ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, May 19, 2016

በግንቦት 20 ሰሞን የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ




መብራት ከመጥፋቱ በፊት ማስታወቂያ የሚነግርበት፣
ውሃ አጠራቅሙ ነገ ልጠፋ ነው ብሎ ቀድሞ የምያስታውቅበት ፣
መብራትም ሆነ ውሃ እንመለሳለን ባሉበት ሰዓት የሚመጡበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ

ቢሻኝ ተነስቼ እስከ ዳህላክ ሄጄ አደይን የማይበት፣
ከፈለኩ ቄራ ሰፈር አቦይ ጋራዥ ሄጄ በፍቅር መኪናዬን የማሰራበት፣
ገብረ ተንሳይ ኬክ ቤት የማነው የማልልበት፣
በፈለኩት ቋንቋ ታክሲ ውስጥ ጮክ ብዬ ቢሻኝ በኦሮምኛ፣ወይ በትግርኛ ከፈለኩ ወላይትኛ ሳወራ የማልሸማቀቅበት፣
ሰውም ስለምናገረው ነገር ከቁም ነገር ሳይቆጥር በእራሱ ሥራ የምጠመድበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ

ለልጆቼ ገበያ በ24 ብር 2 ኪሎ ስጋ የምገዛበት፣
በግ ቢያምረኝ ከእነቆዳው በመቶ ብር የምገዛበት፣
ሩዝ  እና ፓስታ ለአንድ ቀን እራት የበላ ጎረቤት ተቸገረ ተብሎ ጉድ የሚባልበት፣
ዘይት የድሃ እና ሃብታም መለያ ያልሆነበት፣
የሾላ ወተት በላስቲክ ገዝቶ ወደ ቤት መሄድ ሃብታም የማያስብልበት፣
እናት ልጆቿን የሾላ ወተት አጠጣች ተብሎ ከተወራ ነውር የሆነበት፣
ወተት ኮንትራት ከብት ካላቸው ሰዎች መከራየት ቅንጦት ያልሆነበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።

የሸዋ ዳቦ በ10 ሳንቲም ገዝቶ መብላት የተማሪ ሥራ የሆነበት፣
ደብረ ዘይት ደርሶ ለመምጣት 5 ብር ብቻ የሚበቃበት፣
የልጆች ደብተር፣እርሳስ መግዛት ያማያስጨንቅበት፣
ለትምህርት ቤት ክፍያ የማይከፈልበት፣
ዩንቨርስቲ መግባት አንሶላ እና ብርድልብስ ብቻ ተይዞ የሚገባበት፣
የውጭ መጋራት ጣጣ የሌለበት፣
የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ወጡ ላይ ብዙ ስጋ የለበትም ብለው የሚያማርሩበት፣
ዳቦ ዩንቨርስቲ በር ላይ ለሚጠርግ ሊስትሮ ሲሰጠው ''አቦ ፓስታ በልቻለሁ'' የሚልበት፣
ሻይ ቤት በአንድ ብር ባለ በርበሬ ስጎ  ፓስታ የሚሸጥበት፣
የቀን ሰራተኛው በሁለት ብር እንጀራ በወጥ የሚበላበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።

የአገር መሪዎች በሁለት እና ሶስት ወር ክፍለ ሃገሩን በሙሉ እየዞሩ የምጎበኙበት፣
ዓመት በዓል የከተማው ሕዝብ እንዳይቸገር ዋንኬ በግ የሚመጣበት፣
ዋንኬ በግ ላት የለውም ጮማ ይበዛዋል፣ቆዳው አይረባም እየተባለ የምንቀናጣበት፣
አንድ ሙሉ የዶሮ ወጥ ከ24 እንቁላል ጋር መስራት የሃብታም መለያ ያልሆነበት፣
የዶሮ ዋጋ የበጉን የበጉ ዋጋ የበሬውን ያልተካበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።

ከሶስት መቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ለአረብ አገር ያልተሸጡበት፣
በእነርሱ ሽያጭ የውጭ ምንዛሪ የሚሰበስብ መንግስት የሌለበት፣
ኢትዮጵያውያን በስደት በዓለም ዙርያ ያልታወቁበት፣
ባህሩ የኢትዮጵያውያንን ስጋ መብላት ሱስ ያላደረገበት፣
እነ ታንዛንያ የመሰሉ አገሮች ባቅማቸው የኢትዮጵያ ስደተኛ አንቀበልም ያላሉበት፣
በዓለም ላይ ሁለት የታወቁ ስደተኞች ብቻ የነበሩበት፣
ኢትዮጵያዊ ሁሉ ትምህርቱን ተምሮ መቼ ወደ አገሬ በተመለስኩ የሚልበት፣
ከዩንቨርስቲ የተመረቀ ሁሉ ሥራ የሚይዝበት
ያ የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።

ሰው ከቤቱ የማይፈናቀልበት፣
ቤቱን በድንገት መንግስት የማያፈርስበት፣
መንግስት የእራሱን ሕዝብ ጎዳና ተዳዳሪ ለማድረግ የማይተጋበት፣
77 ሚልዮን ብር በፕሮጀክት ስም የማይዘረፍበት
200 ሕፃናት የማይጠለፉበት
2000 ከብት የማይዘረፍበት፣
ከግማሽ ሚልዮን በላይ ጎዳና ላይ የወደቁ ጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት ያልበዙበት፣
በሃምሳ አመታት ውስጥ ያልታየ ርሃብ የማይታይበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።


ቢሻኝ ተነስቼ እስከ ዳህላክ ሄጄ አደይን የማይበት፣
ከፈለኩ ቄራ ሰፈር አቦይ ጋራዥ ሄጄ በፍቅር መኪናዬን የማሰራበት፣
ገብረ ተንሳይ ኬክ ቤት የማነው የማልልበት፣
በፈለኩት ቋንቋ ታክሲ ውስጥ ጮክ ብዬ ቢሻኝ በኦሮምኛ፣ወይ በትግርኛ ከፈለኩ ወላይትኛ ሳወራ የማልሸማቀቅበት፣
ሰውም ስለምናገረው ነገር ከቁም ነገር ሳይቆጥር በእራሱ ሥራ የምጠመድበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።

ግርማ ሞገስ የሌለው ቀላል መሪ በቤተ መንግስቱ የማይጎማለልበት፣
መሪው ከውጭ አገር ሰው ጋር በተገናኘ ቁጥር እና ንግግር ባደርገ ቁጥር ምን ይዘባርቅ እና አገሬን ያሰድብ ይሆን ብዬ የማልሳቀቅበት፣
በአነጋገሩ እና በምላሽ አሰጣጡ የምረካበት፣
በምግብ እራሴን ስላችል ችለሃል ብሎ የማያስፈራራኝ መሪ የማይበት፣
በምክር ቤት ስብሰባ ባለጌ ስድብ የማልሰማበት፣
ኢትዮጵያውያን በሊብያ አለቁ ሲባል ቆይ ዜግነት ላጣራ የማይል መንግስት የማላይበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።

ጋዜጠኛ መሆን በአንድ ጦር ሜዳ እራሱን ለሞት ከሰጠ ወታደር እኩል የማይታይበት፣
የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከ40 ዓመት በፊት ከነበረበት የመፃፍ መብት የባሰበት፣
የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከአርባ ዓመት በፊት የነበረው የመደራጀት መብት የተንኮላሻበት፣
የሰራተኛ ማህበር ለሠራተኞች መብት እኩል ተደራድሮ የህብረት ስምምነት የሚፈርምበት፣
የመምህራን ማኅበር የእራሱ መፅሄት፣አደረጃጀት፣እና መብት ለማስከበር የሚንቀሳቀስበት፣
ተማሪዎች የተሰማቸውን በፅሁፍ የሚገልጡበት፣
ተማሪዎች በመቃወማቸው መምህራን በመሰለፋቸው የጥይት እሩምታ የማይወርድበት፣
ለተማሪ በዱላ ለመምህር አስለቃሽ ጋዝ የሚለቀቅበት፣
 የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።

የኢትዮጵያን ድንበር የማንም ዘላን እንደፈለገ ጥሶ የማይገባበት፣
ጎረቤቶቻችን በእኛ የወታደር አቅም አንፃር ስታዩ ከጥቃቅን ግልገል የሚቆጠሩበት፣
እስር ቤቱ በጋዜጠኛ ፣ፀሐፊ እና ደራሲ ያልታጨቀበት፣
የሃይማኖት አባት በጎጥ እና በመንደር አስቦ ውሎ በማያድርበት፣
እድር በካድሬ ቢሮ ስር ያልዋለበት፣
የቤተ ዘመድ ስብሰባ ሆን ተብሎ እንዲበተን በስውር ያልተሰራበት፣
ሰው ቤተሰቡን የማይፈራበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።

አንድ ለአምስት ያልተጠረነፈ ሕዝብ እና አገር ያለበት፣
ኢቲቪ የውሸት ሁሉ አባት ያልሆነበት፣
የኢቲቪ ዜና ፎቶ ከኢራቅ እየተገለበጠ ያልተወሸከጠበት፣
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አውስትራልያ የምትኖር ኢትዮጵያዊት 20 ሚልዮን ዶላር ሎተሪ ደረሳት ብለው ልቤን የማያስደነግጡበት፣
ቆይተውም በስህተት ነው ይቅርታ የማይሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሌሉበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።

ኢትዮጵያን በጎጥ ከፋፍለው የሚስቁ ባለስልጣናት የለሉበት፣
ዲያስፖራውን በጎጥ እየከፋፈሉ ፈስቲቫል እያሉ የማይደክሙ ከፋፋዮች የሌለበት፣
ውጭ አገር ልዑክ ሲልኩ በጎጥ የሚልኩ እና የሚሰበስቡ ባለስልጣናት የማላይበት፣
በአንድ ጀንበር 200 ሰው በአዲስ አበባ የማይገድል ፖሊስ የማይበት፣
ከአራት መቶ በላይ ሕዝብ ሰልፍ በሰላማዊ መንገድ ጠየቃችሁ ብሎ የማይገድል መንግስት ያለበት፣
የኢትዮጵያን ድንበር ለሱዳን ለመቁረስ የማይደራደር እና የእራሱን አገር ገበሬ ሽፍታ ብሎ የማይጠራ ጠቅላይ ሚኒስትር የማላይበት፣
የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።
ምን ትሆኑ እንግዲህ የድሮ ስርዓት ናፈቀኝ።በእዚህ በግንቦት 20 ሰሞን አብዝቶ ናፈቀኝ!የተሻለ ስጠብቅ የባሰ መጥቶ የድሮ ስርዓት አስናፈቀኝ።ግንቦት 20 አይለፍልህ!


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...