ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, September 17, 2022

ሰበር ዜና - የሽብርተኛው ህወሃት ቡድን ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሃብቶች ወደ ጂቡቲ እና ናይሮቢ ለመሸሽ ሙከራ አደረጉ።


===============
ጉዳያችን/ Gudayachn
===============

ከዘንድሮው የአዲስ ዓመት በፊት ተከታታይ ስብሰባዎች ከውጭ መንግስታት ደጋፊ ባዕዳን ጋር ተገናኝቷል። በእነኝህ ስብሰባዎች ላይ በሽብር ቡድኑ የፖለቲካ እና የኃይል አመራሮች ጋር የነበራቸው ስብሰባ ላይ የነብሩትን ንትርኮች ለባዕዳኑ ጠቁሟል።ባዕዳኑም ከኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ጥንካሬ አንጻር እና እራሱ የትግራይ ህዝብም በህወሃት ላይ ካለው መማረር አንጻር ወዴትም እንደማያስኬዳቸው መነጋገራቸው ተደርሶበታል።በእዚህ ንግግር ውስጥ የህወሃት አመራሮች አሁን ከቀድሞው የተለየ አካሄድ እንደሚሄዱ ለባዕዳኑ ጠቁመዋል። 

ይህ ከበፊቱ የተለየ የተባለው አካሄድ ደግሞ ግልጽ የሆነው መስከረም 1፣2015 ዓም ምሽት ላይ ህወሃት ታዛዥነቱ ለባዕዳን ነውና በኢትዮጵያ ፊደል ሳይሆን በእንግሊዝኛ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚደራደር እና የአፍሪካ ሕብረትንም አደራዳሪነት እንደሚቀበል አስታወቀ።ይህ ድንገተኛ የድርድር ጥያቄ ግን ከጀርባው ይዞት የነበረው ምን እንደነበር ውይይቱ ውስጥ ከነበሩ ከፍተኛ የሽብር ቡድኑ ዘግይተው አውጥተውታል። እንደመረጃው ህወሃት ድንገት ምሽቱን በእውር ድንብር በእንግሊዝኛ የለቀቀው የእንደራደር መግለጫ ዋና ዓላማ ለመደራደር አይደለም።በመደራደር ስም ጥቂት ጊዜ ወስዶ ሰራዊቱን ለማደራጀትም አይደለም።ህወሃቶች ሁሉ ነገር እንዳበቃ እራሳቸውም ገምግመው አውቀውታል።ባዕዳኑም በግምገማቸው ነግረዋቸዋል። የእንቁጣጣሽ ምሽት የእንግሊዝኛ መግለጫ ዋና ዓላማ ህወሃት አመራሩን ይዞ በድርድር ስም ወደ ጂቡቲ እና ኬንያ ለማምለጥ ነበር። ቀደም ብሎ የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ከእኛ በኩል የሚደራደሩት ስም አንገልጽም ብሎ የነበረ ቢሆንም በእንቁጣጣሽ ምሽት ላይ ግን ጌታቸው ረዳ እና ጻድቃን መመረጣቸውን ተናገረ።ዓላማው ከፍተኛ አመራሩ ከትግራይ እንደሚወጣ ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለመንግስት ገልጾ የመሹለክ ዓላማ ብቻ የያዘ መግለጫ ነበር።

ለመደራደር ጂቡቲ መጣን ያለው የህወሃት መግለጫ ተከትሎ ሊያመልጡ የነበሩት ጌታቸው እና ጻድቃንን ጨምሮ ከ13 በላይ ጄነራሎች፣ከ25 በላይ የሚሆኑ የሲቪል አመራሮች፣6 ጋዜጠኞች፣12 የትግራይ ዩንቨርስቲ አመራሮች እና ከ3 ቢልዮን ዶላር በላይ የሚቆጠር ገንዘብ ያላቸው ባለሃብቶችን ይዞ ወደ ጂቡቲ ወይንም ናይሮቢ ድርድሩ ሊደረግ ነው ወደተባለበት ሃገር በህጋዊ ከለላ ለመውጣት እና ለማመለጥ የታቀደ እንደነበር ተጋልጧል። ይህ በድርድር ስም የመውጣት ዕቅድ ለማምለጥ የታቀደ እንደነበር በእዚሁ ሳምንት ህወሃት ባደረገው ስብሰባ ላይ ለድርድር ሊሄዱ ነበር የተባለው ሰው መብዛት የተመለከቱ እና እነርሱ ከዝያ ዝርዝር ያልተጨመሩበት አሳማኝ ምክንያት እንዲነገራቸው የህወሃት አመራሮችን ጠይቀዋል። ''እኛን ሜዳ ላይ ዘርግታችሁ ልትሄዱ ነበር። ማምለጥ ካለባችሁም ለምን እንድንነጋገርበት አይደረግም ነበር? አሁን በኋላ ማንንም የህውሃት አመራር ልናምን አንችልም '' የሚል የፊት ለፊት ኢንኪያ ሰላምታ እንደነበር መረጃው ጨምሮ ያብራራል። ይህ ዜናም መቀሌ ህዝቡ መሃል በበታች ካድሬዎቹ ስለተሰማ አሁን የህወሃት አመራሮች ወደ ግንባር ዘመትን የሚል ቪድዮ እንስራ የሚል ሃሳብ ከቡድኑ ውስጥ ተሰምቷል።

አሁን የህወሃት አመራር ተመልሶ ከምቾት ሶፋ ላይ ተነስቶ ወደ ደደቢትም ሆነ ተንቤን የመሄድ አንዳች ሞራል የለውም።ላድርግ ቢልም የአሁኑ የመንግስት ስልት የረቀቀ በመሆኑ ከመቀሌ በፊት የሽብር ቡድኑ ሊያመልጥበት ይችላል የተባሉትን ደደቢት እና ተንቤን ስልታዊ ቦታዎች ቀድሞ ከቦ ይዟቸዋል።በመሆኑም ለህወሃት አመራር የቀረው ደደቢት እና ተንቤን ጂቡቲ እና ናይሮቢ ናቸው።

ይህ ሁኔታ ለመንግስትም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያሳየው ጉዳይ ምንም ዓይነት መዘግየት ሳይሰጡ የሽብርተኛው ቡድኑ አመራሮችንም ሆነ ጀሌውን በቶሎ ወደ ሕግ አቅርቦ የትግራይን ህዝብ ከህወሃት መንጋጋ የማውጫው ጊዜ አሁን መሆኑን ነው።አንዳንድ የምዕራብ አገሮች የሽብር ቡድኑ ደጋፊዎች የኢትዮጵያን መንግስት የሚወቅሱበት አዲስ ርዕስ ስላጡ በመገናኛ ብዙሃኖቻቸው ዙርያ ጥምጥም ከማውራት ሌላ አሁን የሽብር ቡድኑን የሚረዱበት ርዕስ ፍለጋ እንዲረዳቸው የውሸት የሰብዓዊ መብት ሪፖርት የሚል ከሰሞኑ ይዘው ለመውጣት ላይ ታች እያሉ ነው።ሪፖርቱን ካወጡ በኋላ ያንን እየጠቀሱ በየሚድያው ላይ ለማለቅለቅ እንደሚመች አምነውበታል። ይህ ግን አሁንም መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ አንዳች አይቀይረውም። 
========

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...