ኤምባሲው ድረ-ገፁ ላይ የለጠፈው
- ጉዳዩ አስቂኝም አሳዛኝም ነው።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ አገራት የሚመድባቸው የኤምባሲ ሰራተኞች መስፈርቶቹ የትምህርት
ዝግጅት እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮ
ሳይሆን ካድሬ መሆን እና ለስርዓቱ ታማኝነት መሆኑ የታወቀ ነው።አንዳንዶቹ ኤምባሲዎች የቤተ ዘመድ መሰብሰብያ ከመሆናቸው የተነሳ የአንዱ ዘመድ
ከሞተ አብዛኛው ሰራተኛ ጥቁር ይለብሳል እየተባሉ ይታማሉ።የኤምባሲ ሰራተኞች ቢያንስ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ሕግ ዙርያ በቂ እውቀት እንዲኖራቸው የስራው
ባህሪ ይጠይቃል። ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ ግን የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የሰው ኃይል ይዞታ ከትንንሽ የአፍሪካ አገራት አንፃርም
ሲታይ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ የሚገኝ ነው። አልፎ አልፎ የሚገኙት በቂ የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ያላቸውም በካድሬ አለቆቻቸው እየተማረሩ
አገር ጥለው መሄዳቸውን ቀጥለዋል።
ይህ በእንዲህ
እንዳለ አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጣም ኃላ ቀር አሰራር በ21ኛው ክ/ዘመን ላይ ተቀምጦ ሲያስተዋውቅ ተሰምቷል።ይሄውም
'' ከአሁን በኃላ የኮንሱላር አገርልግሎት የሚሰጠው በፖስታ ብቻ ነው ይላል።'' ዛሬ ዓለም የኮንሱላር አገልግሎት በኢንተርኔት
በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በሚያጠናቅቅበት ወቅት የእኛዎቹ ማንም ሰው የምናስተናግደው በፖስታ ብቻ ነው ብለዋል።ይህ
የፍርሃት ደረጃ ነው።የእራሱን አገር ዜጋ የፈራ ኤምባሲ የት ይደርሳል? የሚገርመው ደግሞ ይህ አሰራር ያቀላጥፋል እያሉ በካድሬ
ቃላት ሲያጅቡት መሰማቱ ነው።የኮንሱላሩ ጉዳይ ኃላፊ ለአንድ ዩትዩብ ለምን በፖስታ ብቻ እንዳደረጉ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ
'' በዓል የሆነ ቀን ኢትዮጵያውያን ሳያውቁ ይመጣሉ እናም በፖስታ መሆኑ ለእዚህ ይረዳቸዋል'' ሲሉ ማሾፍ አይሉት ቀልድ መሰል
ምላሽ ሰጥተዋል።አሁን ባለንበት ዘመን የፖስታ አገልግሎት በእራሱ ወደ ኤሌክትሮኒክስ ፖስታ ኢትየተቀየረ ነው።የፖስታ ድርጅቶችም
አዳዲስ የገቢ መስክ ለምሳሌ የገንዘብ ሐዋላ አገልግሎት የመሳሰሉትን የሚሰጡት ጥንታዊው የፖስታ አገልግሎት እየቀረ እንደሚሄድ
ከወዲሁ ስለተገነዘቡ ነው።
በአሜሪካን አገርም ውስጥ ቢሆን አንድ ተራ ፖስታ በዕለቱ እንደማይደርስ የታወቀ ነው።ቢያንስ አርባ ስምንት ሰዓታት ወይንም ሁለት ቀን በትንሹ ማስፈለጉ አይቀርም።ይህም አንድ ሰው በአካል መጥቶ ጉዳዩን ከሚፈፅምበት ጊዜ የበለጠ ነው ማለት ነው።ሰነዱን የላከ ሰው እስኪመለስበት የሚጠብቀውን ጊዜ ደግሞ ሲታሰብ በጣም እረጅም ነው።አሁን ባለንበት ዘመን ገንዘን ያህል ሀብትም በቁልፍ ቁጥሮች ማውጣት እየተቻለ በካድሬ አቅም የታሰበች ሃሳብ በፖስታ ብቻ መጠቀም ሥራ ያቀላጥፋል እየተባለ ይነገረን ገባ።
ባጠቃላይ
የዶ/ር ቴዎድሮስ መስርያ ቤት ከእለት እለት ደረጃው እየወረደ እና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የበለጠ የሚያስተች መስርያቤት
እየሆነ ነው።ከሁለት አመታት በፊት ዋሽንግተን የሚገኘው ኤምባሲ ፀጥታ የሰፈነበትን የዲፕሎማቶች ሰፈር
በተኩስ ያናወጠው ስለ ዓለም አቀፍ ሕግ እና ድንጋጌዎች ፈፅሞ የማያውቅ ካድሬ የመመደቡ ጦስ መሆኑ ይታወቃል።በሌላ በኩል
በግብፅ የሚገኘው ኤምባሲ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩ ሰራተኞች ባለቤት መሆኑን ማረጋገጣቸውን በሊብያ የነበሩ ኢትዮጵያውያን
መናገራቸውን አንዘነጋውም። ለሁሉም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአሜሪካ ኢትዮጵያውያንን የማገኛችሁ በፖስታ ብቻ ነው ብሏል።መምጣት
የፈለገ ደግሞ ቀድሞ አሳውቆ ነው እንጂ ድንገት ብቅ አትበሉ ብሏል። ይሁን እንጂ የእንጀራ ልጅ ያልሆነ በፈለገ ጊዜ እንደሚገባ እና እንደሚወጣ
ማንም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ወደፊት ግን እንደ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት አጥር በአጠገቡ አትለፉ እንዳይባል? ያስፈራል።የእራሱን ዜጋ
የሚፈራ ኤምባሲ ከእዚህም ሌላ ብዙ ያደርጋል።ለሁሉም ግን የዶ/ር ቴዎድሮስ መስርያ ቤት በአሜሪካ ወደ 18ኛው ክ/ዘመን
የጫካ አሰራር ተመልሷል።
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment