ በማይፈቀድበት ሁኔታ እንዴት ተብሎ ነው መሳርያ ተጭኖ የሚኬደው በማለት ሃሳቡን አጣጥለውታል።

በመጨረሻም የግንባሩ ወታደራዊ መግለጫ በወጣበት በዛሬው ተመሳሳይ ቀን ዘሐበሻ የተሰኘው ድረ-ገፅ እንደዘገበው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጪው ወር መጀመርያ ሳምንት ከኤርትራ ወደ አውሮፓ መጥተው ከሕዝብ ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ እና ጁን 4 የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ዝግጅት  በኦስሎ እንደሚደረግ ያብራራል።

ዘሐበሻ የተገኘው ፅሁፍ እንደሚከተለው ቀርቧል።


ጁን 4፥ 2016 የሚያካሂደዉን የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሰሜን አዉሮፓ አቀፍ ህዝባዊ ውይይትና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተመለከተ የተሰጠ አጭር ጋዜጣዊ መግለጫ
ሃገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካለችበት ውስብስብ ችግር ለመታደግ ለሃገሪቱና ህዝቧ ቅን የሚመኝ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ህወሓትን ለማስወገድ በሚደረገዉ ተግባራዊ ትግል ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
ኢትዮጵያ በአጣብቂኝና በመንታ መንገድ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑንና፣ ፋሽስቱን የህወሓት አገዛዝ ከመደገፍ ተለይቶ እንደማይታይ ብዙዎቻችን እንስማማበታለን።
አርበኞች ግንቦት ሰባት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ መሰማራት ይችል ዘንድ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ጥሪዉን ካስተላለፈ ሰንበት ብሏል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ አርበኛ ታጋዮችና ከፍተኛ የአመራር ብቃት ያላቸዉን ምሁራን ጨምሮ በረሃ ወርደው የወያኔን አገዛዝ መፋለም ጀምረዋል። በግምባር መሰለፍ ያልቻሉት ደግሞ በገንዘባቸዉና በእዉቀታቸዉ የሚፈለግባቸዉን በማበርከት ላይ ይገኛሉ፣
ትግሉ የሚካሄደዉ ሃገሪቱን ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠረ፣ ብሎም የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት፣እንዲሁም በልመናና በብድር የሚገኘዉን መዋእለ ንዋይ በማሟጠጥ ተቃዋሚዎቹን ለማጥፋት በሚንቀሳቀስ የወንበዴ ቡድንና ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ዉጭ ሌላ ምንም አጋር በሌለዉ የነጻነት ታጋይ መካከል ነዉ፣፣
ለነጻነት የሚደረግ ትግል እልህ አስጨራሽና አድካሚ ነዉ፣ ዉድ ዋጋና በገንዘብ የማይተመነዉን ህይወትም ያስከፍላል፣ዉጤቱ ግን ከሁሉም ነገር የበለጠና ዉድ ነዉ፣፣ በመሆኑም ይህ ወሳኝ ሐገርን የማዳን ጥረት ዉጤታማ እስኪሆን ድረስ ነጻነት ናፋቂ የሆን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ያላሳለሰና ሁለገብ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፣፣
ይህንን መሰረት በማድረግ June 4, 2016 የሰሜን አዉሮፓ ሃገራትን ያማከለ ታላቅ ህዝባዊ ዉይይትና የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም በኖርዌ ሃገር ኦስሎ ከተማ ተዘጋጅቷል፣፣
በዚህ ፕሮግራም ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ መሪ ታጋይ አርበኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከበረሃ በመንቀሳቀስ በመካከላችን በአካል በመገኘት ስለትግሉ ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ፕሮግራሙ የተዘጋጀዉ ከተለያዩ የሰሜን አዉሮፓ ሃገሮች ተዉጣጥቶ በተቋቋመ ግብረ ሃይል ሲሆን በኖርዌ ሃገር በሚገኘዉ የዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት የበላይ አሰተባባሪነት ነዉ፣፣ በዚህ ታላቅ አህጉራዊ ስብሰባ ላይ በኖርዌይና በተለያዩ የሰሜን አዉሮፓ ሃገራት የሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በብዛት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፣
ፕሮግራሙ ከየትኛዉም የአለማችን ክፍል ለሚመጣ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ ክፍት ነዉ፣፣ በተለይም በስካንዲኒቪያንና፣ በአጎራባች የአውሮፓ ሃገራት የምንኖር ነጻነት ናፋቂ ዜጎች የፕሮግራሙ ታዳሚዎች በመሆን የበኩላችንን እንድንወጣ ግብረሃይሉ በትህትና ያሳስባል፣፣
በተለያዩ አህጉራት ያላችሁና በአካል መገኘት የማትችሉ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ ሃገር የማዳን ጥሪ የትግል አጋርነታችሁን በሚያመቻችሁ መንገድ ታሳዩ ዘንድ አስተባባሪ ግብረ ሃይሉ በአክብሮት ይጋብዛል።
የፕሮጋራሙ ቀን፣ June 4, 2016
ሰአት፣ ከ14፣00 ሰአት ጀምሮ
የፕሮግራሙ ቦታ፣ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል
ተጋባዥ እንግዳ፣ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ መሪ ከኤርትራ

ኢትዮጵያችን በክብር ለዘላለም ትኖራለች!!
የዲሞራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
ሜይ 13፣ 2016 ኖርዌይ፣ ኦስሎ,




ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Tuesday, May 10, 2016

ሰበር ዜና - የደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ መንግስትን በትጥቅ ትግል የሚጥል አዲስ የታጠቀ ተቃዋሚ ኃይል ተመሰረተ ጦርነት አውጀዋል። New rebel group formed in Northern Bahr el Ghazal state

ደቡብ ሱዳን 

የደቡብ ሱዳን  የእርስ በርስ ጦርነት በስምምነት ተደመደመ የሚለው ዜና ከተሰማ ገና አንድ ወር ሳይሆነው አዲስ ኃይል እራሱን ከደቡብ ሱዳን ሰራዊት ገንጥሎ ማውጣቱን ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 2/2008 (ሜይ 10/2016) ዓም ለሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ገልጧል።እንደጋዜጣው ዘገባ:

  • ተቃዋሚው ከአስሩ የሱዳን ክ/ሀገሮች አንዱ በሆነው በሰሜን ''ባህር አል-ገዚ'' ክፍለ ሀገር የሚገኘው የጦር ክፍል እራሱን ለይቶ መመሸጉን ይገልጣል፣
  • እራሳቸውን የለዩት መኮንንኖች እና በታጣቂ ተቃዋሚነት የቆሙት ኃይሎች በቅርቡ ከርክ ማቻር ጋር  የተደረገው ስምምነት ከደቡብ ሱዳን ችግር ጋር ምንም የማይገናኝ እና ችግሩንም የማይፈታ ነው ይላሉ፣
  • አዲሱ ቡድን ስሙን እና አመራሩን በቅርቡ እንደሚገልፅ ገልጧል፣
  • አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት አሰራር (እንደነርሱ አገላለጥ ሲስተም) በአዲስ መቀየር አለበት ብለዋል፣
  • ''ባህር አል-ገዚ'' ክፍለ ሀገር ስልታዊ ክ/ሀገር ስትሆን ከዳርፉር እና አወዛጋቢው አብዬ ግዛት ጋር ትዋሰናለች።
የሱዳን ትሪቡን ሙሉ ዘገባ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።


May 10, 2016 (JUBA) - Officers from the armed opposition faction of the Sudan People’s Liberation Movement (SPLM) in Opposition in Northern Bahr el Ghazal state have defected and formed their own faction.
JPEG - 7.5 kb
General Dau Aturjong
The officers previously under the overall leadership of the First Vice-President, Riek Machar, have asserted that the 2015 peace agreement signed with president Salva Kiir, has not addressed the cause of the war.
The group is yet to announce the name of their faction and under whose leadership and the objective of the war they have declared to pursue.
An armed man identifying himself as Colonel James Deng Mayar told Sudan Tribune on Tuesday that they have announced a peaceful split from the armed opposition forces under the overall command of General Dau Aturjong, who allied himself and his forces to the First Vice President, Riek Machar.
The group, according to Mayar, has decided to join rank with brigadier General Agany Ayiii, one of the government officers who changed allegiance and joined General Peter Gatdet Yak, one of the senior rebel commanders, who defected from the rebel faction under Machar.
Gadet and several officers, some of whom have already returned to the country under separate arrangements, have rejected the peace agreement signed by the government and armed opposition in August last year.
“I confirm that we have split from SPLA-IO and joined General Agany Ayii,” Mayar told Sudan Tribune during an exclusive interview on Tuesday.
“We decided to continue with the struggle because we have to realize [Machar] was not committed enough to lead the struggle to achieve the objective of the war. We wanted to change that system and to establish a new system based on democratic principles," he explained.
He accused Machar of having allegedly failed to fulfil commitment he made to change the government under President Kiir and accepted the position in unity government under the terms of the peace deal which did not address the issues which caused the war.
Thousands of lives have been lost and properties destroyed, mainly in Upper Nile region at the height of conflict.
(ST)

SOURCE: SUDAN TRIBUNE MAY10,2016


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Saturday, May 7, 2016

ሚያዝያ 30/1997 በአዲስ አበባ ከአንድ ሚልዮን በላይ ሕዝብ በለውጥ ፍላጎት ሰልፍ የወጣበት 11ኛ ዓመት ሲታወስ (ቪድዮ) It is exactly 11 years since over one million Ethiopians demonstrated in Addis Ababa to bring democratic change and express their opposition against the current regime.

ይህንን ሚያዝያ 30/1997 ዓም የተደረገው ሰላማዊ  ሰልፍ በተመለከተ:
1/ ይህ የአንድነታችን ታሪክ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።ይህንን ታሪክ ማደብዘዝ በእራሱ አደጋ ነው።የፌስ ቡክ ባለቤቶች በሙሉ በመለጠፍ ትውልዱን ኢትዮጵያዊነት አለመሞቱን በዘመናችን ይህ ታሪክ ከሆነ ገና 11 ዓመቱ ነው አይዞን ማለት ተገቢ ነው ኢትዮጵያ አለች።ለዘላለምም ትኖራለች።
2/  ይህ ሁሉ ሰልፈኛ በ11 ዓመታት ውስጥ ካለፉት ከጥቂቶቹ በቀር ሌላው አሁንም ከእዚህ የለውጥ ፍላጎት አንዳች ስንዝር ወደኃላ እንዳላለ ለማወቅ ሳይንቲስት መሆን አያስፈልግም።
3/ በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ ሰልፍ ወጥቶ አንዳች የዘረፋ ወይንም ንብረት መውደም ተግባር ሳይፈፀም በሰላም የገባ ሕዝብ ነው።አስደናቂ እና ታሪካዊ ሰልፍ።


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, May 5, 2016

ጀግናው አርበኛ ኮ/ል አብዲሳ አጋ የቦሌ ቅዱስ ሚካኤልን ታቦት ካስተከሉ አባቶች ውስጥ አንዱ ናቸው።እውነተኛ ታሪክ (የጉዳያችን ማስታወሻ - Gudayachn Exclusive)

ኮ/ል አብዲሳ አጋ 
ከጌታቸው በቀለ  

የኮ/ል አብዲሳ አጋ ሃውልት አዲስ አበባ ላይ ባለመቆሙ ሁል ጊዜ ይፀፅተኛል።የኮ/ል አብዲሳ ቤት እኔ አዲስ አበባ ካደኩበት ቤት ቅርብ ስለነበር እና አባቴ ደግሞ አርበኛው ከእዚህ ዓለም ሳያርፉ በጣም ያውቃቸው ስለነበር  ስለ እርሳቸው ብዙ እንዳውቅ እና ትልቅ ክብር እንዲኖረኝ አድርጎኛል።በልጅነቴ ፀበል ቅመሱ ወይንም ሌላ መልዕክት ተልኬ እቤታቸው ስሄድ የኮ/ል አብዲሳ ባለቤት ብዙ ጊዜ ሰፊው ግቢያቸው ላይ በተንጣለለው ቤት በረንዳ ላይ ሆነው አገኛቸዋለሁ። ስለ አባቴ እና  ቤተሰቡ ደህንነት ከጠየቁኝ በኃላ ነው የመጣሁበትን ጉዳይ የሚጠይቁኝ።ከግቢያቸው ጎን ያለው ወፍጮቤትም አንዱ በኮ/ል አብዲሳ በር በኩል የሚያመላልሰን ሌላው ምክንያት ነበር።

የግቢውን የብረት በር አልፌ ስገባ ውሻቸው ለአመል ያህል በታሰረበት ሲጮህ ትዝ ይለኛል። ከሁሉ ትዝ የሚለኝ የኮ/ል አብዲሳ አጋ ወንድ ልጃቸው ነው።ስሙ  ዲያቆን ሳሙኤል ይባላል (የፊቱ ቅላት አሁን ድረስ አይረሳኝም) ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን በትርፍ ጊዜው ይቀድስ ነበር። በተለይ በፆመ ፍልሰታ ወቅት በአባታችን ቭኦልስ መኪና ውስጥ ሆነን እቤታቸው ድረስ አብሮን ይመጣ ነበር።አባቴ ስለ ኮ/ል አብዲሳ አጋ አውርቶ አይጠግብም። ቦሌ መንገድ የሚገኘው ወሎ ሰፈር ላይ ከአባቴ ጋር ድሮ ቤት ሲሰሩ አንድ ላይ ነው የሰሩት።ኮ/ል አብዲሳ ቤቱም መሬቱም በንጉሡ እንደተሰጣቸው ሰምቻለሁ።ኮ/ል አብዲሳ ቤት ሳሎን ስትገቡ (እኔ ስለገባሁ በኩራት አወራለሁ) የኮ/ል አብዲሳ በወታደራዊ ማዕረግ የተንቆጠቆጠ የቁም ፎቶ እና በአርበኝነት የነበሩበት ፎቶ ይገኛል።በመካከል ደግሞ የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ ፎቶ ተሰቅሏል።
ኮ/ል አብዲሳ አጋ ከክብር  ኒሻን ጋር 

ሌላው የማውቀው ጉዳይ ደግሞ ቦሌ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ካስተከሉት አባቶች ውስጥ አንዱ ጀግናው ኮ/ል አብዲሳ አጋ እንደ ነበሩ ነው።በወቅቱ ቤተ ክርስቲያኑ ሊሰራ የታሰበው ወሎ ሰፈር ፊት ለፊት (ካራማራ ሆቴል የነበረበት ፊት ለፊት) የሚገኘው ሜዳ ላይ ነበር።ይህ  ቦታ እስከ ቦሌ ማተምያ ቤት ማዶ ያለው ቦታ  የራስ ብሩ ቦታ  ይባል ነበር አሉ።ቀድሞ እዚህ ቦታ ላይ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ነበር። ጣልያን ነው ያቃጠለው ሲሉ አባቶች ነግረውኛል።ቦታውም ላይ ታቦት የነበረበት ቅዱስ ቦታ ትቼ አልሄድም ብለው የሚኖሩ መነኩሴ ነበሩ።ስለሆነም ቦታው ''የአባ ሜዳ'' ተባለ።ኢህአዴግ መጥቶ ቦታው ላይ ህንፃ እስኪሰራ ድረስ ቦታው 'አባ' አንዳንዴ በልማድ 'አባይ ሜዳ'  ይባል ነበር።እዚህ ቦታ ላይ ነበር ኮ/ል አብዲሳ የሰበካ አባል የነበሩበት የቦሌ ሚካኤል ታቦት ሊተከል የታሰበው።በኃላ ግን  በምክር እንደ ገዳም ይሁን ተብሎ ያን ጊዜ የነበረውን ጫካ አልፈው አሁን ካለበት ቦታ ተተከለ።

ይህ ቀድሞ አባ ሜዳ የተባለው ቦታ ላይ የአካባቢው ሕዝብ ቤተ ክርስቲያን ሊሰራ በኢህአዴግ ዘመን 1987 ዓም ከ10 ሺህ ሕዝብ በላይ ፍርም ፈርሞ (እራሴም ነበርኩበት) ለአቡነ ጳውሎስ ማመልከቻ አስገባ።አቡኑም ደብዳቤ ለማዘጋጃ ቤት በወቅቱ ለነበሩት ተፈራ ዋልዋ ፃፉ።አንድ ወቅትም ወርደው ቦታውን አዩት።የራስ ብሩ የልጅ ልጅ የነበሩት (አሁን አርፈዋል) ወ/ሮ በልዩ ቦታው የአያታቸው በነበረ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት እንደነበረበት በፅሁፍ መሰከሩ።ማዘጋጃ ቦታውን ምልክት አደረገ።ካርታ ክፍል ተመራ። ጉዳዩን የሚከታተሉት አባቶች ጋር ቦታው ላይ ተከታታይ እሁዶች ፀሎት ተደረገ።በመካከል አሊ አብዶ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነ።ፋይሉ ተደበቀ።ሕዝብ ጮሆ ቢናገር የሚሰማው አጣ። አሊ አብዶ ካርታ ለቤተ ክርስቲያንነት ካርታ የተሰራለትን ቦታ ለልማት በሚል ህንፃ እንዲሰራ አደረገ።አሁንም ግን ወንዙ ተጠግቶ የቤተ ክርስቲያኑ ቦታ አለ።የፍትህ ያለህ እያለ።ለሁሉም ኮ/ል አብዲሳ አጋ ሊያስተክሉበት የነበረበት ቦታ ታሪክ ይህን ይመስላል።ለኮ/ል አብዲሳ ግን ሃውልት ያስፈልጋቸዋል።የሁላችንም ታሪክ የሆነ ያውም በጣልያን ምድር ላይ ሠርተዋልና።ዛሬ ዛሬ የኮ/ል አብዲሳን ቤተሰብ እና ስለ እርሳቸውም የቀረበ ግንዛቤ ሳይኖረው በጎሳ ስሜት እየተነዳ የሚፅፍ ሰው ፅሁፍ ስመለከት በጣም ያንስብኛል።

በነገራችን ላይ ወሎ ሰፈር የሚገኘው በንጉሡ የተበረከተላቸው የኮ/ል አብዲሳ አጋ ቦታ በኢህአዴግ የዛሬ አራት ዓመት ገደማ ቦታው ለልማት ይፈለጋል ተብሎ ተነስተዋል።ድሮም ስርዓቱ ስለ ብሔር ይዘፍናል እንጂ አርበኛ ማክበር አልፈጠረበትም።ዛሬ 75ኛው የድል ቀን ሲዘከር ኮ/ል አብዲሳ አጋን ማንሳት ተገቢ ነው።ክብር በክብር እንድንቆም ላደረጉን አርበኞቻችን።

ከእዚህ በታች ከድረ ገፅ ስለ ጀግናው አርበኛ ኮ/ል አብዲሳ አጋ የተገኘውን ታሪክ እንደሚከተለው ይቀርባል 

አብዲሳ አጋ ጣልያን በአድዋ የደረሰበትን ሽንፈት ለመበቀል ባደረገው የ1928ዓ.ም ወረራ ወቅትበምርኮኝነት ጣልያን ተወስዶ ከታሰረ በኋላ የተሰጠውንብርድልብስ ቀዳዶ በመቀጣጠል በመስኮት በኩል ማምለጡ ጎልቶ የሚወሳለት አርበኛ ነበር። ተሳክቶለት ቢያመልጥ እንግዳ የሆነ አገር እንደሚቀላቀል እና ለሃገሩም እሩቅ መሆኑን እያወቀ እንኳን ነጻነቱን አሳልፎላለመስጠት በሚል ብልጠት በታከለበት ሁኔታ ያመለጠው አብዲሳ አጋ አስገራሚ ጀግንነቱን ያሳየው ከእስር ቤቱካመለጠ በኋላ ነበር።በኦሮሚያ ወለጋ የተወለደው አብዲሳ የኢትዮጲያን ጦር የተቀላቀለው በ14 አመቱ ሲሆን ጣልያን ኢትዮጲያን ስትወር አገሩን ለመከላከል በውጊያ ላይ በአስደናቂ ወኔ ይዋጋ ነበር። በውጊያ ከተማረከ በኋላ ጣልያኖች አገራቸው ወስደው በሲሲሊ ደሴት ላይ ባሰሩት ግዜ ነበር አብሮት የታሰረውን የዩጎዝላቪያ ምርኮኛ ሁሊዮ የተወዳጀው። በጋራ እቅድ ካወጡ በኋላ ከእስር ቤት ያመለጡት እነ አብዲሳ በሲሲሊ ደሴት ላይ ተደብቀውአልተቀመጡም። ካመለጡ ከጥቂት ቀናት በኋላ በአብዲሳ መሪነት እና እቅድ አውጪነት በሌሊት ታስረው ወደነበረበት እስር ቤት በመሄድ እና ጥቃት በመፈጸም የታሰሩትን እስረኞች ነጻ በማውጣት የኢትዮጲያውያንን ጀግንነት በአድዋ ብቻ ሳይሆን በጣልያን ምድርም ያስመሰከረ ድንቅ ተዋጊ ነበር። 

የአብዲሳ ጀግንነት በዚህ አላበቃም ከእስር ቤት ያስመለጧቸውን ሰዎች በማሰባሰብ የራሱን ጦር ካደራጀ በኋላ ጣልያኖችን በገዛ አገራቸው ያንቆራጥጣቸው ገባ። ከአድዋ ጀምሮ የኢትዮጲያውያንን ወኔ የተረዱት ጣልያኖች የአብዲሳን ጦር በፍርሃት ያዩ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች ከጣልያን ጦር ጋር በመዋጋት ብዙ ድሎችን እያስመዘገበ ነበር። ቆራጥነቱን የተረዱት ጣልያኖች የሚያረጉት ግራ ቢገባቸው ከበርካታ ስጦታዎች ጋር ጦሩን ይዞ የጣልያንን ሰራዊት እንዲቀላቀል መማጸን ጀምረው ነበር። ለፋሺስት ጦር መዋጋት አገር መክዳት እንደሆነ አስረግጦ የተናገረው አብዲሳ ትግሉን አፋፍሞ በቀጠለበት ወቅት የሁለተኛው የአለም ጦርነት ተቀሰቀሰ። የተባበሩት የአሜሪካ እና እንግሊዝ መንግስታት ከጀርመን ጋር ያበረችውን ጣልያንን እየተዋጉ በነበረ ሰዓት ስለ አብዲሳ ዝና ከሰሙ በኋላ ለጦሩ የሚገባውን ድጋፍ በማድረግ ፋሺስት ስራቱን ለማዳከም እንደ ዋንኛ መንገድ ሆኗቸው ነበር። 

በድጋፉ በመጠናከርም የጣልያንን ሰራዊት ድባቅ በመምታት ጦሩን እየመራ ሮም ከተማ ከአሜሪካኖቹ ሁላ ቀድሞ የኢትዮጲያን ባንዲራ እያውለበለበ የገባው ጀግናው አብዲሳ አጋ ነበር። በኋላ ሮም የደረሰው የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ እና የአሜሪካ ጦር አብዲሳን በማሞካሸት ከተጨማሪ ወታደሮች ጋር በአለም አቀፉ ህብረት ስር የሚመራ ጦር መሪ አድርገው ሾመውት ነበር። በኋላም ጀርመንን ለማሸነፍ በሚደረገው የመጨረሻ ውጊያ ወቅት የአብዲሳ አመራር መኖር ያመኑበት እንግሊዞች ወደ ጀርመን ልከውት ግዳጁን በሚገባ በመወጣት የኢትዮጲያን ባንዲራ ከእጁ ሳይለይ በርካታየጀርመን ከተሞችን ነጻ ማውጣት ችሎ ነበር። 

ከጦርነቱ መገባደድ በኋላም የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካመንግስታት ጦራቸውን ተቀላቅሎ እንዲቀጥል በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን አቅርበውለት ነበር። እብዲሳ ግን ኢትዮጲያ ምንም ያህል ድሃ ብትሆንም ህዝቡን እና መንግስቱን ጥሎ እንደማይሄድ አስረግጦ በመናገር ጥያቄውን ውድቅ አደረገ። በዚህ የተናደዱምዕራብውያንም በፈጠራ ወንጀል ከሰው ወደ እስር ቤት አስገብተውት ነበር። በኋላም እስሩ ወደ ገንዘብ ቅጣት ተቀይሮ ከተከፈለ በኋላ በክብር ወደ ሃገሩ ሊመለስ ችሏል።ወደ ኢትዮጲያ ከተመለሰ በኋላ ሰራዊቱን በቅንነት ያገለገለው አብዲሳ በኮረኔልነት ማዕረግ የአጼ ሃይለስላሴ ልዩ ጠባቂ ጦር እየመራ ቆይቶ ንጉሱ ከስልጣን ከወረዱከጥቂት አመታት በኋላ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። የአብዲሳ አጋን ሙሉ የህይወት ታሪክ በደንብ ማወቅከፈለጉ “በኢጣሊያ በረሃዎች (ሻምበል አብዲሳ አጋበአርበኝነት ጀብዱ የሰራ ኢትዮጵያዊ ታሪክ) “ የተሰኘየህይወት ታሪክ መጽኃፉን ማንበብ ይችላሉ።



ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

''በ1928 ዓም ለዓለም ማኅበር ለተናገርነው ይሄው ታሪክ መሰከረ። ዛሬም በሚያሳፍር መንገድ የፈረሰው የዓለም ማኅበር ወራሽ ለሆነው የተባበሩት መንግስታት ቃላችንን ለማሰማት ቆመናል '' ቀ/አፄ ኃይለ ስላሴ በ1956 ዓም (1963 ዓም እ ኤ አ) ጄኔቭ ያደረጉት ሙሉ ንግግር (ኦድዮ-ቪድዮ)

ዛሬ ሚያዝያ 27/ 2008 ዓም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከአምስት ዓመታት ከጣልያን ጋር ከተደረገ የነፃነት ትግል በኃላ ተመልሶ በቦታው የተተከለበት ዕለት ነው።ኢትዮጵያ በአምስት ዓመታቱ የትግል ወቅት በዓለም ማኅበር (አሁን የተባበሩት መንግሥታት በሚባለው) የነበራት መቀመጫ እንዳይነሳ የተደረገበት አንዱ ምክንያት የንጉሡ በጄነቭ ተገኝቶ መከራከር ነው።ጣልያኖች እና አንዳንድ የእነርሱ የጥቅም ተጋሪ መንግሥታት ''የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ያለበት የዓለም ማህበር ወንበር ይነሳ ኢትዮጵያ በኢጣልያ ስር ነች'' እያሉ ሲደነፉ ንጉሰ ነገስቱ ከኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጋር መክረው ያመጡት ሃሳብ ታሪካዊ እና አሸናፊ ሆነ። 

ይህም ሃሳብ ኢትዮጵያ የንጉሰ ነገስት መንግስቷ አልፈረሰም።አዲስ አበባ ተያዘች ማለት ኢትዮጵያ ተያዘች ማለት አይደለም።ይልቁንም የመንግስታችንን መቀመጫ ዋና ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ጎሬ (የዛሬዋ ኢሊባቦር) አዙረናል።እዚያ የሚገኘው መንግስታችንም ትእዛዝ እየተቀበለ እየሰራ ነው።ለእዚህም ከአርበኞች ጋር ያደረጉት የመልክት ልውውጥ ሁሉ በእጄ አለ።የሚሉ ማብራርያዎች የኢትዮጵያን ቦታ ከዓለም ማህበር እንዳይነሳ አስደረገ። ይህ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ተገዝታ እንደማታውቅ ትልቁ የመከራከርያ ሃሳብ ነው።ብዙ የታሪክ ምሁራን ይህንን ነጥብ ስዘነጉት ይታያል።አንድ መንግስት በዓለም ማኅበር (የተባበሩት መንግሥታት) ላይ ቦታው ካልተነካ በመንግሥትነት አለ ማለት ነው።የንጉሰ ነገስቱ ጄኔቭ መገኘት የሰራው ትልቁ ነገር ይህ ነው።ከእዚህ በላይ ጣልያን ንጉሱን ይዞ አስሮ ወይንም ገድሎ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አንድነት በኃላ ምን ይሆን ነበር? የሚለው ሌላው ሃሳብ ነው።ከእዚህ በታች ንጉሡ የተባበሩት መንግሥታት የሚገጥመውን መፃኢ ተግዳሮት የገለጡበት ንግግር እነሆ: 
ንግግሩ በ1956 ዓም (1963 ዓም እ ኤ አ) ጄኔቭ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተደረገ ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Saturday, April 30, 2016

ሰበር ዜና - በዴር ሱልጣን የሚገኘው የኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ትናንት በስቅለት በዓል ወቅት ግብፆች ሁከት ለማንሳት ሞክረው ነበር ( Gudayachn exclusive)



ለጉዳያችን በደረሰ መረጃ መሰረት በኢየሩሳሌም ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ጎልጎታ፣ ዴር ሱልጣን የሚገኘው የኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ትናንት ሚያዝያ 29/2008 ዓም በስቅለት ዕለት ግብፆች በቦታው ይገባናል ሁከት ለማስነሳት ሞክረው ነበር።በስፍራው ለትንሣኤ በዓል የመጡ እና በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ''አባቶቻችን ባቆዩት ቅርስ ላይ መቃብራችን እዚሁ ይሆናል'' ብለው የመጣውን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንዳሉ በመካከል የእስራኤል ፖሊስ ገብቶ ጉዳዩን ለማብረድ ችሏል።ግብፆች የእዚህ አይነቱን ግርግር በዴር ሱልጣን የኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ሲፈፅሙ ይህ የመጀመርያ አይደለም።የዴር ሱልጣን ጉዳይ በሁሉም ወገኖች ትኩረት የሚሻ እና በተለይ በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገዳማቱን የማስከበር ኃላፊነታቸውን በተደራጀ መልክ መወጣት እንዳለባቸው የሁሉም እምነት ነው። 

ከእዚህ በታች የኢትዮጵያ ይዞታ የሆኑ ገዳማት በኢየሩሳሌም የሚገኙባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ይረዳን ዘንድ ከቀሲስ ፋሲል ታደሰ ገፅ ላይ የተገኘውን ፅሁፍ  የገዳማቱን ቦታ የሚገልፀው ክፍል ብቻ እንደሚከተለው ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ገዳማት በኢየሩሳሌም

የኢትዮጵያና የእስራኤል ግንኙነት በዘመነ ብሉይ በንግሥተ ሳባ ወደ ሰሎሞን በመሄዷ የተጀመረ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሕዝበ ኢትዮጵያ ለበዓል /ሊሠግዱ/ ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዙ ኖረዋል፡፡ በመሆኑም ከዴር ሱልጣን ጀምሮ የኢትዮጵያ ቦታዎች አሏት፡፡ 

1.    ዴር ሱልጣን፡- ንግሥት ሳባ ከክ.ል በፊት በ1013 ዓመተ ዓለም ገደማ ኢየሩሳሌም ስትሄድ ሠራዊቷን እና ጓዟን ያሳረፈችበት ቦታ ነው፡፡ 1ኛ ነገ. 10፣ 2ኛ ዜና. 9÷1-9 ቀራንዮ (ጎልጎታ) አጠገብ ይገኛል፡፡ በተለያዩ የተንኮል ተግባራት ዋናውን ግብጻውያን የወሰዱት ሲሆን አሁን የአርባዕቱ እንስሳ እና የቅዱስ ሚካኤል ታቦታት የሚገኝበት ጠበብ ያሉ ቤተመቅደሶች እና በጥም ጠባብ የሆኑ የመነኮሳት ማደሪያዎች ይገኙበታል፡፡ 

2.   ቅዱስ ፊልጶስ፡- የኢትዮጵያ መንበረ ጵጵስና የሚገኝበት ሲሆን የገዳሙ ጽ/ቤት እና ኢትዮጵያዊውን ጀንደረባ ባጠመቀው በቅዱስ ፊልጶስ ስም ቤተክርስቲያን ይገኛል፡፡ በአፄ ዮሐንስ ትእዛዝ መ/ር ወልደሰማዕት በ1883 ዓ.ም የገዙት ቦታ ነው፡፡ 

3.   ደብረገነት ኪዳነምህረት፡- አሮጌ ከተማ ከሚባለው ውጪ በነቢያት መንገድ አጠገበት ትገኛለች፡፡ የመነኮሳት መኖሪያ የእንግዶች መቀበያ እና አዳራሽ በመግቢያዋ የሚገኝ ሰፋ ያለ ይዞታችን ሲሆን ወደ ገዳሙ የሚወስደው መግቢያ መንገድም “ርሆብ ኢትዮጵያ” ተብሎ ይጠራል፡፡  ቦታው በ1882 ዓ.ም አፄ ዮሐንስ በላኩት ወርቅ የተገዛ ሲሆን ሕንጻውን ያስፈጸሙት በ1885 ዓ.ም. አፄ ምኒልክ ናቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ይዞታቸው በኢሩሳሌም ከተማ የሚገኙ ናቸው፡፡ 

4.   አቡነ ተክለሃይማኖት/አልአዛር/- በኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ 12ሺህ ሜትር ካሬ ስፋት ለው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ይዞታ ሲገኝ በጽድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ስም ቤ/ክ ታንጿል፡፡  የኢትዮጵያን መካነ መቃብር በዚህ ይገኛል፡፡ አፄ ኃ/ሥላሴ ያስገዙት ቦታ ሲሆን በአቡነ ፊልጶስ ጊዜ በ1953 ዓ.ም. ተመሠረተ፡፡ 


5.   ቅድስት ሥላሴ፡- በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ከሩብ ጋሻ የማያንስ ቦታ ሲኖር የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተሰርቷል፡፡ ነገር ግን በአረቦችና በእሥራኤል ጦርነት ምክንያት በአካባቢ ሰው ሊኖር ባለመቻሉ ታቦቱም መነኮሳቱም ተዘዋውረው በኢያሪኮ ይኖራሉ፡፡ ቤተክርስቲያኑ በ1925 ዓ.ም. በእቴጌ መነን የጠተሠራ እንደነበረ ይነገራል፡፡ 

6.   ቅዱስ ገብርኤል፡- በኢያሪኮ ከተማ ለብዙ ጊዜያት የአትክልት ቦታ ሆኖ የቆየው የኢትዮጵያ ይዞታ የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ይገኝበታል፡፡ ቦታውን የሠጡት ወ/ሮ አማረች ዋለሉ በኋላ እማሆይ አማረች የተባሉ እናት በ1928 ዓ.ም ገዝተውት ለገዳሙ ሰጥተዋል፡፡ 

7.   ቤተልሔም፡- በምድረ ፍልስጥኤም ጌታችን ከተወለደበት ቦታ አጠገብ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ይገኛል፡፡ ቦታው ልዑል ራስ ካሣና ልዑል መኮንን ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ ያስገዙት ነው፡፡ 

                                                 
ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com 

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...