ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, August 1, 2018

የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን የሲኖዶስ አንድነቷን በመጪው ቅዳሜ በሚሊንየም አዳራሽ በይፋ በልዩ መንፈሳዊ መርሐግብር ታውጃለች።4ኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበረ ጵጵስናቸው ተመልሰዋል ( ሰላሳ ፎቶዎች ይመልከቱ)




ጉዳያችን / Gudayachn
ሐምሌ 25/2010 ዓም (ኦገስት 1/2018 ዓም)

የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን የሲኖዶስ አንድነቷን በመጪው ቅዳሜ ሐምሌ 28፣2010 ዓም በሚሊንየም አዳራሽ በይፋ ታውጃለች።በዝግጅቱ ላይ ከሀያ አምስት ሺህ በላይ ምእመናን፣የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች፣ሊቃውንት፣ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከብፁዓን ጳጳሳት ጋር ከሀያ ስድስት ዓመት ስደት በኃላ ዛሬ ሐምሌ 25/2010 ዓም አስራ ዘጠኝ ሊቃነ ጳጳሳት እና አገልጋይ ካህናት ጋር ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል።አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ጣብያ በተደረገ መንፈሳዊ እና መንግስታዊ የአቀባበል ስነ ስርዓት ለቅዱስ ፓትርያሪኩ እና ከስደት ለተመለሱት ብፁዓን ጳጳስት ከመደረጉም በላይ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከስድስት ሰዓታት በላይ የአቀባበል ስነ ስርዓቱን ከቦሌ እስከ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የነበረውን መርሐግብር የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ሰጥቷል።ከኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በተጨማሪ ፋና ቴሌቭዥን እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ሰጥተዋል።

ባለፈው ሳምንት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአሜሪካ ባደረጉት ''ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን ኢኝገንባ'' በሚል ርዕስ በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን፣ሎስ አንጀለስ እና ሚኒሶታ ባደረጉት ጉብኝት በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር መገናኘታቸው እና ልዩ ልዩ የዲያስፖራ ማኅበረሰብ አካላት ጋር ውይይት አድረገዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ዕርቅ እንድታደርግ ግፊት በማድረግ፣አወያይ ልዑካንን በማበረታታት፣ብፁዓን አባቶችን በማነጋገር እና በመጨረሻም እርቁ ከተፈፀመ በኃላ አባቶች በመስከረም ወር የያዙትን የመመለስ እቅድ ትተው ከእርሳቸው ጋር እንዲመለሱ በማግባባት ያደረጉት ጥረት ከፍተኛ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።ይህንኑም አስመልክተው ከአቡነ መርቆርዮስ ጋር ከ26 ዓመት በኃላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የአውሮፓ እና አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በተደረገው የአቀባበል መንፈሳዊ መርሐግብር ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚና ቀላል እንዳልነበር ገልጠው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የዛሬዋ ቀን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ ትልቅ የድል ቀን ነው።ይህ ማለት ግን በርካታ ስራዎች የሉም ማለት አይደለም።የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር፣የገንዘብ አያይዝ፣የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድታደርግ ማድረግ፣የስብከተ ወንጌል አገልግሎቷን ማስፋፋት እና የሚድያ ሽፋን እንዲኖራት የራሷ የ24 ሰዓት ቴሌቭዥን እንዲኖራት ማድረግ እና ሌሎች ስራዎች አሁንም ቤተ ክርስቲያኒቱ ጊዜ ሳትሰጥ መስራት ከሚገቧት ቀዳም ስራዎች ውስጥ ናቸው።

በመጨረሻም ከስኖዶሳዊ ዕርቅ በኃላ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  እና ብፁዓን ጳጳሳት አቀባበል፣ ከአሜሪካ እስከ ቦሌ እና ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የነበሩ መርሐ ግብሮችን የሚያሳዩ ሰላሳ ፎቶዎች ከእዚህ በታች ይመልከቱ።






























ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...