ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, March 15, 2016

ኦኬሎ ይፈታ! ኖርዌይ ኢትዮጵያውያንን በግዳጅ መመለስ ታቁም! ኢትዮጵያውያንን መግደል ይቁም! በሚል በኖርዋይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ አደረጉ።







ዛሬ መጋቢት 6/2008 ዓም በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ኢትዮጵያውያን የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊው  ኦከሎ አክዋይ ኦቻላ በወያኔ ደቡብ ሱዳን ላይ ተጠልፈው ለእስር መዳረጋቸውን፣ የኖርዌይ መንግስት በግዳጅ ኢትዮጵያውያንን ከአገሩ ለማስወጣት እና ወደ ኢትዮጵያ ለመውሰድ ማቀዱን በመቃወም እና በኦሮምያ እና ልዩ ልዩ የአገራችን ክፍሎች የተፈፀሙትን እና በመፈፀም ላይ ያሉትን ግድያዎች እና እስራቶች በመቃወም  ሰልፍ ወጥተዋል።ሰልፉ የአገሪቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ፅህፈት ቤት ከሚገኝበት እስከ ምክርቤቱ ድረስ የ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ በማድረግ የተከናወነ ሲሆን በሰልፉ ወቅት የኖርዌይ ፖሊስ በፈረሰኛ እና በመኪና በመታገዝ ጥበቃ አድርገዋል።

በሰልፉ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ የኖርዌይ ዜጎች ከደቡብ ሱዳን በግዳጅ ታግቶ የተወሰደው የቀድሞ የጋምቤላ አስተዳደር ኦኬሎ በፍጥነት እንዲፈታ የሚጠይቅ መፈክር እና ፎቶ ግራፍ ይዘው ነበር። በሰልፉ ላይ የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች፣የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ በኖርዌይ እና የኖርዌይ እና ዓለም አቀፍ ሰብአዊ እና ፀረ ዘረኝነት ድርጅቶች ተወካዮች የተገኙ እና ንግግር ያደረጉ  ሲሆን የሰልፈኛውን ጥያቄ የያዘ ደብዳቤም ለኖርዌይ ፓርላማ እንዲደርስ  መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

ከእዚህ በታች በጉዳያችን የተነሱ የሰልፉን ገፅታ የሚያሳዩ ፎቶዎች ይመልከቱ።













ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
መጋቢት 7/2008 ዓም


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...