ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, June 8, 2015

የሰኔ አንድ 1997 ዓም ትዝታዬ የቢቢሲ ዘጋቢ ድምፅ ጆሮዬ ላይ ይጮሃል (የጉዳያችን ማስታወሻ)

ፎቶ ''ዘጋርድያን'' ሰኔ 2/1997 ዓም Photo - The Guardian June 9/2005
=======================================
''የፀጥታ ኃይሎቹ በእውነተኛ ጥይት የተሰላፍዎቹን አናት በጥይት ሲመቱ ተመልክቻለሁ'' የቢቢሲ ዘጋቢ ከአዲስ አበባ
ሰኔ 1/1997 ዓም ያስተላለፈው
=======================================
ይህ ቀን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃዘን ጨለማ ከገባባቸው ቀናት ውስጥ አንዱ ነበር።በአዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ድምፁ የተሰረቀበት ሕዝብ ውሸት በቃኝ! ብሎ ተነሳ።የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪዎች ሥራ አቆሙ።የ''አጋዚ ጦር''  ማንኛውንም ሰው በማንኛውም ነገር የማጥቃት መብት ተሰጠው።ምናልባት የእዚህ አይነት መብት ለአንድ የታጠቀ ኃይል ሲሰጠው በጣልያን ወረራ ወቅት ግራዚያኒ በየካቲት 12/1929 ዓም በአዲስ አበባ ላይ ካወጀው እልቂት እና ከቀይ ሽብር ወዲህ ይህኛው በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያ ሳይሆን አይቀርም።

የቢቢሲ ዘጋቢ ከአዲስ አበባ  የዘገበው ዘገባ እስካሁን ጆሮዬ ላይ ይጮሃል።(ድምፁን ያገኛችሁ አካፍሉን) ይዘቱ እንዲህ የሚል ነበር -
ከለንደን ትጠይቀዋለች - ''የፀጥታ ኃይሎቹ የያዙት አስለቃሽ ጭስ ወይንም የጎማ (ትክክለኛ ጥይት ያልሆነ) ነው?''
ከአዲስ አበባ የቢቢሲ ዘጋቢ (ካልተሳሳትኩ ቀድሞ ከአስመራ ይዘግብ የነበረው አሌክስ ላስት ይመስለኛል) እንዲህ መለሰላት  - ''ፈፅሞ ፈፅሞ የያዙት live bulet (እውነተኛ ጥይት ነው የሚገርምሽ ሲተኩሱ ሌላ የሰውነት ክፍል ላይ እንዳያርፍ ተሰላፊዎቹ ጭንቅላት ላይ ነበር የሚያነጣጥሩት።''
ከለንደን ጠየቀች - ''ጭንቅላት ላይ ነው የምትለኝ?''
ከአዲስ አበባ መለሰ - '' አዎን! አዎን እያየሁ ያለሁት በትክክል ኢላማቸው  የተሰላፊዎቹ ጭንቅላት ነው።የሚያስደነግጥ ነው''
ከእዚህ በታች ያለው ፎቶ እና ፅሁፍ ደግሞ ''ዘ ጋርድያን'' የተሰኘው ጋዜጣ በማግሥቱ ሰኔ 2/1997 ዓም ካወጣው ፅሁፍ የተወሰደ ነው
''...በዋና ከተማዋ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢ እንደተመለከተው ከ11 አስከሬን ውስጥ 4ቱ ጭንቅላታቸው ላይ የተመቱ ናቸው።...መንግስት እንደሚለው ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለማስቆም ማናቸውንም መንገድ እንዲጠቀም (ባዶ እጁን ያለ ተሰላፊ በጥይት እራስ እራስ ማለትን ጨምሮ መሆኑን እዚህ ላይ ልብ በሉ) ተፈቅዶለታል።የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ የታክሲ እና የግል አውቶብስ ሹፌሮች ለፍርድ ይቀርባሉ''  ''ዘጋርድያን'' ሰኔ 2/1997 ዓም ያወጣው ዘገባ
ቀጥታ የእንግሊዝኛ ቅጂው እንዲህ የነበባል -
 ''...At one hospital in the capital, four of the 11 bodies seen by an Associated Press reporter had gunshot wounds to the head.....The government said police were allowed to use any means necessary to quell disturbances, and that taxi and private bus drivers who did not work faced criminal charges.'' The guardian June 9,2005

''ዘጋርድያን'' ከላይ  የምትመለከቱት ፎቶ ስር እንዲህ የሚል ፅሁፍ በወቅቱ አስነብቦ ነበር -
'' በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች በተከፈተባቸው ተኩስ ለቆሰሉ እና ሕይወታቸው ላለፈ  ኢትዮጵያውያን የሟች ዘመዶች የአስከሬን ሳጥኖችን ሲጠብቁ ምንሊክ ሆስፒታል አዲስ አበባ ''

''A relative waits next to empty coffins at the morgue in Menelik hospital in Addis Ababa for news of those injured or missing after Ethiopian security forces opened fire yesterday''

 ''በእውነተኛ ጥይት እያነጣጠሩ የተሰላፊዎችን እራስ ነው የሚመቱት የሚለው'' ዘገባ ግን ብዙ ጥያቄ ያስነሳል።የአጋዚ ሰራዊት ህዝብን እንደ ጠላት እንዴት የሚመለከት ሆነ።በየትኛውም ሀገር ያለ የፀጥታ ፖሊስ ሰልፉን ለመበተን የአስለቃሽ ጭስ ወይንም የጎማ ጥይት የተቀማል እንጂ የጥይት ውርጅብኝ ያውም አናት ላይ።እስካሁን ጆሮዬ ላይ አለች።''ወታደሮቹ አናት ላይ እያነጣጠሩ ነበር የሚተኩሱት''

በነገራችን ላይ የሰኔ አንዱን በሰልፈኞቹ ላይ የተከፈተውን ተኩስ ያስቆመው የበላይ ትዕዛዝ ወይንም የተሰላፊው ወደኃላ ማፈግፈግ አይደለም።ወደ እኩለ ቀን አካባቢ ከየት መጣ ያልተባለ እጅግ ኃይለኛ ውሽንፍር እና ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ በከባዱ መዝነብ ጀመረ።ንፋሱ የአንዳንድ ቤቶችን ጣርያ ከመገንተሉም በላይ የዝናቡ የጎንዮሽ መዝነብ ሰልፈኛውም እንዳይሰለፍ ፖሊሶቹም እንዳይተኩሱ አስቆማቸው።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ሰኔ 1፣2007 ዓም (ጁን 8/2015)

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...