አምባገነኑ የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስት ቅጥ ያጣ የመንደር ፖለቲካውን ህገ መንግስት በሚል ቃል ሸፍኖ በነፃ ሃሳባቸውን የገለፁትን ሁሉ ''ህገ መንግስት የጣሱ'' ሲል እንዳልነበር ''ህገ መንግስቱ ይከበር'' ብለው ከሕገ መንግስቱ አንቀፅ እየጠቀሱ የመፃፍ፣የመናገር እና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቶች ይከበሩ'' ያሉት 'የዞን ዘጠኝ' ጦማርያንን ትናንት ሚያዝያ 17/2006 ዓም ቤት ለቤት እያሸበረ ከእስር ቤት ማጎሩን ለማወቅ ተችሏል።ዛሬ ሚያዝያ 18/2006 ዓም የጦማርያኑ ድረ-ገፅ እንደጠቆመው ስድስቱ ታሳሪዎች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስን ጨምሮ ማዕከላዊ እስር ቤት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
በሌላ በኩል ሰማያዊ ፓርቲ ለሚያዝያ 19/2006 ዓም የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በተያዘለት መርሃግብር መሰረት እንደሚደረግ እና ዝግጅቱ መጠናቀቁን ፓርቲው በድረ-ገፁ እና በፌስ ቡክ በለቀቀው ተከታታትይ ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ትውልድ አምባገነንነትን የምሸከምበት፣ ሃገሩ ወደ እንጦሮጦስ ስትወርድ እየተመለከተ ጥቂቶች ''ሀገር ሰላም ነው፣እያደግን ነው'' እያሉ የሀገርን ሀብት ሲምነሸነሹበት የሚመለከትበት ዘመን በትክክል አብቅቷል።ቢያንስ በዝምታ የተሸበበ አንደበት መከፈት እንዳለበት እና ኢትዮጵያዊነት ቃል ኪዳኑን የሚያድስበት ጊዜ ላይ መሆናችንን ለማወቅ ይቻላል።
ዛሬ አዲስ አበባ አንድ ወዳጄ ታክሲ ውስጥ የወቅቱን የጎሳ ፖለቲካ እየኮነነች ካለምንም ፍርሃት ስትናገር የነበረች ወጣትን የሰማ ወያላ ''የምትይው ይገባኛል ግን መርሳት የሌለብሽ ብዙ ሸቤ አሉ'' ብሎ ሲመልስላት ከታክሲው ስትወርድ የሰጠችውን የመጨረሻ መልስ ከትቦ ላከልኝ።''ወጣቱ የደረሰበትን ደረጃ ተመልከት አምባገነኖችን የሚሸከሙ ጫንቃዎች የአገልግሎት ዘመናቸውን ጨርሰዋል።'' ካለ በኃላ ወዳጄ ወጣቷ ያለችውን እንዲህ ያስቀምጠዋል- '' 'ቁርጥ ቀን ባይመጣ ሁሉም ጀግና ነበር' በላዬ ላይ የተሰካውን የአምባገነኖች እና የጎሰኞች እሾህ እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በመገኘት ማራገፍ እጀምራለሁ''
ጉዳያችን
ሚያዝያ 18/2006 ዓም
No comments:
Post a Comment