ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, October 15, 2018

የአዲስ አበባ ወጣቶችን በጅምላ ያሳፈሱ ስውር የፖሊስ አመራሮች፣ከጀርባ የሚገፉ ፅንፈኛ ጎሰኞች ተለይተው ለፍርድ ይቅረቡ! (ጉዳያችን)

ጉዳያችን/ Gudayachn
ጥቅምት 6/2011 ዓም  (ኦክቶበር 16/2018 ዓም)
  • ማን ነህ? ከየት መጣህ? የማያውቀው የአዲስ አበባ ወጣት አዲስ አበባን በጎጥ መስፈርት መለካትን ተቃወመ።ተቃውሞው መደረጉ በጎጥ ስም በሚስጥር የተደራጁ እና በፖሊስ መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ እና ከባህር ማዶ የመጡ የመንግስት ሆቴል ተቀላቢዎችን አደናገጠ።
  • ወጣቶቹን ከይቅርታ ጋር ፍቱልን! ያሰሩት የጎሳ አድናቂዎች ለፍርድ ይቅረቡ! 
  • የዶ/ር ዓብይ መንግስትም በፍጥነት በፖሊስ ውስጥ የተሰገሰጉ ፀረ ኢትዮጵያ አላማ የሚያራምዱ ''የጭቃ ውስጥ እሾሆችን'' መንጥሮ ማውጣት አለበት::
በቅርቡ በቡራዩ እራሳቸውን የቄሮ እንቅስቃሴ እና የኦነግ ደጋፊ መሆናቸውን የሚናገሩ ወጣቶች የቡራዩ ዙርያ ነዋሪዎችን በስለት ጨምሮ በርካቶች በምሽት ተጠቅተዋል።ከአስር ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል (የተፈናቀሉት ከከፍተኛ የስነ ልቦና ችግር ጋር መመለሳቸው ተነግሯል)።ይህ ድርጊት ኢትዮጵያውያንን ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ድረስ ልብ የነካ ሃዘን አሳድሯል።ይህንን ድርጊት የፈፀሙት እነማን እንደሆኑ በቡድንም ሆነ በድርጅት ወይንም በግለሰብ ደረጃ የምርመራው ውጤት እስካሁን አልተገለጠም።ለምን? ከስድስት መቶ በላይ በቡራዩ ዙርያ ጥቃት የፈፀሙ እና የተሳተፉ ታስረዋል የሚል ዘገባ ፖሊስ ሰጥቷል።ሆኖም ምርመራው የድርጊቱን ፈፃሚዎች ማንነት አልተገለጠም።ይህ በእንዲህ እያለ ነው የአዲስ አበባ ወጣቶች ፍትህ ለአዲስ አበባ በሚል በመስቀል አደባባይ  ሰልፍ የወጡት።
 
ፎቶ =የአዲስ አበባ ወጣት ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ የኦነግ ደጋፊዎች ምግብ በነፃ ሲያድል

በአዲስ አበባ የቡራዩን ጥቃት ተከትሎ በተደረገው ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ጎሳ የለሹ የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ማን ነህ? ከየት መጣህ? የማያውቀው የአዲስ አበባ ወጣት አዲስ አበባን በጎጥ መስፈርት መለካትን ተቃወመ።ተቃውሞው መደረጉ በጎጥ ስም በሚስጥር የተደራጁ እና በፖሊስ መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ እና ከባህር ማዶ የመጡ የመንግስት ሆቴል ተቀላቢዎችን አደናገጠ።በመሆኑም ሰልፉ ከተጠናቀቀ በኃላ የአዲስ አበባን ወጣት ማፈስ ተያያዙት።አፈሳው የተከናወነው ሰልፉ ካበቀ ሰዓታት በኃላ በምሽት ሲሆን ቀጣይ አፈሳው ሰልፉ ካበቃ ከቀናት በኃላ ሁሉ ነበር።

እስካሁን ፖሊስ ባመነው መሰረት ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ወጣቶች መታፈሳቸው የተሰማ ሲሆን  የፈድራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ የሰጠው መግለጫ እርስ በርሱ የሚጋጭ ነው።አንድ ጊዜ ከሽሻ ቤት ያፈሱ መሆናቸውን ሲናገሩ፣በሌላ በኩል ደግሞ ስልጠና ለመስጠት ነው የሚል መግለጫ በመስጠት የሚሉት የጠፋቸው ስውር የጎሳ ፖለቲካ አራማጅ የሕግ አስከባሪዎች የሌለ ሕግ ሊያስተምሩን ሲዳዳቸው ተስተውሏል። ይህ ብቻ አይደለም።የቡራዩ ግጭት ፈፃሚዎች ለፍርድ ይቅረቡ።የሚል ጥያቄ እንደሚነሳ የፈሩት የጎጥ አራማጆች ወጣቶቹን ወደ ጦላይ ማሰልጠኛ ወስደው አጎሯቸው።አንድ ሰው በፖሊስ ከተያዘ ፍርድ ቤት ቀርቦ ወንጀሉ ሊነገረው ይገባል።በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ የተፈፀመው ግን ታፍሰው ስልጠና መስጠትም ሆነ እንዲያርም መብት ባልተሰጠው ፖሊስ በእራሱ መብት ጦላይ አጉሮ ከቤተሰብ ነጥሎ እያሰቃየ መሆኑ ነው የከፋው ወንጀል።

ይህ ሁሉ ሲሆን በየትኛውም የሕግ አግባብ ድርጊቱ ህገ ወጥ መሆኑን የሚያውቀው የአቃቢ ሕግም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አንዳች እርምጃ አለመውሰዳቸው  ከፍተኛ ቁጣ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችም ቀስቅሷል።አሁን ወጣቶቹን መፍታት ብቻ አይደለም።ይህንን በህገወጥ መንገድ ወጣቶቹን በማጎር ተግባር ላይ የተሳተፉ በሙሉ  ምርመራ ተደርጎባቸው ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።ለተግባራዊነቱም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት መቆም አለበት።የዶ/ር ዓብይ መንግስትም በፍጥነት በፖሊስ ውስጥ የተሰገሰጉ ፀረ ኢትዮጵያ አላማ የሚያራምዱ ''የጭቃ ውስጥ እሾሆችን'' መንጥሮ ማውጣት አለበት።ከእዚህ በተጨማሪ ለሃያ ሰባት ዓመታት የአዲስ አበባ ሕዝብ የተነፈገውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ቢሮ ለከተማው መስተዳደር የመመልስ መልካም ጅምር ተፋጥኖ ሕዝብ የራሱን ፀጥታ በራሱ እንዲጠብቅ መደረግ አለበት።አዲስ አበባ ሞግዚት ሰልችቷታል።ከእዚህ በፊት የነበረ የአዲስ አበባ ዝምታ በጎሳ ለሚራኮት ግጭት ላለመወገን እንጂ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ማንም ጋር የሌለ አንድነት እና ተጋድሎ አዲስ አበቤ ውስጥ ከልዩ ፈጠራ ጋር እንዳለ አለመዘንጋት ጥሩ ነው። አሁንም ጊዜው አልረፈደም።ወጣቶቹን ከይቅርታ ጋር ፍቱልን! ያሰሩት የጎሳ አድናቂዎች ለፍርድ ይቅረቡ! ዶ/ር ዓብይ ይህንን ያደርጋሉ ብለን እናምናለን።

ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ''አዲስ አበባ ቤቴ'' 


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...