ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, September 18, 2022

አዲሱ የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ የኢትዮጵያ ትንሳዔ አብሳሪ ልጆች ማፍርያ ፖሊሲ ነው። ፖሊሲውን በተመለከተ የማያውቋቸውን ጥቂት ነጥቦች ጉዳያችን ምጥን ለመዘርዘር ሞክራለች።


========
ጉዳያችን ምጥን
=========
''አንድ ዛፍ ተ ተጣሞ ካደገ በኃላ ፈፅሞ አታቃናውም።የተጣመመ የትምህርት ፖሊሲ ውስጥ የተማረ ተማሪም ካደገ በኃላ አታቃናውም'' ይህ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የተነገረ ነው። ሀገር በተለያየ መንገድ ሄዶ ከሚፈርስበት ወይንም አንድነቱን ከሚጠበቅበት መንገድ አንዱ ወጥ የሆነ አፍራሽ ወይንም ገንቢ  የትምህር ፖሊስ በአንድ አገር ላይ መኖር እና አለመኖር ላይ የተመሰረተ ነው።ይህ ለውጥ አንደመጣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ከምክር ቤት ስብሰባ በኃላ መጀመርያ የታዩበት መድረክ የትምህር ፖሊሲ አንዲቀየር የሚያጠና ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነበር።በስብሰባው ላይ ያደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ ምን ያህል ኢትዮጵያን ለመከፋፈል አስተዋጽኦ እንዳደረገ በሚገባ አሳይተዋል።ያለፈዐው የትምህርት ፖሊሲ ኢትዮጵያን ቀውስ ውስጥ ከቷት አልፏል።ገና መዘዙም ለቀጣይ ዓመታት የሚለቀን አይደለም።ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው አዲስ የትምህርት ፖሊሲ ምን ምን ይዟል? ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው ለመዘርዘር እሞክራለሁ።
  • የመማርያ መፃህፍት ዝግጅቱ ሦስት ዓመታት ፈጅቷል።
  • በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከነገ መስከረም 9/2015 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።
  •  ከአንደኛ አስከ ስድስተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የግብረገብ ትምህርት ይማራሉ።
  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አዲሱ ፖሊሲ በ80 ትምህርትቤቶች የሙከራ ሥራ ዘንድሮ ተሰርቶ በመጪው ዓመት ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ይውላል።
  •  የሰባተኛና የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ‹‹ኬሪየር ኤንድ ቴክኒካል ኤጁኬሽን›› የተባለ የትምህርት ዓይነት ይሰጣቸዋል።
  • ይህ የትምህርት ዓይነት] መጠነኛ የሆነ የአካውንቲንግ፣ ቢዝነስ፣ እርሻና ሌሎች የሙያ ትምህርቶችን ዕውቀት የሚያስጨብጥ ነው።
  • ተማሪዎቹ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ሲደርሱ ይኼ ትምህርት ራሳቸውን የቻሉ እንደ ማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ ጤና፣ ግብርና፣ ቢዝነስና አካውንቲንግ ባሉ የሙያ ትምህርት መስኮች ተበትኖ ይሰጣቸዋል።
  •  ስለሆነም አንድ ተማሪ 12ኛ ክፍል ሲጨርስ አንደ ድሮው ጨረሰ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሙያዎች ይዞ ስለሚወጣ ምረቃ ይኖረዋል።ይህ በሌሎች አገሮች የተለመደ ነው።
  • 12ኛ ክፍል የጨረሰ ተማሪ በመለስተኛ ሥራዎች ተቀጥሮም ሆነ የራሱን ሥራ ለመስራት የሚያስችል አውቀት ይዞ ይወጣል።
  • የእንግሊዝ ኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ከሥርዓተ ትምህርት ጥናት እስከ መጻሕፍት ዝግጅት በገምጋሚነት ተሳትፎበታል።
  •  ለአንደኛ ደረጃ የተዘጋጁት መጻሕፍት በሙሉ በትምህርት ሚኒስቴር ድረ-ገፅ ላይ ይለቀቃሉ።መፃሕፍ የለኝም ማለት የለም ኮምፕዩተር ከፍቶ መፅሐፉን ማንበብይ ይቻላል።ወላጆችም ልጆቻቸውን ለማስጠናት ቀድመው መዘጋጀት ይችላሉ።
  •  የኬምብርጅ ዩንቨርስቲ አንዱ ያገዘው ያለፉ መፃህፍት ብዙ ነገር ያጨቁ አና ተግባራዊ አሰራሮች የማያሳዩ አና የ21ኛውን ክ/ዘመን የቴክኖሎጂ ለውጥ ያላገናዘበ መሆኑ ላይ ጠቃሚ ሃሳብ ሰጥቷል።
  •  አንደኛ ደረጃ›› ትምህርት የሚባለው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያለው ሲሆን፣ ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል ‹‹መካከለኛ›› ደረጃ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ከዚህ ቀደም ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ በሚል ተከፍሎ የነበረው ከዘጠነኛ እስከ 12ተኛ ክፍል ያለው የአራት ዓመት ቆይታ አሁን ሁለተኛ ደረጃ በሚል ተጠቃሏል።
  •  የአሁኑ የትምህርት ፖሊሲ አንዱ አና ልዩ የሚያደርገው የአገር በቀል አውቀቶች ቦታ ተሰጥቷቸው ተጠቃልለውበታል።
  •  ሌላው ሕፃናት አንደኛ ክፍል ሳይገቡ የሚሰጠው ትምህርት 0 ክፍል ተብሎ የትምህርት ካሪኩለም የሌለው፣በቂ ባለሙያ ያልነበረው ሲሆን አሁን በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ከአምስት ዓመት አስከ 7 ዓመት ያሉ ሕፃናት የሚማሩበት ሥርዓት አና ባለሙያ ተቁአማዊ በሆነ መልኩ ተደራጅቷል።
  • የሁሉም የትምህርት ውድቀት የሚጀምረው ከሰባት ዓመት በፊት ያሉ ልጆች ወጥ የሆነ መሰረት ይዘው ስለማይሄዱ አና ድንገት 7 ዓመት ሆኗቸው አንደኛ ክፍል ሲጀምሩ የአአምሮ ዝግጅት ሳይኖር ብቻ ሳይሆን ትምህርት አንዲወዱ ከስር ሳይሰራ የተሄደበት ሂደት አንዱ ውድቀት እንደነበር አዲሱ ፖሊሲ ተገንዝቦ አሁን አርሞታል።

    =========////=============

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...