ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, October 17, 2018

በአቡነ ሕርያቆስ የተፃፈው ''ፍኖተ ቤተ ክህነት ወቤተ መንግስት'' የተሰኘው መፅሐፍ ቅዳሜ አዲስ አበባ ላይ ይመረቃል (ጉዳያችን ዜና)


ጉዳያችን / Gudayachn Exclusive
ጥቅምት 8/2011 ዓም (ኦክቶበር 18/2018 ዓም)

መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አውሮፓ አህጉረ ስብከት በኖርዌይ፣ኦስሎ መካነ ቅዱሳን የቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አድርገው፣ የአቡነ ኤልያስ ረዳት ጳጳስ እና የደብሩ አስተዳዳሪ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት አቡነ ሕርያቆስ የፃፉት ''ፍኖተ ቤተ ክህነት ወቤተ መንግስት'' የተሰኘው አዲስ መፅሐፍ በመጪው ቅዳሜ ጥቅምት 10፣2011 ዓም አዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ከቀኑ 8ከ 30 ጀምሮ እንደሚመረቅ ለማወቅ ተችሏል።የመፅሐፉ አዘጋጅ እና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በአሁነ ሰዓት ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አዲስ አበባ የሚገኙ መሆኑ የታወቀ ሲሆን  በመፅሐፋቸው ምረቃ ላይ መፅሐፉን አስመልክቶ ማብራርያ እንደሚሰጡም ለማወቅ ተችሏል።በአሁኑ ወቅት የመፅሐፉ ሕትመት ጥቂት ስለሆነ  በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ቀድመው የመጡ ብቻ መፅሐፉን ለመግዛት የሚችሉ መሆኑ ተሰምቷል።

በእዚሁ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ከውጭ ሀገር የተለያዩ አህጉረ ስብከቶች እና ከሀገር ቤትም ከተለያዩ ሀገረ ስብከቶች በመጪው ሰኞ ጥቅምት 12/2011 ዓም በሚጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ወ\ደ አዲስ አበባ ከሄዱት ብፁዓን አባቶች ውስጥ አቡነ ኤልያስን ጨምሮ ሌሎች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት፣የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህራን እና ደራስያንም ጭምር  የሚታደሙበት የመፅሐፍ ምረቃ መርሐ ግብር እንደሚሆን  ለማወቅ ተችሏል።

በመሆኑም በሀገር ቤት የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮችም ሆኑ ኢትዮጵያውያን በሙሉ  በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

''ፍኖተ ቤተ ክህነት ወቤተ መንግስት'' የተሰኘው  መፅሐፍ  ይዘት በተመለከተ በመጠኑ የተጠቀሰበትን ፅሁፍ ለማንበብ ይህንን  ይጫኑ። 
ገብርኤል ኃያል 



ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...