Pages

Pages

Thursday, February 11, 2021

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ ድራጎት ድርጅት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የማኅተመ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታልን ወለደ።የጋንዲ መታሰብያ ሆስፒታል ትናንት አዲስ ''ልጅ'' ሆስፒታል ወለደ።(ሙሉ ፊልሙን ይመልከቱ)

ጉዳያችን /Gudayachn

በኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ታሪክ ስመ ጥሩ ድርጅት የነበረው የቀዳማዊ  አፄ ኃይለ ሥላሴ በጎ ድራጎት ድርጅት (የቀ.ኃ.ሥ ፋውንዴሽን) ነበር። የድርጅቱ ማቋቋሚያ ቻርተር በሐምሌ 15 ቀን 1951ዓ.ም በመንግሥት ማስታወቂያ ቁ. 253/51 መሠረት ወጥቶ፤ በየካቲት 21 ቀን 1952ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 261/52 መሠረት ፀድቋል። ድርጅቱ  ዘርፈ-በዙ ተግባራትን አከናውኗል። በሥሩም የቀ.ኃ.ሥ ሽልማት ድርጅትን፣ የአባድር እርሻ ልማትን፣ የቤተሳይዳ ቀ.ኃ.ሥ ሆስፒታልን (የዛሬው የካቲት 12 ሆስፒታል መሆኑ ነው)፤ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልን (ያኔ የዛሬው ክፍለ ሀገር አውቶቡስ ተራ ጋር ነበር)፤ የሐረር ልዑል ራስ መኮንን ሆስፒታልን (በተለምዶ ጀጉላ ሆስፒታል ይባላል)፤ በቅደስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን ጀርባ የነበረውን የቀ.ኃ.ሥ ዕጓለ ማውታ ትምህርት ቤትን፤ ስድስት ኪሎ የሚገኘውን የመርሐ ዕውራን ትምህርት ቤትን፤ የማኅተመ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታልንና ደብረ ሊባኖስ የሚገኘውን የቤተ ሰሊሆም (ጡረተኞች ቤት) የያዘ ነበር።

ዛሬ የካቲት 4/2013 ዓም የማኅተመ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል በአንድ ጊዜ ሰባት እናቶችን በተመሳሳይ ሰዓት ቀዶ ጥገና ማድረግ የሚችል አገልግሎት የያዘ ዘመናዊ ሆስፒታል ወልዷል።ለዝርዝሩ ይህንን የፋና የቀጥታ ስርጭት ይመልከቱ።
============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 

አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

Post a Comment

አስተያየትዎን እዚህ ላይ ይስጡ