ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, August 29, 2022

በትግራይ ህዝብ ስም የተለመነውን እህል ከህዝቡ ነጥቆ በልቶ እያገሳ ኢትዮጵያን ለመውረር የተነሳውን ሽብርተኛው ህወሃትን ኢትዮጵያ በምን ዓይነት ቅጣት ትቅጣው?


ህወሃት በህዝቡ ስም እርዳታ ለምኖ ለህዝብ የሚሰጠው ግን የለም

  • በትግራይ ህዝብ ስም የገባውን የእርዳታ እህል ለህዝብ ሳይሰጡ በልተው የሚያገሱት እና በተለመነ እህል እየወፈሩ ያሉት እነ ጌታቸው ረዳ እና ደብረጽዮን ናቸው።

=======
ጉዳያችን 
=======

ኢትዮጵያ ማንንም በድላ አታውቅም።ለማንም አድልታ አታውቅም።እናት ያላትን ለሁሉም ሳታዳላ ሁሉንም እኩል አሳድጋለች። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያህል ታጋሽ ብቻ ሳይሆን የዘር ፖለቲካ በእዚህ ደረጃ ተነዝቶበት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ቢያልፍም ተቻችሎ ውሎ የሚያድር በሌላ ዓለም እምብዛም አይገኝም። የህወሃት የሽብር ቡድን በአማራ እና በአፋር ከህጻናት እስከ አዛውንት ሲገድል ከአንድ ሚልዮን የሚልቁ የትግራይ ተወላጆች ላይ መሃል አገር የተፈጠረ የህዝብ ለህዝብ ግጭት የለም።

የኢትዮጵያ ህዝብ ቆራጥ እና ጀግና ህዝብ እንደመሆኑ፣መንፈሳዊም ህዝብ ነው። ቀን አዘቀዘቀ ብሎ ጎረቤቱ ላይ አንዳች ክፉ ሲደረግ ዝም አይልም።የወንድሙ እና የእህቱ ጠባቂ እራሱ ጎረቤቱ ሆኖ እስከ ዘመናችን ዘልቋል። ይህ ማለት በአንዳንድ ቦታዎች ችግር አልነበሩም ማለት አይደለም።ነገር ግን እንደ ህዝብ በዘረኞች የደረሰበት ቢከፋም ሁሉን ታግሶ አሳልፎ፣አንዱ ለአንዱ መጠለያ ሆኖ ኖሯል። ወደፊትም ይኖራል።

የሽብርተኛው ህወሃት በኢትዮጵያ ላይ የሰራው ግፍ ግን ሞልቶ ከመፍሰስ አልፏል።ኢትዮጵያ ያላትን ሰጥታ በትግራይ ህዝብ ውስጥ የተደበቀውን የህወሃት ጀሌ እንደሌሎች ልጆቿል ያላትን አብልታ፣ሳትለብስ አልብሳ አሳድጋለች። ልጇ ግን ደጋግሞ ከድቷታል።ሰውነቷል ወግቷታል።መለያ ሰንደቅ ዓላማዋን አውርዶ በራሱ እራፊ ተክቷል። ከእናቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ኢትዮጵያን ለማፍረስ አሲሮባታል።ይህንን ሁሉ አድርጓት ግን ኢትዮጵያ ልጇ እርሷን ሲወጋ የአዝመራው ጊዜ ስላለፈበት ርሃብ ሲገባ የእርዳታ እህል ከውጭ ለምና ልጇን አበላች።የትግራይ ጀሌው ግን ለእርዳታ የመጣበትን መኪና ሳይቀር ከእናቱ ከኢትዮጵያ ነጥቆ የበላበትን መሶብ መልሶ እናቱን ሊወጋበት ተጋበዘ። ከእዚህ ሁሉ ግፍ በኋላየተለመነ የእርዳታ እህል በልቶ የተለመነ እህል እያገሳ ኢትዮጵያን ለመውረር የተነሳውን የእርግማን ልጅ ህወሃትን ኢትዮጵያ በምን ዓይነት ቅጣት ትቅጣው? የሚለው ወቅታዊ ጥያቄ ነው። እናት ልጇ መጀመርያ ሲረብሽ ታልፈዋለች።ሁለተኛ መጥቶ ሲበጠብጣት በምክር እና በልምጭ መለሰችው። ይህንን ሁሉ እረስቶ የእርዳታ እህል በልቶ እያገሳ በጩቤ ሊወጋት የመጣውን የእርግማን ልጅ ህወአትን ኢትዮጵያ በምን ዓይነት ቅጣት ትቅጣው?
============/////=========

No comments:

መንግስት ከዲፕሎማሲያዊ መፋዘዝ ይውጣ! የአረብ ሊግ በአባይ ግድብ አንጻር የወሰነውን የጸብጫሪነት ተግባር በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የምላሽ መግለጫ ብቻ የሚበቃ ሊሆን አይገባም።መንግስት ያልሰራው ግዙፍ ስራ ኢትዮጵያን ለአደጋ እንዳያጋልጣት ያሰጋል።

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያቤት መንግስት በፍጥነት ሊሰራቸው የሚገቡት አምስት ወሳኝ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራት ========= ጉዳያችን አለርት ========= የአረብሊግ አንዱ የሚታወቅበት መለያው እንደባዶ ቆር...