Wednesday, February 18, 2015

የየካቲት 12 አርበኞቻችን እና ሰማዕታቱ


ገነተ ልዑል ቤተ መንግስት 

በእዚህ ፅሁፍ ስር የሚከተሉትን ርዕሶች ያገኛሉ 
  • አብርሃም ደቦጭ፣ሞገስ አስገዶም እና ስምዖን አደፍርስ እነማን ናቸው?
  • 'እልል! በሉ' ልዕልት ተወለደች፣
  • የካቲት 12፣1929 ዓም ደም እንደ ጎርፍ፣
  • ሞግስ አስገዶም፣አብርሃም ደቦጭ እና ስምዖን አደፍርስ ፍቅር እስከ መቃብር፣
ጉዳያችን / Gudayachn
የካቲት 12/2008 ዓም (ፈብሯሪ 18/2015 ዓም)

ታሪክ ምን ያስተምረናል?


የካቲት 12 /1929 ዓም አዲስ አበባ ሰላሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎችዋ አንዲት ጀንበር ሰማአትነት የተቀበሉባት ቀን ነበረች። ይህ ታሪክ አስተማሪነቱ ዘርፈ ብዙ ነው።የሀገራችን ፖለቲካ የየካቲት 12 አይነት ታሪኮችን ትውልዱ በማስተማር በተለይ ከታሪክ አንፃር ብዙ ቁም ነገር ሊሰራበት ይገባል ለመሆኑ ዛሬ ስማንያ አራት ዓመት አዲስ አበባ ምን ሆነች? ብዙዎቻች ታሪኩን የምናውቀው የሚመስለን ግን አውቀነውም ቁምነገሩን እና አንደምታውን ችላ ያልነው ጥቂቶች አይደለንም። 
የዛሬ ሰማንያ አራት ዓመት አብርሃም፣ሞገስ እ ስምዖን በግራዝያን ላይ ባቀናበሩት ቦንብ አደጋ (ጣልያን አሸባሪ ብሏቸው የነበረ መሆኑን ሳንረሳ) የጣሉበት እና አዲስ አበባ ደም ጎርፍ የታጠበችበት መከራ ቀን፣የካቲት 12/1929

አብርሃም ደቦጭ፣ሞገስ አስገዶም እና ስምዖን አደፍርስ እነማን ናቸው?


 አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1936 (1929 ዓም )  ዓለም ፖለቲካ ብዙ አዳዲስ ክስተቶች የታዩበት ነበር።

- የጣልያኑ ፋሺሽት መሪ ሞሶሎኒ  ሮማ 'ኤምፓየር' አዲስ መሬት   አዲስ አበባን መያዙን  ያሳወቀበት፣ ቀደም    ብለው ተግባሩን  በስውር ሲደግፉ የነበሩ ሀገሮች ማንነታቸው የለየበት፣
 - ብሪታንያ ዜና አገልግሎት' ቢቢሲ' የመጀመርያ ቴሌቪዥን ፕሮግራሙን  የጀመረበት፣ 
 - አሜሪካው ፕሬዝዳንት  ሩዝቬልት ሁለተኛ ጊዜ የተመረጡበት
 - ጃፓን ባህር ኃይል ቻይናን ሻንጋይ ክፍለ ሀገር የወረረበት  እ ባጠቃላይ ጊዜው ዓለም ወደ ሁለተኛው ታላቁ ጦርነት ለመግባት አራት አመታት ብቻ ቀርቷት የምትታትርበት ጊዜ ነበር።

አብርሃም ደቦጭ እ ሞገስ አስገዶም ሐማሴን አና አካለጉዛይ (አሁኗ ኤርትራ)ተነስተው በፋሺሽት እጅ የወደቀችው የሀገራቸውን ኢትዮጵያ አርበኞች ሊቀላቀሉ መጡ።
ከለበሱት ልብስ ውስጥ ኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አጥፈው ይዘዋል።ህልማቸው፣ሳጋቸውን እየተናነቀ የሚይዛቸው ሀገራቸው መከራ እረፍት ነሳቸው።


በወቅቱ ከነበሩት ትምህርት ቤቶች ጣልያንኛ ተምረው ስለነበር ቅኝ ግዛት ችግርን ሀገራቸው ኢትዮጵያ ላይ የሚያመጣውን አንደምታ ጊዜው ፖለቲካ ጋር አዛምደው መረዳታቸው ሌላው የእግር ውስጥ እሳት ነበርእዚህ ጊዜ ነበር እንደነሱ በሀገሩ ጉዳይ ውስጡ ይንተከተክ የነበረውን ስምዖን አደፍርስን  ያገኙት።

ስምዖን አደፍርስ ''በመናደድ ብቻ መቆም የለብንም  ወሳኝ የሆነ ሥራ መስራት አለብን ፋሽሽትን ደሞ ትጥቅ ትግል በቀር ምንም ሌላ መንገድ የሚዋጋው  የለም'' ይላቸው ነበር። ስምዖን አደፍርስ ገና የከተማ መልክ አየያዘች በነበረችው አዲስ አበባ ውስጥ ጅቡቲ ይኖር ከነበረው ወንድሙ በተላከለት ታክሲ  ሥራ ላይ ነበር። ስራው ላይ አያሌ ፋሺሽት ጣልያኖች ግፍ በደል እ  ሃገሩ የወደፊት እጣ ሲያስበው ንዴት ፣ውርደት አልገዛም ባይነት አንድ ላይ ተደባልቀው ውስጡን አናውጠውታል። ይህን ስሜት ይዞ ነበር ሌሎቹ ሀገራቸው  ኢትዮጵያ ፍቅር ያንገበገባቸውን ሁለቱን ወጣቶች አብርሃም ደቦጭ  ሞገስ አስገዶምን ያገኛቸው።

እልል! በሉ ልዕልት ተወለደች

አብርሃም፣ሞገስና ስምዖን አዚህ ሃሳብ ላይ ሳሉ ነበር ሞሶሎን ኢትዮጵያ ሹመኛ ግራዝያን'' ልእልት ተወለደች ተሰብሰቡቸርነቴን ተመልከቱ ላብላችሁ፣ላጠጣችሁ''ብሎ አሁኑ ስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ የያኔው አፄ ኃይለስላሴ ገነተ ልዑል ቤተመንግስት አዲስ አበባን ሕዝብ የጠራው። ይህ አጋጣሚ እነ አብርሃም ታላቅ አጋጣሚ ሆነ። ድግሱ ላይ ንግግር እንደሚያደርግ  የሚጠበቀው ግራዝያን ላይ የእጅ ቦንብ ወርውረው መግደል የሚል አቅድ አዘጋጁ።እዚህ ሃሳብ ደግሞ እጅ ቦንብ አጠቃቀም መማር ያስፈልጋል።ስምዖን ደጃዝማች አፈወርቅ ወታደሮች በድብቅ አንዲያስተምሯቸው ሁኔታውን አመቻቸ። በየቀኑ ወደ ስፍራው አዲስ አበባ ውጭ ከሁለት ሰዓት በላይ በታክሲው  እየወሰደ አስተማራቸው  ቀኑ ደረሰ።በአቅዳቸው መሰረት ሞገስ እ አብርሃም ግራዝያንን ቦንብ ገደሉ በሁዋላ አሁኑ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስትያን አጥር በኩል ይዘሉና ቆሞ  የሚጠብቃቸው ስምዖን ታክሲ ውስጥ ገብተው አዲስ አበባ መውጣት ቀጥለውም ሰሜን ሸዋ ላይ በውጊያ ላይ ካለው ራስ አበበ አረጋይ አርበኛ  ጦር ጋር መቀላቀል እ መዋጋት የሚል  ታላቁ አቅድ ብለው መከወን ተግባራቸው ሊሆን' ቃል ለምድር ለሰማይ 'መሀላቸው  ነበር።

የካቲት 12፣1929 ዓም ደም እንደ ጎርፍ

የካቲት ከገባ ገና አስራ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።የ አዲስ አበባ አየር ደመናማ ነበር። የተለመደው በልግ ዝናብ ሊመጣ ዳር ዳር የሚል ይመስላል። አዲስ አበባ መንገዶች ጣልያን ወታደሮች ይታመሳል። ሰሜን ሸዋ ላይ የሚዋጋው አንዳንዴም አዲስ አበባ መግብያ በር ደረሰ እየተባለ የሚወራለት  አርበኛው ራስ አበበ አረጋይ ሰራዊት ጠጅ ቤቱ በ ቅኔ አዘል ግጥም ይሞገሳል። ቅኔው የገባቸው ባንዳዎችም አዝማሪውን እየጠቆሙ ፍዳውን ያሳዩታል። አዝማሪው ገና አለ ገና በሚል መልክ ውግያው ይቀጥላል የሚል ቃና ያለው ግጥም  ያንቆረቁራል-

 '' የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ፣
  ልጅሽን አሞራ እንጂ አይቀብረውም ዘመድ''

እየተባለ ሴት ወንዱ ውጊያ የተዘጋጀበት አርበኛ ሆኖ መሞት የተናፈቀበት  ጊዜ ነበር። ስድስት ኪሎ የያኔው ቤተመንግስት አሁኑ ዩንቨርስቲ አዲስ አበባ በግድም በውድም በተሰበሰቡ ባብዛኛው ሴቶች ሕፃናት ተሞላ። እብሪት የተሞላበት ግራዝያኒ ንግግር ተጀመረ። በንቀት ያየው ሕዝብ ላይ ስለ ''ታላቂቱ ጣልያን'' መደስኮር ጀመረ። ግን ብዙ አልቆየም አብርሃም እ ሞገስ ሕዝቡን ጥሰው ከፊቱ ደረሱ ሰባት ቦንቦችን አከታትለው ወረወሩበት፣ግራዝያን ቆሰለ፣ አየር ኃይሉ ኃላፊ ተገደለ። አብርሃም እ ሞገስ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስትያን በኩል ባለው ቤተመንግስቱ ጋራ  አጥር ዘለው ወጡ እ ታክሲ ይዞ ወደሚጠብቃቸው ስምዖን ገሰገሱ፣ ስምዖን በታክሲ ወጣቶቹን ይዞ ነጎደ፣ እንጦጦ ተራራ ላይ ውጥተው አዲስ አበባን ቁልቁል አይዋት፣ ግራዝያን በቆሰለበት ሆኖ አዋጅ አውጆ ለካ አዲስ አበባ ወንድ ሴት ሕፃን አዋቂ ሳይባል ጥይት፣በ አካፋ እ ዶማ በተገኘው ሁሉ መፈጀት ተጀምሯል።

ሶስቱ ወጣቶች ተቃቅፈው ተላቀሱ።ጊዜው እስኪመሽ ጠበቁ እ ስምዖን ወደ ደብረሊባኖስ ይዟቸው ነጎደ።ለ ሰሜን ሸዋ ራስ አበበ አረጋይ ቅርብ የሆነችው -ደብረሊባኖስ አመቺ መስመር እንደሆነች ሁሉም አምነውበታል። ስምዖን ተልኮውን ፈፅሞ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ። አብርሃም ሞገስ ራስ አበበ አረጋይ ጦር ጋር ተቀላቀሉ።

የካቲት አስራ ሁለት ቀን አዲስ አበባ ብቻ ሰላሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎችዋ ሰማአትነት ተቀብለዋል። ብዙ የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለዋል። ግድያው በመንገድ ላይ የተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ ሲሆን ለመግደል  የሚፈለገው መስፈርት ኢትዮጵያው መሆኑ ብቻ ነበር።



አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ የሚገኘው የካቲት 12 የሰማዕታት ሃውልት

ሞግስ አስገዶም፣አብርሃም ደቦጭ እና ስምዖን አደፍርስ ፍቅር እስከ መቃብር 

ስምዖን አብርሃም እ ሞገስን ደብረሊባኖስ ወደ ሰሜን ሸዋ መንገድ ከሚያውቃቸው አርበኞች ጋር አገናኝቶ ተመለሰ።ብዙም አልቆየ ፋሽስቱ ጥቁር ለባሾች ተይዞ ብዙ መከራ እና ስቃይ ተገደለ። የታሪክ ምሁራን እንዳስቀመጡት ስምዖን እጁም ሆነ እግሩ ጥፍር በጉጠት እየተነቀለ ጣቶቹን እየሰባበሩ አሰቃይተው ገደሉት።

አብርሃም ደቦጭ እ ሞገስ አስገዶም 

አብርሃም ደቦጭ ሞገስ አስገዶም ራስ አበበ አረጋይ አርበኞች ጦር ጋር ከተቀላቀሉ በኃላ ራስ አበበ አረጋይ ልዩ እንክብካቤ እንዲያገኙ አደረጉ።ቆይተው ግን የነበራቸውን ትምርት ደረጃ በመረዳት ሀገር ውጭ ወጥተው ሀገራቸው ቢሰሩ ይጠቅማሉ ብለው በማሰብ ስንቅ እ ገንዘብ ጋር ወደ ሱዳን እንዲሄዱ መከሯቸው። ሆኖም  ግን ጉዞአቸው ላይ ሱዳን ሊገቡ ትንሽ ሲቀራቸው  ፎቶዋቸው ገጠር ባሉ ፋሺሽት ወታደሮች ሁሉ ተናኝቶ ነበርና ፋሺሽቶች  ተይዘው በስቅላት ሰማዕት ሆኑ።በኃላ ግን አፄ ኃይለሰላሴ ሱዳን በኩል ጣልያንን እንግሊዝ ሰራዊት ጋር ሆነው ድል ሲያደርጉ አብርሃም እ  የሞገስ አስከሬን ተቆፍሮ ወጥቶ አሁን አዲስ አበባ በሚገኘው ቅድስት ስላሴ አርበኞች ሃውልት ስር እንዲያርፍ አድርገዋል።

ዘመኑን ዋጁት
'
ዛሬ ላይ ሆነን ዛሬ ሰማንያ አራት  ዓመታት የነበሩትን ወጣቶች ስናስብ እ ሐማሴን እ አካለጉዛይ እኛ ኢትዮጵያውያን የተለዩ አስመስለው ሊያወሩን ለሚፈልጉ መረብ ማዶም ሆነ ከመረብ ወዲህ ላሉት ባለ ጊዜዎች ትንሽ ጊዜ ወስደው እንዲያስቡ ማረግ ተገቢ ነው።መረብ ማዶውን መረብ ወዲሁ የተለያየው ታሪክ፣በዘር፣ ሃይማኖት አይደለም።ከእዚህ ይልቅ '' ውሸት ሲደጋገም እውነት የመሆን እድል ይኖረዋል'' የሚለውን ብሂል ሁል ጊዜ የሚሰራ የሚመስላቸው ወገኖች በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ብቻ ነው።

ፅሁፌን ከመጠቅለሌ በፊት አንዲት ሃሳቤን የምታሳርግልኝ ታዋቂው አሜሪካዊውን  ሀገራችን ታሪክ አዋቂ እ ስለ ኢትዮጵያ በመፃፍ የሚታወቁት አማርኛም አቀላጥፈው የሚናገሩት ፕሮፌሰር ዶናልድ ለቪን ከስምንት ዓመታት በፊት ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በተናገሩት ንግግር ልደምድም።እንዲህ ነበር ያሉት :-''ኢትዮጵያን በአሁኑ ሰዓት የሚያስተዳድሯት የሀገሪቱን  ታሪክ በሚገባ የማያውቁ ናቸው።ስለዚህ የምመክረው ታሪክን በደንብ ይረዱ .......እናንት ኢትዮጵያውያን የችግሮቻችሁ ሁሉ መፍቻ ታሪካችሁ ላይ አለ በደንብ ተረዱት'' ፕሮፌሰር ዶናልድ ለቪን ።



ጉዳያችን Gudayachn

www.gudayachn.com  



ማሳሰብያ - ይህ ፅሁፍ ከአራት ዓመታት በፊት ለመጀመርያ ጊዜ በእዚሁ ገፅ  ላይ ወጥቶ ነበር።በሌሎች ድረ-ገፆችም ከእዚህ ገፅ ተወስዶ ተለጥፎ ነበር።


የፅሁፉ መርጃዎች

፩/ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ  http://www.ethioobserver.net/forgoten_heroes.ሕትም

፪/ኢሳት ራድዮ የካቲት 11/2004 ዓም ዝግጅት

፫/ ግሎባል አልያንስ ኢትዮጵያ  http://www.globalallianceforethiopia.org























Monday, February 16, 2015

የትናንቱ የ''አይ ኤስ ኤስ'' በግብፅ ክርስቲያኖች ላይ የፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ አንፃር ምን ያመላክተናል? ኢትዮጵያን ከ''አይ ኤስ ኤስ'' እና ''ግልገሎቹ'' ለማዳን መፍትሄው ምንድነው? (የጉዳያችን ልዩ ማስታወሻ)ISS terrorist movement from Horn of Africa current political condition point of view and possible solution.

'አይ ኤስ ኤስ' ባለፈው ዓመት ያወጣው አዲሱ ካርታ 
ትናንት የካቲት 8/2007 ዓም  እኩለ ሌሊት ላይ ''ሮይተርስ'' በሊብያ በ''አይ ኤስ ኤስ'' (ISS) የታገቱት ሃያ አንድ የግብፅ ክርስቲያኖች በአሰቃቂ መንገድ መገደላቸውን፣የአገዳደሉንም ቪድዮ በአሸባሪው ድርጅት መለቀቁን እና የግብፅ ኮፕት ቤተ ክርስቲያንም ድርጊቱ መፈፀሙን ማረጋገጧን ጠቅሶ የዘገበው ዜና ብዙዎቻችንን አሳዝኗል።ይሄው በ ''ሜጫዊ''(ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ በሰይፍ የመቅላት አባዜ)  አስተሳሰብ አራማጅነቱ የሚታወቀው ቡድን እንደ 'አሜባ' እራሱን እየለጠጠ ከኢራቅ እስከ ሶርያ ከሶርያ እስከ ሊብያ እየተስፋፋ ነው።አለማችን ለአሸባሪ ተግባሮች አዲስ ባትሆንም በእንዲህ አይነት ሕብረ-ብሔራዊ ባህሪ ያለው እና የመካከለኛው ምሥራቅን እና የምስራቅ አፍሪካን ማኅበራዊ እና መልካ-ምድራዊ አቀማመጥ የደም ጎርፍ በማፍሰስ ለመቀየር መነሳቱን በአደባባይ በማወጁ ቡድኑን ከሌሎች አሸባሪዎች ይለየዋል።

ቡድኑ ኢትዮጵያን እና ኤርትራን ሙሉ በሙሉ ባካለለ መልኩ የሰሜን አፍሪካን እና የአውሮፓ ከፊልን ጨምሮ አዲስ ካርታ ማውጣቱን እና የሚታገለውም ከእዚህ አንፃር እንደሆነ በተዳጋጋሚ ይገልፃል።ይህንን አላማውን ለማሳካት በሀገሮች ውስጥ ያሉት ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታዎች ለእንቅስቃሴው ግብአትነት እንደሚጠቀምበት የታወቀ ነው።

ከእዚህ በተጨማሪ መገንዘብ ያለብን ቡድኑ ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን መሰረት ያደረገ ነው።አንደኛው እና ቀዳሚው ክርስቲያን የተባለ ሰው የሆነ ፍጥረትን መግደል ሲሆን በእዚሁ መስመር የግዛት ስፋቱን ማስፋፋት ነው።እነኝህን ተግባራት የሚፈፅመው ደግሞ የቀደሙ ታሪኮችን በሙሉ በመደምሰስ የእራሱን የ''ሜጫዊ'' ወይንም በሰይፍ የመቅላት አባዜ መመርያው ያደርጋል።የእዚህ አይነቱ አስተሳሰብ በግልገል ተከታዮቹ በሀገራችን የፖለቲካ መድረኮች በተለይ በባህር ማዶዎቹ ግልገሎች ላይ መንፀባረቁን ልብ ይሏል።

 ከፍተኛ ውድመት ያደረሱት ሁለቱ የውጭ እስላማዊ  ፅንፈኛ እንቅስቃሴዎች  

ከኢትዮጵያ አንፃር የእዚህ አይነቱ ፅንፈኛ እንቅስቃሴ በሁለት ታሪካዊ ወቅቶች ጎልቶ ወጥቷል።የመጀመርያው በ16ኛው ክ/ዘመን ቱርክ ወደ አፍሪካ የባህር ዳርቻዎች ይዞታዋን ባጠናከረችበት ወቅትሲሆን ሁለተኛው የአረቡ ዓለም የነዳጅ ዘይት ካገኘበት ከ 1960ዎቹ ወዲህ ነው።በሁለቱም ወቅቶች ኢትዮጵያ ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳቶች ደርሰዋል።እዚህ ላይ ሁለቱም የታሪክ ክስተቶች መነሻ ያደረጉት የውስጥ ፖለቲካዊ ጉዳያችንን በማጦዝ መሆኑን መዘንጋት አይገባም።

ከሁለቱ የታሪክ ክስተቶች ውስጥ የመጀመርያው የቱርክ መንግስት ወደ አፍሪካ የባህር ዳርቻዎች ያሉት ይዞታዎቹን ያጠናከረበት ወቅት ስንመለከት ቱርክ ቀደም ብላ የደቡብ ምስራቃዊ እና ምስራቃዊ አፍሪካን በንግድ እና ህዝቦችን በግድ ወደ እስልምና በመቀየር ተግባር ብትታወቅም በኢትዮጵያ ግን እጇን ያስገባችበት ሂደት ከውስጥ የተነሳውን ቅራኔ በቀጥታ በመደገፍ መሆኑን እንመለከታለን። ይሄውም ከሀገራችን ምስራቃዊ ግዛት የተነሳው በታሪክ ''የግራኝ መሐመድ እንቅስቃሴ'' ቱርክ በወታደራዊ፣በቁሳቁስ እና በሞራል ድጋፍ በማድረግ ግንባር ቀደም ነበረች።በወቅቱ ኢትዮጵያ በታሪክ ከደረሰባት የጥፋት መዓት በላይ በቀዳሚነት ክርስቲያኖች ደማቸው እንደ ጎርፍ የወረደበት፣አብያተ ክርስቲያናት እና ቅርሶች የተቃጠሉበት፣'ማኅበራዊ ጀሃድ'  የተፈፀመበት የጥፋት ዘመን ሆኖ አልፏል።በተለይ ከግራኝ መሐመድ ወረራ በኃላ ኢትዮጵያ በሰሜን ምፅዋ ተከትሎ እስከ ቀድሞዋ አፋር እና ኢሳ (የዛሬዋ ጅቡቲ) ድረስ ያለው ከአንድ ሺህ ኪሎሜትሮች በላይ የሆነው ግዛቷ በተለያዩ ለቱርክ ባደሩ ሱልጣኖች እና በቱርኮች በቀጥታ መጠቃት የተባባሰበት ወቅት ነበር።

ሁለተኛው በኢትዮጵያ ላይ ጉዳት ያደረሰ የፅንፈኛ የእስልምና እንቅስቃሴ ከ1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እጁን የከተተው ኃይል ነው።በተለይ ይህንን ወቅት አደገኛ የሚያደረገው በቀጣዩ አስር አመታት ውስጥ የአረቡ ዓለም በነዳጅ ሀብት የተንበሸበሸበት ወቅት ከመሆኑ አንፃር በሀገራት ላይ ተፅኖ የመፍጠር አቅሙ በእጅጉ በማደጉ ነበር።በእዚህ ወቅት ነበር የኤርትራ በፌድሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ በተባበሩት መንግሥታት መፅደቁ እና ያንን ተከትሎ በኤርትራ ሕዝብ እንደራሴዎች ከፍተኛ ጉትጎታ ፌድሬሽኑ መፍረሱ (''የኤርትራ ጉዳይ'' አምባሳደር ዘውዴ ረታ The Eritrean Affair (1941-1963) by Ambassador Zewde Retta) ኤርትራ ከጥንትም አብራ ከነበረችው ኢትዮጵያ ጋር መሃዷን ተከትሎ ''ጀብሃ'' በአረብ ሃገራቱ ከፍተኛ የገንዘብ፣የቁሳቁስ እና የሰው ኃይል ድጋፍ ተመሰረተ።በቀጣዮቹ ጊዜያት ''ሻብያ'' ጀብሃን ካባረረ በኃላም ሆነ ''ህወሓት'' እና ''ሻብያ'' በጥምር ከደርግ ጋር ባደረጉት ውግያ የመካከለኛው ምስራቅ አረብ ሃገራት እርዳታ አልተለያቸውም።እዚህ ላይ እርዳታዎቹ ዋና አላማቸው ኤርትራን አረባዊ ሀገር ማድረግ እና ኢትዮጵያን በሂደት በእዚሁ ተፅኖ ስር እንድትወድቅ ማድረግ ነው። 

እዚህ ላይ የደርግ አምባገነን ስርዓት ለሕዝብ ተቃውሞ በቂ ምክንያት አልነበረም ለማለት ባልደፍርም ማጉላት የምፈልገው ጉዳይ ግን በማናቸውም የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የአረብ ሃገራቱ ዘሎ መግባት በተለይ ኢትዮጵያ የውስጥ ቅራኔዋን እንዳትፈታ የራሱን ጥላ አጥልቷል።እዚህ ላይ አቶ ኢሳያስ የኤርትራን ጥያቄ በመገንጠል ደረጃ ማስቀመጥ ከአረብ ሃገራት ለሚገኝ እርዳታ ቅድመ ሁኔታ እንደነበር ብዙዎች ይስማሙበታል።እዚህ ላይ የቀድሞ የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ እና የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ የነበሩት አቶ ገብረ መድህን አርአያ በጦርነቱ ወቅት ከኢራቁ ሳዳም ሁሴን እና ከሊብያው ጋዳፊ አይሮፕላን ሙሉ መሳርያ እና ቁሳቁስ ይሰጣቸው እንደነበር ኢሳት ቴሌቭዥን ቀርበው መናገራቸውን መጥቀስ ብቻ ይበቃል።

ሆኖም ግን ያለፉት ሃያ አመታት ያሳዩን ጉዳይ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተለያይተው መኖር የማይችሉ ይልቁንም ጉዳዩን የቅኝ ግዛት ግንኙነት ነበራቸው የሚለው ተረታ ተረት ዘመን በሄደ ቁጥር ሐሰትነቱ ፍንትው ብሎ እየታየ መሆኑን ነው።ለእዚህም ይመስላል አቶ ኢሳያስ ሰሞኑ በኢሳት ቴሌቭዥን  ''የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጉዳይን እንዴት ይመለከቱታል?'' ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጉዳዩን  ''ወደ አንዳንድ የታሪክ መፋለሶች'' (historical distortion) ደረጃ ለማውረድ የተገደዱት።ለእዚህም ምክንያቶቹ አንድም ካለፈው ታሪክ ከመማር አልያም አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ህብረት እና አንድነት ብቻ የሚያድነው መሆኑን ከመረዳት ይሆናል።

ከ''አይ ኤስ ኤስ'' እና ግልገሎቹ ኢትዮጵያን ለማዳን መፍትሄው ምንድነው?

አሁን ያለው ወቅት ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ከመረብ ማዶ ያሉ የኤርትራ ምድር ህዝቦች አዲስ የፖለቲካ ራዕይ መመልከት ያለባቸው ወሳኝ ወቅት ነው።በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጎሳ ፖለቲካ ለዓለም አቀፍ ፅንፈኛ እንቅስቃሴ ምቹ የሆነ እና ኢትዮጵያን እንደሀገር ለማስቀጠል ፈፅሞ ፍላጎት እንደሌለው በተለያዩ ድርጊቶቹ ያረጋገጠ ነው።

የህወሓት የፖለቲካ መመርያ፣ጎሳዊ የምጣኔ ሀብት አደረጃጀቱ እና በታሪክ ላይ ያለው የተፋለሰ አስተያየት ሁሉ አሁን በሕይወት ካለነው ዜጎች ብቻ ሳይሆን ከመጪው እና ካለፉት ጋር ሁሉ የተቃረነ ነው።ይህ ሁኔታ ደግሞ ተወደደም ተጠላ ኢትዮጵያን ወደ አንድ አይነት ውስጣዊ ቅራኔ መምራቱ ሳይታለም የተፈታ ነው።ሆኖም ግን ቅራኔው በሕዝብ እና እራሱን በተደጋጋሚ ጊዜ እንዲያርም ዕድል የተሰጠው ህወሓት መካከል መሆኑን መዘንጋት አይገባም።ኢትዮጵያን ለማዳን እና እንደ ''አይ ኤስ ኤስ'' እና ግልገሎቹ ለመታደግ አይነት አደጋ ለመታደግ የህዝብ አንድነት፣ኢትዮጵያዊ መንግስት እና ራዕይ ያለው መሪ የፖለቲካ መዋቅር እጅግ ያስፈልጋል።አሁንም ይህንን በህወሓት ስር ባለች ኢትዮጵያ ውስጥ ፈፅሞ አይታሰብም።ለእዚህ ነው ''ኢትዮጵያ በፍጥነት ዲሞክራስያዊት ሀገር መሆኗ ለእራሷ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ብሎም ለመላው አፍሪካ ወሳኝ ነው'' ሲል ለአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ግብዓት የተዘጋጀ ጥናታዊ ፊልም አበክሮ ያሳሰበው።

ባጭሩ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ከመረብ ማዶ ያሉ ኢትዮጵያውያንም በዓለም አቀፉ የፅንፈኛ እንቅስቃሴ ታልቅ አደጋ ላይ ናቸው።ይህንን አደጋ ለመከላከል የቤት ስራው የሚጀምረው ከውስጥ ነው።መጀመርያ ውስጣችን ያለው የጎሰኛ ስርዓት ከእነ አሰራሩ ሙሉ በሙሉ መነቀስ አለበት።ቀጥሎ ኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ፖለቲካዊ፣ማጣኔ ሃብታዊ እና ማህበራዊ ቦታዋ በአግባቡ የሚያስጠብቅላት መንግስት ያስፈልጋታል።ይህንንም ከመረብ ማዶ ያሉትም በአግባቡ ሊገነዘቡት እና ላለፉት 40 ዓመታት በአንዳንድ አረብ ሃገራት የታለሉትባቸውን መንገዶች በሙሉ በውል ሊያጠኑት ይገባል።በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች እና አቶ ኢሳያስ መካከል ያለው መናበብም አስፈላጊ ያምያደርገው ከእዚህ ሁሉ አንፃር ነው።ጉዳዩ ከስልታዊ ግንኙነት በዘለለ ታሪካዊ እውነታን ያገናዘበ መሆን እንደሚገባውም የሚሰመርበት ለእዚህ ነው።የምዕራቡ ዓለም በቀዳሚነት የፅንፈኛ እንቅስቃሴ አደጋ የመሆን ዕድል ኢትዮጵያ እንዳላት ይገነዘባል።ለእዚህም ህወሓት ከሕዝቡ ጋር የተጣላ መንግስት ከመሆኑ አንፃር ኢትዮጵያን አይደለም እራሱንም መከላከል የማይችልበት ወቅት እሩቅ አይደለም።ስለዚህ የአንድነት ኃይሎች መጠናከር ብቸኛ መንገድ መሆኑ ከፍተኛ ግንዛቤ ተወስዶበታል።በመሆኑም የአይ ኤስ ኤስን አደጋ ስንመለከት መጀመርያ የቤታችንን ጉዳይ በፍጥነት ማስተካከል እንዳለብን ግንዛቤ እንዳይጎለን።ጉዳዩ ሁሉ ከጊዜ ጋር ነውና።


ጉዳያችን GUDAYACHN
የካቲት 9/2005 ዓም (February 16/2015)

Friday, February 13, 2015

ኢትዮጵያ በ40 ሚልዮን ብር ለ''ህወሓት'' በዓል ትከሰክሳለች ዩጋንዳ ለዝነኛው ዩንቨርስቲዋ ''ማካራሬ ዩንቨርስቲ'' በ50 ሚልዮን ዶላር በአፍሪካ ልዩ የሆነ ዘመናዊ መፃህፍት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ትጥላለች።

በዩጋንዳ ማካረሬ ዩንቨርሲቲ አዲስ የሚገነባው መፃህፍት ቤት 

ኢትዮጵያ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን እና የትምህርት ተቋማትን በመመስረት ከአፍሪካ ሃገራት ቀደምት ነበረች።ይልቁንም ኢትዮጵያ ከአየር መንገድ እስከ ዩንቨርሲቲ፣ከባህር ኃይል እስከ አየር ኃይል ድረስ ያሉ ተቋማት ሲመሰረቱ ብዙዎቹ ከሳሃራ በታች ያሉ ሃገራት ገና ነፃነታቸውን አልተቀዳጁም ነበር።ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ የገጠማት የአምባገነንነት፣የገንጣይ እንቅስቃሴ እና የጎሰኛ ርዕዮት ከእርስ በርስ ጦርነት ጋር ተዳምሮ ዛሬም ከፍተኛ የማደግ እድሏን ወደ ኃላ የጎተተ ጉዳይ ሆኗል።

አንዲት ሀገር ዛሬ እድገት ላይ ነች የሚባለው በእያንዳንዱ ሰው ላይ ከሚሰራው የልማት ሥራ በተጨማሪ በትክክለኛ የእድገት ፖሊሲ ላይ መሆኗ ከሁሉ በላይ አንገብጋቢው ጥያቄ ነው።ቀጣይነት ያለው ልማት ሲነሳ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ጀምሮ ትክክለኛ ሁለንተናዊ የዕድገት መስመር መከተል ይህ መስመርም በሕዝቡ ዘንድ በቂ ግንዛቤ እና ተስፋ የፈነጠቀ መሆን ይገባዋል።ከእዚህ ውጭ እንደ ኢህአዲግ/ህወሓት እኔ አውቅልሃለሁ የጎሳ ፖለቲካ ግን ውጤቱ ውድቀትን ማስከተል ብቻ ሆኗል።ስርዓቱ በተለይ ልማትን በተመለከተ ተግባር ሁሉ የታይታ፣ምርጫን ታሳቢ ያደረገ እና ጎሳዊ አድሏዊነት ስለሚንፀባረቅበት ውጤታማ አለመሆን ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ አደገኛ መስመሮችን ለነገዋ ኢትዮጵያ እየዘረጋ መሄዱ ነው ክፋቱ።

ይህ ብቻ አይደለም በትምህርት ዕድል በኢትዮጵያ ስም የነፃ ትምህርት ዕድል ያገገኙ ''የሜጫ'' አስተሳሰብ አራማጆች እነርሱ በነፃ የትምህርት ዕድል ሲያገኙ ሀገር ቤት ላለው ወገናችን (ቆመንለታል ለሚሉት ጎሳ) ግን ''የጡት ሃውልት'' በ20 ሚልዮን ብር መገንባቱን እንደ ትልቅ ስኬት ሲነግሩን የነበሩቱ የባህር ማዶ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆችን እኩይ አስተሳሰብ ሳይጠቅሱ ማለፍ ተገቢ አይደለም።

ዕውቀት ላይ የተመሰረተ የልማት መስመር የሚከተሉ ሀገሮች ሁል ጊዜ ቅድምያ የሚሰጡት ለትምህርት ነው።ትምህርት ላይ በጥራት እና በብዛት መዋለ ንዋያቸውን ያፈሰሱ ሃገራት ለምሳሌ ህንድ፣ሲንጋፖር እና ቻይናን ብንመለከት የልማት ደረጃቸው በአንድ ትውልድ ብቻ ተመንጥቆ ሲሄድ እናየዋለን።

ኢትዮጵያ በትምህርት መስክ ከፍተኛ የጥራት ማሽቆልቆል ያሳየች፣በዋና ከተማዋ አንፃር 'ምንም የለም' ለማለት በሚያስደፍር ደረጃ ህዝቧ መፃህፍት ቤት መጠቀም ያልቻለበት፣የትምህርት ፖሊሲው በጎሳ ፖለቲካ እንዲጠረነፍ የተደረገባት ሀገር ነች።ለእዚህም ነው አንድ መፃህፍት ቤት ከመክፈት ይልቅ 20 ሚልዮን ብር አውጥቶ ከመቶ ዓመት በፊት ላልተደረገ በሬ ወለደ ታሪክ ሃውልት እንዲሰራ የሚወስኑ ባለስልጣናት ያሉባት ሀገር የሆነችው።ለእዚህም ነው አዲስ አበባ ከ 4 ሚልዮን ሕዝብ በላይ ይዛ የማንበብያ መፃህፍት ቤት የሌላት ከተማ ሆና የቀረችው።ለእዚህም ነው ወጣቶቿ በእየሽሻ ቤት እና ጫት ቤት እንዲውሉ እንጂ የሚያነቡት መፅሐፍ እንዲኖራቸው የማይደረጉት።ለእዚህም ነው ጋዜጠኞች፣ደራስያን እና ሳይንቲስቶቿን ከሀገር እየተባረሩ የህወሓትን በዓል ለማክበር 40 ሚልዮን የሚሆን የሀገር ሀብት እንዲጠፋ የሚደረገው።

ዩጋንዳ ከምትኮራበት እና የሀገሪቱ ''አይከን'' ተብሎ የሚጠቀሰው ተቋሟ ውስጥ ''ማካረሬ ዩንቨርሲቲ'' አንዱ እና ተጠቃሽ ነው።ዩንቨርስቲው ''የአፍሪካ ኦክስፎርድ'' የሚል ስያሜ ይሰጠው እንደነበር እና ዛሬም ትምህርት በጥራት ከሚሰጥባቸው አፍሪካዊ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።ሰሞኑን ዩንቨርስቲው አዲስ ፕሮጀክት ይዞ ብቅ ብሏል።በ50 ሚልዮን ዶላር አዲስ መፃህፍት ቤት መገንባት።በመሰረት መጣሉ ላይ ቀደም ብለው ከዩንቨርስቲው የተመረቁት እና የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ምዋይ ኪባኪ ስም ይሰየማል።ዩንቨርስቲው ለአፍሪካዊ ምሁር ዋጋ ሰጥቶ መሰየሙ የሚያስመሰግነው ነው።ከእዚህ በታች የዩንቨርስቲው ቻንስለር ፕሮፌሰር ሞንዶ ካጎንየራ ጉዳዩን አስመልክተው የተናገሩትን ቪድዮ ይመልከቱ።

አዎን! ኢትዮጵያ በአምባገነን ይልቁንም በጎሳ ላይ በተመሰረተ ስርዓት እየማቀቀች ነው።ሰሞኑን እንደተዘገበው ከፍተኛ የሀገሪቱ የፖሊሲ ቀራጮች የትምህርት ደረጃቸው ካልታወቀ እና አንዳንዱም በገንዘብ ኃይል ባገኙት ዲግሪ ሀገሪቱን እየመሩ መሆናቸው ተሰምቷል።እርግጥ ነው ትምህርትን በእዚህ አይነት የሚያውቅ ባለስልጣን መፃህፍት ቤቶችን እንዲወድ አይጠበቅበትም።ለእርሱ እድገት 40 ሚልዮን ብር እያወጡ የህወሓት በዓል ማክበር ይሆናል።ዩጋንዳውያን ግን ለሀገር የሚያስቡ ባለስልጣናት እውቀት ላይ የተመሰረቱ ባለሙያዎች አሏት እና በ50 ሚልዮን ዶላር መፃህፍት ቤት ይገነባሉ።የኢትዮጵያን ትንሣኤ ያሳየን።




Video from NTV Uganda youtube 
News Source - NTV Uganda 
Makerere to construct $50M Mwai Kibaki library 
The building is estimated to cost 50 million US dollars. Of this amount, $40 million is projected for the presidential Library and the remaining 10 million is for the establishment of a Mwai Kibaki endowed chair in Economics.
Makerere University will construct a 30-storey presidential library, named after Kenya’s former president Mwai Kibaki.The building is estimated to cost 50 million US dollars. Of this amount, $40 million is projected for the presidential Library and the remaining 10 million is for the establishment of a Mwai Kibaki endowed chair in Economics. 

The library and endowment are named after Mwai Kibaki in commeration the fact that he was the first student of Makerere University to get a first class degree in economics.The announcement was made by the Chancellor of Makerere, Mondo Kagonyera. Kibaki is expected to launch this project on Friday at Makerere University.
የካቲት 6/2007 ዓም (ፌብሯሪ 13/2015)

Tuesday, February 10, 2015

Zone 9 Bloggers case, Presented to the United Nations Working Group on Arbitrary Detention




Six Zone 9 bloggers collective members and three other independent journalists are in detention since last April 2014.  Accusation of Ethiopian government which suspected them in working with human rights organisations was changed to terrorism after 23 days of interrogation. After three months on interrogation detention , all of them including one more blogger in absentia  were charged of terrorism at the end of July 2014.  The case is still on its Pre- trial stage which was more focused on the format and the substance of the charges.  With in  the last nine months they were taken to court nineteen times and their constitutionally given rights has been continuously violated since their arrest.

EHRP (Ethiopian Human Rights Project) and Freedom Now ( DC based Human Rights advocacy organisation)  takes the case to the united nation working group on arbitrary detention. This petition against the Ethiopian Government was presented to the working group on January 26th , 2015.  The petition shows the rights violations they have faced during detention and legal analysis why their arrest was arbitrary.

Source - Ethiopian Human Rights Project
                http://ehrp.org

Below is the link of the full petition.
http://ehrp.org/wp-content/uploads/2015/02/UNWGAD-Petition-Zone-9-Ethiopia-1.26.15_4-updated.pdf

ጉዳያችን GUDAYACHN

February 10/2015

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...