Tuesday, April 4, 2017

የኢትዮጵያ ጉዳይ እጅግ አደገኛ የሚባል ደረጃ ደርሷል።የኢትዮጵያ ሰራዊት፣ ኢትዮጵያዊነት የሚሰማችሁ የስርዓቱ አካላት፣የተቃዋሚ ኃይሎች እና መላ ህዝብ ኢትዮጵያ መንግስት እንዲኖራት በቶሎ መነሳት ይጠበቅባቸዋል።ምን ይደረግ? ባለ ሰባት ነጥብ ሃሳቦች ቀርበዋል።(የጉዳያችን ወቅታዊ ሃሳብ)



ጉዳያችን /Gudayachn 
መጋቢት 27፣2009 ዓም (April 5,2017)

መግቢያ 

አሁን በስልጣን ላይ ያለው የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ጎማ ከእዚህ በላይ ኢትዮጵያን ሊያሽከረክር አይችልም።ኢትዮጵያ ካለ አንዳች ለውጥ አንዲት ቀን መቆየት የማትችልበት ደረጃ ላይ ነች።በሀገር ውስጥ እና ዙርያዋን እየሆነ ያለው ሁሉ መንግስት የሌላት ሀገር የሚል ስም የሚያሰጥ፣ስርዓት አልበኝነት ከምንገምተው በላይ የሚሄድበት ትልቅ ዕድል አለ።ሕወሓት/ኢህአዴግ ኢትዮጵያን የመምራት አቅም አይደለም እራሱን ብቻ ተሸክሞ መራመድ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።እራሱን መሸከም አለመቻል ብቻ ሳይሆን እርስ በርሱ በገባው ቅራኔ መንገዱ ሁሉ ታጥሮበታል።የውስጥ ቅራኔው መስፋት ቀድሞ ከነበረው ደካማ አቅም በባሰ እጅግ ደካማ በሆነ የሰው ኃይል ከወዲያ ወዲህ ያለ አንዳች ሥራ እየተንገላወደ ነው።

ይህ ከአቅም በታች የሆነ የሰው ኃይል ከዋናው የህወሓት አስኳል ጋር በመሆን ኢትዮጵያን በአራቱም ማዕዘን ዘረፋውን አጧጡፈውታል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የልማት ባንክ በቢልዮን የሚቆጠር  ገንዘብ ዕዳ ውስጥ ገብቷል።ስርዓት አልበኞቹ ባለስልጣናት ከአቶ ሃይለማርያም ጀምሮ ኢትዮጵያን የግል ንብረታቸው አድርገው የመንግስት ስራን  ከሚገመተው በላይ አቡክተውታል።በአባይ ወልዱ የሚመራው የትግራይ ክልል (በእራሱ ለማዕከላዊ መንግስት ባለፉት አመታት ሲያደረገው እንደነበረው ሁሉ) የእራሱ የዘመነ መሳፍንት ዓለም ፈጥሮ በእያንዳንዱ የኢትዮጵያዊ መንግስታዊ እና የግል ድርጅቶች የውስጥ ጉዳይ ሁሉ  እየገባ እያመሰ እና እየዘረፈ ነው። የስርዓቱ አስተዳደር መዋቅር ተበጣጥሶ ሁሉም የእራሱን ሕግ በሚገዛው ቀበሌ ውስጥ ገዢ ሆኗል።የአዲስ አበባ አስተዳደርን ብቻ ብንወስድ እታች ቀበሌ ያለውን ሥራ የመምራትም ሆነ የመቆጣጠር አቅሙ ወርዶ ሰዎች ከሰሜን በመጣ እና ባልመጣ አነጋገር እየተለየ  ያልነበረሕግ የሚሰራበት ደረጃ  ላይ ተደርሷል።

ኢትዮጵያ እየፈረሰች ነው ክልሎች በባእዳን እጅ የመግባት መጥፎ ዕድል አላቸው 

የሱማሌ ክልል ከአዲስ አበባ ጋር ከሚያደርገው ግንኙነት ይልቅ ከሞቃዲሾ የሚመጡ ኮብራ መኪናዎች ይቀርቡታል።ክልሉ የኢትዮጵያን የቁም ከብት እና ጫት እንዲሁም ፍራፍሬ እየሸጠ በምትኩ የጦር መሳርያ እየሸመተ ነው።ይህ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያን ድንበር ከፓኪስታን እና ከአፍጋኒስታን የመጡ አሸባሪዎች ሳይቀሩ እንደፈለጉ የሚገቡበት እና የሚወጡበት የውሃ መንገድ አስደርጎታል።አቶ ሃይለማርያም ኢትዮጵያን የመምራት አይደለም ፒያሳ ስላለው ጉዳይ አያውቁም።ከጀርባ እየመራ ነው የሚባለው የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ እርስ በርሱ ለመመታታት ሰዓታትን እየጠበቀ ነው።አቦይ ስብሐት እራሳቸው ግራ ተጋብተው ደጋግመው የሚወዱትን ሬድ ሌበል ውስኪ ከመጎንጨት በቀር የሚሰሩት ግራ ገብቷቸዋል። 

ከጎንደር እና ጎጃም በእየሰዓቱ  የሚመጣው ዜና የኢህአዴግ/ህወሓት ወታደር የሆነ ሁሉ ጥቃት እየተፈፀመበት እንደሆነ ነው።ሰራዊቱ እራሱ ጎንደር ላይ ለመዝመት አንዳች ፍላጎት የለውም።ምክንያቱም ዘመቻው እራሱ ምክንያታዊ ሳይሆን በሕወሓት እብሪት የተፈጠረ እሳት መሆኑን ሰራዊቱ ይስማማበታል።ይህ ሁሉ ጉዳይ ያስጨነቀው ሕወሓት የሱዳኑን ፕሬዝዳንት ዛሬ አዲስ አበባ ድረስ ጠርቶ ማናገር ይዟል።የሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሽር እራሳቸው አዲስ አበባን ሲረግጡ ከእዚህ በፊት ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ሲመጡ የሚያውቁት ሀገር አልሆነባቸውም።አሁን ለውጥ ለውጥ የሚል ሽታ እና የስርዓቱ ባለስልጣናት አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ የተደናገጠ ፊት ብቻ ነው የተመለከቱት።ጉብኝታቸው ሁሉ የውሸት ስለሆነባቸው የሚያደርጉት ውል ሁሉ የማይረጋ መሆኑን ስሜታቸው እንደነግራቸው ከፊታቸው ይነበባል። 

የኢትዮጵያ ዙርያ ያሉ መሬቶች በአረብ ሀገር ወታደሮች እየተከበቡ ነው።ከሱማሌ እስከ አሰብ ድረስ ጂቡቲን ጨምሮ ከእዚህ በፊት ሰራዊታቸውን ከሀገራቸው ውጭ አስፍረው የማያውቁ የአረብ ሀገሮች በሙሉ የኢትዮጵያን በሕወሓት ደካማ እና በዘር ላይ የተመለከተ መንግስት እጅ መውደቅ ተመልክተው  ዙርያችን ሰፍረዋል።የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ጉዳይ ተሞክሮ እዚህ ግባ የማይባል ልምድ በሌላቸው ግለሰብ እጅ በመውደቁ ሚንስትሩ  ዛሬ ለምክር ቤት ያለፈ የስድስት ወር ሪፖርት ሲያቀርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደረጃ መነገር የማይገባቸው ቃላት ሲጠቀሙ መመልከት የብስለት ብቻ ሳይሆን  የዓለም አቀፍ እውቀት እና ልምድ ማነስ ምን ያህል ኢትዮጵያን አፈር ድሜ እንዳስገባ ለመረዳት ቀላል ነው።

የህዝቡ የጉስቁልና ደረጃ በቀላሉ በማንኛውም የውጭ ኃይል የመማረክ መጥፎ እጣ ያሰጋዋል።

የምጣኔ ሃብቱ ድቀት የድሀውን እና የደሞዝተኛውን የመግዛት አቅም ከተጠበቀው በታች አውርዶታል።በመምህራን ደረጃ የመኖር እና አለመኖር ግብግብ ውስጥ ስለገቡ ሰልቫጅ ልብስ መንገድ ላይ በመሸጥ ከማስተማር ሙያቸው በተጨማሪ  የሚሰሩ መምህራን አዲስ አበባ ላይ መኖራቸው የእዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ ሰምቷል። በእዚህ ወር የዋጋ ግሽበቱ መጨመሩን ሮይተርስ በለቀው ዘገባ አረጋግጧል።የዓለም ባንክ ከውሃ እና ፍሳሽ ጋር በተያያዘ በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር ብድር መፍቀዱ ትናንት ቢሰማም ብድሩን ለማግኘት በእራሱ ብዙ ደረጃዎች አሉት።ስለሆነም ለአሁኑ የህወሓት የውጭ ምንዛሪ ጥማት ሊደርስለት አይችልም።የዓለም ባንክ ይህንን የሚያደርገው የቻይና እጅ በበለጠ እንዳይረዝም ከማሰብ ውጭ የብድር መመለስ አስተማማኝ ዋስትና ኖሮት አይደለም። 

እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች ኢትዮጵያን በደርግ ዘመን ከነበረችበት ደረጃ እና አሁን በሕወሓት ዘመንም  ካለንበት አስከፊ ደረጃ በባሰ ሁኔታ ሀገሪቱን ይዞ የሚወርድ አደገኛ ደረጃ ነው።ስለሆነም ምን መደረግ አለበት? ሙስናው የኢትዮጵያን ሀብት እየዘረፈ፣ባእዳን ጥርሳቸውን እያሳዩን ሀገራችንን ሲያጠፉ እንመልከት? ወይንስ ኢትዮጵያን ለማዳን የሚጠበቅብንን  ለመስራት በቁርጠኝነት እንነሳ? ደግሞስ ማን ምን ይስራ? 

ኢትዮጵያን ለማዳን አሁን  ምን ያድርግ?

የኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ምጣኔያዊ ሀብት እና ማኅበራዊ ሁኔታ ላለፉት 26 አመታት በኢህአዴግ/ሕወሓት እጅጉን ቆስሏል።ይህ ቁስል ለመጠገግ ቢያንስ ሁለት ዓመታት ይፈልጋል።ይህንን ታሳቢ በማድረግ ከሕወሓት መውደቅ በኃላ ወድያው ጤናማ ምርጫ ይደረጋል ብሎ ማሰብ በእራሱ ሞኝነት ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያን ለማዳን ደረጃ በደረጃ ምን ይደረግ?

1ኛ/ ከኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት፣ከኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ከስርዓቱ ጋር ያልተነካኩ እና የቆሸሸ ስም የሌለባቸው የሃይማኖት ተወካዮች፣ምሁራን፣ከበሬታ ከህዝብ ያገኙ ዜጎች ያቀፈ ጊዚያዊ የኢትዮጵያ መንግስት በቶሎ አዲስ አበባ ላይ መመስረት አለበት።ይህ ጊዜያዊ መንግስት ለሁለት አመታት የሚቆይ (ዓመቱ ግምት ነው። ሊያንስ ይችላል) መሪ የዜጎች የጋራ መርህ ያወጣል።

ይህ እንዴት ይችላል? ሕወሓት ስልጣን ይለቃል ወይ? ብለን ልንጠይቅ እንችላለን።ሆኖም ግን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ የተረዱ የሰራዊቱ አባላት እና የህዝብ ንቅናቄ ሁሉ ሕወሃትን ማስገደድ አለባቸው።ይህ እንደሚሆን እራሳቸው ህወሐቶችም በሚገባ ያውቁታል።በማንኛውም ደረጃ የሚነሳ የስልጣን ነጠቃ እንደሚኖር ያውቃሉ።አሁን የቀረው መረረኝ ብሎ የቆረጠ የሰራዊቱ አባል እና ሕዝብ እራሱን ባጭር ጊዜ አደራጅቶ የመነሳቱ ጉዳይ ብቻ ነው።

2ኛ/ ይህ ጊዜያዊ የኢትዮጵያ መንግስት በቅድምያ የኢትዮጵያን ሰራዊት ከሁሉም የሀገሪቱ ግጭቶች ገለልተኛ የሆነ የሁሉ ጠባቂ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ስራዎችን ይሰራል።ምክንያቱም ግዝያዊ መንግስት ሲመሰረት በአንዳንድ ክልሎች አንዳንድ ግጭቶች ዕለቱን አይቆሙም።ለምሳሌ በሰሜን ጎንደር እና ትግራይ፣በኦሮሞ እና ሱማሌ መካከል ያሉት ግጭቶች እና መስል ግጭቶች ሕወሓት ወለድ እና ቀደም ብሎ የነበረ ታሪካዊ ሂደት ስላላቸው ሰራዊቱ የሁሉንም ችግር የሚያዳምጥ እና የሚጠብቅ በቅድምያ ግን የኢትዮጵያን አንድነት እና ድንበር ጥበቃ አስተማማኝነት ላይ ያተኩራል።

3ኛ/ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ስር ሆነው ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን ይመሰርታሉ።ለምሳሌ የሀኪሞች ባለሙያዎች፣የግብርና ሙያ ባለሙያዎች ወዘተ በእየሀገሩ ይደራጃሉ ወይንም የነበረ አደረጃጀታቸውን ያስመዘግባሉ። ሁሉም አደረጃጀቶች ጊዜያዊ የኢትዮጵያ መንግስት በሚያወጣው የዜጎች የጋራ መርህ ይመራሉ።

4ኛ/ ጊዚያዊ የኢትዮጵያ መንግስት ዋናው መንግስት መጣም አልመጣም ነፃ ከመሆን የሚያግዳቸው የማይኖረው የፍትህ አካላት እና የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ለሁሉም የቆመ መሆኑ ላይ አበክሮ ይሰራል።ነፃ የምርጫ ቦርድ የመመስረት፣ የፕሬስ ሕጉ ለሁሉም የሚሰራ መሆኑ ላይ እና የህዝቡ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሕይወት በሽግግር ጊዜው ወቅት እንዳይታወክ አበክሮ ይሰራል።ይህ ማለት በከፍተኛ ደረጃ እርስ በርስ መቃቃር ያቆሰለውን ሕዝብ በበጎ የእርስ በርስ ግንኙነቶች እንዲዳብር በሁሉም መስክ ይሰራል።

5ኛ/ ዚያዊ የኢትዮጵያ መንግስ ነፃ ምርጫ (እንደ እዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ) እንዲደረግ የምርጫ ቦርዱ በነፃ እንዲያስደርግ  ሙሉ እገዛ ያደርጋል። የፕሬዝዳንት ምርጫ እንደ ኢትዮጵያ ትልልቅ ብሔሮች ላሉባት እና ሌሎች በርካታ ውሁዳንም ለሚኖሩባት ሀገር  ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት፣ልምድ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ  አቅም ያለው ፕሬዝዳንት ከየትኛውም ብሔር ቢመጣ እና በዙር ለሌላውም ሲደርሰው ላለፉት 26 አመታት የተዘራውን መርዝ ያረክሰዋል።

6ኛ/ የኢትዮጵያ ዋናው ምክር ቤት በነፃ ምርጫ ይመሰረታል፣የኢትዮጵያ መጪ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ፣ የውጭ ፖሊሲ እና የአጠቃላይ የልማት አቅጣጫ ይቀየሳል።በመካከለኛው ምስራቅ፣አፍሪካ እና ሌሎች አለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የሚገቡበት አግባብ ይቀየሳል፣በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ቅራኔዎች እንዳይኖሩ የይቅርታ እና የኢትዮጵያዊነት ቀን ይታወጃል። በሀገር ላይ ከፍተኛ በደል የፈፀሙ ግልፅ በሆነ መንገድ ለፍርድ እንዲቀርቡ ያደርጋል።

7ኛ/ የኢትዮጵያውያን የጋራ ተቋማት ግንባታ ላይ ያተኮሩ ስራዎች፣የስራ ዕድል ፈጠራዎች፣የስነ-ጥበብ እና ኪነ-ጥበብ እድገት ላይ ያተኮሩ ስራዎች እና ኢትዮጵያን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚችሉ ስራዎች ወደ ተግባር ይቀየራሉ።

ከላይ የተጠቀሱት ስራዎች የሕልም ወሬ ያህል የምንገምተው እንኖራለን።ሆኖም ግን አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ጠቃሚው እና እንደ ሀገር የመቀጠል እድላችንን የሚያጎላ ነው።የግድ ካልሆነ ከእንጦጦ ጀምሮ እስከ አራት ኪሎ ድረስ መንገዱ በመድፍ እየታረሰ መገባት ላይኖርበት ይችላል።በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ሕዝብ፣ሰራዊቱ እና ተቃዋሚዎች ልብ ለልብ መገናኘት በቂ ነው።ከእዚህ ሲዘል ደግሞ የስርዓቱ አቀንቃኞች ይህ ለመቸውም ቢሆን ከስህተቱ የማይታረም ስርዓት ለማስወገድ እና ለልጆቻቸው የሚተርፍ የደስታ ዘመን ለማስተላለፍ ቁርጠኝነት የተላበሰ ውሳኔ ብቻ ነው የሚፈልገው።ውሳኔ ሕልምን እውን ያደርጋል።ኢትዮጵያን ለማዳን እንወስን ወስኑ !


ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Monday, April 3, 2017

የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ ዛሬ ከትራምፕ ጋር በአካል ተገናኙ።አልሲሲ ትራምፕን "ልዩ ስብዕና የተላበሱ ሰው" በማለት አሞካሽተዋቸዋል።

ጉዳያችን ዜና /Gudayachn News
መጋቢት 25፣2009 ዓም (March 3,2017)

የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ ከአሜሪካው አቻቸው ጋር በዋይት ሃውስ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 25፣2009 ዓም ተገናኝተዋል።በቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ሞቅ ያለ አቀባበል የጠበቃቸው የግብፁ ፕሬዝዳንት ፕሬዝዳንት ትራምፕን አግራሞት እና አድናቆት በተላበሰ እይታ ተመልክተዋቸዋል።በአፀፋውም ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአክብሮት ሰላምታ መለሱ።አልሲሲ ከአረብ ሀገሮች የመጀመርያው ለትራምፕ ስልክ ደውለው ደስታቸውን የገለጡ ሲሆኑ ትራምፕም መጀመርያ መልሰው ከደወሉላቸው የዓለም መሪዎች የግብፁ ፕሬዝዳንት ቀዳሚ ነበር።

´´ያንን ነገር አብረን እናደርገዋለን! ሽብርተኝነትን እና ሌሎች ነገሮችን አብረን እንዋጋለን"  ("we will do that thing together. We will fight terrorism and other things together")  አሏቸው ትራምፕ የግብፁ አቻቸውን  አተኩረው እየተመለከቱ። ትራምፕ "ያንን ነገር" ያሉት ፀረ ሽብር ዘመቻውን እንደሆነ ተገምቷል። "ሌሎቹ ነገሮች" ያሏቸው የትኞቹን ነገሮች እንደሆነ አላብራሩም።አልሲሲ በሃሳቡ ከተስማሙ በኃላ ትራምፕን "ልዩ ስብዕና የተላበሱ ሰው" በማለት አሞካሿቸው። ትራምፕ ፈገግ አሉ።ዓለም በሙሉ ትራምፕ የሚለውን ስም በሚወቅስበት ሰዓት ከግብፁ አቻቸው ይህንን ሙገሳ ማግኘት እልም ባለ በረሃ ላይ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ የማግኘት ያህል ውድ ነበር ለትራምፕ። ትራምፕ ቀጠሉ "ለእረጅም ጊዜ ወዳጅ እንደሆንን እንቆያለን" "We will become friends for a long time," አሏቸው።አልሲሲ በፈገግታ መለሱላቸው።

የግብፅ ፕሬዝዳንት ዋይት ሃውስን ለመጨረሻ ጊዜ የጎበኘው እ.ኤ.አቆጣጠር በ2010 ዓም በፕሬዝዳንት ሁስኔ ሙባረክ ወቅት ነበር።በወቅቱ ኦባማ የግብፅን ጉዳይ በጣም ቀዳሚ እና አንገብጋቢ አጀንዳ አላደረጉትም ነበር።

ይህ በእንዲህ እያለ የግብፁ ፕሬዝዳንት ከትራምፕ ጋር ባደረጉት የዛሬ ንግግር ግብፅ ቀዳሚ ´የፀጥታ እና የደህንነቴ ስጋት´ ብላ የምትቆጥረው የውሃ ጉዳይ እና በኢትዮጵያ እየተሰራ ነው በተባለው የዓባይ ግድብ ዙርያ እንዲሁም በሕወሓት መንግስት ጉዳይ እና የደቡብ ሱዳን ሁኔታ ዙርያ ለትራምፕ ምንም ነገር ሹክ አላሉም ማለት አይቻልም።

ኢትዮጵያ በሕዝብ ተቀባይነት ያላቸው፣በእውቀት እና ችሎታ ላይ የተመሰረቱ ባለስልጣናት ቢኖራት ኖሮ በአካባቢው ላይ ተፅኖ የመፍጠር አቅሟ ባደገ እና በዛሬው የአልሲሲ ቦታ ላይ የኢትዮጵያ መሪ በክብር በተገኘ ነበር።ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያ መልሳ አትነሳም ማለት አይደለም።በዘር ላይ የተመሰረተ መንግስት ፍፃሜውን ማፋጠን ማለት ኢትዮጵያን መልሶ ማንሳት ነው።ላለፉት 26 አመታት ሕወሓት ከመግደል እና ከማሰር እንዲሁም ኢትዮጵያውያንን እንዲሰደዱ እና አንጡራ ሀብታቸው ለባዕዳን ከመሸጥ ያለፈ አንዳች ፍሬ ሊያፈራ አልቻለም።ወደፊትም አይችልም።በቂም እና በመንደር ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ ከአዲስ አበባ ዋይት ሃውስ ድረስ የሚደርስ ዓለም አቀፋዊ ተፅኖ የመፍጠር አቅም የለውም። ስለ አድዋ እና መቀሌ ብቻ የሚያስቡ መሪዎች ኢትዮጵያን የምታህል ትልቅ ሀገር የማስተዳደር አቅምም ሆነ ችሎታ የላቸውም።ይልቁንም ኢትዮጵያን ለማንሳት ኢትዮጵያውያን ትልቅ ርእይ ይዘው መነሳት ካለባቸው ጊዜው አሁን ነው።የእራሳችንን ጉዳይ ሌሎች እንዲነጋገሩበት እና አጀንዳ እንዲያደርጉት ዕድል ልንሰጣቸው አይገባም። 

የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በዋይት ሃውስ ከትራምፕ ጋር የሰጡት መግለጫ ከእዚህ በታች ባለው ቪድዮ ይመልከቱ። የግብፁ ፕሬዝዳንት እንግሊዝኛ ስለማይችሉ አይደለም በሀገራቸው ቋንቋ የሚናገሩት። ኢትዮጵያ ባለስልጣናቷ እስከ ደረግ ዘመን ድረስ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ሳይቀር የሚናገሩት በሀገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ነበር። 





ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Monday, March 27, 2017

የዓለም ባንክን የሚገዳደር የእስያ መሰረተ ልማት እና መዋለ ንዋይ ባንክን ቻይና እያጠናከረች ነው።

ጉዳያችን/ Gudayachn
መጋቢት 19፣2009 ዓም ( march 28,2017)

የእስያ መሰረተ ልማት እና መዋለ ንዋይ ባንክ ቦርድ አባላት 
(Foto: AIIB)

በአለማችን ላይ መሰረታዊ የምጣኔ ሀብት መዋቅር ከመቀየር አንፃር የገንዘብ ተቋማት ያላቸው ሚና ቀላል የሚባል አይደለም።ላለፈው ግማሽ ክ/ዘመን እና በተለይ ከ 1980 ዎቹ እንደ ´አውሮፓውያን አቆጣጠር ማለትም ከሶቭየት ህብረት መበተን በኃላ የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ተፅኖ በአፍሪካ፣ላቲን አሜሪካ እና ሩቅ ምስራቅ ሀገሮች ውስጥ ቀላል አልነበረም።በተለይ በ1990ዎቹ ውስጥ የነበረው የዓለም ባንክ መዋቅራዊ ለውጥ ፕሮግራም ኢትዮጵያን ጨምሮ የብዙ አፍሪካ ሀገር ህዝቦችን ሕይወት አመሰቃቅሎ እና ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል።የመዋቅራዊ ለውጥ መርሃ ግብሩ ጉድለት በእራሱ በዓለም ባንክ የተወቀሰው በርካታ ማኅበራዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ካስከተለ በኃላ መሆኑ ሌላው ህመም ነበር።

ባለፈው ዓመት መጀመርያ ላይ ከወደ ቻይና የተሰማው የግዙፍ ዓለም አቀፍ ባንክ ምስረታ ግን አዲስ ታሪክ ይዞ መጥቷል።ከአንድ ዓመት ከሶስት ወራት ዝግጅት በኃላ እንደ ኤውሮፓውያኑ የጊዜ ቀመር በጥር ወር 2016 ዓም በሩን የከፈተው የእስያ መሰረተ ልማት እና መዋለ ንዋይ ባንክ (Asian Infrastructure Investment Bank - AIIB)መሰረታዊ ፍልስፍናው ግልፅነት፣ተጠያቂነት፣ከጥገኝነት የፀዳ እና አረንጓዴ ልማትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ይናገራል።

በሌላ በኩል ባንኩ የዓለም ባንክ ላለፉት አመታት ሲወቀስባቸው የነበሩትን የሀገሮች የተጭበረበረ የምጣኔ ሀብት እድገት ሪፖርት ማውጣት እና ሙስና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በእዚህ ባንክ እንዳይታዩ ከወዲሁ መሰረት የጣለ ይመስላል።በመሆኑም የባንኩ ቀዳሚ መመርያ መልካም አስተዳደር (Good governance) መሆኑን እና የተሳሳተ ሪፖርት ይዞ መውጣት ፈፅሞ እንደማይታሰብ ባንኩ በመተዳደርያው ላይ ያትታል።ይህ ምን ያህል ተአማኒነት አለው? የሚለው እራሱን የቻለ ጥያቄ ነው።እርግጥ በሙስና ደረጃ ቻይና የተሻለ ወሳኝ እርምጃ የምትወስድ ሀገር ነች።ይህንን ግን አፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ ሀገሮች ላይ ታደርገዋለች ወይ? የሚለው ጥያቄ እራሱን የቻለ መልስ ይፈልጋል። 
"ቀን እባብ ያየ ምሽት ላይ በልጥ ይደነብራል" ነው ነገሩ እና የቻይና "ስግብግብነት" የሚታይበት የአፍሪካን ምጣኔ ሀብት የመቆጣጠር አባዜን ላለፉት አስር አመታት የተመለከተ ሰው ሚዛናዊነትን መጠበቅ ባይችል አይፈረድበትም።

ባጠቃላይ ግን የዓለም ባንክን የሚገዳደር ግዙፍ ከጀርባ በቻይና የተደገፈ ነው የተባለ የገንዘብ ድርጅት አድማሱን እያሰፋ ነው።አባል ሀገሮቹ ከአውሮፓ እንደ ጀርመን እና ደንማርክ፣ሩስያ ከመካከለኛው ምስራቅ እንደ ኢራን እና እስራኤል ከሩቅ ምስራቅ ቻይና እና ህንድ እንዲሁም አውስትራሊያ አህጉርን ጨምሮ እና ካናዳ እና ሌሎች ሀገሮችን አካቶ አቅሙን እየገነባ ነው።አሜሪካ እና ጃፓን አባልነት ላለመግባት ያንገራገሩበት ይሄው ባንክ እንግሊዝ፣ስዊዘርላንድ፣ግብፅ እና በቅርቡ ደግሞ ኢትዮጵያን በአባልነት ተቀብሏል።ዋና መስርያ ቤቱን በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ ፋይናንሻል መንገድ ቁጥር ቢ9 ያደረገው ይሄው ባንክ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ብዙ ሀገሮችን ወደ አባልነት እያሰባሰበ ነው።

ከእዚህ በታች በባንኩ እድገት እና የምዕራቡ ዓለም በተለይ የአሜሪካ ስሜት ዙርያ የተደረገ አጭር የቪድዮ ውይይት ነው።

የውይይት ርዕስ : -  "አሜሪካ ለምን በእስያ መሰረተ ልማት እና የመዋለ ንዋይ ባንክ መጠናከር ስጋት አደረባት? " የሚል ነው።
Why is the US so threatened by the rise of the AIIB? 
Video source: World Finance Video 









ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Friday, March 24, 2017

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ሳምንት አዲስ በረራ ወደ ኦስሎ፣ኖርዌይ ይጀምራል። Next week Ethiopian Airlines will start new flight to Norwegian capital, Oslo. Neste uke vil Etiopia Flyselskaper starte et nytt fly til Oslo.



ጉዳያችን/Gudayachn
መጋቢት 14፣2009 ዓም (March 23,2017)
=================
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ስካንዲንቭያን ሀገሮች የሚያደርገውን በረራ የኖርዌይ፣ኦስሎን በመጨመር ከፍ እንዳደረገ በድረ-ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።Three new flights to three new destinations (በሶስት ቀናት ውስጥ ሶስት አዳዲስ መዳረሻዎች) በሚል ርዕስ ስር ያወጣውን መግለጫ የዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።በእዚሁ መግለጫው ላይም መጋቢት 26-28/2017 እኤአ አየር መንገዱ ወደ ኦስሎ፣አንታናናሪቭ እና ቪክቶርያ ፎል በረራ እንደሚጀምር ይገልፃል። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአግልግሎት ጥራቱን ጠብቆ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን የብዙ ኢትዮጵያውያን ምኞት ነው።አየር መንገዱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታዩበትን አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነቶች እና የሰራተኞቹን ብሶቶች በአግባቡ እንዲያዳምጥ እና ተወዳዳሪነቱን እንዲጨምር አሁንም የብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ያላሰለሰ ምክር እና ምኞት ነው።




ከእዚህ በታች አየር መንገዱ በእዚህ ሳምንት አጋማሽ ላይ ያወጣው መግለጫ ነው።




Three new flights to three new destinations in just three days
March 22, 2017
Africa’s largest airline group, Ethiopian Airlines, is delighted to announce that it has finalized preparations to launch flights to three new destinations – Victoria Falls, Oslo and Antananarivo – within three days, 26-28 March 2017.
....to read more click here 



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Thursday, March 23, 2017

ሰበር ዜና - Breaking News Ethiopia - የተባበሩት አረብ ኢምሬት አምባሳደር ትናንት መከላከያ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ታይተዋል ድርጊቱ ያልተለመደ ነው።UAE Ambassador makes extraordinary meeting with chief of staff of Ethiopian Army



ጉዳያችን/ Gudayachn 
መጋቢት 14፣2009 ዓም (March 23,2017)
(የአማርኛ ፅሁፍ ከእንግሊዝኛው ስር ያንብቡ )

On March 22, 2017, United Arab Emirates - UAE Ambassador to Ethiopia, Gazi Abdullah Al Mahri,  makes extraordinary meeting  with chief of staff of Ethiopian Army General Samora Yenus with in Ethiopian ministry of defence premises. Even if the meeting was given a cover of " discussion on terrorism", Gudayachn can learn as many questions are arising around the meeting. First of all, the UAE Ambassador did not keep his diplomatic protocol to meet the chief of staff. Because the concerned office to arrange such meeting in Ethiopia was ministry of Foreign Affairs. Secondly, the meeting was not disclosed to other high officials in the country. Non confirmed news from Addis are reporting as there is power straggle among high military officials. In the past few days, top urgently needed corrupt officials were leaving the country legally with the assistance of corrupt immigration officials exit visa from Ethiopia. 

It is over six months, since the state of emergency was declared in Ethiopia. The declaration could not improve the security condition and uprising of the mass against the brutal TPLF government. On the other hand, It is known as TPLF army is under pressure of fighting with Patriotic Ginbot 7 and KEFAGN rebel forces in Amhara region. This week the rebel groups announced as they got significant victory over TPLF army in the North west part of the country. 
==================================
የተባበሩት አረብ ኢምሬት አምባሳደር ትናንት መከላከያ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ታይተዋል ድርጊቱ ያልተለመደ ነው። 
===================================
ጀነራል  ሳሞራ የኑስ አዲስ አበባ የሚገኙትን የተባበሩት አረብ ኢምሬት አምባሳደርን ትናንት ፅህፈት ቤታቸው ጠርተው ማነጋገራቸውን አንድ የመካከለኛ ምስራቅ ድረ-ገፅ ገልጧል። አምባሳደር ጋዚ አብዱላህ አል ማሃሪ (Gazi Abdullah Al Mahri) ከሳሞራ የኑስ ጋር የተናጋገሩት ስለ ሽብርተኝነት የምትል ከሶስት መስመር ያልበለጠ ዜና የዘገበው ዜና ለምን አምባሳደሩ ፕሮቶኮሉን ጠብቀው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኩል እንዳልተነጋገሩ ያለው ነገር የለም።አምባሳደሩ ከጀነራል ሳሞራ የኑስ ጋር የተነጋገሩት መከላከያ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ድረስ በመሄድ ነው።

አምባሳደሩ መከላከያ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ድረስ ሄደው ከሳሞራ የኑስ ጋር መነጋገራቸው በሚስጥር እንደነበር እና መከላከያ ውስጥ ያሉ ሰዎችም አለመስማታቸው እየተሰማ ነው።ድርጊቱ ያልተለመደ ነው።ጉዳዩ በኢትዮጵያ የጦር ሰራዊቱ አመራር እና ባለስልጣናት መካከል የስልጣን ፍትግያ መጀመሩን የሚያመላክት መሆኑ እየተሰማ ነው።በሌላ በኩል ጀነራል ሳሞራ የኑስ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ስልጣን በዘለለ መንገድ የእራሳቸውን ግንኙነት ከአምባሳደሮች ጋር እያደረጉ ነው የሚሉ ወገኖችም አሉ።

ሰሞኑን እንደሚታወቀው የሕወሓት መንግስት ከአርበኞች ግንቦት 7 እና ከፋኝ ጦር ጋር በተለያዩ ቦታዎች ውግያ እንዳደረገ እየተነገረ ነው።የአርበኞች ግንቦት 7 እና ከፋኝም የበላይነት እንደተቀዳጁ በእዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ አሳውቀዋል።አርበኞች ግንቦት 7 ባልተለመደ መልኩ " ኢትዮጵያውያን ሚናቸውን የሚለዩበት ጊዜ ላይ ደርሰናል" የሚል ሃሳብ ያለው ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷል።




ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Wednesday, March 22, 2017

የኦስሎ ዩንቨርሲቲ ምሩቁ የሱማሊያው አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ማናቸው? ጠ/ሚሩ የካቢኔ አባሎቻቸውን ትናንት አስተዋውቀዋል። Somalian PM announced his cabinet ministers.

የሱማልያው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስተር አሊ ካይረ


ጉዳያችን/ Gudayachn 
መጋቢት 13/2009 ዓም (March 22,2017)

የሱማልያው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስተር አሊ ካይረ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተመረጡ እና በፓርላማ ስልጣናቸው ከፀደቀ ገና ሶስተኛ ሳምንቱን ቢይዝም አዲሱ ካቢናቸውን መስርተዋል።
የመጀመርያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞቃዲሾ እንደጨረሱ የሚነገርላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር በ1994 ዓም እኤአ በኖርዌይ ዋና ከተማ በሚገኘው የኦስሎ ዩንቨርስቲ ተማሪ የነበሩ እና በሱማሌ ተማሪዎች ህብረት እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደ ነበራቸው ለማወቅ ተችሏል። 

በኦስሎ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ´ማይነራቸውን´ ሶሾሎጂ የጨረሱ ሲሆን በመቀጠል በኤደንበርግ ቢዝነስ ኮሌጅ( Edinburgh Business School) የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። ከምርቃት በኃላ ሚስተር አሊ ካደር ወደ ኦስሎ ተመልሰው በአንደኛ ደረጃ መምህርነት በመቀጠል ደግሞ በኖርወጅያን ስደተኞች ካውንስል (Norwegian Refugee Council) ዋና መስርያ ቤት ውስጥ በአስተባባሪነት ሰርተዋል።በመሃል ለግል ሥራ ካቆሙ በኃላ ተመልሰው ወደ  የኖርወጅያን ስደተኞች ካውንስል መስርያቤት ውስጥ በመግባት ለ9 ዓመታት በማገልገል እስከ ሪጅናል ዳይሬክተርነት ደረጃ  ደርሰው ነበር።በመስርያ ቤቱ ውስጥም በምስራቅ አፍሪካ በተለይ ሰሜናዊ  ኬንያ ውስጥ ሰርተዋል።

በሰሜን ኬንያ በኖርወጅያን የስደተኞች ካውንስል ኃላፊ በነበሩበት ወቅት በነበረው የፀጥታ ችግር የተለያዩ ሃገራት የስራ ባልደረቦቻቸውን በሞት  ያጡ ሲሆን በኃላፊነታቸው ሳብያ የፀጥታ ሁኔታው በሚገባ እንዲጠበቅ አላደረጉም ተብሎ መስርያቤታቸው ሲከሰስ እርሳቸውም በዋናነት  በኖርዌይ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው ነበር።በመቀጠል የሚስተር አሊ ካይረ የስራ መስክ ያመራው  በእንግሊዝ ካምፓኒ ´ሶማ ኦይል´ (Soma Oil) ውስጥ ነበር። ሚስተር አሊ ከእዚህ ወር መጀመርያ ጀምሮ የሱማሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል።በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱን ካቢኔ አስተዋውቀዋል።

በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ ስድስት ሴት ሚኒስትሮች ተሹመዋል።ይህ ሁሉ ሆኖ የሱማሌ ሁኔታ ግን ገና መረጋጋት ይጎድለዋል።በትናንትናው እለትም ወደ ቤተ መንግስት የሚያመራ መንገድ ላይ በቆመ አንድ አውቶብስ ላይ የተጠመደ ፈንጅ ፈንድቷል።አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሁኑ የሕወሓት አስተዳደር ጋር ያላቸው ግንኙነት የተቀዛቀዘ መሆኑን የሚናገሩ አሉ።ለእዚህም ማስረጃ የሚያደርጉት በሱማሌ የተሾሙ ሹማምንት የመጀመርያ ጉዞ የሚያደርጉት ወደ ኢትዮጵያ ሲሆን ሚስተር አሊ ግን የመጀመርያ ጉዟቸውን ያደረጉት ወደ ሳውዲ አረብያ መሆኑን ነው።


የፕሬዝዳንት አሊ አዲሱ ካቢኔ አባላት ስም ዝርዝር ከእዚህ በታች ይመልከቱ። 


Somalia’s Premier Hassan Ali Khayre on Tuesday announced his cabinet ministers.
Mr. Khayre made the announcement at a press conference in the Somali capital, Mogadishu.

The names of the new ministers are:

  1. Abdi Farah Juha – Interior Minister
  2. Yousuf  Garad Omar – Minister of Foreign Affairs
  3. Mohamed Abukar Islow – Minister of National Security
  4. Jamal Mohamed Hassan – Minister of Planning
  5. Abdirahman Duale Beyle – Minister of Finance
  6. Khadija Mohamed Dirie – Minister of Youth and Sports
  7. Abdirahman Omar Osman – Minister Of Information
  8. Maryan Qasim Ahmed – Minister of Humanitarian Affairs and Disaster Management
  9. Abdirashid Mohamed Abdullahi – Minister of Defence
  10. Abdirahman Dahir Osman – Minister of Education and Higher Education
  11. Abdirahman Hosh Jibril – Minister of Constitutional Affairs
  12. Maryan Aweys Jama – Minister of Ports and Aviation
  13. Abdi Anshur Hassan – Minister of Posts and Technology
  14. Sheikh Nur Mohamed Hassan – Minister of Livestock
  15. Khadro Ahmed Duale – Minister of Trade and Industry
  16. Abbas Sheikh Abdullah Siraaji – Minister of Public Works and Rebuilding
  17. Abdirashid Mohamed Ahmed – Minister of Petroleum and Mineral Resources
  18. Said Hussein Eid – Minister of Agriculture
  19. Fawzia Yusuf Haji Nur – Minister of Health and Social Welfare
  20. Hassan Hussein Haji – Minister of Justice
  21. Saleh Ahmed Jama – Minister of Labour and Employment
  22. Salim Aliyow Ibrow – Minister of Electricity and Water
  23. Iman Abdullahi Ali – Minister of Religious affairs
  24. Deqa Yasin Haji Yousuf – Minister of Women and Human Rights
  25. Abdirahman Abdi Hashi – Minister of Fisheries and Marine Resources 
  26. Mahad Ahmed Guled – Deputy Prime Ministe  

Six of the new ministers are women.

The new cabinet ministers will face a confidence vote in the parliament next days, according to the Somalia’s constitution.



ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com