ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, May 17, 2024

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው።

  • አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰውት የነበረው አደገኛ እልቂት ታሪክ ያወጣዋል።

  • ኢንጅነር ይልቃል የተመድ ጦር ኢትዮጵያ እንዲገባ እና ኢትዮጵያ ካለመከላከያ እንድትቀር በይፋ ጥሪ ያደረጉ በኢትዮጵያውያን የምሑራን ታሪክ ኢትዮጵያን በእዚህ ደረጃ ለባዕዳን ለመስጠት ተዳፍሮ የተናገረ ''ምሑር '' ባለመኖሩ ክብረወሰኑን ሰብረዋል።

  • ፕሮፌሰር መራራ ከመኢሶን እስከ ቅንጅት፣ከቅንጅት እስከ ኦፌኮ ስለ ኢትዮጵያና የኦሮሞ ህዝብ ቢያወሩም ዛሬም ለሀገራዊ ውይይት ጥሪ ሲደረግላቸው ምላሽ አልሰጡም። 

  • ጀዋር ናይሮቢ ተቀምጦ ከተቃዋሚዎች ጋር በመደራደር ደካማነት የኢትዮጵያ መንግስትን በአሜሪካ መንግስት አስታኮ ሊወቅስ ይሞክራል። እውን የኢትዮጵያ መንግስት ከተዋጋቸው ጋር ቁጭ ብሎ ባለመነጋገር የሚታማ መንግስት ነው? ክህወሓት ጋር ፕሪቶርያ ድረስ ተጉዞ የተፈራረመ፣ የሽኔውን ጃልመሮ በኢሊኮፍተር ታንዛንያ ድረስ እንዲሄድ ፈቅዶ ከኢታማዦር ሹም እስከ ከፍተኛ የመንግስት ሚኒስትሮች ድረስ የተነጋገር፣ በአማራ ክልል ያላችሁ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት ተመለሱ እያለ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በየስብሰባው የሚናገርባት ሀገር መንግስትን የአሜሪካ አምባሳደርን ንግግር አስታኮ መንግስት ለአሜሪካው አምባሳደር ለምን ምላሽ ሰጠ ብሎ ''ያዙኝ ልቀቁኝ '' ምን ይሉታል?

  • አቶ ልደቱ፣ ተቃዋሚውን በጣም ንቀውታል።እዚህ ላይ ተሳስተዋል ማለት አይቻልም። ወደ ግራ፣ወደቀኝ፣ወደላይ እና ወደታች ሲመለከቱ ሁሉም ተቃዋሚ ነጥብ ስለሌለውና እንደ እርሳቸው የስልጣን ፍላጎት ብቻ ያሰቃየው መሆኑን ሲያዩ የራሳቸው እና ህወሓት በጀርባ የምትዘውረው የተቃዋሚ ቅብ በእንወያይ ሰበብ በባሕር ማዶ ማደራጀት አምሯቸዋል። ከምንም ንክኪ የጸዳ ግን ውይይት ላይ ያተኮረ ስራ ቢሆን ባልከፋ። የአቶ ልደቱ ያለፈ ታሪክ ግን ይህንን አያሳይም።አቶ ልደቱ አንዴ ተቃዋሚ ጎራ፣ቀጥለው የኢህአዴግ ለዘብተኛ፣ቀጥለው ከጀዋር እና ኦኤም ጋር ''እፍ'' ያለ ፍቅር ወድቀው ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም በሚል ዘመቻ ለህወሓት መንገድ ጠራጊ ፖለቲካ ሲያራምዱ አይተናቸዋል።
አራታችሁም ከቻላችሁ በምርጫ ኑ! ከእዚህ ውጪ ስልጣን የማትበላ ወፍ እንደሆነችባችሁ ገና ብዙ መስከረሞች ያልፋሉ።የኢትዮጵያ ህዝብ የጎሳ ፖለቲካን እንደማይሸከም በተግባር ስላሳየ፣ ጀዋር ሳይቀር ''የብሔር ፖለቲካ የግድ አስፈላጊ ነው ማለት አይደለም '' የሚል ማባበያ እና በአራዳ ልጆች አነጋገር ''የመሸቀያ'' ቃላት ከሰሞኑ ሲያሰማ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለሚረዳ አፍንጫው ምን እንደሚሸተው ማውቅ ቀላል ነው። ትንሽ የኢትዮጵያዊነት ቆሎ እያሳያችሁ ወደ አሻሮው ለመጠጋት ነው።ኢትዮጵያ ለስልጣን መሸቀጫ ለሚቀርቧት ሁሉ ዛሬም  የማትበላ ወፍ ነች! 

ማንም ምንም ቢል ኢትዮጵያ በቁርጥ ቀን ልጆቿ ማዕበሉን በትክክል ቀዝፋ እያለፈችው ነው። 

የማትበላ ወፍ







No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...