- አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰውት የነበረው አደገኛ እልቂት ታሪክ ያወጣዋል።
- ኢንጅነር ይልቃል የተመድ ጦር ኢትዮጵያ እንዲገባ እና ኢትዮጵያ ካለመከላከያ እንድትቀር በይፋ ጥሪ ያደረጉ በኢትዮጵያውያን የምሑራን ታሪክ ኢትዮጵያን በእዚህ ደረጃ ለባዕዳን ለመስጠት ተዳፍሮ የተናገረ ''ምሑር '' ባለመኖሩ ክብረወሰኑን ሰብረዋል።
- ፕሮፌሰር መራራ ከመኢሶን እስከ ቅንጅት፣ከቅንጅት እስከ ኦፌኮ ስለ ኢትዮጵያና የኦሮሞ ህዝብ ቢያወሩም ዛሬም ለሀገራዊ ውይይት ጥሪ ሲደረግላቸው ምላሽ አልሰጡም።
- ጀዋር ናይሮቢ ተቀምጦ ከተቃዋሚዎች ጋር በመደራደር ደካማነት የኢትዮጵያ መንግስትን በአሜሪካ መንግስት አስታኮ ሊወቅስ ይሞክራል። እውን የኢትዮጵያ መንግስት ከተዋጋቸው ጋር ቁጭ ብሎ ባለመነጋገር የሚታማ መንግስት ነው? ክህወሓት ጋር ፕሪቶርያ ድረስ ተጉዞ የተፈራረመ፣ የሽኔውን ጃልመሮ በኢሊኮፍተር ታንዛንያ ድረስ እንዲሄድ ፈቅዶ ከኢታማዦር ሹም እስከ ከፍተኛ የመንግስት ሚኒስትሮች ድረስ የተነጋገር፣ በአማራ ክልል ያላችሁ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት ተመለሱ እያለ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በየስብሰባው የሚናገርባት ሀገር መንግስትን የአሜሪካ አምባሳደርን ንግግር አስታኮ መንግስት ለአሜሪካው አምባሳደር ለምን ምላሽ ሰጠ ብሎ ''ያዙኝ ልቀቁኝ '' ምን ይሉታል?
- አቶ ልደቱ፣ ተቃዋሚውን በጣም ንቀውታል።እዚህ ላይ ተሳስተዋል ማለት አይቻልም። ወደ ግራ፣ወደቀኝ፣ወደላይ እና ወደታች ሲመለከቱ ሁሉም ተቃዋሚ ነጥብ ስለሌለውና እንደ እርሳቸው የስልጣን ፍላጎት ብቻ ያሰቃየው መሆኑን ሲያዩ የራሳቸው እና ህወሓት በጀርባ የምትዘውረው የተቃዋሚ ቅብ በእንወያይ ሰበብ በባሕር ማዶ ማደራጀት አምሯቸዋል። ከምንም ንክኪ የጸዳ ግን ውይይት ላይ ያተኮረ ስራ ቢሆን ባልከፋ። የአቶ ልደቱ ያለፈ ታሪክ ግን ይህንን አያሳይም።አቶ ልደቱ አንዴ ተቃዋሚ ጎራ፣ቀጥለው የኢህአዴግ ለዘብተኛ፣ቀጥለው ከጀዋር እና ኦኤም ጋር ''እፍ'' ያለ ፍቅር ወድቀው ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም በሚል ዘመቻ ለህወሓት መንገድ ጠራጊ ፖለቲካ ሲያራምዱ አይተናቸዋል።
ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
Friday, May 17, 2024
ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።
Saturday, April 20, 2024
ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።
- ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል
- ''ስኩዌር ዋን'' ህወሓት ወደ ቀደመ ፕሮፓጋንዳውና የጦርነት ገንዘብ ማሰባሰቡ ተመልሷል።
- ህወሓት ለአራተኛ ጊዜ ''አደገኛ ወጥ እረግጧል''
የህወሓትን ወረራ አስመልክቶ የውጭ ሚድያዎች በለሆሳስ እየተናገሩ ነው።በለሆሳስ ያልኩበት ምክንያት የህወሓት ውል ጥሶ ብቻ ሳይሆን ከአንድሚልዮን ህዝብ እልቂት በኋላም መልሶ ለስልጣኑ ወደ ጦርነት አረንቋ ለመግባት የሚያደርገውን መላላጥ ለመውቀስ ሲሽኮረመሙ ብቻ ሳይሆን በሚገባ እና በሚወቅስ መልክ የጻፈ አላጋጠመኝም። ይህ የደንባራው እና የራሱን ጥቅም ብቻ ከሚያነፈንፈው የባዕዳን የሚድያ ፖሊሲ የሚመነጭ ምግባር የለሽ የአለቆቻቸውን አስተያየት እና አቅጣጫ ከመጠበቅ የመጣ እንጂ የህወሓት ድርጊት እጅግ ግዙፍ እና ሌላ ወንጀል በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመበት ተግባር መሆኑ ጠፍቷቸው አይደለም።
ባትሰባ ሰይፉ የኒውዮርክ ዩንቨርስቲ የሕዝብ አስተዳደር ማስተርስ ተመራቂ ነች። ዛሬ ''ሞደርን ዲፕሎማሲ ዶት ኢዩ''ላይ የፕሪቶርያ ውል መክሸፍን በገለጸችበት ጽሑፍ ጉዳዩ የሕገመንግስታዊ ቀውስ መሆኑን፣ትግራይ በቂ እርዳታ በመንግስት ቢሮክራሲ አለማግኘቷንና ሌላው ቀርቶ በህወሓት በራሱ የተዘረፈውን የዕርዳታ እህል ህወሓትን ለመውቀስ ወደ ሌላ በመቀሰር ለማብራራት ሞክራለች። ባትሰባ ሰይፉ በእዚሁ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በጻፈችው እና ''The Fractured Reality After the Pretoria Peace Agreement'' የሚል ርዕስ የሰጠችው ጽሑፍ ውስጥ የፕሪቶርያው ውል ሦስት ምሰሶዎች እንደነበሩት ታብራራለች። እነርሱም ፡ የሰብዓዊ ርዳታ ተደራሽነት፣ሕገመንግስታዊ ስርዓት ማስከበር እና ሰብዓዊ መብት የሚሉ ሲሆኑ የህገመንግስታዊ ስርዓትን እንደ እርሷ አገላለጽ ''የአማራ ክልል ኃይሎች እና የኤርትራ ወረራ'' የፕሪቶርያን ውል ዋጋ እንዳሳጣው ለማሳየት በእዚሁ ጽሑፏ የውጪውን ዓለም ለማታለል ተጠቅማበታለች። በእዚህ ሁሉ ገለጻ ውስጥ ግን ህወሓት ሰሜን ወሎን ውርሮ በአስር ሺዎች ማፈናቀሉን፣ ትጥቅ እፈታለሁ ብሎ ዛሬም ክላሽ እየወዘወዙ የአማራ ክልልን የሚወሩ በሺህ የሚቆጠሩ ታጣቂዎች ለፕሪቶርያ ውል መፍረስ ምክንያት እንደሆነ ማብራራ አልሞከረችም።
በመጨረሻው መጨረሻ ግን ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።ህወሓት ትጥቅ መፍታት አለበት። ይህ የፕሪቶርያው ውል አካል ካልሆነ ይነገርን።አልያም የፕሪቶርያውን ውል ህወሓት እንዳፈረሰ የመንግስት የፖለቲካውም ሆነ የወታደራዊው አመራር በግልጽ ይንገረን።
Tuesday, April 9, 2024
Saturday, March 16, 2024
ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)
Monday, February 19, 2024
የኢትዮጵያ ድንቅ መስተንግዶ ዳግም የተመሰከረበት የአፍሪካ ኅብረት 37ኛ የመሪዎች ጉብዔ ዛሬ ሰኞ ተጠናቀቀ።ኢትዮጵያን የሚመጥነው የኢትዮጵያ መስተንግዶ በቪድዮ።
- መሪዎቹ የተወያዩባቸው አራቱ አጀንዳዎች ምን ነበሩ? (አጀንዳዎቹ በአጭሩ ተዘርዝረዋል)
- እድሳቱ በቅርቡ የተጠናቀቀው ብሔራዊ ቤተመንግስት የተደረገው የራት ግብዣ የእንግዶች አቀባባል (ቪድዮ ይመልከቱ)
- የአዲስ አበባ ከተማ ቸርችል ጎዳና የሰሞኑ የምሽት ገጽታ እንደወረደ (ቪድዮ ይመልከቱ)
የአፍሪካ ኅብረት 37ኛ የመሪዎች ጉባዔ አራቱ አጀንዳዎች፡
1. የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት የዘንድሮ የፈረንጆች ዓመት የትምህርት ዘመን ተብሎ መሰየሙን ተከትሎ የኅብረቱ ጉባኤ በአህጉሪቱ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል። የመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፤ በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በታች በሚገኘው የአህጉሪቱ ቀጣና በዓለም የትምህርት ተደራሽነት ካልተረጋገጠበት አከባቢ ቀዳሚ ነው። ለአብነትም አጠቃላይ በአህጉሪቱ ከሚገኙ እድሜያቸው ከ15 እስከ 17 የመሆኑ ታዳጊ ወጣቶች 60 በመቶ የሚሆኑት ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው። ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ታዳጊዎች ቁጥርም አጅግ ከፍተኛ ነው። ብቂ መምህራን የማሰማራት እንዲሁም አህጉሪቱን ለመለወጥ የሚያስችሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ የተግባር ትምህርቶች ተደራሽነትም ከሚፈለገው በታቸ ነው።
2. አህጉራዊ ምጣኔ ኃብታዊ ትስስር የአፍሪካን ከውጭ የፋይናንስ ጥገኝነት ለማላቀቅና ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊና ምጣኔ ኃብታው ችግሮችን ለመቅረፍ የውስጥ አቅምን አሟጦ መጠቀም በተመለከተ ውይይት ተደርጓል። በዚህ ረገድ በተለይም ትልቅ ግምት የተሰጠው አሁን በሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኘው አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የእስካሁኑ ሂደትና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ምክክር ተደርጓል። ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በአህጉሪቱ 30 ሚለየን ሰዎችን ከድኅነት የማውጣት እንዲሁም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር በ2035 በአፍሪካ ገቢን በ7 በመቶ እንደሚጨምር ተስፋ የተጣለበት ይኸው የንግድ ቀጣና በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ አገራት ከታሪፍና ከሌሎች የንግድ ሂደት ጋር ያሉ ውስብስብ አሰራሮችን እንዲያስወግዱ አቅጣጫ ላይ መክሯል።
3. አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሥፍራ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ተቋማት ያላትን ውክልና ተገቢውን ሥፍራ እንድትይዝ በተለይም በመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ያላትን ውክልና በተመለከተ ለበርካታ ዓመታት ስትጠይቅ ቆይታለች። ይህንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትም የአፍሪካን ፍላጎት ያገናዘበ ቁመና ሊኖረው ይገባል የሚለውም አጀንዳ የዘንድሮው ጉባኤ አጀንዳ ነበር ። አፍሪካ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን መድረኮች ጋር በተለይም አሁን አፍሪካ የቡድን 20 አገራት አባል መሆኗን ተከትሎ እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪነቱ እየገነነ ከመጣው ከብሪክስ ጋር ባላትና ሊኖራት በሚችለው ግንኙነት ዙሪያም ምክክር ተደርጎበታል። በተለይም አፍሪካ እንደ ተጨማሪ የቡድን 20 አባልነቷ፤ ምን ይዛ ልትሄድና ልታመጣ ትችላለች እንዲሁም አባልነቷን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለበርካታ ዓመታት ተፈልጎ የታጣውን ውክልና ለመካስ ወይም የአህጉሪቱን ድምጽ ይበልጥ ለማሰማት በሚቻልባቸው ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።
4. የሠላምና ደኅንነት ተግዳሮቶችና መፍትሄያቸው የመሪዎቹ ጉባኤ ዘንድሮም በአፍሪካ የጸጥታ ችግሮች ዙርያ ምክክር አድርጓል። አህጉሪቱን ከድኅረ -ነጻነት በኋላ በእጅጉ እየፈተኑ ከሚገኙ ከነገረ ፖለቲካዊ ጉዳዮች መካከል ቀዳሚውን ሥፍራየሚይዘው የጸጥታ መደፍረስ ነው። ሽብርተኝነት፣ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ የሥልጣን መቆናጠጥ፣ ግጭቶችና ከምርጫ ጋር የተያያዙ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ሌሎች መሰል ቸግሮች አሁንም ለአፍሪካ ፈተና ሆነው ቀጥለዋል። እነዚህ የፖለቲካ ቀውሶች አህጉሪቱ በየትኛውም ማኅበራዊና ምጣኔ ኃብታዊ መስክ ወደፊት ፈቅ እንዳትል ካደረጓት ምክንያቶ ዋነኛው መሆኑን ነው የተለያዩ ጥናቶች የሚያሳዩት። እነዚህን ግጭቶች ባሉበት ለማቆምና ሌሎችም በቀጣይ እንዳይከሰቱ በተለይም የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል (ውይይት) ብቸኛ አማራጭ ለማድረግ ኅብረቱ ከዚህ ቀደም የጀመራቸውን ሥራዎችና ሌሎች ተግባራትን ለማጠናከር በሚያስቸሉ ጉዳዮች ላይ መሪዎቹ ውይይት አድርገዋል፣የመፍትሄ አቅጣጫዎችም ስብሰባው አስቀምጧል።
እድሳቱ በቅርቡ የተጠናቀቀው ብሔራዊ ቤተመንግስት የተደረገው የራት ግብዣ የእንግዶች አቀባባል (ቪድዮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ቸርችል ጎዳና የሰሞኑ የምሽት ገጽታ እንደወረደ (ቪድዮ)
ለጽሑፉና ቪድዮዎች ምንጮች ፡
- ENA
- FBC
- J.Walking Tour
Tuesday, January 23, 2024
ኢጃት ማን ነው? እንዴት ተመሰረተ? (ቪድዮ)
- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምሕርትቤቶች ማደራጃ መምርያ ስር መዝግባ ዕውቅና ሰጥታዋለች።
- ከክፍሎቹ ውስጥ ሦስቱ ፡የመዝሙር ክፍሉ ጃን ያሬድ ሰሞኑን የአዕላፋት ዝማሬን ያቀረበው ሲሆን ሁለተኛው ጃን አጋፋሪ የዝግጅቶች አስተባብሪ ነው።ሦስተኛው ጃን ምኩራብ የሚድያ ክፍል ነው።
- ኢጃት ሐያሁለት ፕሮጀክቶች ይዞ እየሰራ ነው።
- ዋና ዓላማው በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገለገልና የሚያገለግል ትውልድ ማፍራት ዓላማው የሆነውን የኢጃትን መልካም ሥራውን ለማጣጣል '' የክርስቶስ የሆኑትን ሊሳደብ አውሬው አፉን ከፈተ'' ተብሎ በመጽሐፍ ላይ እንደተጻፈ በባሕር ማዶ ሆኖ በኢጃት ውጥን ስራዎች ላይ ሊሳለቅ የሞከረውን ከሰሞኑ ታዝበናል።በጎ ሥራ የሚሰራ ትውልድን ሁልጊዜ እናበረታታ!
Thursday, January 11, 2024
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲን እጅግ ዘመናዊ በሆነ አቀራረብ የተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ ዛሬ አዲስ አበባ በሳይንስ ሙዝየም ተከፍቷል (ቪድዮውን ይመልከቱ)
- ዐውደ ርዕዩ ከንግስት ሳባ ጀምሮ ያለውን የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት ያሳያል።
- ኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያቤትን ስራ ካስጀመረች 116 ዓመታት እንደሆናት ዐውደ ርዕዩ ያሳያል።
- በዛሬው መክፈቻ ስነስርዓት ላይ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገሮች አምባሳደሮች ጨምሮ፣ከተልያየ ዓለም የመጡ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።
- ዐውደ ርዕዩ ከሁለት ሳምንታት በላይ ክፍት ሆኖ ይቆያል።በቀጣይ ቀናት በአዲስ አበባ ነዋሪ እና የዓለም ዓቀፍ ኮሚኒቲ ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል።
- በቅርቡ በአዲስ አበባ እንደሚደረግ የሚጠበቀው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ ላይ የሚገኙ የሀገራት መሪዎች፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ዓለም ዓቀፍ ጋዜጠኞች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል።
የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።
======== ልዩ ሪፖርታዥ ======== በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡ የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል? ግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል...
-
በቀሲስ መንግሥቱ ጐበዜ ሉንድ ዩንቨርሲቲ ፣ ስዊድን (ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አርኪኦሎጂ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና በሉንድ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት...
-
The Ethiopian herald News Paper August 20 , 2020 BY STAFF REPORTER Addis Ababa ************************** (EPA) ADDIS ABABA - Over sixty-mil...
-
አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን =============== ጉዳያችን /Gudayachn =============== ብሉምበርግ የተሰኘው የአሜሪካ ድረገፅ በፖለቲካ እና ፖሊሲ አምድ ስር የአድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን አሜሪካ ኢትዮጵ...