Saturday, November 16, 2019

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ደህንነቷን ለመጠበቅ በፍጥነት መውሰድ የሚገባት ሁለት የመፍትሄ ርምጃዎች ።



ጉዳያችን / Gudayachn
ህዳር 6/2012 ዓም (ኖቬምበር 16/2019 ዓም)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ የለውጥ ነፋስ በነፈሰ ቁጥር የመጀመርያ ኢላማ ስትሆን ኖራለች።በ1966 ዓም የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ መውረድን ተከትሎ ፓትርያርክ ቲዎፍሎስ በደርግ ተገደሉባት፣በ1983 ዓም ኢህአዴግ አዲስ አበባን መቆጣጠሩን ተከትሎ አቡነ መርቆርዮስ ከመንበረ ፕትርክናቸው ተነስተው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆነ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሲኖዶስ ተከፍላ ቆየች።በ2010 ዓም ከኢህአዴግ ጥገናዊ ለውጥ በኃላ የቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ አንድነት ቢመለስም የቤተ ክርስቲያን መቃጠል፣የምእመናን መገደል እና ስደት በተለይ በኦሮምያ ክልል ተባብሶ ቀጥሏል። ባሳለፍነው አንድ ወር ውስጥ ብቻ በመንግስት የተረጋገጠ ሰማንያ ስድስት ኢትዮጵያውያን በፅንፈኞች መገደላቸው ተገልጧል።

ለውጡን ተከትሎ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለማጥቃት መልካም አጋጣሚ ያገኙ የመሰላቸው የፅንፍ ኃይሎች ቤተ ክርስቲያንን ህንፃዋን ከማቃጠል እስከ ምመናኗን መግደል እና ከይዞታቸው መንቀል ድረስ ከፍተኛ ዘመቻ ከፍተዋል።በእዚህም መሰረት ከሲዳማ ዞን እስከ ባሌ፣አርሲ እና ምስራቅ ሐረርጌ ድረስ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ሴት ልጅ ጭምር በድንጋይ ተወግራ ተገድላለች፣አዛውንት በስለት ተገድለዋል። ቅዱስ ሲኖዶስም ተከታታይ የምሕላ ፀሎት ከማወጅ ባለፈ ምዕመናንን ወርደው እስከ ማፅናናት ስራዎች እየሰሩ ነው።

በእነኚህ ሁሉ ፈተናዎች ውስጥ ቤተ ክርስቲያን  አፋጣኝ መፍትሄ መውሰድ የሚገባት በተለይ ከደህንነቷ አጠባበቅ ጋር በተያያዘ ምንድነው የሚለውን ጉዳያችን እንደሚከተለው ሃሳብ ታቀርባለች። ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ መመርያ ሰጪነት ሁለት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ይገባታል። እነርሱም -

1) የቤተ ክርስቲያን የጥበቃ (የዘበኛ)  ከቤተ ክህነት እስከ አጥብያ  በአዲስ ዲፓርትመንት ማለትም በወታደራዊ ሙያ በሰለጠነ እና ዘመናዊ መሳርያ ትጥቅ ማደራጀት እና  ማዋቀር 

በኢትዮጵያ  በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ መንግስታዊ መስርያ ቤቶች የጥበቃ ዲፓርመንት  ራሱን በቻለ ዲፓርትመንት የሚመራ ነው።ለምሳሌ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በምሳሌነት መውሰድ ይቻልል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጥበቃ ክፍል አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋናው መስርያ ቤት  እስከ ጫፍ ዶሎ መና ባሌ ያለው የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የጥበቃ ክፍል የሚመራው ራሱን በቻለ ዲፓርትመንት ነው። ይህ ማለት የራሱ በጀት አለው፣በወታደራዊ ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎች፣የፀጥታ አጠባበቅ መመርያ ሁሉ አለው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በኩል ስንመለከት ይህ አሰራር ወጥነት ባለው እና በቂ በወታደራዊ ሙያ የሰለጠነ እና በቂ ትጥቅ ያለው የጥበቃ ኃይል የላትም። ይህ ግን በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው።ከእዚህ በፊት ቤተ ክርስቲያን  ከላይ በተጠቀሰው ደረጃ የጥበቃ ክፍሏን ያላጠናከረችው  ለሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች በቀላሉ ለመንግስት የፀጥታ አካላት ለምሳሌ ለፖሊስ በማሳወቅ ችግሮች ይፈታሉ በሚል ነበር።አሁን በሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ፖሊስ እራሱ የፀጥታ ችግር በሆነበት ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን የራሷን የጥበቃ ኃይል በፍጥነት ማጠናከር ይጠበቅባታል።

በኢትዮጵያ ሕግ ማንኛውም ግለሰብ ቤት ሆነ የእምነት ድርጅት አጥር ግቢ  ካለፈቃድ መግባት ወንጀል ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ንብረት ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያኗን ስም በበበሩ ላይ መፃፍ አንዱ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።ፅሁፉ እያለ በር ላይ የሚገኘውን የጥበቃ አካል አልፎ ለመግባት በተለይ በኃይል ለመግባት የሚሞክር ማናቸውም አካል ላይ ጥበቃ በያዘው መሳርያ ከማስጠንቀቅያ  ጋር ቤተ ክርስቲያንን ለመከላከል ማናቸውንም እርምጃ የመውሰድ ሕጋዊ መብት አለው።ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን የጥበቃ ኃይሏን መብታቸው እና ግዴታቸውን ማሳወቅ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።ከጥበቃ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን  ለምታደርገው የጥበቃ አካላት ስልጠና እና የትጥቅ ማሟላት ሂደት ሁሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይገባዋል። ለምሳሌ የተቀጠሩትን የጥበቃ አካላት ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ላይ እና ከኃላ ቀር መሳርያ ቢያንስ በክላሽ ደረጃ የታጠቁ የጥበቃ ኃይል እያንዳንዱ አጥብያ ከከተማ እስከ ገጠር እንዲኖር ለማድረግ መንግስት ሕጋዊ ስልጣኑን እና ትጥቅ በግዥም የማቅረብ ሥራ መስራት አለበት።ይህ ሥራ በራሱ የመንግስትን ሥራ በተለይ በፀጥታ በኩል የሚያቀልለት ሥራ መሆኑ እሙን ነው።እዚህ ላይ ቤተ ክርስቲያን የጥበቃ ስራውን እራሷ ባደራጀችው ሕጋዊ በሆነ የጥበቃ አካል እንጂ ቤተ ክርስቲያን አንዳንድ ድርጅቶች እንደሚያደርጉት ለጥበቃ ኤጀንሲዎች ስራውን ለመስጠት ከሞከረች ትልቅ ችግር ቤትክርስትያን ላይ ሊያስከትል ይችላል።ኤጀንሲዎች ተፈላጊ እንዲሆኑ እራሳቸው የፀጥታ ችግር የሚሆኑበት አጋጣሚ በብዙ አገሮች የታየ ነው።ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን በጥንቃቄ በራሷ ልጆች ልፀራው የሚገባ ሥራ ነው።

የጥበቃ ክፍልን (ድፓርትመንት) ቤተ ክርስቲያን በአጭር ጊዜ ለማደራጀት የሚከተሉትን ተግባራት በቶሎ መስራት ትችላለች። እነርሱም -

  • የጥበቃ ክፍሉን በአገር አቀፍ ደረጃ ማዕከላዊ አደረጃጀት እንዲኖረው ማድረግ፣
  • ክፍሉ በአገረ ስብከት እስከ አጥብያ የሚወርድ ወጥ የሆነ አሰራር፣አጠባበቅ፣የስልጠና አቅም እና የመሳርያ ትጥቅ ማሟላት፣
  • የጥበቃ ክፍሉ በተለይ በማዘዣው በቤተ ክህነት ደረጃ ያለው የጥበቃ ዋና ክፍል በአገረ ስብከት ደረጃ እና እስከ አጥብያ ድረስ ያለውን የጥበቃ  ሁኔታ ለመከታተል እንዲረዳ ቢያንስ በኮለኔል ደረጃ የሚመራ ይሆናል፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጅች የሆኑ ነገር ግን በወታደራዊ ስልጠናም ሆነ ስነምግባር የተመሰገኑ መሆን ይገባቸዋል፣
  • የጥበቃ ዲፓርትመንት በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ አጥብያዎች ስጋት የተደቀነባቸውን እና ቅድምያ ትኩረት የሚሹትን አካባቢዎች ይለያል፣ መረጃ ይተነትናል አስፈላጊ ሲሆን መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ የቅድመ አደጋ ጥንቃቄ ማስጠንቀቅያ ይሰጣል፣
  • የጥበቃ ክፍል ከኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ፈቃድ ያለው የራሱ የመገናኛ ራድዮ መገናኛ ይኖረዋል።በእዚህም መሰረት በአገረ ስብከት ደረጃ እስከ አጥብያ ያለው ጥበቃ ድረስ የሚገናኝበት በመንግስት ፈቃድ ያለው የራድዮ መገናኛ መስመር ይዘረጋል።
  • የጥበቃ ክፍሉ መተዳደርያ ደንቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ፀድቆ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል።

2) የአይቲ (ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ) ክፍል በመምርያ ደረጃ መመስረት  

አሁን ባለንበት ዓለም አይደለም ከሃምሳ ሚልዮን በላይ ሕዝብ በስሩ የያዘች እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያለ ትልቅ አደረጃጀት ያላት አገራዊ  አካል ቀርቶ ትንንሽ ድርጅቶችም ከአይቲ (የኢንፎርሜሻን ቴክኖሎጂ) ክፍል በመምርያ ደረጃ በቤተ ክህነት መመስረት እና ክፍሉ ከአገረ ስብከት እስከ አጥብያ ድረስ በኔት ዎርክ ማያያዝ በፍጥነት መሰራት የሚችል ሥራ ነው። የአይቲ ኔትዎርክ መመስረት በጣም ውስብስብ ሥራ እና የማይቻል አድርጎ ማሰብ አይቻልም። 

ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ ሁለት ሀብት አላት።አንዱ የሰለጠነ እና የተማረ የሰው ኃይል ሲሆን ሌላው የገንዘብ አቅም ነው። ስለሆነም የአይቲ መረቡን መዘርጋት በቤተ ክህነት ደረጃ ቅዱስ ሲኖዶስ በፍጥነት መመርያ ቢሰጥበት  ስራውን የሚከታተል ልዩ ኮሚቴ ሰይማ ስራውን የሚሰሩ በአገር ውስጥ ወይንም በውጭ የታወቁ ኩባንያዎች በጨረታ ስራውን መስጠት ትችላለች።የኔትዎርኩ ሥራ በአንዴ ሁሉም ጋር ባይደርስ ደረጃ በደረጃ ለመስራት ስራውን መጀመር ግን ጊዜ የሚሰጠው አይደለም።የአይቲ መምርያ ማስቀመጥ እና አሰራርን በአይቲ አስደግፎ መስራት ከቤተ ክርስቲያኒቱ የፀጥታ ሥራ ጋር አብፎ የሚታይ ብቻ ሳይሆን መጪውን የዋጀ አሰራር የመዘርጋት ተግባር አካል ነው።የአይቲ መምርያ መስርቶ እስከ አጥብያ ድረስ ስራውን መተግበር ለቤተክርስቲያን  የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጣል። እነርሱም -


  • የቤተ ክርስቲያን የገንዘብ አጠቃቀም፣የአጥብያ ሁኔታ፣ውሎ እና ተግባራት በቀጥታ በደቀቃዎች ውስጥ ሪፖርት ለአገረ ስብከት እና ለቤተ ክህነት ለመላክ ይረዳል፣
  • በእርቀት የሚገኝ አጥብያ የፀጥታ ስጋት ቢኖርበት በደቂቃዎች ውስጥ ለሚመለከተው ሁሉ ለመግለጥ አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል፣ 
  • ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ ያሉ አጥብያዎች በኔት ዎርክ እንዲገናኙ ያደርጋል፣
  • ወጥ የሆነ የእቅድ ፎርማት ለመላክ ለሁሉም አጥብያዎች ማድረስ ይቻላል፣
  • አጥብያዎች ወጥ የሆነ እቅድ ትግበራ ሪፖርት እንዲልኩ እና በአገረ ስብከት እና በቤተ ክህነት ደረጃ እንዲገመገም ይረዳል፣
  • ቤተ ክርስቲያን ያላትን የሰው ኃይል፣የገንዘብ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት በሚገባ መዝግባ ለመያዝ እና የንብረቷን ሁኔታ ለመቆጣጠር  ይረዳታል፣
  • እያንዳንዱ አጥብያ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መዋቅር ውስጥ የአይቲ ክፍል እንዲኖረው ቃለ አዋዲው ማሻሻያ እንዲደረግበት ይረዳል። 


ለማጠቃለል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አሁን የገጠማትን የፀጥታ ችግር ከላይ በተጠቀሱት ሁለት መንገዶች ችግሩን በዘለቄታው ለመፍታት የሚያስችላት እንደሚሆን አምናለሁ።በተለይ የጥበቃ ክፍሉ በዲፓርትመንት (መምርያ) ደረጃ ስትመሰርት በርካታ የበጎ ፍቃድ አገልጋዮች ማንቀሳቀስ የምትችልበት ዕድል አላት።በጎ ፍቃድ የጥበቃ አካላት ለማንቀሳቀስ ግን ራሱን የቻለ ጉዳዩን የሚከታተል እና በወታደራዊ ሙያ የሰለጠነ አስተባባሪ ያስፈልጋል። በእዚህ ደረጃ የተጠናከረች ቤተ ክርስቲያንን እሳትና ጎመድ ይዞ ለሚመጣ ፅንፈኛ ከጥበቃ ክፍሉ የሚሰጠውን ምላሽ ስለሚረዳ በቀላሉ አንድ አጥብያ ለማጥቃት አይደፋፈርም። ምክንያቱም  የሁሉም አጥብያ ጥበቃዎች የቤተ ክርስቲያኑን አጥር ጥሶ የሚመጣ ማንኛውም አካል ላይ የመተኮስ እና ቤተ ክርስቲያኑን የመከላከል ሕጋዊ ስልጣን ስለሚኖረው ፅንፈኛም አደብ እንዲገዛ ያስገድደዋል። በሌላ በኩል የጥበቃ ክፍሉ አንዱ አጥብያ ላይ ችግር ካለ ሌላ አካባቢ ያሉ አጥብያ የጥበቃ አካላት በራድዮ መገናኛ ተጠቅመው ችግሩ ያለበት አጥብያ  በፍጥነት የሚደርሱበት ዕድል አለ።

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Monday, November 11, 2019

የኢህአዴግ ውሕደት ላይ ያተኮረው የድርጅቱ ወሳኝ ስብሰባ የፊታችን ሮብ ይጀመራል።ውህደቱ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ አንድ ምዕራፍ እንዲያሸጋግር ጉጉታችን ነው።ህወሓት በውህደቱ ከመሳተፍ ሌላ ምንም ምርጫ እንደሌለው ሶስት ምክንያቶች አሉ።

ጉዳያችን /Gudayachn
ሕዳር 1/2012 ዓም (ኖቬምበር 11/2019 ዓም)

ኢህአዴግ ቀድም ብሎ በሐዋሳ ላይ በወሰነው ውሳኔ መሰረት በውሕደቱ ላይ ያተኮረው ጉባኤውን ለማካሄድ በመጪው ሮብ ለስብሰባ ይቀመጣል።እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት በውህደቱ ላይ የተስማሙ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ፣የዓማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) እና የደቡብ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ደሕዴድ)  ሲሆኑ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ግልጥ ውሳኔውን አላሳወቀም።ሆኖም ቀደም ብሎ ድርጅቱ ባወጣቸው መግለጫዎች ውህደቱን እንደሚቃወም አስታውቆ ነበር። በሌላ በኩል ህወሓት በውህደቱ ባይሳተፍ ይህ የድርጅት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ጉዳይ ስለሆነ ሌሎች የትግራይ ክልልን ወክለው በውህደቱ ሂደት ላይ ለመሳተፍ  የሚፈልጉ እንዳሉ ከአዲስ አበባ የሚሰሙ ዜናዎች አሉ።

ኢህአዴግ ወደ ውህደት ስመጣ ከእዚህ በፊት በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የጎላ ድርሻ ያልነበራቸው ማለትም በአጋርነት ብቻ ሲጠሩ የነበሩ የሐረሪ፣የቤንሻንጉል፣የጋምቤላ፣የአፋር እና የሱማሌ ድርጅቶች በአሁኑ የኢህአዴግ ውህደት ላይ ለመሳተፍ  ስምምነታቸውን መግለጣቸው ለማወቅ ተችሏል።ሆኖም ግን በውህደቱ የውሳኔ ድምፅ መስጠት ላይ ወሳኞቹ አራቱ ድርጅቶች ማለትም ኦዴፓ፣አዴፓ፣ህወሓት እና ድህዴድ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።ከውሳኔው በኃላ ግን አጋር ድርጅቶች የውሕደት ጥያቄያቸው ወዲያውኑ ተቀባይነት እንደሚኖረው እና ውሕደቱ እንደሚከናወን ይታመናል።

ህወሓት በውህደቱ ከመሳተፍ ሌላ ምንም አይነት ምርጫ የለውም 

ይህ በእንዲህ እያለ ህወሓት በእዚህ ውህደት ላይ ከመሳተፍ ሌላ ምንም አይነት አምራጭ እንደሌለው በሶስት ምክንያቶች ማወቅ ይቻላል።እነኝህ ምክንያቶችም -

1ኛ) የትግራይ ምሁራን እና የንግዱ ማኅበረሰብ ውሕደቱን ስለሚደግፍ


የትግራይ ምሁራን እና  በተለይ ላለፉት 27 ዓመታት ከፍተኛ ሀብት ያገኘው የትግራይ ባለሀብት አሁን የሚፈልገው በየትኛውም ቦታ አድልዎ ሳይደረግበት ካፒታሉን ማፍሰስ እና መስራት ነው።ሌላው ምክንያት አሁንም ከፍተኛው ሀብት ያለው በአዲስ አበባ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍል ከመሆኑ አንፃር (በተለይ የማይንቀሳቀሰው ሀብት) ውህደቱን በከፍተኛ ደረጃ ይደግፋል። ህወሓት ውህደቱን ተቃውማ ብትቆም የመጀመርያ ጠብ ያለባት ከእዝህኛው የህብረተሰብ ክፍል ጋር ነው።

2ኛ) ህወሓት በሌላ የፖለቲካ ድርጅት የመተካት ዕጣ ሊገጥማት ስለሚችል

ህወሓት የኢህአዴግን ውህደት አልቀበልም ብትል ለተወሰነ ጊዜ ከማኩረፍ እና የተወሰኑ ችግሮች ለመፍጠር ከመሞከር ባለፈ በዘለቄታው ግን ሕወሃትን የሚቃረን የፖለቲካ ድርጅት በቀጥታ ወደ ውህደቱ የትግራይን ሕዝብ ወክሎ ሊቀላቀል ይችላል። ይህ ማለት ከአረና ትግራይ ጀምሮ ሌሎች አዳዲስ ድርጅቶች መፈጠራቸው ስለማይቀር ህወሓት በውህደቱ ባለመሳተፍ ትግራይ የነበራትን የፖለቲካ እና ማኅበራዊ መሰረት የማጣት ዕጣ ሊገጥማት ስለሚችል ከመዋሃድ ሌላ አማራጭ የለም።

3ኛ) ውህደቱ በራሱ ለሕወሀት ጥቅም ስላለው 

ህወሓት ከኢህአዴግ ውህደት ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ አይደለችም።ህወሓት የበላይ በሆነችበት ኢህአዴግ ውስጥ ውህደት ላይጠቅማት ይችላል።አሁን ግን የበላይነት በሌለበት የፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ህወሓት በውህደት ውስጥ በመሆን ቢያንስ ትግራይ ያላትን  የበላይነት በምርጫው ወቅት አስጠብቆ ሌላ አመቺ ጊዜ መጠበቅ ብቸኛው አማራጭ ነው።ስለሆነም  ውህደቱን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የጥቅም ሜዳ ሊኖራት አይችልም።


ስለሆነም ውህደቱ ሙሉ በሙሉ የሚሳካ እንደሚሆን ከወዲሁ ማወቅ ይቻላል።

በመጨረሻም የኦሮሞ የፅንፍ ኃይሎች ይህንን ውህደት በመቃወም አንዳንድ መግለጫ ሲሰጡ እንደሰነበቱ ይታወሳል።ሆኖም ግን ይህ ውህደት አንዱ ይዞ የሚመጣው ጉዳይ  የፅንፍ የኦሮሞ ድርጅቶችን ለብቻቸው የመነጠል መልካም የአደጋ ዕድል ይዞላቸው ይመጣል። ለእዚህም ነው ውህደቱን የፈድራሊዝም ጠላት እንደሆነ ለመለፈፍ ሲሞከር የከረመው። በእርግጥ ውህደቱ በርካታ ጥያቄዎች የሉትም ማለት አይደለም። ለምሳሌ ከውህደቱ በኃላ ሌላ የተረኝነት ወይንም አንዱ የበላይ የሚሆንበት ሂደት እንዳይከሰት የሚወሰዱ ምን እርምጃዎች አሉ? ውህደቱ ፍፁም ውህደት ካልሆነ እና የጎሳ አደረጃጀችን ካላጠፋ መልሶ የጎሳ ስሜትን እንዳይፈጥር እንዴት መከላከል ይቻላል? እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች መመለስ ያስፈልጋል። በሌላ በኩል እነኝህ ጥያቄዎች የሚወሰኑት በክልሎች አከላል ዙርያ ያለው ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ጥያቄ እንደሚሆን ይታመናል። ለሁሉም ግን የኢህአዴግ ውህደት የህዝብ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ አንድ ምዕራፍ እንዲያሸጋግር ጉጉታችን ነው።

ድምፃዊ አብርሐም ገብረመድሕን ''አገሬ''



ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Tuesday, November 5, 2019

Leaked document: Cairo, Kampala, Juba conspiring against Addis Ababa ግብፅ፣ዑጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ላይ እያሴሩ መሆኑን አንድ ምስጢራዊ ዶክመንት አመለከተ

El-Sisi (right, Museveni (left). Photo: Egypt Today/File
Kampala, November 5, 2019 (SSNA) — 
The leaders of South Sudan, Uganda, and Egypt are working days and nights to prevent Ethiopia from completing the construction of the $4 billion dollars Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD), a Ugandan ex-spy who uses a pseudonym name James Moises to protect his identity has claimed.
In a 3-page documented he delivered to a South Sudan News Agency’s (SSNA) reporter through an intermediary in Kampala, the former intelligence officer who previously worked for Uganda’ s External Security Organisation (ESO) exposes what seems to be an extensive campaign to put more pressure on Ethiopia through diplomatic and military means. The text also reveals how the three countries are coordinating their corporation to achieve their interests in the East African region.
“We have a situation where my country [Uganda] has become the number one ally of Egypt in the region. There is no problem of being an ally of a sovereign nation, but it is wrong when you do it to cause harm to other countries,” James wrote.
James’s claims point finger at Egypt, Uganda, and South Sudan.
“The Egyptian President Abdel Fattah El-Sisi, Ugandan President Yoweri Museveni, South Sudanese President Salva Kiir are conspiring against Ethiopia to make sure Ethiopian mega project Grand Ethiopian Renaissance Dam does not go forward,” he explains, adding, “I have worked for many years as a spy and most of my assignments were in the East African region. I have never seen anything like it before.”
The former ex-spy accuses the three nations of being driven by self-fish interests.
“El-Sisi, Museveni, and Kiir have their own interests they want to achieve. The President of Egypt wants to continue controlling the water of the Nile River, Uganda wants to keep Salva Kiir in power with help from Egypt, and South Sudan’s leader future depends on Museveni, James explains.
In the document, James says he uncovers “serious techniques” designed to prevent Addis Ababa from completing its Dam. He asserts that “the plan includes Uganda and South Sudan to assist Egypt” if Cairo decides to go to war with Addis Ababa.
James, who claims he has “Ugandan best intelligence connections” also accused Egypt of using ‘covert channels’ to deliver weapons to South Sudan.
“El-Sisi always delivers weapons and ammunition to Juba in two different ways. He delivers them in the form of medicines or agricultural products, or he uses Uganda as an intermediary. These are all cover channels,” he says.
The construction of the Ethiopian Grand Ethiopian Renaissance Dam began in 2011. The project encountered several obstacles before including an attack by a rebel group. The Ethiopian authorities accused Egypt and Eritrea of being the sponsors of the rebel.
The 6.4GW project is set to become the biggest hydropower dam in Africa if completed.
James Moises is known for being the first foreigner to expose secrets between Uganda and South Sudan. His July 2013 article exposed Kiir and Museveni’s plan in weeks, months, and years leading up to the eruption of civil war in December 2013.
Source = South Sudan News Agency 
                November 5, 2019 (SSNA) 
ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Friday, November 1, 2019

ኢትዮጵያውያን ከአገር ቤት እስከ ባህር ማዶ እጃችሁ ይያያዝ፣የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቀርቧል። (ጉዳያችን መልዕክት)

ጉዳያችን / Gudayachn
ጥቅምት 22/2012 ዓም  (ኖቬምበር 2/2019 ዓም)

ከንፈር ሳይነቃነቅ ልሳን ሳይጋራ፣
በዝምታ ድባብ በዝምታ ጎራ፣
ሳየወሩ ማውራት መልካም ባልንጀራ።

የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ግጥም ለመሞነጫጨር አንድ ሰሞን ተፍ ተፍ ያረገኝ ነበር።ከላይ ያለው ስንኝ አንድ በዝምታ በማውራት የሚግባቡ ገፀ ባህርያት ከአፋቸው አንዳች ቃላት ሳይወጣ የተግባቡ ሰዎች በገለጥኩበት መጣጥፍ ላይ የተጠቀምኩበት አገላለጥ ነበር። ዛሬ ይህንን ፅሁፍ ሳስብ ሃሳቤን የሚገልጥልኝ መሆኑን ስላሳመነኝ መግቢያ አደረኩት።

በዛሬው የጉዳያችን መልዕክት በረጅሙ ሃሳቦችን በማርዘም አላደክማችሁም።ሳይጀመር አለቀ እንዳትሉ እንጂ፣ የመልእክቱ ዋና ጭብጥ ሲጠቃለል ኢትዮጵያውያን ከደብረ ዳሞ፣ምፅዋ  እስከ ሞያሌ፣ ከአኮቦ እስከ ፈርፈር፣ከአሜሪካ እስከ ጃፓን፣ከፊንላንድ እስከ ደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ የምንያያዝበት፣ በጎሳ፣በሃይማኖት ሳንለያይ እና በልዩ ልዩ ጉዳዮች፣ በማኅበራዊ ቦታዎች ሁሉ ወጣቶች፣እናቶች፣አባቶች፣ሁላችሁ የምትያያዙበት ጊዜ ነው።

ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ለማያያዝ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ ሁሉ ኢትዮጵያውያን  እርስ በርስ ግንኙነታቸውን እንዲያዳብሩ ለመስራት ተነሱ።እናቶች ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን እጅ ለእጅ አያይዙ እንጂ ከቤታችሁ ሆናችሁ የምትተክዙበት ጊዜ አይሁን። አባቶች ወደ ጎዳናው ውጡ  ኢትዮጵያውያንን እጅ ለእጅ አያይዙ፣ የሃይማኖት አባቶች ወደ ጎዳናው ውጡ፣ በክልል መሬት የተጣሉትን እና የፖለቲካ እሾህ የተዘራባቸው የግጭት ቀጠናዎችን ባዶ የተረት ተረት ሥራ መሆኑን አውጁ። እናቶች ቡና ከቤታችሁ አታፍሉ፣ አውራ ጎዳናው ዳር ውጡ፣ጉዝጉአዙን ጎዝጉዙት ወጣቶቹን ጥሩ የሰፈራችሁን ሰው ጥሩ እጅ ለእጅ አያይዙ። የኢትዮጵያ አምላክ ኢትዮጵያውያንን ሊታደግ ከበር ላይ ቆሟል።እንዳይገባ በር የዘጋበት ኢትዮጵያውያን እጅ በእጅ አለመያያዝ ነው።

በባሕር ማዶ ያላችሁ።በአገር ቤት ሰላም ከማውራታችሁ በፊት በዋሽንግተን ጎዳና የተገለማመጠ ካለ እጅ ለእጅ አያይዙ፣ አገር ቤት ለሚመጣ ፈተና ሁሉ አለሁልህ ለማለት የባሕር ማዶዎቹ በቅድምያ ሳትውሉ ሳታድሩ እጅ ለእጅ ተያያዙ። የኢትዮጵያ ትንሣኤ በር ላይ ነው።ትንሣኤዋን ለማየት የምትታለፈውን ትንሽ መራራ መዝለል ብቻ ይፈለጋል።ይህችን ትንሽ መራራ  ለመዝለል ኢትዮጵያውያን ከአገር ቤት እስከ ባሕር ማዶ ሳትተያዩ የምትግባቡ እና አንዱ አንዱን ሳይጠብቅ እጅ ለእጅ የምትያያዙ  መሆን ያስፈልጋል። ለእዚህ ደግሞ እናቶች፣ወጣቶች እና አባቶች በሙሉ የማንንም ትእዛዝ ሳትጠብቁ ኢትዮጵያውያንን  ለማያያዝ ራሳችሁ ኃላፊነት ወስዳችሁ ከሰፈራችሁ ጀምሩ።ከንፈር ሳይነቃነቅ ተግባቡ፣ልሳን ንግግር ሳያወጣ ተግብሩት።ኢትዮጵያውያን ሳታወሩ ተግባቡ እና እጅ ለእጅ ተያያዙ።የኢትዮጵያ ትንሣኤ በር ላይ ነው።ይህ ተራ እና ባዶ ምኞት አይደለም።እውነት ነው።ውጤቱ እያንዳንዱ ግለሰብ በሚያሳየው ፍሬ ይወሰናል።

ከንፈር ሳይነቃነቅ ልሳን ሳይጋራ፣
በዝምታ ድባብ በዝምታ ጎራ፣
ሳየወሩ ማውራት መልካም ባልንጀራ።

ድምፃዊው ጥላሁን ገሠሠ መልዕክት አለው።



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።

======== ልዩ ሪፖርታዥ ======== በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡  የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል? ግማደ መስቀሉ  ወደ  ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል...