Tuesday, August 21, 2018

ያለፈው የአርባ ዓመታት የመለያየት ፖለቲካን ለአዲሱ ትውልድ የማገናኘት ሥራ ሰጥቷል።ልብ የሚነካ ታሪክ (ቪድዮ)

ያለፈው ትውልድ የአቶ ኢሳያስ እና አቶ መለስ ትውልድ የዘራው የመለያየት ፖለቲካ ለአሁኑ ትውልድ አካላት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ፣ጋዜጠኛ 'ጆሲ' እና ለሌሎችም የማገናኘት ሥራ ላይ እንዲጠመዱ አስገድዷል።ይህ ለአሁኑ ትውልድ አካላት የተሰጠ ዕድል ነው ማለት ነው።ያለፈው ሥራ ለአሁኑ ዕዳ የሚሆንበት ጊዜ አለ።የአሁኑ ትውልድ አካል ሆነን ያለፈው ትውልድን የማለያየት ፖለቲካ እንዳናራምድ እንጠንቀቅ።ያለፈው ይብቃ።ይህንን ቪድዮ ተመልከቱ እና የተሳሳተ ፖለቲካ ተራው ሕዝብ ላይ የሚፈጥረውን ቀውስ እንመልከት።
ልብ የሚነካ ታሪክ - አባት የቀድሞ ጦር ሰራዊት አባል፣ እናት የአስመራ ልጅ፣ ልጆች አዲስ አበባ እና አስመራ ተለያይተው አደጉ።እንዴት ተገናኙ? ሲገናኙ የነበረው ስሜትስ? (ቪድዮው ላይ ይመልከቱ)

ምንጭ : - ጄቲቪ  (ጄ ቴሌቭዥን)



ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

No comments:

7ኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ግንቦት 24፣2018 ዓም በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ተጠናቋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በሰባተኛው ብሔራዊ ምርጫ ድምፅ ሲሰጡ። ስለምርጫው ዝርዝር ጉዳይ ምን ያውቃሉ? ✓ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ 42 ፓርቲዎች እና 73 የግል ተወዳዳሪዎች ለተለያዩ ምክር ቤቶች ዕጩዎች ...