ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, October 2, 2018

በአቡነ ሕርያቆስ የተፃፈ ''ፍኖተ ቤተ ክህነት ወቤተ መንግስት'' የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በቀናት ውስጥ ገበያ ላይ ይውላል (ጉዳያችን ልዩ ዜና)

ጉዳያችን / Gudayachn (Exclusive)
መስከረም 23/2010 ዓም 

የመፅሐፉ የፊት እና የጀርባ ሽፋን  

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአውሮፓ እና አፍሪካ አህጉረ ስብከት ረዳት ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የተፃፈ ''ፍኖተ ቤተ ክህነት ወቤተ መንግስት'' የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በቀናት ውስጥ ገበያ ላይ ይውላል።ይህ በዓይነቱም ሆነ በስፋቱ ልዩ የሆነ መፅሐፍ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን ብቻ ሳይሆን  የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ያልሆኑም ሊረዱት በሚችሉት መልክ የቀረበ ነው።  መፅሐፉ: -


  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ከክህነት ስርዓት እስከ ሲኖዶስ ስርዓት እና ሌሎች ስርዓቶቿን  በሚገባ የሚያብራራ እና ለማጣቀሻ የሚጠቀሙበት መድበል ነው 
  • በቅርብ ዘመናት (በዘመነ ኢህአዴግ ጨምሮ) ቤተ ክርስቲያን ያለፈችባቸውን ውጣ ውረዶች ከተጨባጭ ማስረጃዎች ጋር ያሳያል፣
  • ቤተ ክርስቲያን በሃይማኖት ቀሳጮች እና በውጭ ኃይሎች የደረሰባትን ፈተና በተለይ ከዘመናችን ሉላዊነት ጋር  አዛምዶ ያመለክታል፣ለመጪው ዘመንም ምን ማድረግ እንዳለባት መንገድ ያሳያል፣
  • ቤተ ክርስቲያን ስትጎዳ የእስልምና እምነትም አብሮ ለምን ማልቀስ እንዳለበት በምክንያት ያመላክታል፣
  • ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሯን በስልታዊ እቅድ እና በበጀት መመራት እንዳለባት ከዝርዝር አሰራር እና ናሙና ጋር  ለማንም አገልጋይ በሚገባ መልኩ የዘመኑ ጥበብ ከደረሰበት አንፃር ያብራራል፣
  • ቤተ ክርስቲያን እና መንግስት ምን አይነት ግንኙነት መያዝ እንዳለባቸው ያሳያል፣
  • በቅርብ በፍጥነት ቤተ ክርስቲያን ካልተገበረቻቸው የምመጡባትን አደጋዎች ይጠቁማል፣
  • ቤተ ክርስቲያን በአይቲ ቴክኖሎጂ በቶሎ መራመድ መቻል እንዳለባት በዝርዝር ያሳያል፣
  • ቅዱስ ሲኖዶስ ለእነኝህ ሁሉ ለውጦች ያለበትን ኃላፊነት በሚገባ ያብራራል።\
ይህ ከአራትመቶ ገፆችን በA5 መጠን የቀረበ ዳጎስ ያለ መፅሐፍ አለማንበብ ብዙ ያሳጣል።መፅሐፉ በጣም ጥቂት ኮፒዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በሚገኝባት የኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ላይ ይታተማል።በሀገር ቤት በምእመናን ጥያቄ መሰረት  በተጨማሪ ወደፊት ይታተማል።መፅሐፉን ለማግኘት የምትችሉበትን መንገድ ቤተ ክርስቲያን በድረ ገፅ ላይ ታወጣለች አያምልጣችሁ።
 የአቡነ ሕርያቆስ ሲመተ ጵጵስና አስመልክቶ በጉዳያችን ላይ ብፁዕነታቸው ያላቸውን አገልግሎት እና በሀገር ቤት የተማሩባቸው፣ያገለገሉባቸው ሀገሮች እና አህጉረ ስብከቶች የያዘ ሙሉ መረጃ ጉዳያችን ላይ መውጣቱ ይታወቃል።ዝርዝሩን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...