Sunday, June 21, 2015

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን፣ሰንዓ ከተጠለፉ በመጪው ማክሰኞ ሰኔ 16 አንድ ዓመት ይሞላቸዋል። who is Ato Andargachew Tsige? አቶ አንዳርጋቸው ማን ናቸው?



Andargachew Tsege was born in Addis Ababa, Ethiopia on 9th of February 1955.  He is one of nine children.  He grew up in a household where it was a sanctuary to the down and out!  His mother who was a teacher by profession had great empathy for people in need and was always helping.  This is where we can say Andargachew’s life-long commitment to fight for the underdogs began!

His love for Ethiopia was greatly influenced by the stories his great grandmother use to recount to him when he was a young boy.  His grandmother who was born towards the end of Theodros’s reign and lived through Menelik’s and later Haileselassie’s reign had lots to tell to the impressionable young boy.

During his high school years in Teferi Mekonnen High School and later as an engineering student at Haile Selassie I University, he became very active in the student movement.

Following the Ethiopian revolution of 1974 when a military dictatorship (Derg) seized power he joined the Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP) and went underground like most of the Ethiopian youth in their struggle against the Marxist regime. During the Derg’s Red Terror campaign of 1974, his younger brother Amha Tsege was murdered by the security forces.  In 1979 he immigrated to the UK as a political refuge.

He studied Philosophy at what is now known as University of Greenwich doing his dissertation on the German philosopher Immanuel Kant in the early 1980s.  When Derg fell in 1991, he went back to Ethiopia to help the newly formed government of Meles Zenawi.  Within two years, he was disillusioned with the whole ethnic based politics and left the government.  He moved back to London and started writing articles that were critical of the regime and its divisive politics.

In 2005, he went back to Ethiopia to publish his bestseller book in Amharic which loosely translates to “Freedom fighter who does not know freedom” an analysis of the current state of Ethiopian politics.  Soon, with an invitation from then leader of Rainbow party Berhanu Nega, he went back to help the party in the ill-fated election of May 2005.  In June 2005, he was imprisoned and tortured during the crackdown by the government of Meles Zenawi after the election.  After his release, he came back to London where he was able to campaign against the regime by testifying at different government or international organization including the US congress and EU Human Rights committee as well as think tanks like Chatham house.  He became the principal spokesperson for the CUD party in exile and was instrumental in mobilizing the global Ethiopian diaspora for a worldwide campaign to secure the release of the CUD leaders and all prisoners of conscience.

In May 2008, he founded Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy with Berhanu Nega one of the exiled leaders of CUD. He was elected as Secretary General of Ginbot 7. He has inspired many especially the young by his selfless devotion and commitment to bring about change in Ethiopia.

Andargachew lived with his partner his 7 year old twins and 14 years old daughter in London.

In June 23, 2014 in the most extraordinary circumstances, he was once again imprisoned by Ethiopian regime.  While in transit in Yemen Sana’a airport, he was abducted and taken back to Ethiopia.

Source - http://freeandargachew.com 

Friday, June 12, 2015

ሰበር ዜና - ከእዚህ በፊት በሰጣቸው ትምህርቶቹ በርካታ ጥያቄዎች የተነሱበት በጋሻው ደሳለኝ ሉንድ፣ስዊድን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌላ ትልቅ ውዝግብ ፈጠረ።።''በጋሻው ስዊድን የገባው በአውሮፓ የምትገኘውን፣በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ አባቶች የምትመራውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማወክ ያለመ ተልኮ ይዞ ነው'' አውሮፓ የሚኖሩ አባቶች እና ምዕመናን።(የደብዳቤ እና የፎቶ ቅጅዎች ተያይዘዋል)


  • ወደ ሉንድ፣ስዊድን የገባበት ሰነድ በራሱ አወዛጋቢ ሆኗል፣
  • ሉንድ፣ስዊድን የሚገኘው ቴዎሎጂ ዩንቨርስቲ የግለሰቡን ወደ ስዊድን መምጣት እንደሚያውቅ ተደርጎ የተገለፀውን ደብዳቤ ሐሰት መሆኑ እየተነገረ ነው፣
  • ዩንቨርስቲው ስለጉዳዩ እንደማያውቅ ለማወቅ ተችሏል፣
  • በአውሮፓ የሚኖሩ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ አባቶች ስር የሚገኙ አጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የበጋሻውን አወዛጋቢ የሀገር ቤት ታሪክ የሚያውቁ አባቶች እና ምዕመናን በብርቱ እያስጠነቀቁ ነው፣
  •  ''ከሀገር ቤት አቡነ ማትያስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እና ቋሚ ሲኖዶስ እንዳስተምራችሁ ፍቃድ ሰጥተውኛል'' በጋሻው ለሉንድ፣ስዊድን ምዕመናን የነገራቸው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በበርካታ የቤተክርስቲያኒቱ ጉባኤያት ላይ ሁከት በመፍጠር፣በአደባባይ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶች በማጥላላት እና በአስተማራቸው ትምህርቶች አፅራረ ቤተ ክርስቲያን ይዘት ከሐዋሳ እስከ ጎንደር ከአዲስ አበባ እስከ ሐረር ባሉ አያሌ አጥብያ አብያተ ክርስቲያናት በሚገኙ  አባቶች ከመድረክ ላይ እንዳያስተምር በሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት፣የደብር አለቆች እና ምዕመናን የታገደው በጋሻው ደሳለኝ ስዊድን፣ሉንድ አንድ ሰንበት በተጭበረበረ መንገድ መድረክ በግድ ነጥቆ ማስተማሩ ምእመናንን በእጅጉ አስቆጥቷል።

በጋሻው መድረኩን በጉልበት ከነጠቀ በኃላ መድረክ ላይ ቆሞ 

ሉንድ፣ስዊድን ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሁለት ሳምንታት በፊት የግንቦት 21 የደብረ ምጥማቅ የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል ለማክበር ዝግጅት ይጀምራሉ።በእዚህ መሰረት ከስዊድን እና ኖርዌይ የሚገኙ አባቶች በአቡነ ኤልያስ ተመድበው ለአገልግሎት ይሄዳሉ።ጉባኤው ሲካሄድ ቀደም ብሎ በጋሻው በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ በማገልገል ላይ በሚገኘው ዲ/ን ያሬድ አማካይነት የግብዣ ደብዳቤ ተልኮለት ስዊድን ገብቶ ነበር።ሆኖም ግን ምእመኑን በመፍራት በዕለቱ በቦታው ዝር ሳይል ይቆያል።

በሳምንቱ ግን በቦታው የዶክትሬት ዲግሪውን በመስራት ላይ በሚገኘው እና ያለውን ትርፍ ጊዜ በሙሉ በቤተ ክርስቲያኒቱን በነፃ በቅዳሴ፣በማስተማር እና ምዕመናንን በመምከር የሚያገለግለው ቀሲስ መንግሥቱ በቦታው የዕለቱን ትምህርት ለመስጠት ሲዘጋጅ ከበጋሻው በኩል ትዕቢት በተሞላበት እና የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት ፈፅሞ በተፃረረ መልክ ካህኑን እላፊ ንግግሮችን ከመናገሩም በላይ መርሃ ግብሩን የሚመራው እና ቀደም ብሎ በጋሻውን ለማስመጣት ደብዳቤዎችን መላኩ የተነገረለት ዲ/ን ያሬድ የድምፅ መናገርያውን ከካህኑ ነጥቆ ለበጋሻው ሲሰጥ እና ቀሲስ መንግስቱ እና ምዕመናን ቤተ ክርስቲያኑን ጥለው እያለቀሱ ሲወጡ ተስተውሏል።ይህ ጉዳይ የበርካታ ምእመናንን ልብ ያሳዘነ ከመሆኑም በላይ ጉዳዩ በእዚህ ሳይቆም  ለቅዳሜ ሰኔ 6/2007 ዓም አሁንም በድጋሚ ምእመናንን የሚጠራ ፖስተር ተዘጋጅቶ እንዲሰራጭ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።



በሌላ በኩል ከእዚሁ ከሉንድ፣ስዊድን በዲያቆን ያሬድ አቀናባሪነት'' በጋሻው መጥቶ ያስተምራችሁ'' የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ ኖርዌይ እና ስዊድን ለሚገኙ አጥብያዎች የዲያቆን ያሬድ ምክትል መሆኑ በሚነገረው አቶ ሰለሞን በተባለ ግለሰብ የተፈረመ ደብዳቤ የተላከ መሆኑ እና የእዚሁ ደብዳቤ መላክ በስዊድንም ሆነ በኖርዌይ ባሉት አጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተቀባይነት ካለማግኘቱም በላይ ጉዳዩን የሰሙ ምዕመናን በሁለቱ ሃገራት ለሚገኙ የመንግስት የፀጥታ አካላት ማሳወቅ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ከፍተኛ ሁከትን ለመፍጠር ያለመ እና ከእዚህ በፊት በሀገር ቤት የተፈጠሩትን ችግሮች በቪድዮ አስደግፈን ማቅረብ ይገባናል ሲሉ ተደምጧል።በአውሮፓ ሕግ መሰረት የእዚህ አይነት ሪፖርት የቀረበበት ግለሰብ በመላው አውሮፓ እስከመቸውም ድረስ እንዳይገባ የመታገድ ዕድል ሊገጥመው ከመቻሉም በላይ በሌሎች ሃገራትም ተመሳሳይ ዕጣ ሊደርሰው ይችላል ሲሉ የሕግ ባለሙያዎች ይገልፃሉ።ይህ በእንዲህ እንዳለ በእዚሁ ሉንድ አጥብያ ያሉት በጋሻውን ያስመጡ ግለሰቦች አጥብያውን በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ካሉ አባቶች የመነጠል እና ሌላ ፈቃድ አውጥቶ ምዕመናንን የመክፈል ሥራ ለመስራት ከቀደመ ጀምሮ የያዙት ዕቅድ መሆኑን መረጃዎቹ ያመላክታሉ።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በጋሻው በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ ሰኔ 6/2006 ዓም የተፈረመ እና በቋሚ ሲኖዶስ የፀደቀ ነው ብሎ እያሳየ ያለው ደብዳቤ ትክከለኛነት መጣራት ያለበት ከመሆኑም በላይ ደብዳቤው ትክክል  ሆኖም ቢሆን ይህ ጉዳይ በሀገር ቤት ባሉ ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ጥያቄ  እንደሚያስነሳ ሳይታለም የተፈታ ነው።

ከእዚህ በተጨማሪ በሉንድ፣ስዊድን የሚገኘው የቴዎሎጂ ትምህርት ዩንቨርሲቲ የበጋሻውን መምጣት እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስር የሚደረገውን ጉባኤ እንደሚያውቅ ተደርጎ በስዊድንኛ የተፃፈው ወደ ስዊድን እንዲገባ ቪዛ የተጠየቀበት ደብዳቤ ላይ የተገለፀ ሲሆን ዩንቨርስቲው ምንም የሚያውቀው ነገር የሌለ መሆኑን እና ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳላደረገ ለማወቅ ተችሏል።


ባጠቃላይ በሀገር ቤት በበርካታ ትምህርቶቹ ከፍተኛ ተቃውሞ የተነሳበት እና ከብዙ መድረኮች የሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት፣የደብር አለቆች፣የሰንበት ትምህርት ቤቶች እና ምዕመናን ዘንድ የተነቀፈው በጋሻው በሉንድ የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት ባልጠበቀ እና መናገርያውን በመንጠቅ በተደረገ ሸፍጥ ለማስተማር መድረክ ላይ መውጣቱ አንድ ሊባል የሚገባ እና ሕግ እና ስርዓት ባለበት አውሮፓ ውስጥ ይህ መፈፀሙ እጅግ አሳፋሪ መሆኑን ምዕመናን በቁጭት ይገልፃሉ።

በመጨረሻም የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ግራና ቀኝን የመመልከት እና የዛሬ የህዝብ መሰብሰብን ብቻ ሳይሆን የነገ የምዕመናንን መድረሻ የማገናዘብ ፀጋው የተሰጣቸው በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ሲኖዶስ የሚገኙ አባቶችን በበጋሻው ''ሀገር ቤት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ እንዳስተምር ደብዳቤ ሰጥተውኛል'' የሚል መነሻ ብቻ በመያዝ ስለ መምህሩ በቂ መረጃ ሳይዙ ወደ ማናቸውም አይነት ውሳኔ እንዳይሄዱ ምዕመናን ተማፅኖ እያቀረቡ ነው። የእዚህ አይነቱ አወዛጋቢ እና በበርካታ ትምህርቶቹ ከፍተኛ ወቀሳ የደረሰበትን ግለሰብ መድረክ መስጠት  በአንፃራዊ ሰላም የምትገኘውን በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት እና ምዕመናንን  አንድነት እና ፍቅር እንዳያናጋ ከፍተኛ ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚገባቸው ለብፁዓን አባቶች በስልክ እና በአካል  ምዕመናን እየገለፁ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ሰኔ 6/2007 ዓም (ጁን 13/2015)

Wednesday, June 10, 2015

ጣልያን እጥፍ ሲል እንደ ሮማ መንገዶች ነው። ይህ ጣልያን ነው (የጉዳያችን ምጥን)


 ከእዚህ በላይ ያለው ፎቶ በአንድ ወቅት ጠላት የነበሩ ሀገሮች መሪዎች ፕሬዝዳንት ኦባማ እና  የጀርመን ቻንስለር አንግሌ መራክልከሶስት ቀናት በፊት በቡድን 7 ስብሰባ ወቅት በእረፍት ሰዓት  ሲነጋገሩ ያሳያል።
  Photo -huffingtonpost.co.uk 

የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማተዎ ረንዚ ( Matteo Renzi) በሶስት ቀናት ልዩነት ውስጥ ብዙ ሥራ እንደሚሰሩ አስመሰከሩ።በሩስያ ላይ እቀባ ካደረጉት ከቡድን ሰባት አባላት ጋር ስብሰባ ተቀምጠው ሩስያ ስትታማ እና ምናልባትም ሲያሟት ከርመው  ዛሬ ዘወር ብለው የሩስያውን ፕሬዝዳንት ፑቲንን  በሀገራቸው እያስተናገዱ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፑቲን ጋር በጋራ በጣልያኗ ከተማ ሚላኖ በሰጡት መግለጫ ''ሩስያ ለዓለም ጠቃሚ ሀገር መሆኗን እና ሽብርተኝነትን ጨምሮ ብዙ የጋራ አጀንዳ ከአውሮፓ ጋር ያላት መሆኑን''ሲያብራሩ ፑቲን እራሳቸውን ወደላይ እና ወደታች እያደረጉ አድንቀውላቸዋል።ይህ ጣልያን ነው።ጣልያን እጥፍ ሲል እንደ ሮማ መንገዶች ነው።ለነገሩ በሩስያ ላይ የተደረገው እቀባ ለአውሮፓ ብዙም እንዳልተመቸው በብርቱ ይታመናል።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ሰኔ 3/2007 ዓም (ጁን 10/2015)

Monday, June 8, 2015

የሰኔ አንድ 1997 ዓም ትዝታዬ የቢቢሲ ዘጋቢ ድምፅ ጆሮዬ ላይ ይጮሃል (የጉዳያችን ማስታወሻ)

ፎቶ ''ዘጋርድያን'' ሰኔ 2/1997 ዓም Photo - The Guardian June 9/2005
=======================================
''የፀጥታ ኃይሎቹ በእውነተኛ ጥይት የተሰላፍዎቹን አናት በጥይት ሲመቱ ተመልክቻለሁ'' የቢቢሲ ዘጋቢ ከአዲስ አበባ
ሰኔ 1/1997 ዓም ያስተላለፈው
=======================================
ይህ ቀን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃዘን ጨለማ ከገባባቸው ቀናት ውስጥ አንዱ ነበር።በአዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ድምፁ የተሰረቀበት ሕዝብ ውሸት በቃኝ! ብሎ ተነሳ።የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪዎች ሥራ አቆሙ።የ''አጋዚ ጦር''  ማንኛውንም ሰው በማንኛውም ነገር የማጥቃት መብት ተሰጠው።ምናልባት የእዚህ አይነት መብት ለአንድ የታጠቀ ኃይል ሲሰጠው በጣልያን ወረራ ወቅት ግራዚያኒ በየካቲት 12/1929 ዓም በአዲስ አበባ ላይ ካወጀው እልቂት እና ከቀይ ሽብር ወዲህ ይህኛው በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያ ሳይሆን አይቀርም።

የቢቢሲ ዘጋቢ ከአዲስ አበባ  የዘገበው ዘገባ እስካሁን ጆሮዬ ላይ ይጮሃል።(ድምፁን ያገኛችሁ አካፍሉን) ይዘቱ እንዲህ የሚል ነበር -
ከለንደን ትጠይቀዋለች - ''የፀጥታ ኃይሎቹ የያዙት አስለቃሽ ጭስ ወይንም የጎማ (ትክክለኛ ጥይት ያልሆነ) ነው?''
ከአዲስ አበባ የቢቢሲ ዘጋቢ (ካልተሳሳትኩ ቀድሞ ከአስመራ ይዘግብ የነበረው አሌክስ ላስት ይመስለኛል) እንዲህ መለሰላት  - ''ፈፅሞ ፈፅሞ የያዙት live bulet (እውነተኛ ጥይት ነው የሚገርምሽ ሲተኩሱ ሌላ የሰውነት ክፍል ላይ እንዳያርፍ ተሰላፊዎቹ ጭንቅላት ላይ ነበር የሚያነጣጥሩት።''
ከለንደን ጠየቀች - ''ጭንቅላት ላይ ነው የምትለኝ?''
ከአዲስ አበባ መለሰ - '' አዎን! አዎን እያየሁ ያለሁት በትክክል ኢላማቸው  የተሰላፊዎቹ ጭንቅላት ነው።የሚያስደነግጥ ነው''
ከእዚህ በታች ያለው ፎቶ እና ፅሁፍ ደግሞ ''ዘ ጋርድያን'' የተሰኘው ጋዜጣ በማግሥቱ ሰኔ 2/1997 ዓም ካወጣው ፅሁፍ የተወሰደ ነው
''...በዋና ከተማዋ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢ እንደተመለከተው ከ11 አስከሬን ውስጥ 4ቱ ጭንቅላታቸው ላይ የተመቱ ናቸው።...መንግስት እንደሚለው ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለማስቆም ማናቸውንም መንገድ እንዲጠቀም (ባዶ እጁን ያለ ተሰላፊ በጥይት እራስ እራስ ማለትን ጨምሮ መሆኑን እዚህ ላይ ልብ በሉ) ተፈቅዶለታል።የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ የታክሲ እና የግል አውቶብስ ሹፌሮች ለፍርድ ይቀርባሉ''  ''ዘጋርድያን'' ሰኔ 2/1997 ዓም ያወጣው ዘገባ
ቀጥታ የእንግሊዝኛ ቅጂው እንዲህ የነበባል -
 ''...At one hospital in the capital, four of the 11 bodies seen by an Associated Press reporter had gunshot wounds to the head.....The government said police were allowed to use any means necessary to quell disturbances, and that taxi and private bus drivers who did not work faced criminal charges.'' The guardian June 9,2005

''ዘጋርድያን'' ከላይ  የምትመለከቱት ፎቶ ስር እንዲህ የሚል ፅሁፍ በወቅቱ አስነብቦ ነበር -
'' በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች በተከፈተባቸው ተኩስ ለቆሰሉ እና ሕይወታቸው ላለፈ  ኢትዮጵያውያን የሟች ዘመዶች የአስከሬን ሳጥኖችን ሲጠብቁ ምንሊክ ሆስፒታል አዲስ አበባ ''

''A relative waits next to empty coffins at the morgue in Menelik hospital in Addis Ababa for news of those injured or missing after Ethiopian security forces opened fire yesterday''

 ''በእውነተኛ ጥይት እያነጣጠሩ የተሰላፊዎችን እራስ ነው የሚመቱት የሚለው'' ዘገባ ግን ብዙ ጥያቄ ያስነሳል።የአጋዚ ሰራዊት ህዝብን እንደ ጠላት እንዴት የሚመለከት ሆነ።በየትኛውም ሀገር ያለ የፀጥታ ፖሊስ ሰልፉን ለመበተን የአስለቃሽ ጭስ ወይንም የጎማ ጥይት የተቀማል እንጂ የጥይት ውርጅብኝ ያውም አናት ላይ።እስካሁን ጆሮዬ ላይ አለች።''ወታደሮቹ አናት ላይ እያነጣጠሩ ነበር የሚተኩሱት''

በነገራችን ላይ የሰኔ አንዱን በሰልፈኞቹ ላይ የተከፈተውን ተኩስ ያስቆመው የበላይ ትዕዛዝ ወይንም የተሰላፊው ወደኃላ ማፈግፈግ አይደለም።ወደ እኩለ ቀን አካባቢ ከየት መጣ ያልተባለ እጅግ ኃይለኛ ውሽንፍር እና ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ በከባዱ መዝነብ ጀመረ።ንፋሱ የአንዳንድ ቤቶችን ጣርያ ከመገንተሉም በላይ የዝናቡ የጎንዮሽ መዝነብ ሰልፈኛውም እንዳይሰለፍ ፖሊሶቹም እንዳይተኩሱ አስቆማቸው።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ሰኔ 1፣2007 ዓም (ጁን 8/2015)

Wednesday, June 3, 2015

ጥንታዊ በግዕዝ የተፃፉ የብራና መፃሕፍትን ጨምሮ በርካታ ጥንታዊ መፃህፍት በሶርያ በረሃ በ''አይኤስ ኤስ'' ከመቃጠል ተረፉ (ቪድዮ)

ከሶርያ ዋና ከተማ ከደማስቆ ሰሜን  200 ኪሜትር እርቀት የምትገኘው የምድረ በዳ ከተማ በግዕዝ የተፃፉ ጥንታዊ የብራና ፅሁፎችን ጨምሮ  በግመል እና አህያ ተጭነው ለመትረፍ ቻሉ።በፊልሙ 3 ደቂቃ ከ22 ሰከንድ ጀምሮ ከሚታዩት መፃፍት ውስጥ በግዕዝ የተፃፈ አነስተኛ መፅሐፍ ይታያል።
የፈረንሳይ ቴሌቭዥን ''ፍራንስ 24'' ትናንት ግንቦት 25/2007 ዓም በለቀቀው ቪድዮ ቄስ ናጅብ ሚካኤል የተሰኙ አባት ቅርሶቹን ዲጂታል ፎቶ በማንሳት፣እራሳቸው በአህያ እና በግመል በማመላለስ እንዲሁም በስደተኛው ሕዝብ ሻንጣ ውስጥ በመጨመር መፃህፍቱ ለትውልድ እንዲተርፉ አድርገዋል።የግዕዝ መፅሐፉ መታየት ግን  ጥንት አባቶቻችን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ያልረገጡት መሬት እንዳልነበር ያሳያል።


የ''ፍራንስ 24'' ቴሌቭዥን  ቪድዮ ከእዚህ በታች ይመለከቱ   -



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG