ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, February 13, 2015

ኢትዮጵያ በ40 ሚልዮን ብር ለ''ህወሓት'' በዓል ትከሰክሳለች ዩጋንዳ ለዝነኛው ዩንቨርስቲዋ ''ማካራሬ ዩንቨርስቲ'' በ50 ሚልዮን ዶላር በአፍሪካ ልዩ የሆነ ዘመናዊ መፃህፍት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ትጥላለች።

በዩጋንዳ ማካረሬ ዩንቨርሲቲ አዲስ የሚገነባው መፃህፍት ቤት 

ኢትዮጵያ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን እና የትምህርት ተቋማትን በመመስረት ከአፍሪካ ሃገራት ቀደምት ነበረች።ይልቁንም ኢትዮጵያ ከአየር መንገድ እስከ ዩንቨርሲቲ፣ከባህር ኃይል እስከ አየር ኃይል ድረስ ያሉ ተቋማት ሲመሰረቱ ብዙዎቹ ከሳሃራ በታች ያሉ ሃገራት ገና ነፃነታቸውን አልተቀዳጁም ነበር።ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ የገጠማት የአምባገነንነት፣የገንጣይ እንቅስቃሴ እና የጎሰኛ ርዕዮት ከእርስ በርስ ጦርነት ጋር ተዳምሮ ዛሬም ከፍተኛ የማደግ እድሏን ወደ ኃላ የጎተተ ጉዳይ ሆኗል።

አንዲት ሀገር ዛሬ እድገት ላይ ነች የሚባለው በእያንዳንዱ ሰው ላይ ከሚሰራው የልማት ሥራ በተጨማሪ በትክክለኛ የእድገት ፖሊሲ ላይ መሆኗ ከሁሉ በላይ አንገብጋቢው ጥያቄ ነው።ቀጣይነት ያለው ልማት ሲነሳ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ጀምሮ ትክክለኛ ሁለንተናዊ የዕድገት መስመር መከተል ይህ መስመርም በሕዝቡ ዘንድ በቂ ግንዛቤ እና ተስፋ የፈነጠቀ መሆን ይገባዋል።ከእዚህ ውጭ እንደ ኢህአዲግ/ህወሓት እኔ አውቅልሃለሁ የጎሳ ፖለቲካ ግን ውጤቱ ውድቀትን ማስከተል ብቻ ሆኗል።ስርዓቱ በተለይ ልማትን በተመለከተ ተግባር ሁሉ የታይታ፣ምርጫን ታሳቢ ያደረገ እና ጎሳዊ አድሏዊነት ስለሚንፀባረቅበት ውጤታማ አለመሆን ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ አደገኛ መስመሮችን ለነገዋ ኢትዮጵያ እየዘረጋ መሄዱ ነው ክፋቱ።

ይህ ብቻ አይደለም በትምህርት ዕድል በኢትዮጵያ ስም የነፃ ትምህርት ዕድል ያገገኙ ''የሜጫ'' አስተሳሰብ አራማጆች እነርሱ በነፃ የትምህርት ዕድል ሲያገኙ ሀገር ቤት ላለው ወገናችን (ቆመንለታል ለሚሉት ጎሳ) ግን ''የጡት ሃውልት'' በ20 ሚልዮን ብር መገንባቱን እንደ ትልቅ ስኬት ሲነግሩን የነበሩቱ የባህር ማዶ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆችን እኩይ አስተሳሰብ ሳይጠቅሱ ማለፍ ተገቢ አይደለም።

ዕውቀት ላይ የተመሰረተ የልማት መስመር የሚከተሉ ሀገሮች ሁል ጊዜ ቅድምያ የሚሰጡት ለትምህርት ነው።ትምህርት ላይ በጥራት እና በብዛት መዋለ ንዋያቸውን ያፈሰሱ ሃገራት ለምሳሌ ህንድ፣ሲንጋፖር እና ቻይናን ብንመለከት የልማት ደረጃቸው በአንድ ትውልድ ብቻ ተመንጥቆ ሲሄድ እናየዋለን።

ኢትዮጵያ በትምህርት መስክ ከፍተኛ የጥራት ማሽቆልቆል ያሳየች፣በዋና ከተማዋ አንፃር 'ምንም የለም' ለማለት በሚያስደፍር ደረጃ ህዝቧ መፃህፍት ቤት መጠቀም ያልቻለበት፣የትምህርት ፖሊሲው በጎሳ ፖለቲካ እንዲጠረነፍ የተደረገባት ሀገር ነች።ለእዚህም ነው አንድ መፃህፍት ቤት ከመክፈት ይልቅ 20 ሚልዮን ብር አውጥቶ ከመቶ ዓመት በፊት ላልተደረገ በሬ ወለደ ታሪክ ሃውልት እንዲሰራ የሚወስኑ ባለስልጣናት ያሉባት ሀገር የሆነችው።ለእዚህም ነው አዲስ አበባ ከ 4 ሚልዮን ሕዝብ በላይ ይዛ የማንበብያ መፃህፍት ቤት የሌላት ከተማ ሆና የቀረችው።ለእዚህም ነው ወጣቶቿ በእየሽሻ ቤት እና ጫት ቤት እንዲውሉ እንጂ የሚያነቡት መፅሐፍ እንዲኖራቸው የማይደረጉት።ለእዚህም ነው ጋዜጠኞች፣ደራስያን እና ሳይንቲስቶቿን ከሀገር እየተባረሩ የህወሓትን በዓል ለማክበር 40 ሚልዮን የሚሆን የሀገር ሀብት እንዲጠፋ የሚደረገው።

ዩጋንዳ ከምትኮራበት እና የሀገሪቱ ''አይከን'' ተብሎ የሚጠቀሰው ተቋሟ ውስጥ ''ማካረሬ ዩንቨርሲቲ'' አንዱ እና ተጠቃሽ ነው።ዩንቨርስቲው ''የአፍሪካ ኦክስፎርድ'' የሚል ስያሜ ይሰጠው እንደነበር እና ዛሬም ትምህርት በጥራት ከሚሰጥባቸው አፍሪካዊ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።ሰሞኑን ዩንቨርስቲው አዲስ ፕሮጀክት ይዞ ብቅ ብሏል።በ50 ሚልዮን ዶላር አዲስ መፃህፍት ቤት መገንባት።በመሰረት መጣሉ ላይ ቀደም ብለው ከዩንቨርስቲው የተመረቁት እና የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ምዋይ ኪባኪ ስም ይሰየማል።ዩንቨርስቲው ለአፍሪካዊ ምሁር ዋጋ ሰጥቶ መሰየሙ የሚያስመሰግነው ነው።ከእዚህ በታች የዩንቨርስቲው ቻንስለር ፕሮፌሰር ሞንዶ ካጎንየራ ጉዳዩን አስመልክተው የተናገሩትን ቪድዮ ይመልከቱ።

አዎን! ኢትዮጵያ በአምባገነን ይልቁንም በጎሳ ላይ በተመሰረተ ስርዓት እየማቀቀች ነው።ሰሞኑን እንደተዘገበው ከፍተኛ የሀገሪቱ የፖሊሲ ቀራጮች የትምህርት ደረጃቸው ካልታወቀ እና አንዳንዱም በገንዘብ ኃይል ባገኙት ዲግሪ ሀገሪቱን እየመሩ መሆናቸው ተሰምቷል።እርግጥ ነው ትምህርትን በእዚህ አይነት የሚያውቅ ባለስልጣን መፃህፍት ቤቶችን እንዲወድ አይጠበቅበትም።ለእርሱ እድገት 40 ሚልዮን ብር እያወጡ የህወሓት በዓል ማክበር ይሆናል።ዩጋንዳውያን ግን ለሀገር የሚያስቡ ባለስልጣናት እውቀት ላይ የተመሰረቱ ባለሙያዎች አሏት እና በ50 ሚልዮን ዶላር መፃህፍት ቤት ይገነባሉ።የኢትዮጵያን ትንሣኤ ያሳየን።




Video from NTV Uganda youtube 
News Source - NTV Uganda 
Makerere to construct $50M Mwai Kibaki library 
The building is estimated to cost 50 million US dollars. Of this amount, $40 million is projected for the presidential Library and the remaining 10 million is for the establishment of a Mwai Kibaki endowed chair in Economics.
Makerere University will construct a 30-storey presidential library, named after Kenya’s former president Mwai Kibaki.The building is estimated to cost 50 million US dollars. Of this amount, $40 million is projected for the presidential Library and the remaining 10 million is for the establishment of a Mwai Kibaki endowed chair in Economics. 

The library and endowment are named after Mwai Kibaki in commeration the fact that he was the first student of Makerere University to get a first class degree in economics.The announcement was made by the Chancellor of Makerere, Mondo Kagonyera. Kibaki is expected to launch this project on Friday at Makerere University.
የካቲት 6/2007 ዓም (ፌብሯሪ 13/2015)

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...