Thursday, November 24, 2016

Breaking News: A heavy fight broke out between Ethiopian government and Patriotic Ginbot 7 forces.

Commander Mesafint Tigabu 


Abbay Media News

By Surafel Aerate

A heavy fight between Ethiopian government troops and Patriotic Ginbot 7 forces broke out in the outskirts of  Gonder. Abbay Media sources from the war zone confirmed that there have been very heavy fight going on between the two foes since yesterday. This is the first time that the Ethiopian army used its military Tanks and sophisticated machine guns against Patriotic Ginbot 7 forces.

Our sources who are participated in this fight told us that there are casualties from both sides. From Patriotic Ginbot 7 side, three of its division (Ganta) leaders have been killed and three other fighters surrendered on the battlefield. In the other hand, from the government side, more than Thirty government troops killed by patriotic forces. In addition, unknown numbers of government troops have surrendered to Patriotic Ginbot 7 forces.

During the fight, Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy ranking official, commander Mesafent Tegabu nicknamed Gebrye refused to surrender and killed himself on the battlefield. When he was asked to surrender, commander Tegabu claimed that he is the son of King Tewodros and he would rather kill himself instead of giving himself up to the fascist regime. After fierce fight with heavily armed with Tanks and machine guns government troops, commander Tegabu refused to give himself up and shot and killed himself.   

Source : Abbay Media News 
             

Monday, November 21, 2016

¨የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስትን ይመሩ ከነበሩ መካከል 5 አዛዦች በአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ተገደሉ።¨ የአግ7 ራድዮ Five state of emergency command post commanders are killed

ፎቶ አርበኞች ግንቦት 7 ድረ-ገፅ 


ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊቱን ወደ ኢትዮጵያ ማስገባቱን እና ገዢ መሬቶችን መቆጣጠሩን እየገለፀ ነው።የድርጅቱ ራድዮ ይህንኑ አስመልክቶ በፎቶ ግራፍ የተደገፈ ዘገባ አቅርቧል። የራድዮው ሙሉ ዘገባ ከእዚህ በታች እንዳለ ቀርቧል።
==================================
November 20, 2016
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
===========================
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ህዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም በቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይነብሪ በተባለው ቦታ ከመቀሌ የተላከ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይል ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ድል ተጐናፅፏል።

ይህ ከመቀሌ የተንቀሳቀሰው የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል ዋና ተልዕኮ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊትን እንቅስቃሴ ለመግታት ታስቦ ሲሆን እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በ56 መኪኖች አጓጉዞ በቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይነብሪ በተባለ ቦታ ቢያሰፍርም ለሀገራቸውና ህዝባቸው ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለመክፈል የማይሰስቱት የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በከፈቱት ድንገተኛ ማጥቃት 92 በመግደልና 65 በማቁሰል አንፀባራቂ ድል ማስመዝገባቸውን ከስፍራው የሚገኘው አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ባደረሰን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።
ፎቶ አርበኞች ግንቦት 7 ድረ-ገፅ 

ይህ በእንዲህ እንዳለም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እንቅስቃሴን ለመግታት የተንቀሳቀሰውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስትን ይመሩ ከነበሩ መካከል 5 አዛዦች የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል መቶ አለቃ ጣዕመ የሚባል እንደሚገኝበትም ታውቋል።

በተያያዘ ዜና የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ህዳር 8 ቀን 2009 ዓ.ም በቃፍቲያ ሁመራ ሩዋሳ አካባቢ ማይጐነጥ ልዩ ስሙ ማይቆማ በተባለው ቦታ ሰፍሮ ከሚገኘው የ24ኛ ክፍለ ጦር ጋር ባደረገው ውጊያ አንድ ብርጌድ ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ከማውደሙም በተጨማሪ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን ከስፍራው የደረሰን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን መረጃ ያመለክታል።

በዚሁ አካባቢ በተደረገው ውጊያ የወያኔው የ24ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጀግኖች የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ተስኖት እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።

በእለቱ በተደረገው ውጊያ 120 የወያኔ መከላከያ ሰራዊትን በመግደልና 80 በማቁሰል በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ከባድና ቀላል ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረካቸውንም ሪፖርተራችን ገልጿል።

በውጊያው እለት የቆሰሉ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ብዛት ቁጥር ስፍር የሌለው ከመሆኑ የተነሳ ሁመራ የሚገኘው ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁንና ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸውን ደግሞ ወደ ጐንደር ሆስፒታል በመላክ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ሰራዊት ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት ርምጃ የአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ እጅጉን ከመደሰቱም በተጨማሪ ከትግሉ ጐን ለመሰለፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት እየገለፁ እንደሚገኙም ታውቋል።

የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናትም በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን አገዛዙን ለመፋለም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጋር እንዳይገናኙ አካባቢውን በመውረር ህብረተሰቡ ከቤቱ ወጥቶ እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ ስራ ላይ ተጠምደው የሚገኙ ሲሆን፤የሞቱ የሰራዊቱ አባሎቻቸውንም ህዝቡ እንዳያይባቸው የራሳቸውን ሰዎች በመመልመል እንዲቀበሩ እያደረጉ መሆናቸውን ሪፖርተራችን አክሎ ገልጿል።

በደረሰባቸው የሰው ህይወትና የንብረት ኪሳራ እጅጉን የተደናገጡት የህወሀት አገዛዝ ባለስልጣናትም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይልና በ24ኛ ክፍለ ጦር ላይ ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የሚሰነዘረው ጥቃት ተጠናክሮ በመቀጠሉና ፋታ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ በአካባቢው የጦር ሄሊኮፕተሮችን በማሰማራት አሰሳና ቅኝት ሲያደርጉ እንደነበረ ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እስከአሁን ባደረጋቸው ውጊያዎችና ባስመዘገባቸው ድሎች በመደሰት በአካባቢው የሚገኙ የሚሊሸያ ታጣቂ ሀይሎች ከወንድሞቻችን ጋር ውጊያ አናደርግም በማለት በአገዛዙ ላይ እንዳመጹና ብዛት ያላቸው የሚሊሸያ አባላትም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጋር መሰለፋቸውን ከስፍራው የደረሰን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን መረጃ ያስረዳል።

ምንጭ - http://www.patriotg7.org/?p=1157 

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Friday, November 18, 2016

ጎዳናው ይገርማል (ግጥም ቪድዮ)

ጀግና ልጅ አትወልድም አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር
በበረከት በላይነህ



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, November 17, 2016

በኦስሎ በወቅታዊ የሀገራችን ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ልዩ ውይይት በኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ ኖርዌይ ተዘጋጀ

ካልተወያዩ ኢትዮጵያን በምኞት አይገነቧትም።ሃሳባችንን እናካፍል!
የሌሎችንም ሃሳብ እንስማ !

ተወያዩ! ዝም አትበሉ።የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል።ሁላችንም ሃሳቦች አሉን።ሃሳቦቻችንን ለሌሎች ማካፈል ካልቻልን ወይንም የሌሎች ሃሳቦችን መስማት ካልቻልን ነገ ምን አይነት ኢትዮጵያ እንድትኖረን እንፈልጋለን? ኢትዮጵያን በምኞት መገንባት አይቻልም ሃሳቦችን በማንሸራሸር የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ግን አንድ እርምጃ ወደፊት መሄድ ይቻላል።

 የትግራይ ነፃ ኣውጭ ግንባር (ሕወሓት) ወደ ኋላ በመጓዝ በዘመነ ደደቢት ላይ ይገኛል::ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ በህዋሃት መኮንኖች ስር ወድቃለች::ማሰር መግደል እያንዳንዱ መኮነን መብት ብቻ ሳይሆን የኣንድ ተራ ወታደርና ፖሊስ መብት ሆኗል:: በአንድ ወር ብቻ እስከ መቶ ሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ወደ ስር ተግዘዋል::በዘመነ ደደቢት ጊዜ እስር ቤቶች የተፈጥሮ ዋሻዎችና ሰው ሰራሽ ጉድጓዶች በነበሩበት ወቅት የእስር ቤቶች ኣዛዦች የነበሩት ኣሁንም መርማሪዎች የእስር ቤቶች ኣለቆች ናቸው:: በኢትዮጵያ ታሪክ ያልታየ እስር ቤቶችን በ እስርኞች እንደተሞሉ ማቃጠል ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ ሆኗል::

• ታዲያ በደረስንበት በዘመነ የተቋሚዎች ኣሰላለፍ ምን ይመስላል?
• በተለይ በነፃ የመደራጀት እድል ያላቸው በውጭ ኣገር የሚገኙ ተቃዋሚዎች ኣሰላለፍ ምን ይመስላል?
• በጣም ሊበረታታ የሚገበው በብሔራዊ ደረጃ ወይም በኣገር ኣቀፍ የተደራጁ ኣሉ
በርካታ ድርጅቶች በብሄራቸው ተደረጅተው የሚታገሉ ኣሉ::  የኦሮሞ ህዝብ በብሔር ተደራጅቷል::  ኣማራም  በብሔር መደራጀት ጀምሯል::

• በኣደረጃጀት ዙሪያ በርካታ ጠንክር ጠንከር ያሉ መተቻቸቶች ይታያሉ::ትችቶች ገንቢ ናቸው?
• የተቀዋሚው ኣደረጃጀት በቂ ነው?
• ራሳቸውንና ህዝቡን ለመከላከል በጎበዝ ኣለቃ ተደራጅተው እየታገሉ እንዳሉ እየተሰማ ነው።በቂ ትኩረትና ድጋፍ ኣግኝተዋል?  ካላገኙ ለምን? ሕዝብ በውጭ እና በአገር ቤት ያለው ምን እያደረገ ነው?

እነኝህን እና ተያያዥ ወቅታዊ የሀገራችን ጉዳዮች ዙርያ የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ በመጪው ቅዳሜ የጠረንጴዛ ዙርያ ውይይት አዘጋጅቷል።ውይይቱ በቪድዮ የሚዘጋጅ ሲሆን በውይይቱ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል በሙሉ መገኘት ይችላል።

የጠረንጴዛ ዙርያ ውይይት 

ኣዘጋጅ  =     የኢትዮጵያውያውያን የጋር መድረክ በኖርዌይ
                     አራት ተወያዮች ተዘጋጅተዋል::
                     ውይይቱ ለሁሉም ከፍት ነው:: ለተወያዮች ጥያቄ
                     ማቅረብ ኣስተያየት መስጠት ይቻላል::
ቀን =           በመጪው ቅዳሜ ህዳር 10፣2009 ዓም
                     (ኖቬምበር 19፣2016)  

ቦታ=            ባትሬት 
አድራሻ       Fredsbogveien 24 A, Oslo, Norway

ሰዓት =         እኩለ ቀን (12 am) ይጀመራል። 


ፀጋዬ እሸቱ እውነት 



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Tuesday, November 15, 2016

በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለፈው ወር ያደረጉት ዝግጅት (ቪድዮ) Ethiopians in Israel discussing on home politics


ቪድዮውን ተመልክተው ሲጨርሱ በእስራኤል ያሉ ኢትዮጵያውያን  በመጪዋ ኢትዮጵያ ላይ ስለሚኖራቸው ሚና እንዲያሰላስሉ ያደርጋል።



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com