ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, August 27, 2022

መከላከያ እንዴት እንደሚዋጋ ያውቃል! የህወሃት ዓለምአቀፍ ሁኔታዎችም ሆነ ይውጭ ደጋፊዎቹም ተቀዛቅዘውበታል። በቀጣይ የመከላከያ እና የአየር ኃይል እርምጃዎች ከመጠንከራቸው የተነሳ ማንም ማንንም ሊወቅስ የማይችልበት ደረጃ ልንደርስ እንችላለን።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዋና መስርያ ቤት

=======
ጉዳያችን
=======
ህወሓት በያዝነው ሳምንት በሰሜን ወሎ አንጻር የከፈተው ጦርነት ባለፈው ዓመት እንዳደረገው በርካታ የሰው ማዕበል በማንደርደር በሺዎች አስከሬን ላይ እየተረማመደ የ16ኛው ክ/ዘመን ጦርነቱን ቀጥሎበታል።ከእዚህ በፊት በነበረው ውግያ ህወሃትን አጅበው የመጡ ታዳጊዎችን የኢትዮጵያ መከላከያ እየተመለከተ እንዴት እነኝህን እገድላለሁ? በሚል ብዙ ቦታዎችን እየለቀቀ በመሄድ በህዝብ ላይ ብዙ አደጋ ደርሷል።በቀደመው ወረራ የከላከያ ኃይል እንዳሁኑ የልሆነበት እና በትጥቅም ደረጃ የአማራና አፋር ክልሎች ገበሬዎች ሳይቀሩ የትጥቅ እጥረት ነበረባቸው።ይህ ሁሉ አሁን አይኖርም።ከራሱ ከህወሃት እየገፈፈ የታጠቀ የአማራ እና አፋር ክልል ገበሬ ቁጥሩ የትዬለሌ የሚባል ነው።የአማራም ሆነ የአፋር ክልል ዛሬ ያወጡት መግለጫ የአፋር መግለጫ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የህወሃትን ድርጊት እንዲያወግዝ ሲጠይቅ የአማራ ክልል ህዝብ ቀጣይ የክልሉን ጥሪ እንዲጠባበቅ አሳስቧል።

ህወሃት ዓላማው ግልጽ ነው።በሰሜን ወሎ በኩል ትንሽ ከገፋ በኋላ ወደ ምዕራብ ትግራይ አቅጣጫ ለመዞር ነው።በእዚህ ጦርነት የትግራይ ወጣትን ከማስፈጀት እና ወጣቱ የትምህርት ጊዜው የመስከረም ወርን ከማሳለፍ ባለፈ አንዳች አይፈይድለትም። ይህ በእንዲህ እያለ ህወሃት ይደግፉኛል ያላቸው የምዕራብ አገሮች እንደጠበቀው ድጋፍ ሳይሰጡት ይልቁንም ከ''ፋኦ'' የሰረቀውን እህል እንዲመልስ ማሳሰብያ ሰጥቷል።የምዕራብ አገሮች ከዩክሬን ጦርነት በፊት እና በኋላ አንድ አይደሉም።ከዩክሬን ጦርነት በፊት የነበረው ኢትዮጵያን በሙሉ ዓይን የማስፈራራት ሁኔታ አሁን በርዷል።ሩስያ የጦርነቱን አድማስ ወደ ባልካን አገሮች በዋናነት ሰርብን ማዕከል አድርጋ ትገፋለች የሚለው ግምት ሰፍቷል። ስለሆነም ኢትዮጵያም የምዕራቡን ዓለም በሙሉ ዓይኗ መጣላቷ የአሜሪካን ጥቅም በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ይላትን ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥለው በመሆኑ አሁን ከህወሃት አንጻር ያለውን ጉዳይ በጥንቃቄ ነው የሚመለከቱት። 

ህወሃትን ሌላው ኪሳራ ላይ የጣለው የራሱ የውጭ ደጋፊዎቹ የማያሸንፈው ጦርነት ውስጥ እንደገባ እየነገሩት ነው። እነኝህ ደጋፊዎቹ መንግስት የሰላም ጉዳይ ማንሳቱን እንደድል ቆጥረው በየቲክቶኩ ሲጨፍሩ የነበሩት ሁሉ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ጠፍተውበታል። ይሄውም አብዛኛው በውጭ ያለው ማኅበረሰብ ዘመዶቹ ትግራይ ውስጥ እንዴት እንዳሉ ያልሰማ ነው።በመሆኑም ከዛሬ ነገ መንግስት ስልክ ሊቀጥልና ከቤተሰብ ጋር ልነጋገር ነው እያለ ሲጓጓ ሌላ የጦርነት አዙሪት ህወሃት ከትቶት ግራ ተጋብቷል።ህወሃት የተለመዱ ሁለት የማደናገርያ መንገዶቹን አሁንም እየደገመ ነው።ይሄውም ጥቂት አደናጋሪዎች ከተሞች ውስጥ ቀድሞ በመላክ ከተማው የተያዘ አስመስሎ አደናግሮ ህዝብ ማሰደድ እና ከኋላ መሳርያ የተደገነባቸው ጀሌዎቹን በብዛት ወደፊት መግፋት ነው።ከእዚህ በተጨማሪ በየከተሞቹ የህወሃት ጀሌ ሳይመጣ መጣ ብለው የሚያወሩትን ከወዲሁ መለየት እና ለህግ ማቅረብ ላይ ህዝቡ ሊሰራበት የሚገባ ዐበይት ተግባር ነው።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ መከላከ በሚገባ የተደራጀ እና የሚሰራውን የሚያውቅ ነው።በብዛት የተግተለተለ ጀሌ ዓይነት ውግያ የሚከተል አይደለም። በወታደራዊ ሳይንስ እንደአገር የቱ ከየት መቅደም እንዳለበት ያውቃል።ከእዚህ በፊት መቀሌን ለቆ ሲወጣ የትግራይ ህዝብ ሁኔታዎችን ይረዳል ቆይቶም የህወሃትን እኩይ ተግባር ተረድቶ በሰራዊቱ ላይ የተፈጸመውን የጥቅምት 24 ግፍ ተረድቶ ወደ ፍትሃዊ ፍርድ መጥቶ ህወሃትን ከጫንቃው ላይ ያስወግዳል በሚል ነበር።እስካሁን የታየው ጉዳይ ግን በህወሃት በግድ የመገዛትም ሆነ በውዴታ አስገዳጅ ምክንያቶች ይህ አልሆነም። ይልቁንም ለሌላ ዙር ወረራ የትግራይ ጀሌ በህወሃት መሪነት ወደ አማራ እና የአፋር ግዛቶች ጦርነት ከፍቷል።አገር ቀልባቸውን ባጡ አሸባሪዎች ዳግም የሺዎች ህይወት ሊታመስ አይችልም።በመሆኑም በቀጣይ ቀናት  የመከላከያ እና የአየር ኃይል እርምጃዎች ከመጠንከራቸው የተነሳ ማንም ማንንም ሊወቅስ የማይችልበት ደረጃ ልንደርስ እንችላለን።አገር ከሁሉ በላይ ነች።ሁሉንም ትበልጣለች። ይህ ለሰራዊቱ ከማናችንም በላይ ይገባዋል። 
===========//////=============                                                                                            

No comments:

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...