ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, August 25, 2018

ስድስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት ነሐሴ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በኢንተር ኮንትነንታል ሆቴል ይከናወናል።እጩዎቹ ይፋ ሆነዋል።

ፎቶ በ2009 ዓም  በአምስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች በከፊል 

በእዚህ ፅሁፍ ስር : - 
- የበጎ ሰው ሽልማት የሚሰጥባቸው አስር ዘርፎች ያገኛሉ፣
- ነሐሴ 27፣2010 ዓም በኢንተርኮንትነንታል ሆቴል የሚደረገው ስድስተኛው የሽልማት ስነ ስርዓት ለመካፈል የሚመዘገቡበትን ኦን ላይን ሊንክ ያገኛሉ፣
- የዘንድሮውን ሽልማት አስመልክቶ ኮሚቴው የሰጠው መግለጫ ቪድዮ ያገኛሉ፣
- በመጨረሻም የአለፈው ዓመት የበጎ ሰው ሽልማት ስነ ስርዓት ቪድዮ ያገኛሉ።
===========================
ጉዳያችን GUDAYACHN 
ነሐሴ 19/2010 ዓም (ኦገስት 25/2018 ዓም)

ኢትዮጵያ ላለፉት አርባ ዓመታት ያህል ከጠፉባት ድርጅቶች ውስጥ ሸላሚ ድርጅቶች ተጠቃሽ ናቸው።በንጉሡ ዘመን የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ ሽልማት ድርጅት፣ቲያትር ቤቶች፣የጦር ሰራዊቱ ሁሉ ዓመታዊ የሽልማት መርሐግብር እንደነበሯቸው  በወቅቱ የነበሩ ማስረጃዎች ይነግሩናል።ኢትዮጵያ የሽልማት ድርጅት ማጣቷ መጪውን ትውልድ እንደሚጎዳ ደጋግሞ ባገኘው አጋጣሚ ሲወተውት የነበረው ሙሀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለኢትዮጵያ ከሰራቸው በርካታ በጎ ተግባራቱ ውስጥ ይህ በጎ ሰው የተሰኘው የሽልማት ድርጅት ከምስረታው እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ  አንዱና ተጠቃሽ በጎ ስራው ነው። 

አሁን የሽልማት ድርጅቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ የማሳደግ፣በገንዘብም ሆነ በሰው ኃይል የማጠናከር ሥራ የሕዝብ እና የመንግስትም ጭምር ኃላፊነት ነው።ሀገራዊ የሽልማት ድርጅት መኖር ፋይዳው ብዙ ነው።ሀገራዊ ያልሆነ የሽልማት ድርጅት መኖር ደግሞ ዕዳው ብዙ ነው። ሀገራዊ ያልሆነ የሽልማት ድርጅት ኢትዮጵያን ስላጠፋህ ለመሸለም ሞራላዊ ችግር የለበትም።ሀገራዊ የሽልማት ድርጅት ግን ኢትዮጵያን ቀና ያደረጉትን ያበረታታል።በጎ ሰው የሽልማት ድርጅት የሀገር ሀብት ነው።


በጎ ሰው የዘንድሮ 2010 ዓም የሽልማት መርሐግብሩን በመጪው ሳምንት መጨረሻ ነሐሴ 27/2010 ዓም በኢንተርኮንትነንታል ሆቴል ያካሂዳል። በእዚሁ ስድስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት ላይ ለመገኘት የሚፈልጉ ሁሉ  ይህንን ሊንክ በመጫን ከፍተው መመዝገብ ይችላሉ።ሊንኩን ተጭነው ከተመዘገቡ በኃላ የሚሰጥዎን ቁጥርና መታወቂያዎን ይዘው ከሰኞ  ነሐሴ 21/2010 ዓም ጀምሮ  አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘው ምርፋቅ ካፌና ሬስቶራንት በመገኘት ካርድ መውሰድ እንደሚቻሉ  ለማወቅ ተችሏል። 

በጎ ሰው የሽልማት መርሐግብር የሚሸልማቸው ግለሰቦች  በአሥር ዘርፎች ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው።እነርሱም : - 

1. በመምህርነት ዘርፍ
2. ንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ
3. ማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ
4. ሳይንስ ዘርፍ
5. ቅርስና ባሕል ዘርፍ
6. መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ
7. ኪነ ጥበብ (በሙዚቃ ዜማ ድርሰት ዘርፍ)
8. ሚዲያና ጋዜጠኛነት ዘርፍ
9. ለኢትዮጵያ በጎ ሥራ የሠሩ የውጭ አገር ዜጎች ዘርፍ
10. በጎ አድራጎት ዘርፍ ናቸው።

የዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት አስመልክቶ የሽልማት ድርጅቱ ኮሚቴ የሰጠው መግለጫ ቪድዮ እና የ2009 ዓም የተደረገው  የሽልማት ስነ ስርዓት  ከእዚህ በታች ባሉት ተከታታይ ቪድዮዎች ላይ ይመልከቱ።

1) የዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት አስመልክቶ የሽልማት ድርጅቱ ኮሚቴ የሰጠው መግለጫ


የ2009 ዓም  አምስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት ስነ ስርዓት






ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...